• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አመታዊ ትምህርታዊ የጥናትና ምርምር ጉባዔውን ዛሬ እያካሄደ ነው

ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አመታዊ ትምህርታዊ የጥናትና ምርምር ጉባዔውን ዛሬ እያካሄደ ነው…ዩኒቨርስቲው ከማስተማር ሥራው በተጨማሪ በየዓመቱ የትምህርት ጥናቶችና የምርምር ውጤቶችን በተከታታይ ማካሄዱ ይታወቃል፡፡ ለሁለት ቀናት በሚቆየው የጥናትና ምርምር ጉባዔ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተሳተፉ ተመራማሪዎች የጥናት ፅሁፋቸውን ያቀርባሉ፡፡ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ለተመራማሪዎቹ በጀት በማዘጋጀት ለሀገር የሚጠቅሙ ናቸው ያላቸውን ለፖሊሲ አርቃቂዎችና ለሌሎችም ይረዳሉ የተባሉ ምርምሮች እንዲሰሩ የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው በጉባዔው መክፈቻ ወቅት ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 17፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ህፃናትን በአደራ አልያም በጉዲፈቻ ወስዳችሁ ለማሳደግ ለምትሹ በሬ ክፍት ነው ብሏል፡፡
 • የአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተደጋጋሚ ስህተት እየተገኘበት ነው ሲል የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት አመለከተ፡፡
 • ኢትዮጵያ እና ኬንያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ግንባታ ለማካሄድ ተስማሙ፡፡
 • ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ100 በላይ የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት እንደተዘጉና ሌሎች ከ160 በላይ የሚሆኑትም ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተሠማ፡፡
 • በአበባ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ወጪ ንግድ ጥሩ ገቢ ተገኘ ተባለ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የናይሮቢ ኬኒያ የሥራ ጉብኝት

ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የናይሮቢ ኬኒያ የሥራ ጉብኝት ተደጋጋሚ ቀረጥን ማስቀረትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ይፈራረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተሰማ…

ሸገር ዛሬ ከውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ተወልደ ሙሉጌታ እንደሰማው ኬኒያና ኢትዮጵያ በ2012 እ.አ.አ የተፈራረሙትን የስምምነት ውጤቶችን ጭምር ይፈትሻሉ ብለዋል፡፡

በጤናና በኢንቨስትመንት ግንኙነት ዙሪያ ስምምነቶችን ያደርጋሉ ተብሎ የሚጠበቀው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምና የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ንግግር ተጨማሪ ስምምነቶችንም ያደርጋል ተብሏል፡፡

በኢትየጵያና በኬኒያ መካከል የተጀመሩት ታላላቅ የጋራ ፕሮጀክቶችን በተመለከተም ሁለቱ መንግሥታት ይነጋገራሉ መባሉን ከአቶ ተወልደ ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ያቀረቧቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ሹመት

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ያቀረቧቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ሹመት በአንድ ድምፀ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ… በውሣኔ ኃሣቡ መሠረትም ላለፉት 16 ዓመታት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ያገለገሉት አቶ ዳኜ መላኩ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል፡፡ አቶ ፀጋዬ አስማማው ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሹመታቸውን ተቀብለዋል፡፡

በቂ የህግ ትምህርትና ልምድ አላቸው የተባሉ 34 ለከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ሌሎች 75 ደግሞ ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ዳኞቹን ለመሾም ለምክር ቤቱ የቀረበው ሰነድ የተለያየ ግድፈት አለበት፣ ሥርዓትም የለውም ሲሉ የተለያዩ የምክር ቤቱ አባላት ተችተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የነርሶችን አለባበስ የሚወስን መመሪያ አውጥቷል

በጤና ተቋማት ህሙማንን የሚንከባከቡ ነርሶችን የአለባበስ ስርዓት የሚወስን ደንብ በሥራ ላይ መዋል ጀመረ…
ነርሶች ብዙ ጊዜያቸውን በጤና ተቋማት ውስጥ ከህሙማን ጋር ያሳልፋሉ፡፡ በዚህ ግንኙነታቸው ራሳቸውን ለህሙማኑ እና ሌሎች ተገልጋዮች ግልፅ አድርገው ማቅረብ እንዳለባቸው የሙያው ስነ-ምግባር ይጠይቃል፡፡
ለዚህ እንዲረዳ የራሳቸው የአለባበስ ደንብ እንደሚኖራቸውም ይጠቅሳል፡፡

ነርሶች ነጭ የደንብ ልብስ እና ቆብ እንደሚያደርጉ በመመሪያ ደረጃ ሰፍሯል፡፡

ትኩረት ባለመስጠት ግን አንዳንድ ነርሶች የደንብ ልብሱን አይጠቀሙም፣ በአለባበሳቸው ምክንያት ክህክምና ዶክተሮች ጋር የሚመሳሰሉበት አጋጣሚ እንዳለ ይነገራል፡፡

እንዲህ ዓይነቱን ችግር ለማስቀረት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የነርሶችን አለባበስ የሚወስን መመሪያ አውጥቷል፡፡

አዲሱ የአለባበስ መመሪያ የነርሶችን ደረጃ የሚያመለክት ጥብጣብ ወይም ሪቫን እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡

ደረጃውን በዲግሪ እና በዲፕሎማ የተመረቁ እንዲሁም ረጅም ዘመን ያገለገሉ ነርሶችን የሚለይ እንደሆነ ሰምተናል፡፡

ከሪቫኑ ጋር ከላይ ቆብ፣ ጉርድ ሸሚዝ እንዲሁም ሱሪ እና ጫማ ነርሶች ይጠቀማሉ ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ከሥልጣን ይውረድልን ያሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ከሥልጣን ይውረድልን ያሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች ዛሬ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ…መነሻቸውን ከገነት ሆቴል ያደረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን ሰሞኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ ላይ ያወጣውን አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡ኢሣያስ ለዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት /ICC/ ይቅረብ ፣ አንባገነኖች ይውደሙ፣ ፍትህ እንፈልጋለን፣ ኤርትራ ለኤርትራዊያን የሚሉ መፈክሮችን በእንግሊዝኛ፣ በአረብኛና በትግርኛ ቋንቋዎች እያሰሙ አፍሪካ ህብረት ድረስ ተጉዘዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ሰኔ 16፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በገብረ ክርስቶስ ደስታ ማዕከል አዳዲስ የሥነ-ጥበብ ሥራዎች ይቀርባሉ ተባለ፡፡
 • የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ፡፡
 • የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንትን ሹመት ዛሬ አፀደቀ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣የመብት ጥሰት ደርሶብኛል ብለው ወደ ኢትዮጵያ ከደረሱ ከ1 ሺህ 419 አቤቱታዎች 999 ያህሉ ተቀባይነት እንዳላገኙ ተሰማ

የመብት ጥሰት ደርሶብኛል ብለው ወደ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደጃፍ ከደረሱ ከ1 ሺህ 419 አቤቱታዎች 999 ያህሉ ተቀባይነት እንዳላገኙ ተሰማ… ባለፉት 11 ወራት ከዜጐች ለኮሚሽኑ የቀረቡ አቤቱታዎች በቁጥርም በዓይነትም ካለፉት ጊዜያት ጋር ሲነፃፀሩ መብዛታቸውን ሰምተናል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር እንዳሉት ከቀረቡት 1 ሺህ 419 አቤቱታዎች መካከል 999 ያህሉ ተቀባይነት ያላገኙባቸው ምክንያቶች መካከል፣ አቤቱታዎቹ ከወንጀል ወይም ከሙስና ጋር የተገናኙ መሆናቸው አንዱ ምክንያት ነው፡፡በተጨማሪም ከመልካም አስተዳደር ጋር በተገናኘ የደረሱ ተደራራቢ በደሎች ሆነው ከዚህ ቀደም ለእንባ ጠባቂ የቀረቡ ሆነው ስለተገኙ አቤቱታዎቹ በኮሚሽኑ ተቀባይነት አላገኙም ብለዋል፡፡ አንዳንዶቹ አቤቱታዎች ደግሞ የቀረቡት ከአዕምሮ መታወክ እና ከስነ-ልቦና ችግር የመነጩ ሆነው አግኝተናቸዋል፡፡ በመሆኑም 999ኙ አቤቱታ አቅራቢዎች የተሸኙት የምክር አገልግሎት ብቻ ተሰጥቷቸው እንደሆነ ከኮሚሽነሩ ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በኬንያ ናይሮቢ ይፋዊ ጉብኝት

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በኬንያ ናይሮቢ ይፋዊ ጉብኝታቸውን ዛሬ ጀመሩ…ትናንት ምሽት ከዱባይ ናይሮቢ የገቡት አቶ ኃይለማርያም በኬንያ ለ3 ቀናት እንደሚቆዩም የኬንያ መንግሥት ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በ3 ቀናት ቆይታቸው ስለ ሁለቱ አገሮች ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት፣ ስለ አካባቢያዊ ሁኔታ ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣የዜጐችን ደህንነት አስጠብቄ ሥምሪቱን ለመጀመር የአቅሜን እየጣርኩ ነው

የውጪ ሀገር የሥራ ስምሪትን መልክ ለማስያዝና የዜጐችን ደህንነት አስጠብቄ ሥምሪቱን ለመጀመር የአቅሜን እየጣርኩ ነው ያለው የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው… የሥራ ፈላጊዎችን ደህንነት የሚያስጠብቅ አዋጅም መውጣቱን ተከትሎ ለአፈፃፀሙ እንዲረዳ ደንብና መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡ በቅርቡም ተቋርጦ የነበረው የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት ህግና ደንቡን ጠብቆ የዜጐች መብት ሳይጣስ እንደሚጀምር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳመነ ዳሮታ ተናግረዋል፡፡

በውጭ አገር ሄደው መሥራት ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ህጉን ተከትለው ጥቅማቸውና ደህንነታቸውን እንዲጠበቅላቸው ከተለያዩ የአረብ አገሮች ጋር ስምምነቶችን እንደተፈራረመም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ እስካሁንም ከኳታር፣ ኩዌትና ጆርዳን አገሮች ጋር በደህንነት ዙሪያ እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ጉዳይ ተፈራርሜያለው ብሏል መሥሪያ ቤቱ፡፡

ከሌሎች ተቀባይ አገሮች ከነዱባይ እና ሳዑዲ አረቢያ ጋርም ስምምነቱን ለመፈራረም መንገዶቼን እያጠናቀቅኩ ነው ብሏል፡፡ እግረ መንገዴንም በውጭ አገር ሥራ ለመሰማራት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የሚደርሱበትን አገር ባህል እንዲያውቁ በፕሮጀክቴ አካትቼዋለው ማለቱን ሰምተናለ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 15፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር ፈጥረዋል በሚል ጉዳያቸው ካለፈው በጀት አመት ወደዚህኛው በጀት አመት የተላለፉ 206 የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው ተባለ፡፡
 • የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አንድ ግለሰብ ከነተባባሪው በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሊያስገባቸው የነበሩ ከ5 ሺህ በላይ የሞባይል ቀፎዎችና መለዋወጫዎችን ያዝኩኝ አለ፡፡
 • የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፉት 11 ወራት ከቀረቡልኝ ከ1 ሺህ 400 በላይ አቤቱታዎች ሁለት ሦስተኛዎቹ ውሃ የሚያነሱ ሆነው አላገኘኋቸውም አለ፡፡
 • በአዲስ አበባ በተወሰኑ አካባቢዎች የ24 ሰዓት የትራፊክ ቁጥጥር ሊደረግ ነው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers