• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የአፍሪካ ሀገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲያስገቡ በተሰጠው ዕድል ኢትዮጵያ እንድትጠቀም...

በኤሜሪካ የተራድኦ ድርጅት /USAID/ የምሥራቅ አፍሪካ የንግድና የመዋዕለ ነዋይ መናኸሪያ ከሰሃራ በስተደቡብ ያሉ የአፍሪካ ሀገራትንና የአሜሪካንን የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስር ለማቀለጣጠፍ የተመሠረተ ነው፡፡የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በአፍሪካ ውስጥ ሥራ ላይ እንዲውል ከሚያስቧቸው ውጥኖች አንዱም ነው፡፡

ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የሚቆይ ውጥን እንደሆነ የድርጅቱ ኃላፊ አቶ ፋሲል ይልማ ነግረውናል፡፡የውጭ ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሰሩ የማግባባት ሥራ ይሰራልም ነው ያሉት፡፡ከኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ጋር በጥምረት መሥራት የሚፈልጉ የውጭ ባለሃብቶችን ድርጅቱ የማፈላለግ ሥራ እንደሚሰራ ሰምተናል፡፡

ንግድና ኢንቨሰትመንት እንዳያድግ የሚገድቡ የፖሊሲ እንቅፋቶች እንዲወገዱም ለመንግሥት ኃሣብ ያቀርባል ብለዋል፡፡ድርጅቱ በእስከ አሁን ሥራው ብዙዎቹ የውጭ ባለሃብቶች ስለ ኢትዮጵያ የተወሰነ መረጃ ብቻ እንዳላቸው ማወቁን ነው አቶ ፋሲል የነገሩን፡፡ ባለሃብቶቹ ከመጡ በኋላም የተቀላጠፈ አገልግሎት አላገኘንም የሚል ቅሬታ ያሰማሉ ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ ገበያ እንዲያስገቡ በተሰጠው ዕድል ኢትዮጵያ እንድትጠቀም ድርጅታቸው እየሰራ መሆኑንም አቶ ፋሲል ነግረውናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በክረምቱ ጫና ምክንያት የኤሌክትሪክ መቆራረጥና መጥፋት ሊደጋገምብኝ ይችላል አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አንዱን ችግር ብፈታ ሌላውን እያመጣ ስራ እያበዛብኝ ነው የመብራት እዚህም እዚያም መቆራረጥ በክረምቱ ምክንያት መደጋገሙ አይቀርም ሲል ተናገረ…በቀን በተደጋጋሚ እንዲሁም ለቀናትና ሣምንታት መብራት ጠፋብን የሚሉ ቅሬታዎች ደጋግመው መሰማታቸው የተለመደ እየሆነ የመጣ ሲሆን በተለይ ክረምቱ ከገባ ወዲህ መጠኑ ጨምሯል፡፡

እንዲህ አይነት ጥያቄና ቅሬታዎች ተደጋግመው ይሰማሉ፡፡ ከመፈታት ይልቅ መጠናቸው ይባስ እየጨመረ የመጣበት ምክንያት ምንድነው? የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረእግዚአብሔር ታፈረ ጥያቄው እየበዛ ስለመምጣቱ እናውቃለን ይላሉ፡፡

መቆራረጡ አለ ከማለት ባለፈ ችግሩን የመፍታቱ ስራስ ስልን አቶ ገብረእግዚአብሔርን ጠይቀናቸው እዚህም እዚያም የሚፈጠረውን መቆራረጥ ለመፍታት እየሞከርን ነው ግን አንዱን ሰራን ስንል ሌላኛው ይተካል ይላሉ፡፡ “ይሄ ደግሞ የክረምቱ ዝናብ ያመጣው ነው” ብለዋል፡፡ኃላፊው ችግሩ ጋብ የሚለው ክረምቱ ሲወጣ ነው የሚል ምላሽን ሰጥተውናል፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 20፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ትላንት አመሻሽ 11፡30 አካባቢ ለካባ በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ አንድ ሰው ገብቶ ሞቷል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የተለያዩ የተቃዋሚ የፖለቲካ ማኅበራትና ድርጅቶች የሚሳተፉበት በግጭት ማስወገድ ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት የሂሣብ ምርመራ ተደጋግመው የሚያጋጥሙ ጉደለቶችን ለማረም የታለመ ሥልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በክረምቱ ጫና ምክንያት የኤሌክትሪክ መቆራረጥና መጥፋት ሊደጋገምብኝ ይችላል አለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ከኮንስትራክሽን ማዕድን ፈቃድ ከ26 ሚሊየን ብር በላይ አገኘሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤታችሁን ያወቃችሁ ተማሪዎች የትምህርትና የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን ማስተካከል ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡ (ምስክር አወል)
 • አትራፊ ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸው ከፍ ያለ ትኩረት በሰጡ ቁጥር ትርፋማነታቸውም እንደሚያድግ የአርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ አበበ ተናገሩ፡፡ ድርጅታቸው በ2008 ዓ.ም ከ39 ሚሊየን ብር በላይ በማትረፉ ለሠራተኞቹ ጠቀም ያለ የደመወዝ እድገትና የማበረታቻ ገንዘብ ሊሰጥ እንደሆነም ነግረውናል፡ (አስፋው ስለሺ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለወሰዱ ተማሪዎች 2009 ዓ.ም በመንግሥትና በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግቢያ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል

በ2009 ዓ.ም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚያስገባው ነጥብ 295 እና ከዛ በላይ ሆኖ ተወስኗል…ወደ መንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የመግቢያ ነጥብ ለተፈጥሮ ሳይንስ የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ለወንዶች 354 እና ከዛ በላይ፣ ለሴቶች 340 እና ከዛ በላይ፣ ለግል ተፈታኞች ለወንዶች 360 እና ከዛ በላይ፣ ለሴቶች 355 እና ከዛ በላይ ያገኙ ይመደባሉ፡፡

ለአርብቶ አደርና ለታዳጊ ክልል ተማሪዎች ለወንዶች 340 እና ከዛ በላይ፣ ለሴቶች 335 እና ከዛ በላይ ፣ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶችም ለሴቶችም 297 እና ከዛ በላይ ካስመዘገቡ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋም እንደሚመደቡ ኤጀንሲው ተናግሯል፡፡

በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ለመደበኛና ለማታ ተማሪዎች ለወንዶች 330ና ከዚያ በላይ ለሴቶች 320 እና ከዛ በላይ ያገኙ ምደባው ይመለከታቸዋል፡፡ የግል ተፈታኞች ለወንዶች 360 እና ከዛ በላይ ለሴቶች 355 እና ከዛ በላይ የተለየ ድጋፍ ለሚሹ ለታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር ተማሪዎች ለወንዶች  320ና ከዛ በላይ፣ ለሴቶች 315ና ከዛ በላይ መስማት ለተሳናቸው ወንዶችና ሴቶች 275 እና ከዛ በላይ ሆኖ ተወስኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በነሐሴ ወር ማህበራቸውን ማሣወቅ ካለባቸው 58 ሺህ ግብር ከፋዬች 60 በመቶ የሚሆኑት እስካሁን አልመጡም አለ

የደረጃ ለ ግብር ከፋዮች ቁጥር 58 ሺህ ያህል ሲሆን እስካሁን ግብራቸውን ያላሳወቁትን 60 በመቶ ያህሉን በመጭዎቹ 16 ቀናት ብቻ ለማስተናገድ መጨናነቅ እንደሚፈጥርና ባለሥልጣኑ እንደሚቸገርም ሰምተናል፡፡ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ታክስ ፕሮግራም ልማት ስራዎች ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ነፃነት አበራ ለሸገር እንደተናገሩት ባለፈው ሐምሌ ወር መስተናገድ ከነበረባቸው 200 ሺህ ያህል የደረጃ ሐ ግብር ከፋይ መካከል በጊዜው ግብራቸውን ያሳወቁት 96 ነጥብ 7 በመቶ ናቸው ብለዋል፡፡

ቀሪዎቹም በዚህ ወር ከወለድና ከቅጣት ጋር ይስተናገዳሉ ተብሏል፡፡ ከባለሥልጣኑ አቅም በላይ በሆነ ምክንያት የመብራትና የሲስተም መቋራረጥ እንደሚያጋጥም የተናገሩት ወ/ሮ ነፃነት መብራትና ሲስተም በጠፋባቸው ጊዜዎችም በማኗል መስተንግዶው እንደሚሰጥ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ የሰመመን ሰጭዎችን ቁጥር ለመጨመር የጤና ሳይንስ ኮሌጆች እየሰሩ ነው ተባለ

በኢትዮጵያ የሰመመን ሰጪ ባለሙያዎችን ቁጥር ለመጨመር በ16 ዩኒቨርስቲዎች እና በ8 የክልል ጤና ሳይንስ ኮሌጆች ውስጥ በተለያየ ደረጃ የአንስቴቲክስ ትምህርት እየተሰጠ ነው ተባለ፡፡ በየአመቱም 400 ተማሪዎች ተመርቀው ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሏል፡፡

ይህን የሰማነው ዛሬ 12ኛው የኢትዮጵያ አንስቴቲክሶች ማህበር ብሔራዊ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ልዑልአየሁ አካሉ ባለፉት አራት አመታት የባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ ነው በየአመቱም 400 ባለሙያዎች ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እና ጤና ሳይንስ ኮሌጆች ተመርቀው ወደ ሥራ ይገባሉ ብለዋል፡፡

የሰመመን ባለሙያዎች ቁጥር ከአገልግሎት ፈላጊው ጋር ባለመጣጣሙ በተለይ በቀዶ ጥገና ህክምና ላይ ትልቅ ጫና አሳድሯል ሲሉ አቶ ልዑልአየሁ ተናግረዋል፡፡ የሙያ ማህበሩም የባለሙያዎችን ቁጥር ከጥራት ጋር ለማሳደግ ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመሆን እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ ዛሬ የተጀመረው ሀገር አቀፍ ጉባኤ እስከ ቅዳሜ ይዘልቃል፡፡

መሰረት በዙ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ጥናትና ምርምር ተደርጐ እየተመከረበት ነው ተባለ

እንዲህ ያለው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሲሆን በነኚህ በሽታዎች ላይ ጉባኤ እየተደረገ ያለው በጂግጂጋ ነው ተብሏል፡፡ ትኩረት የሚሹ በሽታዎች የቴክኒክ አማካሪ የሆኑት አቶ ፋንታሁን ታደሰ ለሸገር እንደተናገሩት በተለይም 8 በሽታዎች ተለይተው ጥናትና ምክክር ተደርጐባቸዋል፡፡

ትራኰማ፣ ዝሆኔና ፎከትን እንደ ጐርጐሮሣውያን አቆጣጠር የዛሬ አራት አመት በ2020 ከኢትዮጵያ ለማጥፍት በሚቻልበት ዘዴ ላይ ጥናት ቀርቧልም ተብሏል፡፡ የጊኒ ዎርም በሽታም በአለም ላይ በአራት ሀገሮች ብቻ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ አራትና ሦስት የሚሆኑ የበሽታው ተጠቂዎች ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ይህንንም በሽታ በሦስት አመት ውስጥ ከኢትዮጵያ ለማጥፋት በሚቻልበት ዘዴ ላይ ጥናት ተደርጓል፡፡ የአንጀት ጥገኛ ትላትሎች፣ ብላሀርዚያ እና ካላዛርም ትኩረት ከተሰጠባቸው በሽታዎች መሀል አንደሆኑም ሰምተናል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ዘንድሮ ከተከራዮቼ ከ357 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ሰበሰብኩ አለ

የሚዲያ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን መሪው አቶ ለቤዛ አለሙ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ ኤጀንሲው ከቤት ኪራይ፣ ከውዝፍ እና ከወቅታዊ ቤት ኪራይ ነው ገንዘቡን የሰበሰበው ብለዋል፡፡ በልማት ምክንያት የፈረሱ ቤቶች በመኖራቸው አምና ከተገኘው 384 ሚሊየን ብር የዘንድሮ እንደቀነሰ የነገሩን አቶ ለቤዛ ዘንድሮ 318 ነጥብ 38 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅደን ነው 357 ነጥብ 36 ሚሊየን ብር ያገኘነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው በአዲስ አበባና በድሬዳዋ በድምሩ 17 ሺህ 019 በቶች ያሉት ሲሆን 11 ሺህ 994ቱ መኖሪያ ቤቶች፣ 5 ሺህ 025ስቱ ደግሞ ድርጅቶች ናቸው፡፡ የመሸጥም የማዘዋወርም ሥራ አይሰራም በመጪው አመትም 25 ህንፃዎቹን ለማሳደስ አቅዷል ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 19፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለወሰዱ ተማሪዎች 2009 ዓ.ም በመንግሥትና በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግቢያ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡ (ምስክር አወል)
 • በኢትዮጵያ የሰመመን ሰጭዎችን ቁጥር ለመጨመር የጤና ሳይንስ ኮሌጆች እየሰሩ ነው ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • በዓመት 200 ሚሊዮን ብር ወጪ አለብኝ ያለው የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር የውጪ እርዳታ ስለቀዘቀዘብኝ የራሴን ገቢ የማገኝበት የሶሻል ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ላቋቁም ነው ሲል ተናገረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአውሮፓ ህብረት ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ ሰጠ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ሴቭ ዘቺልድረን እና JSK የተባለው የመድሐኒት አምራች በኢትዮጵያ በህፃናት ጤና ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶችን ሊሸልሙ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በ2008 ዓ.ም 25 ነጥብ 2 ኪ.ሜ ያረጁ የውሃ ማስተላለፊያ መስመሮች ተቀይረዋል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በዚህ አመት ከኪራይ የሰበሰብኩት ገንዘብ ከአምናው የ27 ቢሊየን ብር ቅናሽ አለው አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ጥናትና ምርምር ተደርጐ እየተመከረበት ነው ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በነሐሴ ወር ማህበራቸውን ማሣወቅ ካለባቸው 58 ሺህ ግብር ከፋዬች 60 በመቶ የሚሆኑት እስካሁን አልመጡም አለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ነው ተብሎ በማህበራዊ ድረ-ገፆች የሚሰራጩት የ12ኛ ክፍል ውጤቶች ሀሰት ናቸው ተባለ

ይህንን የነገረን የአገር አቀፍ ትምህርትና ፈተናዎች ኤጀንሲ ነው፡፡ ተፈታኞቹን ወደ ከፍተኛ ትምህርት የሚያስገባውን የውጤት መጠን ኤጀንሲው በጥቂት ቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን ድሬሳ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም የ10ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደርጓል እየተባለ የሚሰራጨው ወሬ ኤጀንሲው የማያውቀው መሆኑን ዶክተር ዘሪሁን ጠቁመል፡፡ እንደ ዶክተር ዘሪሁን ከሆነ የ10ኛ ክፍል ውጤት በቅርብ ቀን በመገናኛ ብዙሀን በኩልና በኤጀንሲው ድረ-ገፅ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎችና ወላጆች የተሳሳተ መረጃዎችን አይታችሁ ግራ እንዳትጋቡ አሳስበዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የተፈታናችሁና የዩኒቨርስቲና የትምህርት ዘርፎችን ማስተካከል የምትፈልጉ እንደገና ለማስተካከል እድሉ እንዳላችሁ ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡

ምስክር አወል
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመንግሥት ጤና ተቋማት የድንገተኛ ህክምና አገግሎት የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር ከሰላሣ በመቶ በላይ ጨምሯል ተባለ

አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ የመንግሥት ሆስፒታሎች በሚሰጡት የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ዙሪያ መረጃ መለዋወጥ ጀምረዋል፡፡ የአምቡላንስ አገልግሎቱም እንዲሁ የተቀናጀ እንዲሆን መደረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ይናገራሉ፡፡

ነርሶች በመስኩ በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሰለጥኑ፣ ሀኪሞች ደግሞ ዋነኛ የጥናት መስካቸው አድርገው እንዲማሩት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡ ለአምቡላንስ ህክምና አገልግሎት ባለሞያዎችም እንዲሁ የተለየ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ነግረውናል፡፡ ማሻሻያዎቹ የጤና ተቋማቱ የሚሰጡትን የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ይለውጡታል ተብሎ ይታሰባል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በድንገተኛ ህክምና አገልግሎት በኩል እያሳየችው ያለው ለውጥ በአለም መፅሔቶች ጭምር ሽፋን እያገኘ መሆኑን ከሚኒስትሩ ሰምተናል፡፡ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን ፈለግ ለመከተል ወስነዋል ብለዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers