• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመተግበር መስማማቱ የኢሮብ ብሔረሰብን ፍላጎት...

“የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመተግበር መስማማቱ የኢሮብ ብሔረሰብን ፍላጎት ያላማከለ ነው እና እንቃወማለን” በሚል በአዲስ አበባ የሚኖሩ የብሔረሰቡ አባላት ትናንት ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተው ነበር፡፡

ነገር ግን ትናንት በተባለው ሰዓት ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡ለምን ሳታካሂዱ ቀራችሁ ስንል ከአስተባባሪዎቹ አንዱ የሆኑት አቶ ስዩም ዮሐንስን ጠይቀናቸዋል፡፡አቶ ስዩም “በማህበራዊ ገፆች ላይ የኛን ሰላማዊ ጥያቄ ለሌላ ዓላማ ለማዋል ያቀዱ ሰዎች መኖራቸውን ተገንዝበን ሰልፉን ሰርዘነዋል” ብለዋል፡፡

“ከመንግስትም እንድንሰርዘው ተጠይቀን ነበር” ያሉት አቶ ስዩም “ቀድመን አስበነው ስለነበር ያለምንም ማቅማማት ተስማምተናል” ብለዋል፡፡“ሰላማዊ ሰልፉ ቀረ እንጂ የብሄረሰቡ ጥያቄ ቀረ ማለት አይደለም” ብለዋል አቶ ስዩም ዮሐንስ፤ ጥያቄያችንን በተለያዩ ዘዴዎች እንጠይቃለንም ብለዋል፡፡ኢሮብ የኢትዮጵያ እንጂ መቼም የኤርትራ አትሆንም ሆናም አታቅም መሬት ቆርሶ በመስጠት ሰላምን ማምጣት አይቻልም የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎችን በማንሳት መንግስት የኢሮብ ብሔረሰብ አባላትን ያድምጥ ብለዋል፡፡

አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“ግጭቱ እንዲቀሰቀስ ያደረጉ ሰዎችን ለህግ ለማቅረብና ወደፊትም መሰል ችግር እንዳይደገም ሕብረተሰቡ ያግዘን…”

“ግጭቱ እንዲቀሰቀስ ያደረጉ ሰዎችን ለህግ ለማቅረብና ወደፊትም መሰል ችግር እንዳይደገም ሕብረተሰቡ ያግዘን…” ሲሉ ጠይቀዋል የኦሮሚያ ክልል ርዕሠ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሣ ከክልሉ የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆችን መልሶ ለማቋቋም ዝግጅት ጨርሰናል አሉ…

ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው ተመልሰው የማቋቋም ዝግጅት ተጠናቅቋል፡፡ ሥራውን የሚሰራ አካል ተለይቶ ወደ ሥራ ተገብቷልም ብለዋል፡፡የወሰን ጥያቄን ሽፍን በማድረግ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን እንዲሁም በደቡብ ክልል ጌድኦ ዞን አዋሳኝ አካባቢ ዜጎች እንዲጋጩ ተደርጓል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ግጭቱ እንዲቆም ሌተ ተቀን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ግጭቱ እንዲቀሰቀስ ያደረጉ ሰዎችን ለህግ ለማቅረብና ወደፊትም መሰል ችግር እንዳይደገም ሕብረተሰቡ ያግዘን ሲሉ ጠይቀዋል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአክሱም 3 ሺ አመት ሙሉ የቆመው ቁጥር 3 ሐውልት እድሳት ሊደረግለት ነው ተባለ

በቅርፅ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ የቅርስ ተመራማሪው አቶ ሀይሉ ዘለቀ ለሸገር ሲናገሩ ሐውልቱ የዛሬ 10 አመት በሮም የነበረው ሐውልት ወደ ስፍራው ተመልሶ በሚቆም ጊዜ ለጥንቃቄ ተብሎ የታሰረበት ገመድም ይፈታል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያዊው ኤም ኤች ኢንጂነሪንግና በጣሊያኑ ክሮቺ ስቲዲዮ ሰሞኑን ይታደሳል የተባለው ይህ ሐውልት በመቃብር ስፍራ ላይ የቆመ ነው ያሉት አቶ ሀይሉ ሌሎቹ ሐውልቶች ሲወዳድቁ እስከ ዛሬ ንቅንቅ ሳይል 3 ሺ አመት ያስቆጠረ ነው አሁንም በከፍተኛ ጥንቃቄ የእድሳት ስራው ይከናወናል በማለትም ነግረውናል፡፡የፊታችን ቅዳሜ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከሚመለከታቸው ጋር በዚያው በአክሱም ስለ እድሳቱ ምክክር ካደረገ በኋላ ወደ ስራው ይገባል ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

፩.መግቢያ፡

የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 3 እስከ 5 ያካሄደዉን አስቸኳይ ሰብሰባ አጠናቋል። ህወሓት/ኢህአዴግ በ17 ዓመቱ የትጥቅ ትግልም ሆነ ሩብ ክፍለ ዘመን ባስቆጠረው የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ትግል ምዕራፎች ሁሉ ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በመሆን ባደረግነው ትግል በርካታ ድሎችን እየተጎናፀፍን እዚህ ላይ መድረስ ችለናል። የ43 ዓመታት የድልና የፅናት ጉዟችን ስኬት ምንጭ የጠራና ብቁ አብዮታዊ መስመር ይዘን የዘለቅን መሆኑ ነው። ይህንን መስመር በፅናት ጨብጦ በፅናት ታግሎ የሚያታግል ድርጅት ባለቤት ስለሆንም ነው። ባለፉት 27 ዓመታት በአጠቃላይ፣ ባለፉት የ17 የተሐድሶ ዓመታት ደግሞ በተለይ ዙርያ መለስ መሰረታዊ ለውጥ ማስመዝገብ ችለናል። ሃገራችን ኢትዮዽያ የነበረችበት እጅግ አስፈሪ የመበታተንና የማሽቆልቆል ጉዞ ተገቶ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንድትሸጋገርና ስምና ክብር ከፍ ብሎ እንዲጠራ ኢህኣዲግ እልህ አስጨራሸ ትግል አካሂዷል። በተደረገዉ ትግል የሃገራችን ህዝቦች የመልማት እኩል ዕድል ያረጋገጠ ስርዓት ተገንብቶ ህዝቦችን በኢኮኖሚና በማሕበራዊ ረገድ ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ዉጤት ለማረጋገጥ ተችሏል። በእርግጥም አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመራችን ሃገራችንን ከጥፋት የታደገ፣ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠበት አዲሲቷ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ያደረገና ለወዲፊትም የሃገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ መሆኑ የእስከአሁኑ ትግላችን ያረጋገጠው እውነት ነው።

ይኸ ተዓምር የፈጠረና የሃገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ የሚያስችል ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አደጋ ውስጥ የወደቀበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ እንዲፈጠር ከምንም በላይ የመሪ ድርጅታችን ኢህኣዴግ አመራር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ባህርይው እየተሸረሸረ በከፋ የጥገኛ ዝቅተት አረንቋ ውስጥ በመዘፈቁ መሆኑን ድርጅታችን ኢህአዴግ በሚገባ የተነተነዉ ጉዳይ ነዉ። ይሁን እንጂ ይህንን ፈተና በሚገባ ለማለፍ ሲባል በድርጅታችን የተጀመረዉ በጥልቅ የመታደስ እንቅስቓሴ ኣሁንም ቢሆን በሚፈለገዉ ደረጃ ሊሳካ አልቻለም።
ይህንን መነሻ በማድረግ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ በወሰናቸዉ ዉሳኔዎች በሃገራችንና ክልላችን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም በቀጣይ የትግል አቅጣዎቻችን ላይ በዝርዝር በመውያየት ውሳኔዎች አሳልፏል።

በአዲስ አበባ የአቢሲኒያ ባንክ ቴሌ መድሃኒዓለም ቅርንጫፍን ለመዝረፍ የሞከሩ ግለሰቦች ተያዙ

ትናንት ምሽት አስራ ሁለት ሰዓት ተኩል ገደማ በተለምዶ ቦሌ መድሃኒዓም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የአቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፍ ላይ የዘረፋ ሙከራ ያደረጉ ግለሰቦች መያዛቸው ተነገረ፡፡እነዚህ የተደራጁ ዘራፊዎች መኪና ይዘው ያደረጉት የዘረፋ ሙከራ በባንኩ ሠራተኛ እና ፖሊስ ብርቱ ጥረት ከሽፏል ተብሏል፡፡የአቢሲኒያ ባንክ የማርኬቲንግ ኮሙኒኬሽን እና ኦፕሬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ አስቻለው ታምሩ ዛሬ ለሸገር እንደተናገሩት፣ በሙከራው በሠው ህይወትም ሆነ በባንኩ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፡፡

ምንም አይነት ገንዘብ ከቅርንጫፉ እንዳልተዘረፈም አቶ አስቻለው ነግረውናል፡፡ሙከራውን ካደረጉ የተደራጁ ዘራፊዎች የተወሰኑት በዚያው ዕለት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ብለዋል፡፡የተወሰኑት ደግሞ ዛሬ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ነግረውናል፡፡ጉዳዩ በፖሊስ ተይዞ ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝም ሠምተናል፡፡

ከምርመራ ውጤቱ በኋላ ሌሎች ተጨማሪ ግለሰቦች ከሙከራው በስተ ጀርባ መኖር አለመኖራቸው ይታወቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡ባንኩም ምርመራው እንዳበቃ ስለ ጉዳዩ ለህዝቡ ስለ ሁኔታው ያሳውቃል ብለዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ብዙዎች ‘አያ ሙሌ’ እያሉ ስሚጠሩት ተወዳጁ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ በሸገሩ የ“ወይ አዲስ አበባ” ፕሮግራም በተከታታይ ሳምንታት ሲቀርብ የነበረው መሰናዶ መቋጫ የሆነውን ይህን እንድታዳምጡ ጋብዘናል..

ብዙዎች ‘አያ ሙሌ’ እያሉ ስሚጠሩት ተወዳጁ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ በሸገሩ የ“ወይ አዲስ አበባ” ፕሮግራም በተከታታይ ሳምንታት ሲቀርብ የነበረው መሰናዶ መቋጫ የሆነውን ይህን እንድታዳምጡ ጋብዘናል..

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተማሩ ያሉና ወደፊትም የሚመዘገቡ ተማሪዎች የተቋማቱን የእውቅና ፈቃድ ማየት ይኖርባቸዋል ተባለ

ተማሪዎቹ ተቋማቱ በሚመዘግቡባቸው የትምህርት መስኮች ፍቃድ ስለማግኘታቸውና ፈቃዱም ስለመታደሱ ማረጋገጥ የሚኖርባቸው መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡ኤጀንሲው 133 የትምህርት ተቋማት በየቅርንጫፎቻቸው እንዲያስተምሩባቸው የተፈቀደላቸው የትምህርት መስኮች በቀን 8/10/2010 ዓ/ም በሚታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

ወላጆችና ተማሪዎችም መረጃውን በመመልከት ለትምህርት የሚያወጡትን ገንዘብ በተገቢው ቦታ ማዋል ይኖርባቸዋል ብሏል፡፡ኤጀንሲው የእውቅና ፈቃድና እድሳት የሚሰጠው በየቅርንጫፉ ስለሆነ ተመዝጋቢዎች የሚቀርብላቸው የዕውቅና ፈቃድ በቅርንጫፉ ስም ስለመሆኑ ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው ተነግሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ተቋማቱም በሚመዘግቡበት ወቅት በፈቃዱ ላይ በተጠቀሱ የስልጠና መስኮች ስለመሆኑ ማረጋገጥ ከተመዝጋቢዎች ይጠበቃል ተብሏል፡፡ተቋማቱ ከኤጀንሲው ያገኙትን ትክክለኛውና ህጋዊውን የእውቅና ፈቃድ መረጃ መስጠትና ለተገልጋይ ግልጽ በሆነ ቦታ መለጠፍ እንደሚኖርባቸው አሳውቋል፡፡

እያንዳንዱ ተቋምም እውቅና ፈቃድና እድሳት ባገኘባቸው ቅርንጫፎች ብቻ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንዲያስተምር ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የትምህርት ተቋማቱን አስመልክቶ የሚቀርብልኝን ማንኛውም ቅሬታ ተቀብዬ አስተናግዳለሁ ብሏል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የጎርፍ ስጋት ያለባቸው መንዶች ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጎ አሳድሷል ተባለ

ከመገናኛ ሳህሊተ ምህረት ባለው ጎዳና የሚጎርፈውን ውሃ ግን ለመከላከል እንደቸገረው ተናግሯል፡፡የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው አቶ ጡኡማይ ወ/ገብርኤል ለሸገር ሲናገሩ ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ ከ90 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጎ ያደሳቸውና ጎርፍ ይደጋገምባቸው የነበሩ 41 መንገዶች ሲሆኑ አምባሳደር፣ ብሔራዊ፣ ባሻ ወልዴ፣ ኮተቤ 02፣ ቦሌ ኤድናሞል፣ ዲያስፖራ አደባባይ፣ አየር ጤና፣ ሀይሌ ጋርመንት መንገዶች ይገኙበታል ብለዋል፡፡

አሁን ከመገናኛ ሳሊተ ምህረት ያለው መንገድ ከፍተኛ ጎርፍ እያጠቃው ነው ይህም ከባቡሩ መንገዱ የሚወርደው ውሃ ታክሎበት የተፈጠረ ሲሆን ከባቡር ድርጅት ጋር በመነጋገር ለመፍታት እየጣርን ነው በማለትም አቶ ጡኡማይ ነግረውናል፡፡ለከተማው መንገዶች እድሳትና ጥገና ግማሽ ሚሊዮን ብር ተመድቧል ያሉት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው የመንገድ ቱቦዎችን የማፅዳትና ውሃውን ከዋናው ቱቦ የማገናኘት ስራ እየተከናወነ ነው፡፡ነዋሪዎች ቱቦዎችን ባለመድፈን ተባበሩን ብለዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሌ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን እና ደቡብ ክልል ጌዲኦን ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ቀደም ብሎ ግጭት መከሰቱ ይታወሳል

የግጭቱ አንዱ መንስኤ በሁለቱም ዞኖች አመራሮች ላይ የታየ ክፍተት እንደሆነ በፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ዘላቂ መፍትሄ ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ንጋቱ አብዲሳ ዛሬ ለሸገር ተናግረዋል፡፡እሳቸው እንዳሉት ስለ ግጭቱ መንስኤ ጥናት ያካሄደው ቡድን ይፋ ያደረገው ውጤቱ ይህንኑ አሳይቷል፡፡

በኋላ ላይም በተካሄደ የእርቅ ሥነ -ሥርዓት ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች መመለሳቸውን አቶ ንጋቱ አስታውሰዋል፡፡ተፈናቃዮቹ ከተመለሱ በኋላ ዳግም ሌላ ግጭት መከሰቱን ነግረውናል፡፡ግጭቱ ዳግም የተከሰበትን ምክንያት የሚያጣራ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ቡድን ዛሬ ወደ አካባቢው ያመራል ብለዋል፡፡ አጣሪ ቡድን ግጭቱን አስመልክቶ የሚደርሰበትን ውጤት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ሰኔ 5፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ስምንተኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል

የድርጅቱ ሊቀመንበርና የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኮንፈረንሱ ማጠቃላይ ላይ ለመገኘት አዳማ ገብተዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ ካለፈው እሁድ አንስቶ ስምንተኛ ድርጅታዊ ኮንፈረንሱን በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሣ ድርጅቱ የተለያዩ ፈተናዎችን እያለፈ ውጤት ማስመዝገብ ጀምሯል ሲሉ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡ኦህዴድ የህዝቡን ጥቅም ይበልጥ ለማስከበር መዘጋጀት አለበትም ብለዋል፡፡

የኦህዴድ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ደግሞ በድርጅቱ አመራር እና አባላት ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን ለማረም ግምገማ መካሄዱን አስታውሰዋል፡፡ይህንኑ ግምገማ ተከትሎ በተለያየ ደረጃ ላይ የነበሩ 1 ሺህ 500 የአመራር አባላት ከስልጣን መነሳታቸውን ተናግረዋል፡፡540 ሃላፊዎች ደግሞ ከደረጃቸው ዝቅ ብለው እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ ወጣቶች በአዲስ አመራርነት እንዲሾሙ ተደርጓልም ብለዋል፡፡በኮንፈረንሱ ላይ ሁለት ሺህ የድርጅቱ አባላት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers