• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ቤት ጠባቂው ዶሮ

ለቤት ጥበቃ ውሻ ማሳደግ የተለመደ ነው፣ የፈረንሳይ ለጋሲዮኑ ቤት ግን የሚጠበቀው በዶሮ ነው ይለናል ወንድሙ ኃይሉ፡፡ ቴኩላ የሚሰኘው ይህ ዶሮ እያለ እዛች ጊቢ ድርሽ ማለት አይታሰብም፡፡ እየዘለለ ይናከሳል፡፡ ሰዎች ወደዛ ጊቢ ሲገቡ ልክ እንደውሻ ይህን ዶሮ ያዝልኝ ተብሎ ነው፡፡ ባለቤቱ ለዚህ ቤት ጠባቂ ሞገደኛ ዶሮ በቀን የ5 ብር በቆሎ መድበውለታል፡፡ ሙሉ ታሪኩን ያዳምጡ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈጥረው የነበሩ ግጭቶች በድርቅ ለተጠቁት ዜጎች በሚደረገው ድጋፍ ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ ተነገረ

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈጥረው የነበሩ ግጭቶች በድርቅ ለተጠቁት ዜጎች በሚደረገው ድጋፍ ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ ተነገረ፡፡ ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከተለያዩ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ አጋሮች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ድርቅ ለደረሰባቸው 7.8 ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ እያደረገ ሳለ ግጭቶች ድንገት በመከሰታቸው ሌላ ድጋፍ እንዲያደርግ መገደዱን ሌላ ተፅእኖ እንደሆነበት ተናግሯል፡፡

የኮሚሽኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለሸገር ሲናገሩ አሁን በድርቅ ከተጠቁት 7.8 ሚሊየን ሰዎች በተጨማሪ ለ50 ሺህ የሶማሌ ክልል የግጭት ተፈናቃዮች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን እያቀረብን ነው ብለዋል፡፡በጌዲዮና በምዕራብ ጉጂ ወደ ቀዬያቸው የተመለሱትን ዜጎች መልሶ የማቋቋሙ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡

አቶ ደበበ እንደነገሩን በድርቅ ከተጠቁት ዜጎች 5.4 ሚሊዮኑ በመንግስት 1.79 ሚሊዮኑ በአለም ምግብ ፕሮግራም 1.5 ሚሊዮኑ ደግሞ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ህብረት የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ እያገኙ ሲሆን ይህ ድጋፍ እስከ ታህሳስ 2011 ይቀጥላል፡፡በመኸር እርሻ ላይ ሰፊ ስራ በማከናወንም ድርቁን ለመቀነስ ጥረት እንደሚደረግ አቶ ደበበ ተናግረዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በቻይና ቤጂንግ ከነሐሴ 28-29፤2010 የቻይና አፍሪካ የትብብር መድረክ ላይ ይገኛሉ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በቻይና ቤጂንግ ከነሐሴ 28-29፤2010 የቻይና አፍሪካ የትብብር መድረክ ላይ እንደሚገኙ፤በኢትዮጵያ ቀጥታ ልማት ላይ ቀዳሚ ከሆነችው ቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግ እና ጠቅላይ ሚንስትር ሊ ኪያንግን ያነጋግራሉ መባሉን ከጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ፍፁም አረጋ የትዊተር ገፅ ተመልክተናል።
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቢሲኒያ ባንክ በአትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ ስም የሰየመውንና ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ የከፈተውን ቅርንጫፍ ዛሬ አስመረቀ

አቢሲኒያ ባንክ በአትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ ስም የሰየመውንና ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ የከፈተውን ቅርንጫፍ ዛሬ አስመረቀ፡፡ባንኩ ቅርንጫፉን አትሌት ዋሚ ቢራቱ በሕይወት እያሉ በ101 አመታቸው በስማቸው የሰየመው ስማቸው እንዲዘከርና የአገር ባለውለታነታቸው እንዲታወስ መሆኑን በሀላፊዎቹ በኩል ተናግረዋል፡፡አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ በአትሌቲክስ ስፖርት በረጅም ርቀት ኢትዮጵያን በአለም መድረክ ያስተዋወቁ ናቸው፡፡

በሮም ኦሎምፒክ 42 ኪሎ ሜትር የማራቶን ውድድርን በባዶ እግሩ ሮጦ ሪከርድ በማሻሻል አለምን ጉድ ያሰኘው የአትሌት አበበ ቢቂላ አሰልጣኝም ነበሩ፡፡አቢሲኒያ ባንክ ለአገራችን ባለውለታ በሆኑ ሰዎች እና የታሪክ ኩነቶች ስም በርካታ ቅርንጫፎችን መክፈቱ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተነግሯል፡፡በአትሌቲክስና እግር ኳሱ የስፖርት ዘርፍ በአትሌት አበበ ቢቂላና በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ቅርንጫፎችን ከፍቻለሁ ብሏል፡፡በዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ የሚሰየም አዲስ ቅርንጫፍም በቅርቡ እንደሚከፍት ተነግሯል፡፡ባንኩ ዛሬ በፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ የከፈተው ቅርንጫፉ 291ኛው እንደሆነም ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አዲስ አበባ ውስጥ በቅርቡ የከተማ አስተዳደሩ ባደረገው ማጣራት የተገኙ ባለቤት አልባ ህንፃዎች እንዲሁም ታጥረው ያለ ግንባታ የተቀመጡ መሬቶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉና ህዝብ እንዲጠቀምባቸው ይደረጋል ተባለ

አዲስ አበባ ውስጥ በቅርቡ የከተማ አስተዳደሩ ባደረገው ማጣራት የተገኙ ባለቤት አልባ ህንፃዎች እንዲሁም ታጥረው ያለ ግንባታ የተቀመጡ መሬቶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉና ህዝብ እንዲጠቀምባቸው ይደረጋል ተባለ፡፡በአዲስ አበባ በተደረገው የማጣራት ስራ በርካታ ባለቤታቸው የማን እንደሆነ የማይታወቁ የተገነቡ ህንፃዎች፣ ታጥረው የተቀመጡ መሬቶች ማግኘቱን የከተማ አስተዳደሩ መናገሩን ይታወሳል፡፡አስተዳደሩ በተለያዩ ቡድኖች በ10ሩም ክፍለ ከተሞች ባደረገው ማጣራት ባለቤት አልባ ህንጻዎች፣ የታጠሩ ቦታዎች እና የከተማዋን የቤት እጥረት ለማቃለል የተገነቡት ኮንዶሚኒየም ቤቶች ደግሞ መኖሪያ ቤት ባላቸው ግለሰቦች ተይዘው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶች የጋራ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች በማጣራት መንገድ የተገኙ ሀብቶችን በዝርዝር ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ሲሉ በአዲስ አበባ ከንቲባ ማዕረግ ምክትል ከንቲባው ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡እስከ መጪው አዲስ አመት ድረስም የማጣራት ስራው ተጠናቆ ብዙ ሀብት ይዘው ለድሃው ነዋሪ በተገነባ ቤት ያለ አግባብ ጥቅም የሚያገኙም በመኖራቸው ፍርድ እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ያቋረጠው የመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮችም በመጪው መስከረም ይጀምራሉ መባሉን ሰምተናል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ የገቢና የወጭ ንግዷን አመጣጥና እድገት ለማሳየት ምን መፍትሄ ታስቧል?

ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት፣ ከወጭ ንግዷ ያገኘችው ገቢ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ከውጭ ለምታስገባቸው ምርቶች የከፈለችው ገንዘብ ባለፉት አምስት አመት ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ታዲያ የገቢና የወጭ ንግዷን አመጣጥና እድገት ለማሳየት ምን መፍትሄ ታስቧል፡፡ የንጋቱ ረጋሣን ዘገባ ያዳምጡ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

እስካሁን ለምን የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ አልተቻለም?

ባለፉት አመታት ሲሰራበት የነበረው የትምህርት ፖሊሲ ክፍተት እንዳለበት ያረጋገጠው አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ የትምህርቱን ፖሊሲ እንደገና ለማረም ተዘጋጅቷል፡፡ ፍኖተ ካርታው በውይይት ዳብሮ የራሱንም ክፍተት አርሞ ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ በውይይቱ ላይ በትምህርት ዘርፍ ባለሙያ የሆኑትና ትምህርት ሚኒስቴርም ሲመሩ ከነበሩትና የአሁኑም መሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ከእነርሱም መካከል የቀድሞዋ የትምህርት ሚኒስቴር ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ይገኙበታል፡፡ በየነ ወልዴ እስካሁን ለምን የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ አልተቻለም ሲል ጠይቋቸዋል፡፡ 

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጀርድ ሙለር:- የጀርመን መንግስት የ100 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንዳደረገ...

የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚንስትር አቶ አብርሀም ተከስተ ከጀርመን መንግስት የኢኮኖሚ፣ ትብብር እና ልማት ሚንስትር ጀርድ ሙለር ጋር ተወያይተው በስልጠና እና የስራ ፈጠራ ጉዳዮች ላይ መስራት የሚቻልበትን ፊርማ ተፈራርመዋል። በተጨማሪም የጀርመን መንግስት የሙያ እና ቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደሚያደርግ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የትዊተር ገፅ ለመረዳት ችለናል።

በስምምነቱ መሰረት የጀርመን መንግስት የ100 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንዳደረገ ሰምተናል።

በተያያዘ ወሬ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ጀርድ ሙለርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፤የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች የምታደርገውን ያልተቋረጠ ድጋፍ እንዳመሰገኑ እና ነባር ግንኙነቱን አጠናክረው ለመቀጠል በሚቻልበት መንገድ ላይ መምከራቸውን ከጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ፍፁም አረጋ ተመልክተናል።
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ(ጥንቅሹ) ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ እስከ መጪው መስከረም ጉባኤ ድረስ መታገዳቸውን ሰምተናል

ሰበር ወሬ፦ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ(ጥንቅሹ) ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ እስከ መጪው መስከረም ጉባኤ ድረስ መታገዳቸውን ሰምተናል። አሁን ባላቸው ወቅታዊ አቋም የአማራን ህዝብ ጥቅም እንደማያስጠብቁ በመረጋገጡና በጥረት ኮርፖሬት ላይ በሰሩት ጥፋት እስከ ሚቀጥለው የድርጅቱ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መታገዳቸውን ተመልክተናል።

ነባር አመራሮች በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያም ተሽሯል፡፡በመሆኑም ከዚህ በኋላ በሚኖረው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አባል ያልሆነ አመራር አይሳተፋም፡፡ ኮሚቴው የሁለት ቀን ስብሰባውን ዛሬ አጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ አማራ ብዙሐን መገናኛ ድርጅት(አብመድ)

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ቅዳሜ ነሐሴ 19፣2010 ዓ.ም ከሰዓት ከ9:00ሰዓት ጀምሮ ከሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ቅዳሜ ነሐሴ 19፣2010 ዓ.ም ከሰዓት ከ9:00ሰዓት ጀምሮ ከሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘዋል። 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ከሶማሌ ክልል ተወካዮች፣ የሐይማኖት እና የማህበረሰብ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ከሶማሌ ክልል ተወካዮች፣ የሐይማኖት እና የማህበረሰብ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል፡፡ ተወካዮቹ ሕግ እንዲተገበር ጠይቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትዕግስታቸውን አድንቀው፣ የመቻቻል፣ የመነጋገር እና የሕግ የበላይነትን ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው መናገራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ የትዊተር መልዕክት ለመረዳት ችለናል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers