በአዲስ አበባ የክረምቱን መግባት ተከትሎ ዋና ለመዋኘት በሚል 3 ታዳጊዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው ሰጥመው መሞታቸው ተነገረ
ከሁለቱ ሕፃናት አንደኛው ደግሞ የ16 አመት ታዳጊ በሐይቅ ውስጥ ሰጥሞ የሞተ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሱሉልታ ከተማ በሚገኘው ወንዝ ሕይወቱ ማለፉን አቶ ስለሺ ነግረውናል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስቀድሞ እንዳሳሰበው የክረምቱ ጊዜ ከበድ ያለ ሊሆን ስለሚችል በወንዝ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራ መስራቱ ተነግሯል፡፡ወላጆች በክረምቱ ጊዜ ልጆቻቸው ዋና ለመዋኘት በሚል ወደ ወንዝ ዳርቻዎች እንዳይሄዱ በመከላከልና በመጠበቅ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ባለስልጣን መስሪያ ቤት አሳስቧል፡፡
ምህረት ሥዩም