• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ኢሮብ እና የፆረና አካባቢ ነዋሪዎች ውሳኔውን ተቃወሙ

በአልጀርሱ ስምምነት ተንተርሶ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመተግበር የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ የወሰደውን አቋም ተከትሎ የፆረና አካባቢ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ መከለላቸውን ተቃወሙ፡፡ የኢሮብ ነዋሪዎችም ወደ ኤርትራ መካለሉን አንደግፈውም ብለው ሰልፍ አድርገዋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በተለያዩ ምክንያቶች በግብፅ እስር ቤት የነበሩ 32 ኢትዮጵያዊያን ከእስር መፈታታቸው ተሰማ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የግብፁ ፕሬዝደንት አል ሲሲ፣ ኢትዮጵያ እና ግብፅ ከአባይ ወንዝ ጉዳይ በዘለለ እና በሌሎችም የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተሰማሙ፡፡በሶማሊያ እና በደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደቶች ላይም ለመተባበር ተስማምተዋል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች በግብፅ እስር ቤት የነበሩ 32 ኢትዮጵያዊያን ከእስር መፈታታቸው ተሰማ፡፡32 ኢትዮጵያዊያን ከግብፅ እስር ቤቶች የተፈቱት ትላንት ሲሆን ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከቅዳሜ አመሻሽ ጀምሮ በካይሮ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር ስለ ሁለቱ አገራት ግንኙነትና አካባቢያዊ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት መነጋገራቸው ተሰምቷል፡፡ግብፅ 32 ኢትዮጵያውያኑን ለመፍታት የወሰናችው ከሁለቱ መሪዎች ንግግር በኋላ መሆኑ አቶ ፍፁም ገልፀዋል፡፡ካይሮ በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀልተው ሕይወታቸው ያለፈ ኢትየጵያዊያን አስከሬን ወደ አገራቸው እንዲገባ ድጋፍ  እንደምታደርግ ቃል መግባቷን አቶ ፍፁም ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አዲስ አበባ ሲገቡ የቀድሞው የኦነግ የጦር መሪ የነበሩት እና ከ100 በላይ ወታደሮች በመያዝ ከዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ ገብተው የነበሩት ኮለኔል አበበ ገረሱ እና የቀድሞ የኦነግ አባል ኦህዴድ መስራች እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የነበሩ አቶ ዮናታን ዱቢሳን አብረዋቸው ገብተዋል፡፡ሁለቱም ኤርትራ ውስጥ የነበራቸውን የጦር ሰፈር በመተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር አዲስ አበባ የገቡ መሆናቸውን ከጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ፍፁም አረጋ ሰምተናል።
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የ939 ነገር…

ወደ 939 የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች የድረሱልኝ ጥሪዎች መቀበያ ቁጥር በቀን ከሚደወሉት 1500 ያህል የስልክ ጥሪዎች 90 ከመቶ ያህሉ የተሳሳቱ ናቸው…ብዙ ጊዜ አገልግሎት በሚሰጡን መስሪያ ቤቶች ላይ ቅሬታ ይሰማናል፡፡ ለአደጋ ድረሱልን የምንላቸው የአምቡላንስና የእሳት አደጋ መከላከያ፣ የመብራት አገልግሎት፣ የሚሰጡን መስሪያ ቤቶች ቢደወልላቸውም የማይቀበሉ፤ ቢሰሙ የማይደነግጡ ሆነዋል የሚላቸው ብዙ ነው፡፡ በዕርግጥ እንዲህ ዓይነት ሰራተኞች የላቸውም ባይባልም፤ ግን እነርሱስ ከደንበኞቻቸው ችግር የለባቸው ይሆን ? ዮሐንስ የኋላወርቅ ወደነርሱ ብቅ ብሎ ነበር፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) በትላንትናው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ መጀመሩ ተሰማ

ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) በትላንትናው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ መጀመሩ ተሰማ፡፡ ሕወሃት በስብሰባው በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ላይ እንዲሁም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውስጥ የግል ባለሐብቶችን ተሳትፎ ማሳደግ በሚሉ ርዕሶች ላይ በዝርዝር ሲወያይ ውሏል፡፡ ስብሰባው ዛሬም ይቀጥላል፡፡በተያያዘ ወሬ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) 8ኛ ኮንፍረንሱን በአዳማ ጀመሯል፡፡ ኦህዴድ በኮንፈረንሱ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተያያዘ ወሬ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) 8ኛ ኮንፍራንሱን በአዳማ ጀምሯል፡፡ ኦህዴድ በኮንፍራንሱ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቶ ሌንጮ ለታ ኦነግ ላይ ይቀርቡ ስለነበሩት ጥያቄዎች ምን ይላሉ?

ከቀድሞ የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር አመራር ከነበሩት መካከል አሁን የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የፖለቲካ ድርጅትን መስርተው፣ በሃገሪቱ ፖለቲካ ለመሳተፍ መምጣታቸው ሲዘገብ ሰንብቷል፡፡ በይዘቱ ከኦነግ ፕሮግራም ጋር ይቀራረባል ግን አዲስ አስተሳሰብ ይዘናል የሚሉት የኦዲግ አባላት የኦነግ ከፍተኛ አመራር በነበሩበት ወቅት በድርጅቱ ላይ ይቀርቡበት ስለነበሩት ጥያቄዎች አሁን ላይ ሆነው ምን ይላሉ? የኔነህ ሲሳይ የቀድሞውን የኦነግ መሪ አቶ ሌንጮ ለታን አነጋግሩዋቸዋል፡፡

ብዙ ጊዜ አገልግሎት በሚሰጡን መስሪያ ቤቶች ላይ ቅሬታ ይሰማናል፡፡ ለአደጋ ድረሱልን የምንላቸው የአምቡላንስና የእሳት አደጋ መከላከያ፣ የመብራት አገልግሎት የሚሰጡን መስሪያ ቤቶች ቢደወልላቸውም የማይቀበሉ፣ ቢሰሙ የማይደነግጡ ሆነዋል የሚላቸው ብዙ ነው፡፡ በዕርግጥ እንዲህ ዓይነት ሰራተኞች የላቸውም ባይባልም ግን እነርሱስ ከደንበኞቻቸው ችግር የለባቸው ይሆን? ዮሐንስ የኋላወርቅ ወደነርሱ ብቅ ብሎ ነበር፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ለሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት ምን ፈየደ?

ኢትዮጵያ ተበድራም ተለቅታም ከምታገኘው ገንዘብ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ገንብታለች፡፡ ይሁንና ከዩኒቨርስቲዎቹ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀውን ውጤት ለማየት አስቸግሩዋል፡፡ ዩኒቨርስቲዎቻችን ብቁ የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት “ወገቤን” የሚሉትን ያህል ለሃገሪቱ ምጣኔ ሐብት ዕድገት ያላቸው እገዛ አናሳ ነው ይባላል፡፡ ንጋቱ ሙሉ የትምህርት ሥርዓታችን ለሃገራችን ምጣኔ ሐብት ዕድገት ምን ያህል አግዟል ሲል ባለሙያ አነጋግሩዋል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኤምራልድ

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ውድ ማዕድናትን በጥቅም ላይ ለማዋል አፋጣኝ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትና አደረጃጀቱንም በኦሮሚያ ክልል እንዲሆን ለማድረግ መታሰቡን አቶ ለማ መገርሳ ተናገሩ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“ሕዝብ ሊመክርበት ይገባ ነበር…”

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ማካለል ኮሚሽን የወሰነው ውሳኔ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል ፍቃደኛ መሆኑን አሳውቋል፡፡ ጦርነቱ የተካሄደባትን ባድመን ጨምሮ ወደ ኤርትራ የሚከለለውን የኮሚሽኑን ውሳኔ እንቀበል ማለቱን የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት ይመለከቱታል ሲል የኔነህ ሲሳይ የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን አነጋግሯል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሁሉም ዘርፍ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት እንዲኖር የተስማሚነት ምዘናና አክሪዲቴሽን ሥርዓት በአግባቡ ሊደራጅ ይገባል ተባለ

“አክሪዲቴሽን ደህንነቱ ለተጠበቀ አለም” በሚል ነገ በሀገራችን ለ8ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ13ኛ ጊዜ እንደሚከበርም ሰምተናል፡፡የስራ፣ የምግብ፣ የትራንስፖርት በአጠቃላይ ሁሉም የህዝቡ የጋራ መገልገያዎች ደህንነታቸው የተጠበቁ ሊሆኑ እንደሚገባ የአለም አቀፉ አክሪዲቴሽን መመሪያ ያስቀምጣል፡፡ይህ እንዲሆን ደግሞ ደህንነታቸው በሚመለከተው አካል ሊፈተሽና ተስማሚነታቸው ሊረጋገጥ ይገባል፡፡
ይህን ሥርዓት ለማካሄድ ኢትዮጵያም አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት ከፍታ እየሰራች ነው፡፡

ጽ/ቤቱ ነገ የሚከበረውን በዓል አስመልክቶ አውደ ጥናት እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡በአውደ ጥናቱም በሀገራችን የአካባቢ ደህንነት እንዲሁም ከምግብና መድኃኒት ደህንነት ጋር የተገናኙ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ብሏል፡፡

ገለልተኛ የሆነ የአክሪዲቴሽን ሥርዓት መኖር ለንግዱ ማህበረሰብ እና ለህብረተሰቡ ለእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴ ወሳኝ ነውም ተብሏል፡፡ይህንን ነፃና ገለልተኛ የአክሪዲቴሽን ጅምር በሰፊው ለማረጋገጥ ጽ/ቤቱ እየሰራ እንደሆነ ከላከው መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡

አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያን የመንግስት ግዢ ሥርዓት በዘመነው የኤሌክትሮኒክስና የኢንተርኔት የግብይት ሥርዓት ለማከናወን ይቻል ዘንድ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ

ይህን የተመለከተ አውደ ጥናት ዛሬ በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተዘጋጀ ሲሆን በአውደ ጥናቱ ላይ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጆንሴ ገደፋ እንዳሉት ከሆነ እስካሁን ይህ ሥርዓት ተግባራዊ ሳይሆን ዘግይቷል፡፡ኔትወርክ የለም፣ ሲስተም ተቆራርጧል እየተባለ በሕዝብ ተቋማትና በግብርና መሰል ክፍያዎች ለመፈፀም ችግር በሆነበት ጊዜ እንዲህ ያለውን ግዢ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እንዴት ይታሰባል የሚል ጥያቄ አንስተን ነበር፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጆንሴ ገደፋ በተደረገው ጥናት ይህን ለማስጀመር ያህል በቂ መሰረተ ልማት መኖሩን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ በአውደ ጥናቱ ላይ የተለያዩ አገሮች ተሞክሮ የቀረበ ሲሆን ይህ ዘመናዊ የግዢ ሥርዓት ተግባራዊ መሆን ከቻለ ሙስናና ሌብነትን ይቀንሳል፣ ግልፅ የሆነ አሰራርንም ያሰፍናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከተለያዩ የሙያ ማህበራት ጋር በመተባበር መስራት ይኖርበታል ተባለ

ኤጀንሲው አሁን ባለው አደረጃጀት የተሰጠውን ጥራት የማስጠበቅ ሚና እየተወጣ አለመሆኑም ሲነገር ሰምተናል፡፡ኤጀንሲው ዛሬ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር ባደረገው ውይይት ከአስተያየት ሰጪዎች እንደሰማነው ለትምህርት ጥራት መውረድ የመንግስትን አሰራር ተጠያቂ አድርገዋል፡፡መንግስት ከትምህርት ተደራሽነት ይልቅም ጥራት ላይ እንዲያተኩር ጠይቀዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደግሎቹ ሁሉ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ይህንኑ ሚናውንም በአግባቡ እንዲወጣ ኤጀንሲው ራሱን የቻለ ሆኖ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ከመሆኑ ይልቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግስት እምነት ሊጣልባቸው ይገባል ብለዋል፡፡ተቋማቱ እምነት የተነፈጋቸው ስለመሆኑ የህግና መምህርነት ስልጠናዎች እንዳይሰጡ መከልከል እንደማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡ በትምህርት ጥራት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት እንደቀጠለ ነው፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers