• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ነሐሴ 30፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • የሚከፍሉት ገንዘብ አጥተው በህክምና እጦት ሳቢያ ለስቃይና ለሞት የሚዳረጉትን የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ህሙማንን ተስፋ የሚያለመልም የምሥራች በአዲስ አመት ዋዜማ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ፈተና በዝቶብኛል አለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • ባዕድ ነገርን ከምግብ ጋር የቀላቀሉ እና ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒት እና የታሸጉ ምግቦችን ለገበያ ያቀረቡ በተለያየ ደረጃ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ሲል የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የብሮድካስት ባለሥልጣን ከአገር ውስጥ የሳተላይት የቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር የጠየቁ 2 ተጨማሪ ድርጅቶች የተሟላ ሰነድ ካቀረቡ ፍቃድ ሊያገኙ ይችላሉ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ የበካይ ጋዞች የልቀት መጠንን የተመለከቱ መረጃዎችን ለሌሎች አካላትም እያጋራሁ ነው አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በሶማሌ ክልል የበልግ ዝናብ ላላገኙ ቀበሌዎች ነዋሪዎች በመንግሥት ምግብና ውሃ እየቀረበላቸው መሆኑ ተሠማ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ተቋርጦ የነበረው የካንሰር የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን ሥራ ጀምሯል፡፡ ሌላኛው ቢታደስም ሥራ አለመጀመሩን ሰምተናል

በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብቻ የሚሰጠው የካንሰር የጨረር ህክምና በማሽኖቹ እርጅና ምክንያት በተፈለገው ፍጥነት ህክምና እየተሰጠ አልነበረም… በእድሜ ምክንያት የጨረር አመንጭ ቁሱ በውጤታማነት መሠራት ያልቻለው አንደኛው ማሽን ከካናዳ በመጣ መለዋወጫ ጥገና ተደርጐለት ሥራ እንደጀመረ የሆስፒታሉ ኃላፊ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን ለሸገር ተናግረዋል፡፡

መለዋወጫውን ለማስመጣትም ከ3 አመት በላይ አንደወሰደ ሰምተናል፡፡ የካንሰር የጨረር ህክምና መስጫ ማሽኑ ከተጠገነ በኋላ ለአንድ ሰው ህክመና በሚሰጥበት ያህል ጊዜ አሁን እስከ አራት ሰዎችን ማከም አስችሏል ተብሏል፡፡ ለኢትዮጵያ የካንሰር የጨረር ህክምና ብቸኛ የሆነው የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አንዱ የተጠገነ ሲሆን ሁለተኛው ማሽን ተበላሽቷል የተባሉ እቃዎቹ በአዲስ ቢተኩለትም እስካሁን መሥራት እንዳልቻለ ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ23ተኛው ዙር የሊዝ ጨረታ በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች አዘጋጅቼያለሁ አለ…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ23ተኛው ዙር የሊዝ ጨረታ በከተማዋ የተለያዩ ቦታዎች አዘጋጅቼያለሁ አለ…በቦሌ፣ በአቃቂ፣ በየካ፣ በንፋስ ስልክ እና በኮልፌ ክፍ ከተማዎች ቦታዎቹ ተዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡ አጠቃላይም 124 ቦታዎች እንደተዘጋጁ ሰምተናል፡፡

በአምስቱም ክፍለ ከተማ ለቅይጥ፣ ለቢዝነስ ለመኖሪያም ጭምር መሬቶቹ እንደተዘጋጁ የነገሩን በአዲስ አበባ መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ አቶ አዲስ የሸዋስ ናቸው፡፡ በ23ተኛ ዙር የመሬት ሊዝ ከቀረቡት ቦታዎች ውስጥም ለትልልቅ የገቢያ ማዕከል መገንቢያዎች ቦታዎቹ ተዘጋጅተዋል፡፡

ተህቦ ንጉሴ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ነሐሴ 27፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

 • አፍሪካ ኃይል የምታገኝባቸው ወንዞቿና ደኖቿ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አቅም እያጡ ስለሆነ ታዳሽ ኃይሎች ላይ ብታተኩር መልካም ነው ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • የእብድ ውሻ በሽታ መከላከያ ክትባት ፍላጐትን በአገር ውስጥ ምርት ማሟላት አልተቻለም ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ከወጣቶች ለተነሱ ኢኮኖሚ ነክ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በህገ-መንግሥቱ አንቀፅ 49 ቁጥር 5 ውስጥ ያለው ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላት ልዩ መብት በአዋጅ ሊፀድቅ ነው፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • በጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ተቋርጦ የነበረው የካንሰር የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን ሥራ ጀምሯል፡፡ ሌላኛው ቢታደስም ሥራ አለመጀመሩን ሰምተናል፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የኢትዮ ቻይና የንግድ ልውውጥ ምጣኔ የተራራቀ ነው ተብሏል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ23ኛው ዙር የሊዝ ጨረታ በተለያዩ ቦታዎች መሬት አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ለልማት ተነሺዎች የሚሰጠው የካሣ መጠን ሊሻሻል ነው ተባለ

ለመጭው አመት በአዲስ አበባ ከተማ ለልማት ተነሺዎች የማሰጠው ካሳ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ጥናት እያደረገ መሆኑን የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ተናገረ…ኤጀንሲው ህዝብ ተማሮባቸዋል ተብሎ ከለያቸው አስራ ስድስት የመልካም አስተዳደር ችግሮች መካከል ለልማት ተነሺዎች የሚሰጠው የካሳ መጠን አንዱ መሆኑንም ከኤጀንሲው ሰምተናል፡፡

ችግሩን ለመፍታትም በየአመቱ የሚሰጠው የካሳ መጠን በየጊዜው ከሚኖረው የገንዘብ የመግዛት አቅም ጋር የተጣጣመ ለማድረግ እየተሞከረ መሆኑን በኤጀንሲው ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

አቶ ግርማ እንዳሉት የከተማዋን የልማት ተነሺዎች የካሳ አነሰኝ ጥያቄ ለመመለስ ካለፈው ሚያዝያ ወር ጀምሮ የግንባታ ነጠላ ዋጋ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡

በማሻሻያ ዋጋው መሰረትም ዝቅተኛው የካሣ ክፍያ ከ115 ሺህ ብር ወደ 144 ሺህ ብር ከፍ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

የሰብል ካሳ ዋጋም በካሬ 28 ብር የነበረ ሲሆን ወደ 34 ብር ከፍ ማለቱንና አጠቃላይ የካሳ አከፋፈል መጠኑም በ14 በመቶ እንዳደገ ከአቶ ግርማ ሰምተናል፡፡

በ2008 ዓ.ም 7 ሺህ 898 ቤቶች ፈርሰው 92 ሄክታር መሬት ለልማት ነፃ ተደርጓል፡፡

የካሳ ክፍያው መጠን ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የተሻሻለ ሲሆን ለ5 ሺህ 549 የልማት ተነሺዎችም ለቤት መስሪያና ለዕቃ ማጓጓዣ የተሰጣቸውን ጨምሮ 598 ሚሊየን ብር ካሳ መከፈሉን ሰምተናል፡፡

በመጭው 2009 ዓ.ም ለልማት ተነሺዎች የሚሰጥ ካሳ ለማሻሻል ጥናት መጀመሩን የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ለሸገር ተናግሯል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በያዝነው ዓመት ብቻ 1 ሚሊየን 334 ሺህ 329 ተገልጋዬችን ማስተናገዱን የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ተናገረ

በያዝነው ዓመት ብቻ 1 ሚሊየን 334 ሺህ 329 ተገልጋዬችን ማስተናገዱን የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ ለመስተንግዶ አስቸጋሪ የሆነውን ወረፋ ለማቃለልም አስራ አራተኛ ቅርንጫፌን በመካኒሳ አካባቢ ልከፍት ነው ብሏል…

የቅርንጫፉ መከፈት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያለውን ወረፋ በመጠኑ ይቀንሰዋል ተብሎ ታምኖበታል ሲሉ የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ረዳት ኃላፊ አቶ አለምሸት መሸሻ ተናግረዋል፡፡

በየቀኑ ሰነድን ለማስመዝገብ እና ለማረጋገጥ በአማካይ 4 ሺህ 970 ሰዎች ኤጀንሲውን ይጐበኛሉ ተብሏል፡፡

ሰነዶችን የመመዝገብና የማረጋገጥ ኃላፊነት የተሰጠው ኤጀንሲ ወክልና ለመስጠትም ሆነ ለማንሳት በድረ-ገፅ በwww.daro.gov.et ላይ የነፃ አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም በዋና መሥሪያ ቤት ብቻ ይሰጥ የነበረው የሚንቀሳቀስ እና የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፉን ሥራ አሁን በተጨማሪ በቅርንጫፍ አምስትም ይሰጣል፡፡ የማህበራትን ሰነድ መመዝገብ እና ማረጋገጥ ከዋና መሥሪያ ቤት በተጨማሪ በቅርንጫፍ 12 እየተሰጠ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

መሰረት በዙ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ውዳሴ ዳግኖስቲክስ ሴንተር የነፃ ሕክምና ወረቀት ላላችሁ በጳጉሜ በነፃ የMRI እና የሲቲ ስካን ምርመራ አደርግላችኋለሁ አለ

ዘመን አመጣሽ አዳዲስ የመመርመሪያ መሣሪያዎች የህክምና ሥራን በማቅለል ገላግሌ ቢሆኑም የጥንቃቄው ነገር ግን በጣም ሊታሰብበት ይገባል ተባለ…ጤንነታችሁን ሁሌም ጠብቁ፣ የአቅም ማነስ ገጥሟችሁ የሕክምና የምርመራ ወረቅት ያላችሁ ግን የኤም አር አይ እና የሲቲ ስካን ምርመራን በነፃ ማግኘት ትችላላችሁ ጳጉሜን ለጤናችሁ ስጡ ተብላችኋል፡፡

ተቋማዊ ማህበራዊ አገልግሎት ማለት ምን ማን ነው? በዚህ ኃሣብ ዙሪያ የሕክምና ተቋም ተወካዮች ዛሬ በሸራተን ሆቴል ተሰባስበው ሲመክሩ አርፍደዋል፡፡ ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ሴንተር በየአመቱ ላለፉት ሰባት ዓመታት ጳጉሜን ለጤና በሚል ነፃ የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ የተነገረ ሲሆን ከነፃ ህክምና ባለፈ በኃሣቡ ዙሪያ እንምከርበት ብሎ የዛሬውን ፕሮግራም አሰናድቷል ተብሏል፡፡

ተቋማዊ፣ ማህበራዊ ኃላፊነት ተቆጥሮ ከተሰጠ ኃላፊነትና ግዴታ አልፎ መገኘት ነው ያሉት አቶ ዳዊት ኃይሉ የውዳሴ ዳግኖስቲክስ ማዕከል መስራችና ሥራ አስኪያጅ ባለፉት ሰባት አመታት አቅም ላነሳቸውና የሐኪም ትዕዛዝ ላላቸው 15 ሺህ ታካሚዎች ነፃ የኤም አር አይ እና የሲቲ ስካን ምርመራን ሰጥተናል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 26፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ቱሪስቶችን በመሳብ፣ የተፈጥሮ መስህቦችን በመጠበቅና ለአለም በማስተዋወቅ በኩል ስኬታማ መሆኑን ተናግሯል፡፡ (ምስክር አወል)
 • የስነ-ተዋልዶ ጤና በሀገራችን ስርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካቶ እየተሰጠ ቢሆንም በወጣቶች ላይ ያመጣው ለውጥ እምብዛም ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአዲስ አበባ ህገ-ወጥ ስጋ ተያዘ ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • ውዳሴ ዳግኖስቲክስ ሴንተር የነፃ ሕክምና ወረቀት ላላችሁ በጳጉሜ በነፃ የMRI እና የሲቲ ስካን ምርመራ አደርግላችኋለሁ አለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የመቐሌና የአክሱም ደም ባንኮች ለትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎችም ደም እያቀረቡ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በኤች አይቪ ኤድስ ዙሪያ አልተሰራም ተባለ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • በአዲስ አበባ ለልማት ተነሺዎች የሚሰጠው የካሣ መጠን ሊሻሻል ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ዘንድሮ በኢትዮጵያ ከምንግዜውም በዛ ያሉ መድሐኒቶችና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች መሠራጨታቸው ተሠማ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በኢትዮጵያ ሚሊኒየም አዳራሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሣለኝ ከመላ አገሪቱ ከመጡ ወጣቶች ጋር እየተመካከሩ ነው፡፡ ወጣቶቹ ጥያቄ አንስተውላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩም ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በያዝነው ዓመት ብቻ 1 ሚሊየን 334 ሺህ 329 ተገልጋዬችን ማስተናገዱን የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ተናገረ፡፡ (መሠረት በዙ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ነሐሴ 24፣2008

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ክፍል ስምንት


በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር የምግብ የደም ስኳር ፍጥነት መጠን የመጨመር አቅም እና የደም የስኳር መጠን ምላሽ ነሐሴ 24፣2008
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ስድስተኛው የቲካርድ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡ ጃፓን ለአፍሪካ ልማት 300 ቢሊየን ዶላር መድባለች

ኢትዮጵያ በ6ኛው የቶኪዮ አፍሪካ ልማት ቲካድ ጉባኤ ላይ የነበራት ተሳትፎ መልካም ነበር ተባለ፡፡ጉባኤው በኢትዮጵያ አለመካሄዱ ያለመመረጥ እንጂ ከጀርባው ሌላ ምክንያት እንደሌለውም ተወርቷል፡፡ በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ የተካሄደው የቲካድ ጉባኤ በመጪዎቹ 3 ዓመታት ጃፓን ለአፍሪካ የ30 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገባችበት ሆኖ አብቅቷል፡፡  

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ በጉባኤው ላይ 3 መሰረታዊ ጉዳዮች ተነስተው እንደነበር ነግረውናል፡፡የቲካድ ጉባኤ በመጪዎቹ 3 ዓመታት ለአፍሪካ ከመደበው የ30 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት 10 ቢሊየኑ ለመሰረተ ልማት የሚውል መሆኑም ታውቋል፡፡

ፋሲል ረዲ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአማራ ክልል ዳግም በተነሳው ተቃውሞ ሰዎች መሞታቸውና የክልሉ መንግስትም የመከላከያ ሃይሉን እርምጃ እንዲወስድ ማዘዙ ተሰማ

የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሶስት ቀናት በነበረው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት መቀጠፉንና ንብረት መውደሙን ለሸገር ዛሬ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የተለያዩ ከተማዎች ውስጥ የአገልግሎት መስጪያ ተቋማት አገልግሎት ተቋርጦ ነበር ሲሉም ነግረውናል፡፡

ህዝቡ የሚያሳቸውን ህጋዊ የመብት ጥያቄዎችን በሌላ መንገድ የሚወስዱ ወገኖች በክልሉ ያለውን ጥፋት በማባባሳቸው የመከላከያ ኃይል እርምጃ እንዲወስዱ በክልሉ መንግስት መታዘዙንም አቶ ንጉሱ ይናገራሉ፡፡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር ከሚገኙ በደብረ ታቦር፣ በባህር ዳር፣ በጎንደርና በደብረ ታቦር የተነሱ ተቃውሞዎች ብዙ ንብረት መውደሙንና ህይወት መጥፋቱን የተለያዩ ወገኖች ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡

ከ3 ቀናት በፊት በተነሳው ዳግም ግጭት ምክንያት  በደብረ ታቦር ብቻ ስድስት ሰዎች ሞተዋል ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ሲናገር ተሰምቷል፡፡ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ንጉሱ በበኩላቸው በ3ቱ ቀናት በታዩት ግጭቶች ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱና ንብረት እንደወደመ ተጠይቀው “ለጊዜው የሚባል ነገር የለም በቅርቡ ጥቅል መረጃዎች ይወጣሉ” ብለዋል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers