• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

እግር አልሰራ ሲል እጅ እግር ይሆናል…

ለማ ጅማ ገና የ3 ዓመት ጨቅላ ሳለ ነበር የእግሩ ነገር አልሆን ያለው፡፡ አላስቆም አላስኬድ አለው፡፡ በእጆቹ ተገልብጦ መሄድ ጀመረ፡፡ የ5 ልጆች አባት የሆነው እና አሁን በሚያገኛት ጡረታ የሚተዳደረው ለማ እያረፍኩም ቢሆን አንድ ጤነኛ ሰው በእግሩ የሚሄደውን ያህል እሄዳለሁ ይላል፡፡

ደረጃ እና ፎቅ መውጣት ቢፈትነኝም ቁልቁለት ግን የውሃ መንገድ ነው ለእኔ ይላል፡፡70 ደረጃን በ5 ደቂቃ እወርዳለሁ ባይ ነው - ለማ፡፡የማይቻል ነገር የለም የሚለው ለማ ደስተኛ ነው፡፡ ተገልብጦ በእነዛ ጠንካራ እጆቹ በፍጥነት ሲሄድ ያዩ ሁሉ ይገረማሉ፡፡

እጆቹ ሁሉ ነገሮቹ ናቸው፡፡ ይሄድባቸዋል፤ ይበላባቸዋል…በኢንጪኒ ወረዳ የአካል ጉዳተኞች ማህበር ሊቀመንበር ሆኖም ብዙዎችን አስተምሯል ይለናል ለማን ያነጋገረው ወንድሙ ኃይሉ፡፡

ለማ እንዲህ የጠነከርኩት በእጄ ስለሄድኩ ነው ይለናል፡፡የለማን ነገር የሰማው ቼሻየር ለለማ ተሽከርካሪ ወንበር ሰጥቶታል…ወደ ዩትዩብ ቻናላችን ጎራ ብላችሁ ሙሉውን ያዳምጡ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መሪ ራስ አማን በላይ (1942-2010) - ሦስተኛ እና የመጨረሻ ክፍል

ተፈሪ ዓለሙ በ“ትዝታ ዘ አራዳ” መሰናዶው በያዝነው ዓመት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩንን ኢትዮጵያዊውን ምሁር መሪ ራስ አማን በላይን የዘከረበትን ሦስተኛ እና የመጨረሻ ክፍል

እነሆ ብለናል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የወንጀል ተከሳሾች የጥብቅና አገልግሎት መስጠቱን ተናገረ

በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የወንጀል ተከሳሾች የጥብቅና አገልግሎት መስጠቱን ተናገረ፡፡የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤቱ በ2010 ዓ/ም 6 ወራት በሁሉም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ባሉ የወንጀል ችሎቶች ለተከሰሱና ጠበቃ የማቆም አቅም ለሌላቸው 3526 ተከሳሾች ነው አገልግሎቱን የሰጠው፡፡

ጽ/ቤቱ ለተከሳሾች በጥብቅና ከመቆም በተጨማሪ በፍ/ቤት ክርክር የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በማዘጋጀት፣ በህግ ምክር በማድረግ ድጋፍ አድርጓልም ተብሏል፡፡በወንጀል ተከሰው በራሳቸው ጠበቃ ለማቆም እና ለመከራከር የማይችሉ ተከሳሾች የክርክር ሰነድ በማዘጋጀት እና ለተከሳሾች በማረሚያ ቤት በመገኘት የህግ ድጋፍ ማድረጉን ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰምተናል፡፡

ጽ/ቤቱ በዚህ አመት በነፃ የጥብቅና አገልግሎት የሰጣቸው ተከሳሾች ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ሲመሳከርም ብልጫ ያለው ነው ተብሏል፡፡የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት ስራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ50 ሺ በላይ ለሚሆኑ ተከሳሾች የነፃ የህግ ድጋፍና የጥብቅና አገልግሎት መስጠቱ ተናግሯል፡፡

ምህረት ስዩም

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ 11 ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ታግደዋል ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ሀሰት መሆኑን እወቁልኝ አለ

የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ 11 ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ታግደዋል ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ሀሰት መሆኑን እወቁልኝ አለ፡፡ኤጀንሲው በላከልን መግለጫ እንደተናገረው ማሪስቶፕስና ቼሻየር ፋውንዴሽንን ጨምሮ 11 ድርጅቶች በአዲስ አበባው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ መታገዳቸው በሚዲያ ተላልፏል፡፡

“ይህ ግን ሀሰት ነው፡፡ በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ማህበራትን ፈቃድ የመስጠትና ጥፋት ሲገኝባቸውም የመዝጋት ስልጣኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ነው” ብለዋል፡፡በመሆኑም ታግደዋል የተባሉት 11 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ስራቸውን እንደወትሮ እየከወኑ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል ኤጀንሲው ፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ባለፉት 10 ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ለልማት የወሰዱትን ቦታ አጥረው ያስቀመጡ የ14 ተቋማትን ውል ማቋረጡን የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ተናገረ

ባለፉት 10 ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ ለልማት የወሰዱትን ቦታ አጥረው ያስቀመጡ የ14 ተቋማትን ውል ማቋረጡን የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ተናገረ፡፡ ከነዚህም ውስጥ 7ቱ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ናቸው፡፡ የመጨረሻ የውል ማራዘሚያ ከተደረገላቸው 120 ተቋማት መካከል እስካሁን በውሉ መሰረት ወደ ግምባታ የገቡ 25 ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

የትዕግስት ዘሪሁንን ዝርዝር ዘገባ ያዳምጡ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ሲዘከር

የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ሲዘከር…ተፈሪ ዓለሙ በ“ትዝታ ዘ አራዳ” መሰናዶው የየካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም የፋሺስት ጣልያን ጭፍጨፋን የዘከረበትን ፕሮግራሙን ወደ ኦፊሺያል የዩትዩብ ቻናላችን ጎራ ብላችሁ እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

16ኛው የአፍሪካ መንገዶች ጥገና ፈንድ ማህበር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

16ኛው የአፍሪካ መንገዶች ጥገና ፈንድ ማህበር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡ጉባኤው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን /ECA/ መሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ የተጀመረ ሲሆን እስከ አርብ ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡የአፍሪካ መንገዶች ጥገና ፈንድ ማህበር የመንገድ ፈንድ መስሪያ ቤት ባላቸው 35 የአፍሪካ አገራት የተቋቋመ ማህበር ሲሆን አላማው በማህበሩ አባል አገራት የሚገኙ መንገዶችን በአግባቡ በመጠገን ለመጠበቅና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መሆኑን በጉባኤው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተን ሰምተናል፡፡

ዛሬ በተጀመረው ጉባኤ ላይ ከ35 ከአፍሪካ አገራት የመጡ የመንግስት ሀላፊዎችና ሙያተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ጉባኤተኞቹ በ5 ቀን ቆይታቸው ስለ መንገድ አጠቃቀም አጠባበቅና እንዲሁም የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ተነግሯል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ተሳታፊዎቹ ከለቡ አዳማ የባቡር ጉዞ ያደርጋሉ ተብሎ ፕሮግራም ተይዞላችኋል፡፡

ጉባኤውን በክብር እንግድነት ተገኝተው የከፈቱት የኢትዮጵያ የትራንስፖርት ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የአገሪቱ የመንገድ ርዝማኔ ከ100 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መድረሱን ተናግረው በአሁኑ ሰዓትም ካለው አጠቃላይ መንገድ 55 በመቶ የሚሆነው በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ነው ብለዋል፡፡ኢትዮጵያ የአፍሪካ መንገዶች ማህበርን ከዛሬ 3 አመት ጀምሮ በፕሬዝዳንትነት እየመራች መሆኑንም ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፉት 5 አመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከቆዩ በኋላ ከእንግዲህ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመባል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፉት 5 አመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከቆዩ በኋላ ከእንግዲህ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመባል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ከስልጣን በገዛ ፈቃድ ለመልቀቅ ብርቅ በሆነበት ኢትዮጵያ እርሳቸው እንዳሉት በፈቃዳቸውና በፍላጎታቸው መልቀቃቸው ስልጣን በሰላም በማሸጋገር ረገድ አርአያ ሆነዋል የሚል አስተያየት ሰጪዎች አሉ፡፡

እሸቴ አሰፋ ከሰነድና ከድምፅ ያገኛቸውን አስተያየቶች አጠናቅሮ ስለ አቶ ኃይለማርያም በጥቂቱ ይነግረናል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈርጌሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አስመልክተው በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው

“የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ሕገመንግሥቱን እና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን ለማስከበርና ከአደጋ ለመጠበቅ፤ የሕዝብና የዜጎችን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፣ ማንኛውም ሁከት፣ ብጥብጥና በሕዝቦች መካከል መጠራጠርና መቃቃር የሚፈጥር ይፋዊም ሆነ የድብቅ ቅስቀሳ ማድረግን፣ ፅሁፍ ማዘጋጀት፣ ማተምና ማሰራጨትን፣ ትዕይንት ማሳየትን በምልክት መግለፅን፣ ወይም መልዕክትን በማንኛውም ሌላ መንገድ ይፋ ማድረግን ይከለክላል፡፡

ማንኛውንም የመገናኛ ዘዴ እንዲዘጋ ወይም እንዲቋረጥ ሊያደርግ ይችላል፡፡የዜጎችንና የሕዝቦችን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል የአደባባይ ሰልፍ፣ ሰልፍ ማድረግን፣ መደራጀት፣ በብዙ ሰው ሆኖ መንቀሳቀስን ይከለክላል - ዝርዝሩ በመመሪያ ይወጣል፡፡

በሕገመንግሥቱና በሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ ላይ የሚቃጡ ወንጀሎችን የጠነሰሰ፣ የመራ፣ ያስተባበረ፣ የጣሰ ወይም ደግሞ በማንኛውም መንገድ በወንጀል ድርጊቱ የተሳተፈ ወይም ተሳትፏል ተብሎ የሚጠረጠርን ማንኛውንም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ያደርጋል፤ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ በመደበኛው ሕግ ተጠያቂ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ወንጀል የተፈፀመባቸውን ወይም ሊፈፀምባቸው የሚችሉ እቃዎችን ለመያዝ ሲባል ማናቸውንም ቤት፣ ቦታ፣ ማጓጓዣ ለመበርበርና እንዲሁም ማናቸውንም ሰው በማስቆም ማንነቱን ለመጠየቅ፣ ለመፈተሽ ይቻላል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለቅኔ እና ፀሐፊ ተውኔት መንግሥቱ ለማ

ባለቅኔ እና ፀሐፊ ተውኔት መንግሥቱ ለማ፣

ተፈሪ ዓለሙ፣ ባለቅኔ እና ፀሐፊ ተውኔት መንግሥቱ ለማን የዘከረበትን መሰናዶውን ወደ ሸገር ኦፊሺያል የዩትዩብ ቻናላችን ጎራ ብላችሁ እንድታዳምጡ እንዲሁም ቻናላችንን Subscribe እንድታደርጉ እንጋብዛለን…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በገዛ ፍቃዳቸው የሥራ መልቀቂያ ማቅረባቸውን ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በገዛ ፍቃዳቸው የሥራ መልቀቂያ ማቅረባቸውን ተናገሩ…ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የመንግሥትና የኢህአዴግ ሀላፊነታቸውን ለመተው ለድርጅታቸውም፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የሥራ መልቀቂያቸውን አስገብተዋል፡፡

የሥራ መልቀቂያቸው ተቀባይነት እንደሚያገኝ ተስፋ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሥራ መልቀቂያ ያስገቡት በአገሪቱ በተከሰተው ችግር የመፍትሄ አካል ለመሆን አስበው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers