• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከ10ኛ እና ከ12 ክፍል ውጪ ያሉትን ከክፍል ክፍል የመዘዋወሪያ ነጥብ በመወሰን በየዓመቱ በከተማዋ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያሳውቃል

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከ10ኛ እና ከ12 ክፍል ውጪ ያሉትን ከክፍል ክፍል የመዘዋወሪያ ነጥብ በመወሰን በየዓመቱ በከተማዋ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ያሳውቃል፡፡ይሁን እንጂ ከቢሮ የሚሰጣቸውን የማለፊያ ነጥብ ችላ በማለት የራሳቸውን በመወሰን የሚሰሩ የግል ትምህርት ቤቶች ያሉ መሆኑ ይነገራል፡፡

ከዚም አልፎ ከመስከረም እስከ ሰኔ ባለው የትምህርት ወቅት ተምረው ያላለፉ ተማሪዎችን ክረምት ውስጥ በማስተማር የሚያዘዋውሩ መሆኑን ሰምተናል፡፡ይህ አሰራር ለትምህርት ቤቶቹ ገንዘብ ከመሰብሰቢያነት ባለፈ ለተማሪዎቹ ምንም የማይጠቅምና ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሊያመጣ እንደማይችል ስለጉዳዩ የተጠየቁ መምህር ለሸገር ተናግረዋል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.በየነ ወልዴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትወልደ ኢትዮጵያውያንን ሊያነጋግሩ ነው

ሥነ ሥርዓቱ ለመጪው ወር አጋማሽ ቀጠሮ እንደተያዘለት ታውቋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዋሽንግተን ዲሲ እና በሌሎችም የአሜሪካ አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለማነጋገር በሐምሌ መጨረሻ ቀጠሮ መያዛቸውን ዛሬ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሰምተናል፡፡ይሄንኑ ሥነ-ሥርዓት የሚያስተናብር ኮሚቴ መቋቋሙ ታውቋል፡፡ከግንቦት ወር ጀምሮ በራሱ ተነሳሽነት ስራ ጀምሯል የተባለው ኮሚቴ “ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የሚነጋገሩበትን መድረክ በዋሸንግተን ዲሲ እና በሎስ አንጀለስ ማዘጋጀቱን የኮሚቴው ሰብሳቢ ተናግረዋል፡፡

በአገር ውስጥ ከተቋቋመው ኮሚቴ በተጨማሪ በዋሽንግተን ዲሲ በአምባሳደር ካሳ ተክለ ብርሃን፣ በሎስ አንጀለስ ደግሞ በዋና ቆንስሉ የሚመሩ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል ተብሏል፡፡በዋሽንግተንና በሎስ አንጀለስ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሚደረገው ንግግር ከ20 ሺ የማያንሱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንደሚካፈሉ ታውቋል፡፡ በአጋጣሚው የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በዚያ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር የምታከናውነው የእርቀ ሰላም ሥነ ሥርዓትም ይጠበቃል ተብሏል፡፡ ለሁለት የተከፈውን ሲኖዶስ ለማሸማገል ባለፉት 6 ወራት በተደረገ ጥረት እርቅ ለማውረድ መስማማታቸውን ሰምተናል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአሜሪካ የሚያደርጉት ጉብኝት ከተለመደው የስራ ጉብኝት በተለየ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ለማነጋገር የተዘጋጀ ብቻ ነው ተብሏል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በውጭ ሀገራት በህክምና ሙያ ላይ ተሰማርተው የሚሰሩ ባለሙያዎች ዘመናዊ የህክምና ማዕከል ሊገነቡ መሆኑ ተነገረ

መኖሪያ እና መስሪያቸው በአሜሪካ እና አውሮፓ እንዲሁም ሌሎች ሀገራት ያደረጉ ከ3 መቶ በላይ የህክምና ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ መሆናቸውን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አሜሪካን ዶክተስ ግሩፕ እና በኢትዮጵያ የፅንስና የማህፀን ሀኪሞች ማህበር በጋራ በተዘጋጀ አመታዊ ምክክር ላይ ተናግረዋል፡፡ባለሙያዎቹ በአዲስ አበባ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የህክምና ማዕከል ግንባታ መጀመራቸውም ተነግሯል፡፡

ኢትዮ አሜሪካን ዶክተርስ ግሩፕ የተባለው የባለሙያዎቹ ስብስብ ትናንት በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት /ፓስተር/ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ስለሚያደርጓቸው እገዛዎች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የህክምና ባለሙያዎች በእውቀታቸው እና በገንዘባቸው ለማገልገል ያሳዩት ፍላጎት የሚበረታታ እንደሆነ እና ከዚህ በላይ መስራት እንዳለባቸው የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ተናግረዋል፡፡

በመንግስት ከተገኘ 60 ሺ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታው የተጀመረው የህክምና ማዕከል 110 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚደረግባት ሲሆን ሆስፒታሉ ግንባታው ሲጠናቀቅ የልብ እና የአጥንት ቀዶ ህክምና እንዲሁም የካንሰር ህክምና አገልግሎችን ይሰጣል ሲሉ የኢትዮ አሜሪካን ዶክተርስ ግሩፕ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ግርማ ተፈራ ተናግረዋል፡፡ሆስፒታሉ ግንባታው በ3 አመታት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የታሰበ ሲሆን ለውጭ ሀገራት ህክምና የሚወጣ ወጭ በማስቀረት የተሻለ የህክምና በሀገር ውስጥ ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የባህል ማዕከላት ጠቃሚ እሴቶችን በማጉላት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲቀሩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ተናገሩ

ሚኒስትሯ ወይዘሮ ፎዚያ አሚን ንግግሩን ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባህል ማዕከል ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል ያዘጋጀውን የባህል ማዕከላት ሚና ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ የሚል መጠሪያ ያለው የውይይት መድረክ በንግግር በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡በንግግራቸውም አንድ ባህል አስፈላጊ የሚሆነው ጠቃሚ እሴቶችን ማጉላትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በተለይም ጥላቻና ቂምን ማስወገድ ሲችል ነው ብለዋል፡፡

ይህ እንዲሆን ደግሞ የባህል ማዕከላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡የባህል ማዕከሎቹ አገር በቀል እውቀቶችን በማልማት እና በማስተዋወቅ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ማወቅ አለባቸው ብለዋል፡፡የባህል ማዕከሎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚፈለግባቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትና የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር መወያየታቸው ተሰማ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትና የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር የተወያዩት በጋራ እና በተናጠል መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ሸገር ሰምቷል፡፡ሁለቱ ወገኖች በመካከላቸው ያሉ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነና በእስልምና አስተምህሮ መሰረት ለመፍታት መስማማታቸው ተነግሯል፡፡ ችግሮቻቸውንም ለመፍታት አዲስ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡

ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት የተቋቋመው ኮሚቴ ዛሬ የሰላም ኮንፍረንስ በእስልምና ጉዳዮችና ጠቅላይ ምክር ቤት እያካሄደ ነው፡፡የኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ ቀዳሚ ሙፍቲ ሃጅ ኡመር እንዳሉት ከሆነ ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሉበት የተቋቋመው ኮሚቴ ዘጠኝ አባላት ያሉት ሲሆን ከምክር ቤቱ ሶስት ፣ ከመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ 3 እንዲሁም ከሕዝበ ሙስሊሙ ደግሞ ሶስት ሆነው ተቋቁሟል ብለዋል፡፡ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች በህዝበ ሙስሊሙ መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በመፍታት ወደፊት በጋራ ለመስራት ጉባኤው እንደተዘጋጀም ሰምተናል፡፡

የኮሚቴው አባላት ከሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ
 • ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣
 • የታሪክ ምሑሩ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል እና
 • ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣
ከመጅሊስ 3 ሰው
 • ሙፍቲ ሐጂ ዑመር፣
 • የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሐጂ ሙሐመድ አሚን እና
 • ሐጂ ከድር፣
 • ከምሑራን እና ሽማግሌዎች 3 ሰው
 • ዶ/ር ኢድሪስ ሙሐመድ፣
 • ዶ/ር ሙሐመድ ሀቢብ እና
 • ሼኽ ሙሐመድ ጀማል አጎናፍር ናቸው፡፡ 

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የጤና ጥበቃ ሚኒሰቴር ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ትኩረት የማደርገው አዲስ የጤና ተቋማትን መገንባት ላይ ሳይሆን ለተቋማቱ የሚያስፈልጉ ግብዐቶችን ማሟላት ላይ ነው ሲል ተናገረ

የጤና ጥበቃ ሚኒሰቴር ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ትኩረት የማደርገው አዲስ የጤና ተቋማትን መገንባት ላይ ሳይሆን ለተቋማቱ የሚያስፈልጉ ግብዐቶችን ማሟላት ላይ ነው ሲል ተናገረ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ምህረት ሥዩምን ዘገባ ያዳምጡ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአደባባይ ሥያሜዎችና ማስታወቂያዎች በሐገር ቤት ቋንቋዎች በወጉ የተቃኙ አይደሉም ተባለ

የአደባባይ ሥያሜዎችና ማስታወቂያዎች በሐገር ቤት ቋንቋዎች በወጉ የተቃኙ አይደሉም ተባለ፡፡ ይህ የተባለው የቱሪዝም ሚኒስቴር በአዲግራት ከተማ ባደረገው ውይይት ላይ በቀረብ ጥናት ነው፡፡ በተለያዩ ክልሎች የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች እና የንግድ ስያሜዎች የሕብረተሰቡን ቋንቋ ከግምት ውስጥ ያስገቡ አይደሉምም ተብሏል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.የዮሐንስ የኋላወርቅን ዘገባ ያዳምጡ…
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መሥራትን የመሰለ ነገር የለም” ዓይነሥውሩ ሰንደል ሻጭ…

በጦርነት ሁለት ዓይኖቹን ያጣው ዓለምሰገድ አጥላው “ባለውለታዬ አፍንጫዬ” ነው ይላል፡፡ በሰው ግፊያ በተሞላው የመርካቶ ምዕራብ አካባቢ በአፍንጫው እያሸተተ ሰንደል እና እጣኑን ሲሸጥ እነሆ 15 ዓመት አለፈው፡፡ ዓለምሰገድ በዚሁ ሥራው ሚስቱን እና ሦስት ልጆቹን ያስተዳድራል ይለናል ወንድሙ ኃይሉ፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ለገቢ ምርቶች የምታወጣው የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ መጠን እያደገ ነው ተባለ

ከስድስት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ለገቢ ምርቶች አስራ አንድ ቢሊየን ዶላር አውጥታ እንደነበር የንግድ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡ ይህ ገንዘብ ከአምስት ዓመት በኋላ ወደ አስራ ሰባት ቢሊየን ዶላር ማደጉን በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ነግረውናል፡፡ ወደ ውጭ ከተላከ ምርት የተገኘው ገቢ ግን ከ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር እስከ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ባለው መካከል ነው ብለዋል፡፡

ወደ ውጭ ከሚላክ ምርት የሚገኘው ገቢ ከዓመት ወደ ዓመት መሻሻል ባለማሳየቱም - ሀገሪቱ ለከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ተዳርጋለች ተብሏል፡፡መድሃኒቶችን ከውጭ ገዝቶ ማስገባት ፈተና ወደ ሆነበት ደረጃ መደረሱንም ተናግረዋል፡፡ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን በመጠን ፤ በአይነትና በጥራት በማሳደግ ማቅርብ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡

ሚኒስቴሩ ባለፈው ሣምንት ከላኪዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ሠምተናል፡፡ ውይይቱን የከፈቱት የንግድ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እየተገኘ ያለውን አነስተኛ የውጭ ምንዛሪም የሀገርን ጥቅም ሊያስጠብቅ በሚችል መልኩ መጠቀም እንደሚገባ መናገራቸውን ሠምተናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሐገሪቱ የሕግና የፍትህ ስርዓት ገለልተኛ ያልሆነና በፍትህ መጓደል በርካታ እሮሮዎች የሚነሱበት ነው

“የሐገሪቱ የሕግና የፍትህ ስርዓት ገለልተኛ ያልሆነና በፍትህ መጓደል በርካታ እሮሮዎች የሚነሱበት ነው፡፡ ይህም የፍትህ ተቋማት በሕዝቡ ዘንድ አመኔታ እንዳይኖራቸው ሐላፊነታቸውም ጥያቄ የሚነሳበት እንዲሆን አድርጎታል” ጠቅላይ አቃቢ ሕግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ፡፡ ይህን ችግር ማስወገድ ይችላል ፣ በህግና ፍትህ ሥርዓቱ ላይ የሚታዩትን የአፈፃፀም ችግሮች ነቅሶ በመጠቆም ችግሩ እንዲወገድ የሚረዳ አማካሪ ጉባኤ በይፋ ተመስርቷል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ምህረት ስዩም የሚከተለውን አዘጋጅታለች
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለመጭው አመት፣ መንግስት ለሚሰራቸው የተለያዩ ተግባራት ማስፈፀሚያ 346.9 ቢሊየን ብር ረቅቅ በጀት መመደቡን መንግስት ተናግሯል

ለመጭው አመት፣ መንግስት ለሚሰራቸው የተለያዩ ተግባራት ማስፈፀሚያ 346.9 ቢሊየን ብር ረቅቅ በጀት መመደቡን መንግስት ተናግሯል፡፡ ይህ ገንዘብ አምና ከተመደበው በጀት ብልጫ ያሳየው በዝቅተኛ ደረጃ ነው፡፡ ይኽ ረቂቅ በጀት ዝቅ ባለ መጠን ማደጉ የኢኮኖሚውን እንቅስቃሴ አያቀዘቅዘውም ወይ ? የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተፈፃሚ እንዳይሆኑ አያደርግም ወይ ? በኑሮ ውድነትና በውጭ ንግድ ላይ ተፅዕኖው የከፋ አይሆንም ወይ ? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ትዕግስት ዘሪሁን ጥያቄዎቹን ይመልሱላት ዘንድ የምጣኔ ሐብት ባለሙያ አነጋግራለች…
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers