• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ነሐሴ 16፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ ድርጅት ታሪፍ ማስተካከያ ላደርግ ነው አለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ለመጪዎቹ 14 አመታት የአፍሪካ ሀገራት የሚተዳደሩበት አለም አቀፍ የወባ መከላከል የተግባር ስትራቴጂ ፀድቋል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በሥራ ባሕሪያቸው የተነሳ ለጉበት በሽታ ሊጋለጡ ለሚችሉ ዜጐች የመከላከያ ክትባት ሊሰጣቸው ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የሙያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከሚወስዱት ከ60 በመቶ በላይ የሚያልፉበት ደረጃ ቢደረስም ውጤቱ አሁንም ደረት የሚያስነፋ አይደለም ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ጂኦሎጂካል ሰርቬይ የኤሌክትሪክና የውሃ መቋረጥ ሥራዬ ላይ እንቅፋት ፈጥሮብኛል አለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

66ኛው የዓለማቀፉ የጤና ድርጅት የአፍሪካ አካባቢ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል

ጉባኤው በ5 ቀናት ቆይታው ወባ እና HIV ኤድስን ጨምሮ በተለያዩ የጤና ችግሮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በጤናው መስክ ቀላል የማይባሉ ውጤቶች በኢትዮጵያና በአፍሪካ መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡

ያም ሆኖ ግን አሁንም ብዙ ቀሪ ስራዎች አሉ ነው ያሉት፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተ ብርሃን አድማሱ በጤናው ዘርፍ እስካሁን የተገኙ ውጤቶች ቁርጠኝነቱ ካለ የማይሳካ ነገር እንደማይኖር ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

የጉባኤውን ተሳታፊዎችም በቆይታችሁ ወቅት የጎደለ ወይም ቅር ያላችሁ ነገር ካለ ንገሩን እኔና የመሰሪያ ቤቴ ሰዎች ፈጥነን እናሟላለን ብለዋል፡፡ ተሰናባቿ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማርጋሬት ቻንን ለጉባኤው ተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ በሚገኙ ሉካንዳ ቤቶች አገር አቀፍ የጤና አጠባበቅ ቁጥጥር ሊካሄድ ነው ተባለ

በወረርሽኝ መልክ የተከሰተው የአተት በሽታ አሁን የታማሚው ቁጥር ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ ግን በቁጥጥር ስር አልዋለም ተባለ፡፡ የክረምት ወቅት ስላልተገባደደ ዳግም እንዳያገረሽ ስጋት መኖሩንም ሰምተናል፡፡

የከተማዋ ጤና ቢሮ እና የምግብና የመድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርተው በሰጡት መግለጫ በ4 ክፍለ ከተሞች አልፎ አልፎ አንድ እና ሁለት ታማሚዎች ብቅ ከማለታቸው ውጪ ቁጥሩ እየጨመረ አይደለም ብለዋል፡፡

ይህም የታየባቸው ክፍለ ከተሞች አቃቂ ቃሊቲ፣ ጉለሌ፣ አራዳ፣ ቂርቆስ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ናቸው፡፡ በቦሌ የካና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች ግን አሁንም የአተት ታማሚዎች ቁጥር የበዛ ነው ተብሏል፡፡

መሰረት በዙ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ከጥጥ አምራቾች እና ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር እየተመካከረ ነው

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ከጥጥ አምራቾች እና ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር እየተመካከረ ይገኛል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ታደሰ ኃይሌ በተገኙበት የ2008 የበጀት ዓመት የጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም የጥጥ አምራቾች ስራን እንቅስቃሴ በተመለከተ ሪፖርቶች ቀርበው ተደምጠዋል፡፡

ከሀገር ውስጥ አምራቾች ጋር በተደረገው ንግግር ችግሮች ተብለው ከተሰሙ ነጥቦች መሃከል ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ከመንግስት የተለያዩ ድጋፎች ተሰጥቷቸው የሚያመርቱ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ፋንታ በሀገር ውስጥ ችርቻሮ ላይ ተሰማርተዋል መባሉ ነው፡፡

ኢንዱስትሪዎቹ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ድጋፍና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ከተሰጧቸው በኋላ ምርቶቻቸውን በሀገር ውስጥ መቸርቸራቸው የሀገር ውስጡ አምራቹን እየጎዳ ነው ተብሏል፡፡ የጥጥ ምርት ገበያው ካለፈው ጊዜ የተሻለ ነው፤ ይሁንና  አሁን ያሉት ኢንዱስትሪዎች አቅማቸው ካልተጠናከረ የጥጥ ምሩቱም ተመልሶ ገበያውን ያጣል ተብሏል፡፡

የ2008 ዓ.ም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ጥጥ አምራቾች ማህበር ከኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በተወያዩ ጊዜ በ2009 ዓ.ም ስለሚሰራቸው እቅዶቹ እና ከመንግስት ሊደረግለት ስለሚገባው ድጋፍ በኢሊሌ ሆቴል እየተወያዩ ይገኛል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 13፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

 • የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ዘንድሮ 350 ሚሊየን ብር ገቢ አግኝቻለሁ ከሁለት መቶ በላይ ቤት የያዙ ህገ-ወጦችን አስለቅቄያሁ ብሏል፡፡ (ምስክር አወል)
 • ኢዴፓ በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ነበረኝ ያለው የልዩነት ኃሳብ አልተነገረልኝም ማለቱን የዕለቱ ሰብሳቢ ሐሰት ነው ማለታቸው ተሰማ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • ዘንድሮ ከበጎ ፍቃደኞች ከአምናው የተሻለ የደም መጠን ተሰበሰበ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ለከተማዋ መንገዶች የአገልግሎት ክፍያ የሚጠይቋችሁ ካሉ ድርጊቱ ህገ-ወጥ ነውና ጠቁሙኝ አለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በወረርሽኝ መልክ የተከሰተው የአተት በሽታ አሁን የታማሚው ቁጥር ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ ግን በቁጥጥር ስር አልዋለም ተባለ፡፡ (መሰረት በዙ)
 • የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ከጥጥ አምራቾች እና ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር እየተመካከረ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የመንግስት ተቋማት እርስ በርስ ተናብበው ባለመስራታቸው በመንገድ ዘርፍ ብቻ በየዓመቱ በቢሊየን የሚቆጠር ብር ይባክናል ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በአዲስ አበባ በሚገኙ ሉካንዳ ቤቶች አገር አቀፍ የጤና አጠባበቅ ቁጥጥር ሊካሄድ ነው ተባለ፡፡ (መሰረት በዙ)
 • 66ኛው የዓለማቀፉ የጤና ድርጅት የአፍሪካ አካባቢ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡ (ንጋቱ ረጋሳ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 12፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በያዝነው የክረምት ወቅት በሶማሌ ክልል በጎርፍ ሊፈናቀሉና ጉዳትም ሊደርስባቸው ይችላሉ የተባሉ 315 ሺ ዜጎች ተለይተዋል ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያ በያዝነው ዓመት ከ42 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ነፃ የአንቡላንስ አገልግሎት ሰጠሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ሰፋፊ የመሬት ይዞታ ላላቸው ኤምባሲዎች ካርታ እየተሰጣቸው ነው ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በኢትዮጵያ ካሉ ተሽከርካሪዎች 60 % ያህሉ የሚሽከረከሩት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ነው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ነሐሴ 10፣2008

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ክፍል ስድስት

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር ነሐሴ 10፣2008
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ቶታል ኢትዮጵያ ነዳጅ በየትኛው ማደያ እንዳለ ለማወቅ የሚያስችል የሞባይል አፕልኬሽን ስራ ላይ አዋልኩ አለ

በአዲስ አበባ ባሉት 35 የቶታል ነዳጅ ማደያዎች መካከል በየትኛው ማደያ ነዳጅ እንደሚገኝ ቦታው ደርሰው ሳይሆን ቀድመው ማወቅ የሚችሉበትን መላ አበጅቻለሁ ሲል ተናግሯል፡፡ አፕልኬሽኑን በዘመን አፈራሽ ስልኮች ላይ በመጫን የት አካባቢ ነዳጅ እንዳለ በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል ሲሉ የቶታል ኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ኃላፊ አቶ መስፍን ተፈሪ ተናግረዋል፡፡

አፕልኬሽኑን ለመጫን በጉግል ፕሌይ ስቶር በአፕል ስቶር ውስጥ በመግባት ቶታል ሰርቪስ የሚለውን በመፈለግ መጫን ይቻላል ተብሏል፡፡ ቶታል ቴክኖሎጂውን ባስተዋወቀበት ስነ ስርዓት ደምበኞች በማደያው የተለያዩ አገልግሎቶችን ከተጠቀሙ በኋላ ከM ብር ጋር በተመተባበር ክፍያውን በተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ማስተላለፍ ዘዴ መክፈል ይችላሉ ሲሉ አቶ መስፍን ተናግረዋል፡፡

መሰረት በዙ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 11፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በሶማሌ ክልል የበልግ ዝናብ ባልጣለባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎችና እንስሶቻቸው ውሃ በቦቴ እየቀረበላቸው ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የጅቡቲ ወደብ ከእርዳታ እህልና ከማዳበሪያ የትኛውን ቅድሚያ ሰጥቼ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ተቸግሬያለሁ ማለቱ ተሰማ፡፡ (ምስክር አወል)
 • ግብፅ የአባይ ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ብትፈርምም እንኳ በአባይ ግድብ ግንባታ ላይ ጥያቄ ማንሳት መብት አይኖራትም ተባለ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ቶታል ኢትዮጵያ ነዳጅ በየትኛው ማደያ ጣቢያ እንዳለ ለማወቅ የሚያስችል የሞባይል አፕልኬሽን ሥራ ላይ አዋልኩኝ አለ፡፡ (መሰረት በዙ)
 • የተወሰነብን የግብር ውሣኔ ትክክል አይደለም ብለው ይግባኝ ላሉ 140 ግብር ከፋዮች ውሣኔ መስጠቱን የአዲስ አበባ የግብር ይግባኝ ጉባኤ ጽ/ቤት ተናገረ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 10፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በዘንድሮው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የጠጣር የመአድን ቁፋሮ ሥራ የታሰበውን ያክል አልተሰራም ተባለ፡፡ ችግሩ የፀጥታ ስጋት ነው ስለመባሉም ተሰምቷል፡፡ ዮሐንስ የኋላወርቅ
 • ኢትዮጵያ በቆዳው ዘርፍ በኩል ያለባትን ችግር ስታነሳ ከዓለም ተለዋዋጭ ሁኔታ ጋር አብሮ የሚያድግ የዲዛይን እውቀት ያለመኖር ይነሳል፡፡ በስራው ውስጥ ያለው የቆዳ ዲዛይን ባለሙያ ደግሞ አቅማችንን ለማሳየት የሚያስጠጋን ከየት ተገኝቶ ይላል፡፡ ቴዎድሮስ ወርቁ
 • ሰሞኑን በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የማግኘቱ ነገር ከቀደመውም ጭርሱን ብሶበት ሰንብቷል፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪም ይህንኑ ጥያቄ ደጋግሞ ሲያነሳ ነበር፡፡ ችግሩ ምንድን ነው ተህቦ ንጉሴ የተቋሙን ኃላፊ ጠይቆ የነገሩትን አሁን ይነግራችኋል፡፡
 • አለም አቀፉ የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አተትን ለመከላከያ ለኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡ ወንድሙ ኃይሉ
 • በአዲስ አበባ የትራንስፖርት እጥረት ያለባቸው 30 መስመሮች በጥናት ተለይተው በአምስቱ ላይ አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ýሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተናገረ፡፡ መሠረት በዙ  
 • የኢትዮጵያ ወጣቶች የዲያስፖራ ፎረም ተመሠረተ፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን
 • መንግሥት ተከላካይ ጠበቃ በነፃ እንዲያቆምላቸው የሚጠይቁ ተከሣሾች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ ንጋቱ ረጋሣ
 • ኢትዮጵያ ዘንድሮ ሻል ያለ የሰብል ምርት እያገኘች ነው፡፡ ወንድሙ ኃይሉ
 • በቀለበት መንገዶች ላይ ተጨማሪ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዬች ሊሰሩ ነው፡፡ መሠረት በዙ     
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ወጣቶች የዲያስፖራ ፎረም ተመሠረተ

የኢትዮጵያ ወጣቶች ዲያስፖራ ፎረም ዛሬ በይፋ ተመሰረተ፡፡ በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ስር የተመሠረተው የወጣቶች ዲያስፖራ ፎረም የተለያየ አቅም ባለቤት የሆኑና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ወጣቶችን ለአገር እድገትና ለውጥ ለመጠቀም ያስችላል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

የፎረሙ ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ የተማረ አወቀ እንዳሉት በተለያዩ ክፍላተ አለማት በሥራና በትምህርት የተሰማሩ የኢትዮጵያ ወጣቶች አዳዲስ የሥራ ኃሳቦችን ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው መጥተው መስራት እንዲችሉ ፎረሙ የራሱን ድርሻ ይወጣል ብለዋል፡፡ ወጣቱን ዲያስፖራ ሀገር ውስጥ ከሚኖሩ ወጣቶች ጋር በማገናኘት የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር ያደርጋል መባሉንም ሰምተናል፡፡

ዛሬ በጊዮን ሆቴል በተካሄደው የስረታ ስነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተን እንደሰማነው በተለይ ሁለተኛ ትውልድ ለሆኑ እና በውጭ ሀገር ተወልደው ላደጉ ዲያስፖራ ወጣቶች የሀገራቸውን ባህልና እሴት እንዲያውቁም የተመሠረተው ፎረም አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ወጣቱ ያለውን እውቀትና ልምድ ይዞ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት እውቀቱንና መዋዕለ ነዋዩን እንዲያፈስ ትክክለኛ መረጃ እንዲደርሰው ይደረጋል መባሉንም ሰምተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers