• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የአባይ ግድብ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገሮች ላይ የሚያስከትለው ተፅዕኖ እንዳለ የሚያጠኑ ድርጅቶች ጋር በቅርቡ ስምምነት ይደረሣል ተባለ

ቢ አር ኤል እና አርቴሊያ የተባሉ ሁለት የፈረንሣይ ተቋማት ለጥናቱ የተመረጡ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ጥናቱን ለማስጀመር የተለያዩ ሰነዶች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡ ከ30-60 ቀን ባለ ጊዜ ውይይቱ ተጠናቆ በቅርቡ የፊርማ ስነ-ስርአት የደረጋል ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ተሾመ አጥናፌ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የአባይ ግድብ የውሃ ፍሰት በታችኛው የተፋሰሱ ሀገሮች ማለትም ግብፅና ሱዳን ላይ የሚያስከትለው ተፅዕኖ መኖር አለመኖሩ እንዲጠና አለም አቀፉ የኤክስፐርቶች ቡድን ምክረ ሃሣብ ማስቀመጡ የሚታወስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የአባይ ግድብ ከግማሽ በላይ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንግሥት ተናግሯል፡፡

ፋሲል ረዲ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 18፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምግብና መጠጥ የሚሸጡ 1 ሺህ 500 ቤቶች ታሸጉ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ነው ተብሎ በማህበራዊ ድረ-ገፆች የሚሰራጩት የ12ኛ ክፍል ውጤቶች ሀሰት ናቸው ተባለ፡፡ (ምስክርአወል)
 • በየሦስት ወሩ በቋሚነት ደም የሚለግሱ ሰዎች ቀጥር ጥቂት በመሆኑ በደም እጥረት ምክንያት የሚሞቱ ህሙማንን ሙሉ በሙሉ መታደግ አልተቻለም ተባለ፡፡ (ትዕግስትዘሪሁን)
 • ለአብዛኛዎቹ አፍሪካ ሀገራት ኤምባሲዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጥቷቸዋል ተባለ፡፡ (ተህቦንጉሴ)
 • ቱርካውያን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያከናውኑት ኢንቨስትመንት ከግዜ ጊዜ አየጨመረ ነው፡፡ (ፋሲልረዲ)
 • ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር የተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሁለትዬሽ ስምምነት ማድረጓን ስትሬትስ ታይም የተባለው የሀገሬው ጋዜጣ ፅፏል፡፡ (ፋሲልረዲ)
 • ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አቋራጭ የቁም እንስሣት ንግድንና ህክምና ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ (ፋሲልረዲ)
 • የአባይ ግድብ በግብፅና ሱዳን ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ እንዳለ የሚያጠኑ ተቋማት በ60 ቀን ውስጥ ሥራ ይጀምራሉ ተባለ፡፡ (ፋሲልረዲ)
 • የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በድርቅ የተጐዱ ወገኖችን ለመርዳት አቅም አጥሮኛል ነገር ግን የቻልኩትን ያህል ረድቻለሁ ብሏል፡፡ (ትዕግስትዘሪሁን)
 • የድንገተኛ ህክምና በመንግሥት ሆስፒታሎች የሚሰጡ ነርሶች በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ እንዲማሩ እየተደረገ ነው የመረጃ አሰጣጡም እየተቀላጠፈ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • በቤላሩስ ኤምባሲ ጐርፍ ጉዳት አደረሰ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የአባይ ግድብ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገሮች ላይ የሚያስከትለው ተፅዕኖ እንዳለ የሚያጠኑ ድርጅቶች ጋር በቅርቡ ስምምነት ይደረሣል ተባለ፡፡ (ፋሲልረዲ)

 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኤንፓ ትምህርት ቤት ለመጪው ዓመት የመዘጋት እጣ ተጋርጦበታል

በልመና የሚተዳደሩ እንዲሁም እጅግ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆችን ከነርሰሪ እስከ አፐር ኬጂ በነፃ የሚያስተምረው ኤንፓ ትምህርት ቤት ለመጪው ዓመት የመዘጋት እጣ ተጋርጦበታል…

በሕጻናት ማሳደጊያ ውስጥ ባደጉ ወጣቶች መዋጮ በ2002 ዓ.ም አዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ የተመሰረተው ኤንፓ ትምህርት ቤት የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው የደሃ ቤተሰብ ሕጻናትን ነው የሚያስተምረው፡፡ ሕጻናቱ እህል ሳይቀምሱ ከቤታቸው ስለሚመጡ ትምህርት ቤቱ የሚያስተምራቸውን 80 ያህል እምቦቀቅላዎች ያለችውን አብቃቅቶ ቁርስና ምሳ ይመግባል፡፡

አሁን ላይ ግን አቅም እየከዳው የመጣው ይህ ትምህርት ቤት በቀጣዩ ዓመት የመዘጋት እጣ ተጋርጦበታል ይለናል የሸገሩ ፋሲል ረዲ ዘገባ…

ከመንግሥት እውቅና ተሰጥቶት ከነርሰሪ እስከ አፐር ኬጂ አስተምሮ ከነትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ሕጻናቱን ወደ ሌላ ትምህርት ቤት የሚልከው ኤንፓ ትምህርት ቤት ሕፃናት ተማሪዎቹን ለመመገብ እጅ እያጠረው ማሕበር የደገሱ ሰዎች የሚያቀርቡለትን ምግብ እየተቀበለ ሕጻናቱን ይመግባል ይለናል ዘገባው...

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ነሐሴ 17፣2008

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ክፍል ሰባት


በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር የወተት ስኳር(ላክቶዝ) አለመስማማት እና መፍትሄዎቹ ነሐሴ 17፣2008
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል

ካለፈው አርብ አንስቶ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብሰባ ማዕከል /ኢሲኤ/ ሲካሄድ የሰነበተው የአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች ጉባዔ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል…ጉባዔተኞቹ በአሁኑ ወቅት ባለፉት ቀናት የተወያዩባቸውን ጉዳዬች ባሰፈረው ቃለ ጉባዔ ላይ በመነጋገር ላይ ናቸው፡፡

በቃለ ጉባዔው አልተካተቱም እንዲሁም ይታረሙልን ያሏቸውን ኃሳቦች እያነሱ ነው፡፡ የዚምባብዌው ተወካይ በቃለ ጉባዔው አልተካተተም በሚል ያነሱት ኃሳብ ግን ጉባዔተኞቹን ፈገግ አሰኝቷል፡፡ ተወካዩ ከዓመት በኋላ አገራቸው በምታስተናግደው የአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ተሣታፊዎቹ ባለቤቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ጭምር ይዘው እንዲገኙ መጋበዟ በቃለ ጉባዔው አለመካተቱ ነው ቅር ያሰኛቸው፡፡

ጉባዔተኞቹ የተወካዩን አስተያየት በፈገግታ አልፈውታል፡፡ ሚኒስትሮቹ ባለፉት ቀናት ቆይታቸው የአለም ጤና ድርጅት ለጐርጐሮሣዊያኑ 2018/2019 ያዘጋጀው ረቂቅ በጀት ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት በ2018/2019 በጀት ከ4 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚሆን ለውይይት የቀረበው ረቂቅ ሰነድ ያሣያል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት አከበረ

የውጭ ሀገራት ለጋሽ ድርጅቶች እጃቸው ስላጠረ የራሴን የገንዘብ ማግኛ መንገድ እየፈለኩ ነው ሲል የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ተናገረ…ማህበሩ ይህን ያለው ዛሬ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ነው፡፡ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ማዕዛ ቅጣው እንደተናገሩት ማህበሩ ላለፉት 50 ዓመታት ሥራውን የሚያከናውነው በውጪ ሀገራት ከሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡

አሁንም ቢሆን 90 ከመቶ የሚሆነውን ገቢ ከእነዚህ ድርጅቶች የሚያገኝ ሲሆን በምዕራባዊያን አገሮች በደረሰው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ሳቢያ እጃቸው እያጠረ ነው፡፡በመሆኑም ላለፉ 50 አመታት የለፋባቸውን የቤተሰብ እቅድና የጤና አገልግሎት ለመቀጠል የራሴን ዘዴ እየፈለኩ ነው ብሏል፡፡መንግሥት ከሚያደርግለት የቁሣቁስ ድጋፍ ባሻገር የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን ድጋፍ መጠየቅ ከታሰቡት ዘዴዎች መሀል ሲሆን በተለይም ግን የራሱን ገቢ የሚያስገኝለትን ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ያቋቁማል ተብሏል፡፡ 

ማህበሩ በአንድ ክሊኒክ የዛሬ 50 ዓመት ሥራውን የጀመረ ሲሆን ዛሬ 50 ያህል የጤና ተቋማት ሲኖሩት ብዙ የወጣት ማዕከላትንም አቋቁሟል ተብሏል፡፡ በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ የመክፈቻ  ንግግር ያደረጉ ሲሆን ማህበሩ ያዘጋጀውን መፃሐፍ መርቀዋል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለፍልሰታ ፆም መፍቻ 3 ሺህ 480 በሬ አርጄ ለተመጋቢዎች አከፋፍያለሁ ሲል የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ተናገረ

ለፍልሰታ ፆም መፍቻ 3 ሺህ 480 በሬ አርጄ ለተመጋቢዎች አከፋፍያለሁ ሲል የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ተናገረ… ድርጅቱ ከበሬ በተጨማሪ 207 ፍየል፣ 338 በግና ድርጅቱ ራሱ ያቀረባቸውን 600 በጐች ለፍልሰታ ፆም መፍቻ ማረዱን ነግሮናል፡፡

ቁጥሩም ከአምናው ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲመሣከር ብልጫ እንዳለው ሰምተናል፡፡ አምና በተመሣሣይ ወቅት 2 ሺህ 964 በሬ፣ 333 በግና 323 ፍየል አርዶ ነበር፡፡ ለዘንድሮው የእርድ ብዛት መጨመርም በአተት በሽታ ፍራቻ ድርጅቱ እርድ እንዲፈፅምላቸው የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር መብዛት ዋናው እንደሆነ ከህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል ሰምተናል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በ2008 የበጀት አመት 25 ሺህ በሬዎች ማረዱን ነግሮናል፡፡ ይህም ከ2007 የበጀት አመት በ2 ሺህ 700 ጭማሪ አለው፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 17፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ከኢትዮጵያ በመለጠቅ የአፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባዔን ዚምባብዌ ታስተናግዳለች ተባለ፡፡ የአዲስ አበባው ጉባዔ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅና አልባሣት ኢንዱስትሪ በበጀት አመቱ ያስገባው ገቢ ከታሰበው 50 በመቶ ብቻ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • የኢትዮጵያ የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም ያዋጣናል ያሉ የአፍሪካ ሀገራት የኢትዮጵያን መንገድ እየኮረጁ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • በጅቡቲ መስመር የመኪኖች መጋጨት የመንገድ ችግር መስተጓጎል ፈጥሮ ነበር ተባለ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • ብሔራዊ ባንክ በሀገር ደረጃ የውጭ ምንዛሪ እጥረት የለም እጥረቱ የተከሰተው በግል ባንኮች ደረጃ ነው ብሏል፡፡ (ምስክርአወል)
 • የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት አከበረ፡፡ (ዮሐንስየኋላወርቅ)
 • የኢትዮጵያ የመግባባት እና አንድነት የሰላም ማህበር ከሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር በወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ሊመክር ነው ተባለ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • የአፍሪካ የጤና ሚኒስትሮች ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • ለፍልሰታ ፆም መፍቻ 3 ሺህ 480 በሬ አርጄ ለተመጋቢዎች አከፋፍያለሁ ሲል የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ተናገረ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአሸንዳ በዓል በድምቀት ሊከበር መታሰቡን ሰማን፡፡

በሃገራችን ካሉት በዓላዊ አከባበር አንዱ የሆነው የአሸንዳ በዓል ከነሐሴ አካባቢ ጀምሮ የሚከበር ሕዝባዊ በዓል ነው፡፡ የዘንድሮው የአሸንዳ በዓል በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎችና አዳራሾች በዓሉ ሲከበር መቆየቱን አስታውሶ ነሐሴ 29/2008 ዓ.ም በድምቀት እንደሚከበር የትግራይ ሴቶች ማህበር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ነግረውናል፡፡

ወ/ሮ ምህረት ምናሰብ ነሐሴ 29 ከ14 ሺህ በላይ ታዳጊዎች በተገኙበት በብሔራዊ ባህላዊ ማዕከል ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከበር በፃፉልን ደብዳቤ ጠቁመዋል፡፡የአሸንዳ በዓል ለሃገራችን ቱሪዝም መስህብ ሊሆን እንደሚችልና ለወጣቶች መተላለፍ ከሚገባቸው እሴቶች አንዱ መሆኑን ወ/ሮ ምህረት ጠቅሰዋል፡፡

እሸቴ አሰፋ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በሥራ ባሕሪያቸው የተነሳ ለጉበት በሽታ ሊጋለጡ ለሚችሉ ዜጐች የመከላከያ ክትባት ሊሰጣቸው ነው

በስራ ባሕሪያቸው ምክንያት ለጉበት በሽታ ለሚጋለጡ የህክምና ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ክትባት መስጠት ልትጀምር ነው፡፡

ክትባቱን በሚቀጥሉት ሦስት አመታት ለሁሉም የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ክትባቱን ለመስጠት ታቅዷል ተብሏል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ እንደተናገሩት ለህክምናው  የሚውለው መድኃኒት በሀገር ውስጥ እንዲመረት ከአንድ የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አምራች ፋብሪካ ጋር መንግሥት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የመድኃኒቱ በሀገር ውሰጥ መመረት ታማሚዎች መድኃኒቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙት ያስችላል ብለዋል፡፡

መድኃኒቱን ለመጠቀም አንዱ ችግር የነበረው የዋጋው ውድነት እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

ፋብሪካው መድኃኒቱን ወደ ውጭም የሚልክበት እድል እንደሚፈጠር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ በጉበት በሽታ ሊጠቁ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡት ዜጐች ከ10 አመት በፊት የተወለዱት እንደሆኑ ዶክተር ከሰተብርሃን ተናግረዋል፡፡

ከአስር አመት ወዲህ ለተወለዱ ህፃናት ግን በሽታውን የሚከላከል ክትባት መስጠት ስለተጀመረ ስጋቱ የሣሣ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሙያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከሚወስዱት ከ60 በመቶ በላይ የሚያልፉበት ደረጃ ቢደረስም ውጤቱ አሁንም ደረት የሚያስነፋ አይደለም ተባለ

በዚህ ዓመት በአዲስ አበባ የሙያ ብቃት ምዘና ከወሰዱ አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ባለሙያዎች መካከል ብቁ ሆነው የተገኙት 62 ነጥብ 2 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ተባለ…

ተመዝነው ያላለፉትም ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ሥልጠና መስጠቱ ላይ ትኩረት እየተሰጠው አይደለም ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ምዘና ከወሰዱት መካከል የቢዝነስ ዘርፉ በዛ ያሉ ባለሙያዎችን በማስመዘን የመጀመሪያውን ደረጃ መያዙን ተናግረዋል፡፡

የግንባታ ዘርፉ በሁለተኛነት ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን የጤና ሙያተኞች በተመዛኞች ቁጥር ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers