• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የሚድዋይፎች ቁጥር አነስተኛ መሆን እናቶች ጥራቱ የተጠበቀና ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ምክንያት ሆኗል ተባለ

የሚድዋይፎች ቁጥር አነስተኛ መሆን እናቶች ጥራቱ የተጠበቀና ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ምክንያት ሆኗል ተባለ፡፡ ይህን የሰማነው የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር 27ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ሲያደርግ ነው፡፡ በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ብዙዎች ኢትዮጵያዊ እናቶች ጥራቱ የተጠበቀ፣ አክባሪና ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን ሰምተናል፡፡

በአገሪቱ ያሉት ሚድዋይፎች ብዛት ከ12 ሺ የማይበልጥ ሲሆን ሁሉንም እናቶች ለመድረስ በትንሹ 50 ሺ ሚድዋይፎች ያስፈልጋሉ ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ሚድዋይፎች ማህበር ላለፉት 27 አመታት ከመንግስትና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በርካታ ስራዎችን ቢሰራም አሁንም ችግሩ በሚፈልገው መጠን አለመቀነሱ የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አዜብ አድማሱ ተናግረዋል፡፡ ማህበሩ አመታዊ ጉባኤውን ጥራት፣ ፍትሃዊነትና ክብር ለእናቶች በሚል መሪ ቃል በዋሽንግተን ሆቴል እያካሄደ ነው፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ማጣራት በጀመረባቸውና ያለ ስራ ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ለልማት የማዋል ስራ ላይ ሁሉም ቦታዎች ለተደራጁ ወጣቶች ይሰጣሉ የሚለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ ማጣራት በጀመረባቸውና ያለ ስራ ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ለልማት የማዋል ስራ ላይ ሁሉም ቦታዎች ለተደራጁ ወጣቶች ይሰጣሉ የሚለው መረጃ ከእውነት የራቀ በመሆኑ ከተሳሳተ መረጃ ተጠበቁ ሲል የከተማ አስተዳደሩ ተናገረ፡፡ በመንግስት ታጥረው የሚገኙ ቦታዎችን በሚመለከት ትክክለኛ ያልሆኑ መረጃዎች በነዋሪው ላይ ውዥንብር እየፈጠረ ነው ተብሏል፡፡ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንደተናገረው በቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች በመንግስት ታጥረው የሚገኙ ቦታዎች በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች ይሰጣሉ በሚል የሀሰት መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን የክፍለ ከተማው አስተዳደር ተናግሯል፡፡

በተለያየ ምክንያት ተከልለው በመንግስት እጅ የሚገኙ ባዶ መሬቶች በማህበር ለተደራጁ ወጣቶች ይሰጣሉ በማለት የሚካሄድ የማህበራት ምዝገባ ከመንግስት እውቅና የሌለው መሆኑ ተነግሯል፡፡ ነዋሪውም የተሳሳተውን መረጃ ሰምቶ ላላስፈላጊ ወጪ እንዳይዳረግ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል፤ ምዝገባውም ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጪ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ ዙሪያም መንግስት የሚያከናውናቸውን ስራዎች በራሱ ለህብረተሰቡ ያሳውቃል መባሉን ከአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ 19 በመቶ ባለድርሻ የሆነችበት የበርበራ ወደብ ማስፋፊያ ግንባታ ተጀመረ

ኢትዮጵያ 19 በመቶ ባለድርሻ የሆነችበት የበርበራ ወደብ ማስፋፊያ ግንባታ ተጀመረ፡፡ በግንባታው ስራ አጀማመር ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና የሶማሌላንድ አስተዳደር ሹማምንት ተገኝተዋል፡፡በርበራ ወደብ ከኢትዮጵያ 19 በመቶ ድርሻ በተጨማሪ የዱባይ ፖርት ኩባንያ 51 በመቶ የሶማሌላንድ አስተዳደር የ30 በመቶ ድርሻ አላቸው፡፡ የመጀመሪያው የወደቡ የግንባታ ምዕራፍ በአንድ አመት እንደሚጠናቀቅ ሰምቼያለሁ ሲል ሱማሌላንድ ኒውስ ዘግቧል፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢጣሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

የኢጣሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ፡፡ በሁለት ቀን የአዲስ አበባ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተነጋግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉትንም ለውጦች አድናቂና ደጋፊ መሆናቸውን ተናግረዋል ተብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትላንትናው ዕለት ለኢጣሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ለክብራቸው የራት ግብዣ አደርገውላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጁሴፔ ኮንቴ ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ አስመራ ሲሄዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ሸኝተዋቸዋል፡፡ ጁሴፕ ኮንቴ በአስመራ አንድ ቀን ጉብኝታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የማነ ገብረመስቀል በቲዊተር ገፃቸው ጠቁመዋል፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

38ኛው የአለም የምግብ ቀን የፊታችን ጥቅምት 6 ቀን እንደሚከበር ተነገረ

“የዛሬ ጥረታችን ለነገ ስኬታችን” በሚል መጠሪያ እንደሚከበርና በዘላቂ የልማት ግቦች መሰረት እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2030 ረሀብን ለማጥፋት ያለመ እንደሆነ የግብርናና የእንስሳት ሀብት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ሚኒስቴሩ ዛሬ በዓሉን አስመልክቶ በመስሪያ ቤቱ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የግብርና፣ እንስሳት እና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ ከኢትዮጵያ ሕዝብና አጋሮች ጋር በጋራ በመሆን የግብርናና የእንስሳት ሀብት ዘርፉን ምርትና ምርታማነት በማሻሻል በ2030 ረሀብን ማጥፋት እንደሚቻል አረጋግጠዋል፡፡

የውሀ አቅርቦት ስራዎቻችን ስኬታማነት ለዚህ እንደማሳያ መሆን የሚችሉ ናቸው ብለዋል፡፡ በዓሉ በሚከበርበት ወቅትም የተለያዩ የልምድ ልውውጦች እንደሚካሄዱ ጠቁመዋል፡፡ ምግብ መምረጥ ሳይሆን ሊበሉ የሚችሉ ነገሮችን ሁሉ በምግብነት በመጠቀም ኢትዮጵያውያን የምግብ አብዮት ሊኖረን ይገባል ብለዋል፡፡ የአለም የምግብ ድርጅት ተወካይ ፋጡማ ሰዒድ በበኩላቸው ግጭት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ኢ-ፍትሃዊነትና የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ አለም ባለፉት አመታት ረሀብን ለመቀነስ እንዳትችል ያደረጓት ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ባለፉት 1 እና 2 አመታት ረሀብ እየጨመረ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በ2030 እንዲሳካ የታሰበውን ውጥን ከግብ ለማድረስ አገራት፣ ተቋማትና ባለሙያዎች ተቀናጅተው በእጥፍ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ኢንቨስትመንትን፣ እውቀትንና መንግስታትን አቀናጅተን ከሰራን እጅ ለእጅ ተያይዘን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የተመጣጠነ ምግብ እናቀርባለን ያሉት ደግሞ የአለም የምግብ ፕሮግራም ተወካይ እስቲቭ ዌር ናቸው፡፡ መንግስት፣ ባለሀብቶች በግብርናው ዘርፍ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ማበረታታትና አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር ለተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች የማህበራዊ ዋስትና መረሃ ግብሮችን ማሳደግና የአምራች ገበሬዎችን ምርቶች ከከተማ ገበያ እድሎች ጋር ማስተሳሰር እንደሚጠበቅበት ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ላይ ሰምተናል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሻሸመኔ ከተማ የሰው ሕይወት አጥፍተዋል፣ ንብረትም እንዲወድም አድርገዋል የተባሉ 21 ተይዘው ክስ የተመሰረተባቸው 6 በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀረቡ ተባለ

በሻሸመኔ ከተማ የሰው ሕይወት አጥፍተዋል፣ ንብረትም እንዲወድም አድርገዋል የተባሉ 21 ተይዘው ክስ የተመሰረተባቸው 6 በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀረቡ ተባለ፡፡ የከተማው ከንቲባ አቶ ደስታ በኩሉ ለሸገር ሲናገሩ፣ በሕዝባዊ አቀባበል ጊዜ የአንድ ሰው ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያልፍና ንብረት እንዲወድም ያደረጉ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ናቸው ፍርድ ቤት የቀረቡት ብለዋል…የወንድሙ ኃይሉን ዝርዝር ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመክፈቻ ንግግር...በፕሬዝዳንቱ የቀረቡ ውጥኖች እንዴት ባለመልኩ ተግባራዊ ቢሆኑ ውጤታማ ይሆናሉ ስትል የምጣኔ ሐብት ባለሙያ

ችግር ውስጥ የገባውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለመታደግ የመንግስት እቅድ በተመለከተ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን በፕሬዝዳንቱ የቀረቡ ውጥኖች እንዴት ባለመልኩ ተግባራዊ ቢሆኑ ውጤታማ ይሆናሉ ስትል የምጣኔ ሐብት ባለሙያ አነጋግራ ያዘጋጀችውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ፋብሪካ የፊታችን እሁድ እንደሚመረቅ የስኳር ኮርፖሬሽን ተናገረ

ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 የስኳር ፋብሪካ የፊታችን እሁድ እንደሚመረቅ የስኳር ኮርፖሬሽን ተናገረ፡፡ የበየነ ወልዴን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ እስካሁን የትራንስፖርት ፖሊሲ እንደሌላት ተነገረ

ኢትዮጵያ እስካሁን የትራንስፖርት ፖሊሲ እንደሌላት ተነገረ፡፡ የቴዎድሮስ ብርሃኑን ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎችና፣ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ድንገተኛ ክትትል እያደረግሁ ነው ሲል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተናገረ

በአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎችና፣ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ድንገተኛ ክትትል እያደረግሁ ነው ሲል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተናገረ፡፡ ኮሚሽኑ፣ በፌደራልና በክልል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች እንዲሁም በፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች የሰበዓዊ መብት አያያዝ ምን እንደሚመስል እፈትሻለሁ ብሏል፡፡ ድንገተኛ ክትትል አስፈላጊ ሆኖ የተገኘውም በማረሚያ ቤቱ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለመረዳትና ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ ሲባል መሆኑን ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡

የሰብዓዊ ኮሚቴ ኮሚሽን በድንገተኛ ክትትሉ ወቅት፣ የማረሚያ ቤቶችንና ፖሊስ ጣቢያዎችን ኃላፊዎች፣ ታራሚዎችን ጭምር አነጋግራለሁ ብሏል፡፡ በተጨማሪም የመኝታ ክፍሎቻቸውን እንደሚፈትሽና ከታራሚዎቹና ከተጠርጣሪዎቹ ጋር የተናጠል እና የቡድን ውይይት እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡ ድንገተኛ ክትትል ያስፈለገው ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች ላይ የተደነገጉ የሰብዓዊ መብቶች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ነው ሲል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገፁ ላይ አስፍሩዋል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሁሉም ዩንቨርሲቲዎች ከተውጣጡ አካላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው

ዛሬ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሁሉም ዩንቨርሲቲዎች ከተውጣጡ አካላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው። ዩንቨርሲቲዎቹ የሚገኙባቸው አካባቢዎች የዞን አስተዳዳሪዎች፣ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎችና የአገር ሽማግሌዎች በውይይቱ ከሚሳተፉት መካከል መሆናቸውን ሰምተናል።

የዩንቨርሲቲዎቹ ፕሬዚደንቶችና ምክትል ፕሬዚደንቶች፣ የኮሌጅ ሃላፊዎች፣ የተማሪዎች ጉዳይ ሀላፊዎችና የተማሪዎች ህብረት አባላትም በውይይቱ የሚካፈሉ መሆናቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ይካሄዳል በተባለው ውይይት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሰላም መከታተል በሚችሉበት መንገድ ላይ ይመከራል ተብሎ ይጠበቃል።

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers