• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የዛሬ ጥቅምት 27፣ 2010 ዓ.ም የሸገር ወሬዎቻችን

 • ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ ያቀረበችው ቡና በሩብ ዓመቱ ከአምናው በመጠን በ8 ቶን፣ በገቢ ደግሞ በ34 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ብልጫ አለው ተብሏል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • አዳዲስ የሽንብራና የምስር ዝርያዎች በምርምር ተፈጠሩ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የአዲስ አበባ ነዋሪ በጋራ መኖሪያ ቤቶች መጠቀም ከጀመረ ሰነበተ፡፡ ይሁንና ሕንፃዎቹ ሲገነቡ፣ ለሕፃናት መዋያ ትኩረት የሚሰጡ ባለመሆናቸው ታዳጊዎች የሚውሉበት አጥተዋል የሚል ሮሮ ይሰማል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ ቢነገርም አዲስ የሚሰሩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉድለቱን ለማስተካከል ሲጥሩ አይታይም፡፡ ነዋሪዎችም ቅሬታቸውን ከማሰማት አልታገዱም፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር የሚገኘው የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት እንፋታ ብለው ለፍርድ ቤት ካመለከቱ ሰዎች ግማሽ ያህሉን በትዳራቸው እንዲቀጥሉ አስማምቻለሁ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአዲስ አበባ ከተማ ከማዘጋጃ ቤታዊ እና ከቤት ኪራይ ገቢ ግብር ተገቢው ገንዘብ እየተገኘ አይደለም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ባለፉት አምስት ዓመታት የወባ ስርጭት በኢትዮጵያ በ50 በመቶ ቀንሷል ተብሏል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • መገናኛ ብዙሃን ፆታን መሠረት ያደረጉ ዘገባዎች ላይ የሚሰሩት ሥራ የተመጣጠነ ባለመሆኑ የሚመሩበትን ፖሊሲ ሊፈትሹ እንደሚገባ ተነገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራትን ለመቆጣር የተቋቋመው ኤጀንሲ ሥራውን በአግባቡ ማካሄድ የሚችልበት አደረጀጀት የለውም ተብሏል፡፡ ኤጀንሲው በበኩሉ ስራዬን ለማካሄድ የሚያስችለኝ መዋቅር በማዘጋጀት ለትምህርት ሚኒስቴር  ልኬያለሁ ብሏል፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • የቤት እንስሣት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ሲነዱ ተገኙ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የትራፊክ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

እናቶች ያላቸውን ባለማወቅ ህፃናት ልጆቻቸውን መመገብ ባለመቻላቸው ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተዳረጉ ነው ተባለ

እናቶች ያላቸውን ባለማወቅ ህፃናት ልጆቻቸውን መመገብ ባለመቻላቸው ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተዳረጉ ነው ተባለ፡፡እንዲህ ያሉት የአማራ ክልል የጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አበባው ገበየሁ ናቸው፡፡ዶክተር አበባው እንዳሉት ከሆነ በክልሉ 46 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት በከፍተኛ ምግብ እጥረት የተዳረጉ ናቸው፡፡ይህን ከፍተኛ ቁጥር ለመቅረፍም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በጋራ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ከነዚህም አንዱ አላይቭ ኤንድ ትራይቭ የተሰኘው ድርጅት ሲሆን ባለፉት ሦስት ዓመታትም በክልሉ 19 ወረዳዎች በሰራው ሥራ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡የድርጅቱ የýሮጀክት ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር የውልሰው አበበ ባለፉት ሦስት ዓመታት 50 በመቶ ችግሩ መቃለሉንና ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡እናቶች በቤታቸውና በጓሯቸው ያለውን ምግብ አመጣጥነው እንዲመግቡ በማድረግ ለውጡ እንደመጣ ተናግረዋል፡፡

በእርግጥ የተመጣጠነ ምግብ በሚገባ ማግኘቱ ፈተና ቢሆንም ቤት ያፈራውንና የተገኘውን ምግብ በማመጣጠን ግን ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በወጣቶች ዘንድ በቴክኒክና ሙያ ሥራዎች ላይ ለመሠማራት ያለው ፍላጎት ከ10 በመቶ በታች ነው ተባለ

በወጣቶች ዘንድ በቴክኒክና ሙያ ሥራዎች ላይ ለመሠማራት ያለው ፍላጎት ከ10 በመቶ በታች ነው ተባለ፡፡ይህም ከግንዛቤ እጥረት የመጣ ነው ተብሏል፡፡እንደየማሰልጠኛ ቦታዎች፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦቶችና ተዘዋዋሪ የወጣቶች ፈንድን የመሳሰሉ የገንዘብ ድጋፎች ቢደረጉም ለውጥ እየታየ አለመሆኑን ነው ፤ ዛሬ የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር ወይም ወወክማ የአፍሪካ የወጣቶች ቀንን አስመልክቶ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የሰማነው፡፡

በመድረኩ ላይ የቀረበው ጥናት እንደሚያመለክተው መንግሥት ለወጣቶች ከመደው 10 ቢሊየን ብር ወጣቱ የተጠቀመው ከ50 በመቶ በታች የሆነውን ነው፡፡ለዚህም ምክንያቱ በመደበኛ ትምህርቶች ስለ ቴክኒክና ሙያ ሥራዎችና ሥልጠናዎች ግንዛቤ የሚሰጡ ýሮግራሞች ስለሌሉ እንደሆን የጥናቱ አቅራቢና የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆነው ወጣት አሸናፊ መንግሥቱ ነግሮናል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ከሚገኙ ወጣቶች 43 በመቶ የሚሆኑት ተቀጥረው መሥራት የሚፈልጉ መሆናቸውንና ቀሪዎቹም በአብዛኛው በጊዜና በቦታ ያልተገደቡ እንዲሁም መደበኛ ያልሆኑ ሥራዎችን መሥራት የሚፈልጉ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር /ወወክማ/ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ዜጎችን ለማፍራት በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጌ እየሰራሁ ነው ሲል ተናግሯል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈረሙ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ለማጥበቅ ቋሚ ኮሚቴዎቹ ...

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈረሙ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ለማጥበቅ ቋሚ ኮሚቴዎቹ በጠቀሷቸው የምክር ቤቱ አሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥርና አንቀፅ ላይ ሳይግባቡ አዋጆቹን ሲያፀድቁ አርፈደዋል፡፡ሊፀድቁ ከቀረቡ አዋጆች ገሚሱ በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 በመጥቀስ የፀደቁ ሲሆን ገሚሶቹን ደግሞ ዘንድሮ በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 7/2010 መሠረት አፅድቀዋቸዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴዎቹ ረቂቅ አዋጆቹን ለማፅደቅ የሚጠቀሙት ደንብ የቀድሞውን ነው ወይንስ የአሁኑን የሚለው በሌላ ጊዜ የሚታይ ይሆናል ሲሉ ምክትል አፈ ጉባዔዋ አስታራቂ ኃሣብ አቅርበዋል፡፡ከአሥር ቀን በፊት በምክር ቤቱ ቀርበው ለዝርዝር እይታ ወደ ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ የተመሩ አራት ስምምነቶች ላይ የተጠቀሰው ዘንድሮ የተሻሻለው የምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 7/2010 ነው፡፡

የምክር ቤቱ አባልና የህግ ባለሙያው አቶ ተስፋዬ ዳባ በበኩላቸው ዘንድሮ የተሻሻለው የምክር ቤቱ የሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ አንድ አንቀፅ ብቻ  ያሻሻለ በመሆኑ መጠቀስ ያለበት የቀድሞ ደንብ ነው የሚል አቋም አላቸው፡፡ በመሆኑም በሰብሣቢነት የሚመሩት የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በምክር ቤቱ ያቀረቧቸው አምስት የስምምነት አዋጆች የቀድሞውን የምክር ቤቱን ደንብ ቁጥር 6/2008 በመጥቀስ ፀድቀዋል፡፡

የዛሬውን የእንደራሴዎቹን ስብሰባ የመሩት ምክትል አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ በቋሚ ኮሚቴዎቹ የተጠቀሱት የደንብና አንቀፅ ቁጥሮች የተለያዩ ቢሆኑም በሚፀድቁ አዋጆች ይዘት ላይ መሠረታዊ ለውጥ ስለማያመጡ ችግር አይፈጥርም ብለዋል፡፡በመጪው ጊዜም ቋሚ ኮሚቴዎቹ ለዝርዝር እይታ የሚመሩላቸውን አዋጆች ለማፅደቅ የውሣኔ ኃሣብ ሲያቀርቡ የትኛውን የአዋጅ ደንብ ቁጥር ይጠቀሙ የሚለው በመጪው ጊዜ ይታያል ብለዋል፡፡እንደራሴዎቹ ዛሬ ባካሄዱት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አራተኛ መደበኛ ስብሰባ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈፀሙ አስር ስምምነቶችን አፅድቀዋል፡፡

ትዕግሥት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥቅምት 23፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • እናቶች ያላቸውን ባለማወቅ ህፃናት ልጆቻቸውን መመገብ ባለመቻላቸው ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተዳረጉ ነው ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በወጣቶች ዘንድ በቴክኒክና ሙያ ሥራዎች ላይ ለመሠማራት ያለው ፍላጎት ከ10 በመቶ በታች ነው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • በቆሎን አጥቂው የአሜሪካ መጤ ተምች አሁንም በበቆሎ የመስኖ ማሳዎች ውስጥ አልጠፋም ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን በአየር ትራፊክ ቁጥጥር ያሰለጠናቸውን አስራ ሰባት የጁቡቲ ዜጐች በመጪው እሁድ ሊያስመርቅ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአገር አቋራጭ አውቶብሶች ትኬት በተጓዦች አቅራቢያ መገኘት በመቻሉ ተቀባይነታቸው እየጨመረ መጥታል፤ እየተለመደም ነው ተብሏል፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የአዳማ ከተማ ፖሊስ አባላት በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች በተከሰተው ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ ሰጡ ተባለ፡፡ (ማኅሌት ታደለ)
 • የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በአዋጅ ማፅደቂያ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥርና አንቀፅ ላይ ሲወዛገቡ አረፈዱ፡፡ አዋጆችን ግን አፅድቀዋል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የጊዜ ቀጠሮ ማስቻያ ችሎት በተጠርጣሪዎች ላይ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ (እሸቴ አሰፋ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ጥቅምት 21፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከውጪ ሃገር ባስገባው የልብ ህክምና ማሽን ከመስከረም 8 ወዲህ...

የቅዱስ ጳውሎስ  ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከውጪ ሃገር ባስገባው የልብ ህክምና ማሽን ከመስከረም 8 ወዲህ ብዛት ያላቸው ህሙማንን ማከሙን ተናገረ፡፡የህክምና ኮሌጁ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ነዋይ ፀጋዬ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ በ120 ሚሊየን ብር ወጪ ከውጪ በተገዛው የልብ ህክምና ማሽን በሚሊኒየም የጤና ኮሌጅ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ብዙ ሰዎች የልብ ህክምና አግኝተውበታል ብለዋል፡፡

ይህ ዘመናዊ የልብ ህክምና ማሽን ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የጤና ህክምና ኮሌጅ በተጨማሪ በጥቁር አንበሣና በመቐሌ ሀይደር ሆስፒታል ብቻ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡የህሙማኑን ብዛት ከግምት በማስገባት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የልብና የካንሰር ማዕከል ግንባታም እየተፋጠነ እንደሆነ አቶ ነዋይ ነግረውናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የዛሬ ጥቅምት 22፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ባለፉት አምስት ዓመታት አባት አይደለንም በሚል በፍርድ ቤት ሲከራከሩ ከቆዩና ወደ ሁለት መቶ ከሚጠጉ ሰዎች የዘጠና በመቶዎቹ አባትነት በባህሪያ ወሳኝ ቅንጣት /ዲ ኤን ኤ/ ምራመራ ተረጋግጧል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች በተመሳሳይ የትምህርት መስኮች ላይ ሲከተሉት የነበረውን የተለያዩ አሰራር የሚያስቀር ወጥ የሆነ ስርዓተ ትምህርት በሥራ ላይ ውሏል ተባለ፡፡ (ማኅሌት ታደለ)
 • የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በ2010 ከ4 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ሥራ አስይዣለሁ ሲል ለተወካዮች ምክር ቤት ማኅበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ተናገረ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ጥንታዊና ታሪካዊ ቤቶች ላልተገባ አገልግሎት እንዳይውሉ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከውጭ ሀገር ባስገባሁት አዲሱ የህክምና ማሽን ብዛት ያላቸው ህሙማንን እያከመ እንደሆነ ተነገረ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ተሾመለት

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ተሾመለት፡፡የዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኙነት አቶ አሰማኸኝ አስረስ እንደነገሩን በግዚያዊነት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ጀይሉ ኡመር ናቸው፡፡

ዶክተሩ አሁን ላይ ሁለቱን ኃላፊነት ተረክበው እንዲሰሩ የተሾሙት ትምህርት ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ መሠረት ነው ተብሏል፡፡ስለ ሹመቱ በደብዳቤው ተጠቅሷል ያሉት አቶ አሰማኸኝ ዶክተሩ የተመረጡት በከፍተኛ ትምህርት አመራር ምልመላና ምደባ መመሪያ መሠረት ሲሆን ፕሬዝዳንት ተመርጦ እስኪሾም ያገለግላሉ ብለዋል፡፡

የቀድሞ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት የነበሩት ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ በኢንዶኔዢያ የኢትዮጵያ አንባሳደር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል፡፡ፕሮፌሰሩ በቅርቡ ኢትዮጵያን የጎበኙትን የህንዱን ፕሬዝዳንት ራም ናት ኦቪንድን በዩኒቨርስቲያቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ይታወሣል፡፡

ምስክር አወል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኦሮሚያ ክልል የኤች.አይቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ከሚገኙ ሰዎች ውስጥ የፀረ ኤች.አይቪ መድኃኒቱን የሚወስዱት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው ተባለ

በኦሮሚያ ክልል የኤች.አይቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ከሚገኙ ሰዎች ውስጥ የፀረ ኤች.አይቪ መድኃኒቱን የሚወስዱት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡ በክልሉ በአሁኑ ሰዓት የቫይረሱ የስርጭት መጠን 0 ነጥብ 9 መሆኑን ሰምተናል፡፡

የኦሮሚያ ክልል የጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊው አቶ ነጋሽ ስሜ ለሸገር እንደተናገሩት በክልሉ በአሁኑ ሰዓት ሁለት መቶ ሺ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ የፀረ ኤች.አይቪ መድኃኒቱን ግን የሚወስዱት ግማሽ ያህሉ ናቸው ብለዋል፡፡በኦሮሚያ ክልል የኤች.አይቪ ኤድስ የስርጭት መጠን ከዚህ በፊት ከነበረበት ጨምሮ አሁን 0 ነጥብ 9 በመቶ መድረሱን የተናገሩት አቶ ነጋሽ በአንዳንድ አካባቢዎች ግን የስርጭቱ መጠን 4 ነጥብ 8 በመቶ ይደርሳል ብለዋል፡፡

የሥርጭት መጠኑ ከፍተኛ ከሆነባቸው አካባቢዎች መካከል እንደ ሞጆና አዳማ የመሳሰሉ አካባቢዎች ይገኙበታል ብለዋል፡፡ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ግዙፍ የኢንቨስትመንት አካባቢዎችም የቫይረሱ የስርጭት መጠን ከፍተኛ ከሆነባቸው አካባቢዎች ይጠቀሳሉ፡፡በክልሉ ያለውን የኤች.አይቪ ኤድስ የሥርጭት መጠን ለመቀነስ ቢሮው ይመለከታቸዋል ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሚገኝም አቶ ነጋሽ ስሜ ነግረውናል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ባለፉት ሦስት ወራት ከአዲስ አበቤ ግብር ከፋዮች 7 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ወጥኖ ነበር

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ባለፉት ሦስት ወራት ከአዲስ አበቤ ግብር ከፋዮች 7 ነጥብ 96 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ወጥኖ ነበር፡፡ተሣክቶለት የሰበሰበው ግን ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ቅናሸ ያለው 6 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መሆኑን ለሸገር ተናግሯል፡፡

የነጋዴዎችን የቀን ገቢ ግምት ክለሣ ተከትሎም የቀረቡ ቅሬታዎችን ለማስተናገድ የወሰደው ጊዜና የሰው ኃይል በገቢ አሰባሰቡ ላይ ትልቅ ጫና ፈጥሮብኛል ብሏል፡፡በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የአዲስ አበባ ግብር አወሣሰንና አሰባሰብ ፕሮግራም ዳይሬክተሩ አቶ ያሬድ ፈቃደ እንደነገሩን ከተሰበሰበው የአንድ ቢሊየን ብር ቅናሽ ካለው ገቢም ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው ከደሞዝተኛው የተገኘው ነው ብለዋል፡፡

ከተቀጣሪው የአዲስ አበባ ነዋሪ 2 ነጥበ 3 ቢሊየን ብር መሰብሰቡንም ነግረውናል፡፡
ይህም ከተገኘው ገቢ 33 በመቶውን ድርሻ ይይዛል የተባለ ሲሆን ከእቅዱም 97 ነጥብ 5 በመቶ የተሣካበት ነው ብለውናል አቶ ያሬድ፡፡ከነጋዴዎች የተሰበሰው ገቢ ከአጠቃላይ ገቢው 22 በመቶውን ድርሻ የያዘ ሲሆን 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ተሰብስቦበታል መባሉንም ሰምተናል፡፡

ባለፈው መስከረም 10 ቀን 2010 ዓ.ም ግብራቸውን ከፍለው ማጠናቀቅ ከሚጠበቅባቸው የደረጃ “ለ” ግብር ከፋዮች መካከልም እስካሁን 20 በመቶው ግብር አልከፈሉም ያሉት አቶ ያሬድ በነጋዴው ዘንድ የቀን ገቢ ግምት ክለሣውን ተከትሎ የነበረው ቅሬታን የማስተናገድ ሥራ በገቢ አሰባሰቡ ላይ ትልቅ ጫና ፈጥሮብን ነበር ብለዋል፡፡

ባለፉት ሦስት ወራት ለመሰብሰብ ከታቀደው የ1 ቢሊየን ብር ቅናሽ ያለው ገቢ ቢገኝም እስካሁን ያልከፈሉት የደረጃ ሀሌታው “ሀ” 69 በመቶዎቹና የደረጃ “ለ” ሃያ በመቶዎቹ ግብራቸውን ሲከፍሉ ገቢው ከፍ ይላል ተብሎም ተስፋ ተደርጓል፡፡

ትዕግሥት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers