• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ኢትዮጵያ ዘንድሮ ሻል ያለ የሰብል ምርት እያገኘች ነው

ዘንድሮ በአየር ንብረት መዛባት ኤልኒኖ ምክንያት አጋጥሞ የነበረውን ድርቅ አሁን መቋቋም እየተቻለ ነው ሲል የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር ተናገር፡፡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ለሸገር ሲናገሩ ዘንድሮ በመላው ኢትዮጵያ 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን ታቅዶ እስካሁን በ10 ሚሊየን ሄክታር መሬት ሰብል ማልማት ተችሏል፡፡

ይህም አጋጥሞ የነበረውን ድርቅ ለመቋቋም ያስቻለ ነው ብለዋል፡፡ ይህንኑ የሰብል ምርት በዚህ ሳምንት ወደ 11 ሚሊየን ሄክታር ፣ በነሐሴ መጨረሻም 13 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር ለማድረስ ለአርሶ አደሩ የማዳበሪያና ምርጥ ዘር አቅርቦት እየተደረገ ነው፡፡ አቶ አለማየሁ በዘንድሮ የመኸር እርሻ መሬቱ በበቆሎ ፣ በገብስ ከስንዴና በጤፍ ምርት ነው እየተሸፈነ ያለው በማለትም ነግረውናል፡፡ ዘንድሮ ዝናቡ በጥሩ ሁኔታ እየጣለ በመሆኑ የሰብል ምርት የታሰበው መጠን እየተገኘ ነው ተብሏል፡፡

 ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በቀለበት መንገዶች ላይ ተጨማሪ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዬች ሊሰሩ ነው

ለእግረኞች መሻገሪያ ርቀት አላቸው በተባሉ ቀለበት መንገዶች ላይ ተጨማሪ መሻገሪያ ድልድዬች ሊሰሩ ነው ተባለ፡፡ መሻገሪያ ድልድዩ እስኪሰራ ጊዜያዊ መፍትሄ የተባለው በቀለበት መንገዱ ላይ እግረኞች እንዳይሻገሩ ብረቱን ማስረዘም ነው ሲል የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተናግሯል፡፡

መሻገሪያ ድልድዬቹ የተራራቁ ሆነው እግረኞች ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ይዘሉበታል የተባሉት 5 ዋና ዋና የቀለበት መንገድ መሆናቸውን የጽ/ቤቱ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሮ ታፈሱ አባይ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ ቦሌ ጉምሩክ ፣ ሀኪም ማሞ ፣ ኮልፌ አጠና ተራ ፣ 18 ማዞሪያ እና ሣሪስ አቦ ቀለበት መንገዶች ተለይተዋል፡፡ የጉምሩክ ሀኪም ማሞ እና የኮልፌ አጠና ተራ የሚገኙ 5 ኪሎ ሜትር የሚሆኑ የቀለበት መንገድ ብረቶችን የማስረዘም ሥራ ተጀምሯል ተብሏል፡፡

ከ7 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 90 ሴ.ሜትር የነበረው ብረት 45 ሴ.ሜትር ላይ ተጨምሮ 135 ሴ.ሜትር ርዝመት ይኖረዋል፡፡ ይህም እግረኞች በቀላሉ እንዳይሻገሩ ያደርጋቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የተራራቁ እና ቀድሞም የቀለበት መንገድ ያልነበራቸው የእግረኞች መሻገሪያ በ2009 ግንባታው ይጀመራል ሙሉ ወጪውም ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡

መሠረት በዙ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

መንግሥት ተከላካይ ጠበቃ በነፃ እንዲያቆምላቸው የሚጠይቁ ተከሣሾች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ

መንግሥት ተከላካይ ጠበቃ በነፃ እንዲያቆምላቸው የሚጠይቁ ተከሳሾች ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ ገቢ ለሌላቸው እና በራሳቸው ተከላካይ ጠበቃ ማቆም ለማይችሉ ተከሣሾች መንግሥት ጠበቃ ያቆማል፡፡ ተከሳሾቹ ጠበቃው የሚቆምላቸው አቅም እንደሌላቸው ሲገልፁና ይህንኑ በመሃላ ሲያረጋግጡ ነው፡፡ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት እንደሚለው አገልግሎቱን የሚፈልጉ ተከሳሾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እንኳን ከሰባት ሺህ ስድስት መቶ ለሚበልጡ ተከሣሾች መንግሥት ጠበቃ እንዳቆመ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አባተ ደጀኔ ነግረውናል፡፡ ከስርቆት አንስቶ እስከ ሽብር ባሉ ወንጀሎች ለተከሰሱ ሰዎች ጥብቅናውን እንዳቆሙም ነግረውናል፡፡ ጽ/ቤቱ አገልግሎቱን የሚሰጡ ሃያ አምስት ጠበቆች እንዳሉት ነው ከአቶ አባተ የሰማነው፡፡

በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የጠበቆቹ ቁጥር ወደ ሰላሳ አምስት ከፍ ይላል ብለውናል፡፡ አንድ ጠበቃ በአማካይ እስከ መቶ ለሚደርሱ ተከሳሾች ተከላካይ ሆኖ እንደሚቆምም ነግረውናል፡፡ ተገቢውን አገልግሎት ባልሰጠ ጠበቃ ለይ ተከሳሾች በፍርድ ቤት ጭምር ቅሬታውን የሚሰሙበት አሰራር እየተለመደ መምጣቱንም ከአቶ አባተ ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ረጋሣ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ተናገረ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ተናገረ…የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን ዱሬሳ ለሸገር እንደተናገሩት ፈተናውን ከወሰዱ 246 ሺህ 570 ተፈታኞች መካከል 50 በመቶዎቹ ከ350 በላይ አስመዝግበዋል ብለዋል፡፡

ይህም ከባለፈው አመት ተፈታኞች ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑን ዶክተር ዘሪሁን ተናግረዋል፡፡ ተፈታኞችም ውጤታችሁን በኤጀንሲው ድረ-ገፅ www.neaea.gov.et በመግባት ወይንም በነፃ የአጭር የፅሁፍ መልዕክት 8181 RTW መለያ ቁጥራችሁን አስገብታችሁ ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡

ውጤቱ አስቀድሞ ይፋ የሆነበት ምክንያትም ተማሪዎች ባላቸው ግዜ ተጠቅመው የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት ዘርፍ ምርጫቸውን እንዲያስተካክሉ ታስቦ መሆኑን ዶክተር ዘሪሁን ነግረውናል፡፡ ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባቸው የውጤት ቁጥርም የዩኒቨርስቲዎች የቅበላ  አቅም ከታየ በኋላ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ሰምተናል፡፡

ምስክር አወል

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ነሐሴ 9፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የኮሙኒኬሽንና የሃይል ማስተላለፍ ኬብል አምራች የሆነው BMET ኩባንያ ለምርት የሚረዱኝን ጥሬ ዕቃዎች ማስገባት እየቸገረኝ ነው አለ፡፡ (ህይወትፍሬስብሃት)
 • የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ጎብኚም ገቢም እየበዛለት ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • በኤሌክትሪክ ኃይል የሚንቀሣቀሱ ባለ 3 ጐማ አገር በቀል ተሽከርካሪዎችን በቅርቡ በየጐዳናው ወዲህ ወዲያ ሲሉ ታይዋቸዋላችሁ ተባለ፡፡ (ሕይወትፍሬስብሃት)
 • የአዲስ አበባ መንገዶች መቆፋፈር የትራፊክ መጨናነቅ አስከትሏል ተባለ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • ኢትዮጵያ ሰሞኑን አህጉራዊ የጤና ጉባዔን ልታስተናግድ ነው፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • የኢትዮጵያ የበጐ አድራጐት ማኅበራትና ድርጅቶች ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት እንዳለባቸው በጥናት መረጋገጡ ተሠማ፡፡ (ትዕግሥትዘሪሁን)
 • የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ተናገረ (ምስክር አወል)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች መማሪያ የሚሆን መፅሀፍ በ38 ሚሊየን ብር ማሣተሙን ተናገረ

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች መማሪያ የሚሆን መፅሀፍ በ38 ሚሊየን ብር ማሣተሙን ተናገረ… የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የመፅሀፍ ዕደላውን ፕሮግራም አውጥቶ ለግል ትምህርት ቤቶች እያዳረሰ መሆኑን በቢሮው የኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ አበበ ቸርነት ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የግል ትምህርት ቤቶች በሚከፍሉት ተዘዋዋሪ ክፍያ የታተሙትና አሁን የሚሰራጩት መፃህፍት በህትመት ዋጋቸው መሠረት ለተማሪዎች እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ማሣሰቢያ ሰጥቷል፡፡

በመፅሀፍ ግዢ ሰበብ የሚጠየቁ ከተመን በላይ የሆኑ ክፍያዎች የተከለከሉ መሆናቸውንም ሰምተናል፡፡ ለ2009 የትምህርት ዘመን መማሪያ የሚሆኑት የተማሪዎች መፃህፍት በበቂ መጠን በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች ታትመው መዘጋጀታቸውን አቶ አበበ ነግረውናል፡፡

የግል ትምህርት ቤቶች ያስፈልግናል ብለው በጠየቁት የመፅሀፍ ዝርዝር ብዛት መሠረት ስርጭቱ እንደሚካሄድ የተናገሩት አቶ አበበ ቸርነት ትምህርት ቢሮ እስከ ነሐሴ 30 ድረስ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች መፅሀፉን ለማሰራጨት ፕሮግራም አውጥቷል ብለዋል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰሞኑን በሃገራችን በተፈጠረው ግጭት ሃዘኑን ገልጿል፡፡ መንግሥት በትዕግስትና በሆደሰፊነት ወጣቶችም ሰላምን ለመጠበቅ እንዲዘጋጁ መክረዋል

ወጣቶች የሀገራቸውን ሰላም የመጠበቅ ድርሻቸውን እንዲወጡና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችም ሆደ ሰፊ ሆነው በከፍተኛ ትዕግስት እንዲቆጣጠሩና እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች ተናገሩ፡፡

ዛሬ ከሰዓት በፊት በኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ ጽ/ቤት ተሰጠው መግለጫ የሃይማኖት አባቶች ለእምነት ተከታዬቻቸው በአገራችን ላይ የታየውን ግጭት መነሻ በማድረግ ምክርና ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶቹ ጉባኤ ወጣቶች በማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚለቀቁ መረጃዎችን ለማጣራትና ጠቀሜታዎቹንና ገንቢነታቸውን እየመረመሩ እንዲጠቀሙባቸው መክረዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶቹ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ህዝብን የማስተዳደር ከባድ አደራ በቅንነት እንዲወጡ ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን የማስተናገድና የመመለስ ጥረት እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል፡፡

ከመንገድ የወጣ ሁኔታ ሲያጋጥምም በሆደ ሰፊነት በትዕግስት፣ በማስተዋል፣ ቁጥጥርና ጥበቃ እንዲያደርጉ መክረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ በዘመናዊ ግብርናና ምግብ ማቀነባበር መስኮች የተማረ የሰው ኃይል እጥረቱ ሥር የሰደደ መሆኑን አንድ ጥናት አሣየ

ኢትዮጵያ በጤናውና በግብርናው ዘርፍ ያላት በሳይንስና ቴክኖሎጂው ሊያግዛት የሚችል የሰው ኃይል ምን ያክል ነው ? በፍላጐትና ባለው መካከል ያለው ልዩነትስ ? ይህንን የተመለከተው በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሲሰራ የነበረው ጥናት ዛሬ በጊዮን ሆቴል ቀርቦ ምክክር እየተደረገበት ነው…

የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ተገኝ ገብረእግዚአብሔር የግብርናውን ዘርፍ የተመለከተውን የጥናት ውጤት ሲያቀርቡ እንደ ባዮቴክኖሎጂ፣ ምግብ ማቀነባበር፣ በወተትና ሥጋ ምርት ቴክኖሎጂ እና በሌሎችም ያለውን የተማረ የሰው ኃይል ዝቅተኛ መሆን አንስተዋል፡፡

ጥናቱ ከተመለከታቸው ዩኒቨርስቲዎች የተወሰኑት ከአመት አመት በግብርናው ዘርፍ ያላቸው የተማሪ የቅበላ መጠን እየቀነሰ ስለመምጣቱም ጥናቱ አሳይቷል ብለዋል፡፡

በዘርፉ ያለውን የተማረ የሰው ኃይል ድርሻን ሲያስረዱም ትልቁና ወደ 11 ነጥብ 6 በመቶ በእንስሣት ሣይንስ ዘርፍ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ካሉ ወደ 2 ሺህ ገደማ በሰብል ምርትና በቁም እንስሣት ማደለብ ከተሰማሩ የግል ድርጅቶች 380ውን ጥናቱ ተመልክቷል፡፡

ከስድስት መቶ ሰባ ወረዳዎች አንድ መቶ አስራ ስድስቱን ከፍተኛ የትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን እንዲሁም ሌሎችንም መሥራያ ቤቶች ተመልክቷል ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 6፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አዳማ ነባሩ መንገድ በ2008 በደረሰ የትራፊክ አደጋ ከ100 በላይ ሰዎች ሞተዋል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች መማሪያ የሚሆን መፅሀፍ በ38 ሚሊየን ብር ማሣተሙን ተናገረ፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • በየጉራንጉሩ እርድ የሚፈፅሙና ለተመጋቢ የሚያቀርቡ ህገ-ወጦች በዝተዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር በአዲስ አበባ ጉባኤ ጠራ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰሞኑን በሃገራችን በተፈጠረው ግጭት ሃዘኑን ገልጿል፡፡ መንግሥት በትዕግስትና በሆደሰፊነት ወጣቶችም ሰላምን ለመጠበቅ እንዲዘጋጁ መክረዋል፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በኢትዮጵያ በዘመናዊ ግብርናና ምግብ ማቀነባበር መስኮች የተማረ የሰው ኃይል እጥረቱ ሥር የሰደደ መሆኑን አንድ ጥናት አሣየ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በኦሮሚያ ክልል የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች የፍጥነት ወሰን መገደቢያ መግጠሚያ የጊዜ ገደብ መራዘሙ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ዘንድሮ ከአበባ ወጪ ምርት ከ275 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የቴክኒክና ሙያ ትምህትና ሥልጠና በሚመለከት ዝርዝርና የተደራጀ መረጃ አያያዙ ጉደለት እንዳለበት ተነገረ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለኢትዮጵያ ምርጥ የተባሉ የሶፍትዌር ፈጠራዎች ተሸለሙ

የጤና ተቋሞችን አገልግሎትና የመረጃ አያያዝ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ያደርጋል የተባለና የአማርኛ የምልክት ቋንቋ ፕሮግራም የአመቱ የላቁ የሶፍትዌር የፈጠራ ፕሮግራሞች ተብለው ተሸለሙ፡፡

ዝግጅቱን ያሰናዳው በአዲስ አበባ ዩኒቨርቲ የአይ.ሲቲ ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንስ ሲሆን የዘንድሮው ለአምስተኛ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

ዛሬ በካፒታል ሆቴል በተሰናዳው ዝግጅት ላይ ከቀረቡት የሶፍት ዌር ፕሮግራሞች ከሀዋሳ በመጡት አቶ መብቱ አበበ የቀረበውና ስማርት ኤሌክትሮኒክ ሜዲካል ሲስተም የተባለው ከአጠቃላይ ምድብ አሸናፊ ሆኗል፡፡

አቶ መብቱ እንደሚሉት የጤና ተቋማት 60 በመቶ ጊዜያቸውን መረጃን መልክ በማስያዝ ያጠፋሉ፡፡ አዲሱ ሶፍት ዌር ይሄንን አድካሚ ሥራ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ቀላል የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ ለሥራውም 75 ሺህ ብር ተሸልመዋል፡፡

ከሴቶች ምድብ አሸናፊ የሆነችው የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ እንግዳወርቅ ከበደ የሠራችው ሶፍት ዌር ደግሞ የአማርኛ የምልክት ቋንቋ ሲሆን ቋንቋውን በሚያውቁትና በማያውቁት መካከል እስካሁን የነበረውን ችግር ሶፍት ዌሩ ይፈታል፣ መግባባት እንዲችሉም ያደርጋል ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ወጪ ንግድ ገቢ እየቀነሰ ነው ተባለ

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከቆዳና የቆዳ ውጤቶች የወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ16 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ቅናሽ አለው ተባለ…ካለቀለት ቆዳና የቆዳ ውጤቶች የወጪ ንግድ 185 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት ተወጥኖ ነበር፤ ማግኘት የተቻለው ግን 116 ነጥብ 35 ሚሊየን ዶላር መሆኑን ሰምተናል፡፡

ይህም ከእቅዱ ጋር ሲመሣከር አፈፃፀሙ 63 በመቶ ብቻ ነው እንደማለት ነው፡፡ ከቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት እንደሰማነው በ2007 የበጀት ዓመት ያለቀለት ቆዳንና የቆዳ ውጤቶችን ለውጪ ሀገራት በመሸጥ 132 ሚሊየን ዶላር ማግኘት ተችሎ ነበር፡፡

በዚህ ዓመት የወጪ ንግዱ በ16 ሚሊየን ዶላር ያነሰ አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡ ከምርቶቹ መካከል ቅናሽ የታየበትም ያለቀለት ቆዳ ሲሆን ከጉድለቱ የ18 ነጥብ 81 ሚሊየን ዶላር ያህሉን ድርሻ ይዟል፡፡ በሌላ በኩል ግን መጠናቸው ትንሽም ቢሆን በሌሎች የቆዳ ውጤቶች የወጪ ንግድ ገቢ ላይ ከአምናው የተሻለ ገቢ መገኘቱንም ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers