• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ:- መንግስት ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ይበልጥ የሚያበረታታቸው ግብዓታቸውን ከሃገር ውስጥ የሚያደርጉትን መሆኑን ተናግረዋል

ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የ2011ን በጀት ለማፅደቅ በተጠራው ጉባኤ ላይ፣ መንግስት ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ይበልጥ የሚያበረታታቸው ግብዓታቸውን ከሃገር ውስጥ የሚያደርጉትን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በኦዲት የተገኙ ክፍተቶችን ካለስተካከለ ስራ አስፈፃሚው ተጠያቂነት እንደማይቀርለት አረጋግጠዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ምሁራን አሁን የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ምሁራን አሁን የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሠላም ኮሚቴ አባላት በእስካሁን ስራዎቻቸው እና ቀጣይ ዕቅዶቻቸው ዙሪያ ትናንት በሃርመኒ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡የኮሚቴዎቹ አስተባባሪዎች እንዳሉት ነሃሴ ወር አጋማሽ ላይ የሁለቱም ሀገራት ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፎች የሚያቀርቡበት አውደ ጥናት እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ በአውደ ጥናቱ የሚቀርቡት ፅሁፎች የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሻሻል የሚረዱ እንደሚሆኑ በኢትዮጵያ በኩል የሠላም ኮሚቴው አስተባባሪ የሆኑት ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሠ ተናግረዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት መንግስታት ግንኙነታቸውን ለማሻሻል እርምጃዎች መውሰድ መጀመራቸው የኮሚቴዎቹን ጥረት የሚደገፍ ነውም ብለዋል፡፡አሁን ያለው ሁኔታ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሙሁራን በነጻነት ተቀራርበው እንዲወያዩ የሚያስችል እንደሆነም ፕሮፌሰር መድሃኔ ተናግረዋል፡፡ምሁራን ያልተሳተፉበት የሠላም ጥረት ብዙም ውጤታማ ይሆናል ተብሎ እንደማይገመትም ተናግረዋል፡፡

በኤርትራ በኩል የሠላም ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ይስሃቅ ዮሴፍ በበኩላቸው በሁለቱ መንግስታት በኩል እየተደረጉ ያሉ ግንኙነትን የማሻሻል ጥረቶች - የህዝቡንም ፍላጎት ከግምት ባስገባ መልኩ ሊሆኑ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ህዝቦች እየተዘጋጀ ያለው የሠላም መዝሙርም ወደ መጠናቀቁ እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ሲነገር ሠምተናል፡፡በአማርኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎች የሚዘጋጀው ይህ መዝሙር በርካታ አርቲስቶች የሚሳተፉበት እንደሆነ በ ሴሌብሪቲ ኢቨንትስ አዘጋጅነት በተሰጠው በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ምሁራን አሁን የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ምሁራን አሁን የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሠላም ኮሚቴ አባላት በእስካሁን ስራዎቻቸው እና ቀጣይ ዕቅዶቻቸው ዙሪያ ትናንት በሃርመኒ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የኮሚቴዎቹ አስተባባሪዎች እንዳሉት ነሃሴ ወር አጋማሽ ላይ የሁለቱም ሀገራት ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፎች የሚያቀርቡበት አውደ ጥናት እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ በአውደ ጥናቱ የሚቀርቡት ፅሁፎች የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሻሻል የሚረዱ እንደሚሆኑ በኢትዮጵያ በኩል የሠላም ኮሚቴው አስተባባሪ የሆኑት ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሠ ተናግረዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት መንግስታት ግንኙነታቸውን ለማሻሻል እርምጃዎች መውሰድ መጀመራቸው የኮሚቴዎቹን ጥረት የሚደገፍ ነውም ብለዋል፡፡አሁን ያለው ሁኔታ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሙሁራን በነጻነት ተቀራርበው እንዲወያዩ የሚያስችል እንደሆነም ፕሮፌሰር መድሃኔ ተናግረዋል፡፡ምሁራን ያልተሳተፉበት የሠላም ጥረት ብዙም ውጤታማ ይሆናል ተብሎ እንደማይገመትም ተናግረዋል፡፡

በኤርትራ በኩል የሠላም ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ይስሃቅ ዮሴፍ በበኩላቸው በሁለቱ መንግስታት በኩል እየተደረጉ ያሉ ግንኙነትን የማሻሻል ጥረቶች - የህዝቡንም ፍላጎት ከግምት ባስገባ መልኩ ሊሆኑ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ ህዝቦች እየተዘጋጀ ያለው የሠላም መዝሙርም ወደ መጠናቀቁ እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ሲነገር ሠምተናል፡፡በአማርኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎች የሚዘጋጀው ይህ መዝሙር በርካታ አርቲስቶች የሚሳተፉበት እንደሆነ በ ሴሌብሪቲ ኢቨንትስ አዘጋጅነት በተሰጠው በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለሀገሪቱ የኪነ-ጥበብ ውድቀት ዋናው ተጠያቂ ድህነት ነው ተባለ

ለሀገሪቱ የኪነ-ጥበብ ውድቀት ዋናው ተጠያቂ ድህነት ነው ተባለ፡፡እንዲህ የተባለው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ትላንት ማምሻውን በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ወርሃዊ ውይይት ባካሄደበት ጊዜ ነው፡፡አካዳሚው ለአመቱ መጨረሻ ነው ባለውና የኢትዮጵያ ሙዚቃና ማህበራዊ ፋይዳው በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ውይይት ላይ አርቲስት አብርሃም ወልዴ ገለፃ አቅርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡

አርቲስት አብርሃም ወልዴ በገለፃው የሙዚቃ ኖታዎች ዛሬ በምዕራባውያን ስማቸው ተቀይሮ ቢመጣም የዚህ ፈጠራ መነሾ ከ1 ሺህ አመታት በፊት በቅዱስ ያሬድ ነው ብሏል፡፡ይህ ዘመናት ያስቆጠረ የሙዚቃ ስራ አሁን ላይ ለውድቀት የተቃረበው በድህነታችን ምክንያት ነው ሲል ተናግሯል፡፡ ይኸው ድህነት ድምፃውያንን የውጪውን የሙዚቃ ቀላዋጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብሏል፡፡የፈጠራ ስራ ከባድ መሆኑና የጥበብ ኩረጃ እጅግ ቀላል እየሆነ መምጣት ሌላው ለሙዚቃው ውድቀት እንደ ምክንያትነት ተነስቷል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የባህረተኞች ኩብለላ ኢትዮጵያን እምነት እያሳጣና ተስፋ እያስቆረጠ መሆኑ ተነገረ

የባህረተኞች ኩብለላ ኢትዮጵያን እምነት እያሳጣና ተስፋ እያስቆረጠ መሆኑ ተነገረ፡፡ 80 ያህል ኢትዮጵያውያን ከሚሰሩበት መርከብ ላይ በመኮብለል ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና እስያ ሐገራት ጭምር መጥፋታቸው ታውቋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ዮሐንስ የኋላወርቅን ሙሉውን ዘገባ ያዳምጡ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር በሆኑ ማግስት ብዙ የለውጥ ተስፋዎችን ብናይም ከሰኔ 16ቱ ሰልፍ በኋላ ነገሮች ተቀልብሰዋል ሲል አረና ፓርቲ ተናገረ

ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር በሆኑ ማግስት ብዙ የለውጥ ተስፋዎችን ብናይም ከሰኔ 16ቱ ሰልፍ በኋላ ነገሮች ተቀልብሰዋል ሲል አረና ፓርቲ ተናገረ፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አብረሃ ደስታ፣ የተደረጉት ሰልፎች የሐገር አንድነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.የኔነህ ሲሳይን ሙሉውን ዘገባ ያዳምጡ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጅቡቲ ገብተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጅቡቲ ገብተዋል፡፡ የጉብኝታቸው ዓላማ በጅቡቲ በኩል የሚገቡና የሚወጡ ሸቀጦች የትራንዚት መጓተት ሳያጋጥማቸው እንዲሁም በተመጣጣኛ ክፍያ በፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ መድረስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ለመነጋገር ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን አስመጪና ላኪዎች የተመቸ ሁኔታ ይኖር ዘንድ የወደብ አጠቃቀም ሥርዓቱ ይበልጡን ፈጣን ይሆን ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለጅቡቲው አቻቸው የመፍትሄ ሐሳባቸውን ያቀርባሉ ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሃላፊው አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብር ጅቡቲ ትልቁን የነፃ ንግድ ቀጠና በማሳካቷ አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ የወደብ አጠቃቀምን፣ ተመጣጣኝና የሌሎችን ዋጋ ታሳቢ ያደረገ የወደብ ክፍያ ሥርዓትን፣ ያልተጓተተ የወደብ አገልግሎትን፣ የወደብ መሰረተ ልማትን በጋራ በማልማት እንዲሁም ከጋላፊ እስከ ጅቡቲ ያለውን መስመር በማጠናከር ዙሪያ ከጅቡቲ ጋር በትብብር ለመስራት ትፈልጋለች ብለዋል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በጌድዮ እና ጉጂ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎችን ሁኔታ የሚያጠና የልዑካን ቡድን ለሶስተኛ ጊዜ መላኩ ተሠማ

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን እና ደቡብ ክልል ጌድዮ ዞን አዋሳኝ አካባቢ ያሉ ዜጎች በስብጥር ይኖራሉ፡፡ በአካባቢው የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ግን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በዶንጎሬ ባህላዊ ስነ ስርዓት ዕርቅ ከተፈጸመ በኋላ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀዬቻቸው ተመልሰው እንደነበር - በፌዴራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስቴር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ዘላቂ መፍትሄ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ንጋቱ አብዲሣ አስታውሰዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ወደ ቀዬያቸው ከተመለሱ በኋላም ግን ሌላ ግጭት ተከስቶ ዳግም መፈናቀል አጋጥሟል ብለዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ሁኔታ የሚገመግም የልዑካን ቡድን ለሶስተኛ ጊዜ ወደ አካባቢው እንደተላከ ከአቶ ንጋቱ ሠምተናል፡፡ ቡድኑ ተፈናቃዮቹን ሊያጋጥም የሚችል የጤና ችግር አለ ወይስ የለም የሚለውን ይገመግማል ብለዋል፡፡ ቡድኑ ፍትሃዊ የዕርዳታ ክፍፍል ስለመኖሩ እንዲሁም በግጭቱ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ሰዎች ወደ ህግ ስለሚቀርቡበት መንገድም ያጣራል ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት የተላኩት ሁለት የልዑካን ቡድኖች ስለ ግጭቱ መንስኤ እና ተፈናቃዮቹ ስላሉበት ሁኔታ አጣርቶ እንደተመለሰ ዳይሬክተር ጄኔራሉ ነግረውናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መንግስት ባጋጠመው የገንዘብ ችግር ምክንያት በ2011 በጀት አመት አዲስ የሚጀመር ፕሮጀክት አይኖርም ተባለ

መንግስት ባጋጠመው የገንዘብ ችግር ምክንያት በ2011 በጀት አመት አዲስ የሚጀመር ፕሮጀክት አይኖርም ተባለ፡፡ የተያዘው ረቂቅ በጀት ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ የሚሆን ነው ተብሏል፡፡ በመጪው አመት በተለየ ሁኔታ የግብር ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ መሰብሰብ ካልተቻለ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅም አስቸጋሪ እንደሚሆን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ተናግረዋል፡፡

የውጪ እርዳታና ብድር የተገኘላቸው ውስን የመንገድ ፕሮጀክቶች ግን በ2011 ዓ/ም ይገነባሉ ተብሎ ውጥን ተይዟል፡፡ በመሆኑም በመጪው አመት የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ 211 ቢሊየን ብር የግብር ገቢ መሰብሰብ ይጠበቅብናል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

ባለፉት 2 አመታት አገሪቱ የሰበሰበችው የግብር ገቢ ዝቅተኛ በመሆኑ ለ2011 ዓ/ም ለፌዴራል መንግስት መደበኛ በጀት የተያዘው ገንዘብ ከዘንድሮ በ4 ነጥብ 4 በመቶ ዝቅ እንዲል የተደረገው ባለው የገቢ ችግር ምክንያት መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም እንዳሉት ኢትዮጵያ ከፍ ባለ ደረጃ ገቢ የመሰብሰብ አቅሟ ካልተሻሻለ እንዲህ ተሸጋሽጎና ተጣቦ የተያዘውን በጀት አግኝቶ ስራዎችን ለመከወን አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ የአገሪቱ የገቢ አቅም ካላደገም የዜጎችን የእድገትና የልማት ፍላጎት ማሟላት ዳገት ይሆንብናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይሄንን ያሉት ከሕዝብ እንደራሴዎች አባላት ጋር ለ2011 ዓ/ም በተያዘው ረቂቅ በጀት ላይ ሲወያዩ ነው፡፡ መንግስት ከያዘው 346 ቢሊየን ብር ረቂቅ በጀት 60 በመቶውን እንደ መንገድ ፣ ጤና ፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እና የምግብ ዋስትና ችግር ላለባቸው ዜጎች የሚሆን ልማታዊ ሴፍቲኔት ላሉ ድህነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን ለመከወን ነው፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለፉት 7 አመታት መንግስት በሽብርተኝነት ፈርጇቸው የቆዩት ኦነግ ኦብነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅቶች ከአሸባሪነት ዝርዝር እንዲሰረዙ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ወሰነ

ባለፉት 7 አመታት መንግስት በሽብርተኝነት ፈርጇቸው የቆዩት ኦነግ ኦብነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅቶች ከአሸባሪነት ዝርዝር እንዲሰረዙ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ወሰነ፡፡ ምክር ቤቱ በ2003 ዓ/ም ሶስቱንም ድርጅቶች አሸባሪዎች ናቸው ሲል ወስኖባቸው እንደነበር ለፍረጃ መሻሪያው የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ አስታውሷል፡፡

መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ የኦነግ ፣ ኦብነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅቶች አመራርና አባላት ሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ዓላማችንን እናራምዳለን የሚል አቋማቸውን በማሳወቃቸው ተሰጥቷቸው ከነበረውን የሽብርተኝነት ስያሜ መሻር አስፈልጓል ተብሏል፡፡ ድርጅቶቹ ሙሉ በሙሉ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ለመንቀሳቀስ የሰጡት ማስተማመኛና ማረጋገጫ ምንድነው የሚል ጥያቄ ያነሱ የምክር ቤት አባላት ነበሩ፡፡
 
ዋና ዐቃቤ ህግ ብርሃኑ ፀጋዬ ድርጅቶቹ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወስነናል ብለው ቃላቸውን ሰጥተውናል ብለዋል፡፡የምናረጋግጠው ግን በተግባርና በሒደት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ድርጅቶቹን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ለመሰረዝ ለምክር ቤቱ ቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በሙሉ ድምፅ ፅድቋል፡፡በተያያዘ በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ለተሳተፉ ሰዎች ምህረት ለመስጠት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች አሁንም የግጭት ስጋቶች መኖራቸው ተነገረ

በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች አሁንም የግጭት ስጋቶች መኖራቸው ተነገረ፡፡ በሁለቱም ወገን የታጠቁ ሃይሎችን ወደ ወሰን የማስጠጋት አዝማሚያ ይታያል ተብሏል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers