• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሐምሌ 21፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የብሔራዊ ቤተ-መፃሕፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ ተገልጋዮች ወጪዬን እንዲጋሩ ላደርግ ነው አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በአዲስ አበባ ከዚህ ቀደም በተካሄደ ቆጠራ በማንም አለመያዛቸው የተደረሰበት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለመምህራን በተመጣጠነ ዋጋ ሊከራይ ነው ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • ኢትዮጵያ የቆዳ ሕመም መድኃኒት እጥረት እንዳለባት ተነገረ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የአዳማ የፍጥነት መንገድ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ዘመናዊ የቁጥጥር ስርዓት ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ (መሠረት በዙ)
 • አፍሪካ ከቅኝ ግዛት ነፃ ብትወጣም ለም መሬቷን እያዩ የሚቀራመቷትና ባህሏን የሚበርዙባት እየበዙ ነው ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርን በ380 ሚሊዮን ብር በጀት በአዲስ መልኩ እያስገነባ ነው ተባለ፡፡ (ፍቅርተ መንገሻ)
 • የሐጂና ኡምራ ጉዞ ምዝገባ ትናንት ተጠናቀቀ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአማራ ክልል የዳያስፖራ ቀን መከበር ጀመረ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ካርታ ሥራዎች ድርጅት ከጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ጋር ስራዬን እያዘመንኩ ነው ብሏል፡፡ (ምስክር አወል)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የተሻሻለው የንግድ ምዝገባ ሕግ ነባር ማነቆዎችን የሚያስወግድ መሆኑ ተነገረ

ተሻሽሎ የፀደቀው የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ የነጋዴውን ህብረተሰብ እንግልትና ቅሬታ ይፈታል ተባለ…

ቅሬታ ይበዛባቸዋል የተባሉ አንቀፆችም ተሽረዋል፡፡

የንግድ ፈቃድ አውጥቶ በግል ለመሥራት ከዚህ ቀደም ድርጅቱ የሚንቀሳቀሰበት በባንክ የተረጋገጠና በዝግ ሂሳብ የተያዘ ገንዘብ ማሳየት የግድ ነበር፡፡

ይህ አንቀፅ በተሻሻለው አዋጅ ከተሻሩት መካከል አንዱ ሆኗል፡፡ በመሆኑም የንግድ ፈቃድ አውጥቶ በንግድና በግል ስራ ላይ መሰማራት የፈለገ ሁሉ አለኝ የሚለውን ካፒታል በማስመዝገብ ብቻ በቀላሉ የንግድ ምዝገባ ማድረግና ፈቃድ ማውጣት ይችላል ተብሏል፡፡

ትናንት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቦ የፀደቀውና የተሻሻለው የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ በ1952 ተደንግጐ ከነበረው የንግድ ህግ የሻረው ሌላም አንቀፅ አለ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ የተከሰተው የአተት በሽታ ሊስፋፋ ስለሚችል ጥንቃቄው እንዲበረታ ምክር ተሰጠ

በተከማዋ የተከሰተው የአተት በሽታ ሊቀጥል ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ተባለ…

ይህንን የሰማነው ዛሬ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋዜጠኞችን ጠርቶ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ተገኝተን ነው፡፡

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ አሸናፊ እንደተናገሩት በሽታው በከተማዋ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች ላይ ምልክቱ ታይቷል፡፡

ከክፍለ ከተሞችና ወረዳዎችም በየቀኑ ስለ በሽታው ሪፖርት እንደሚደረግ ተናግረው ከክረምቱ ጋር ተያይዞ በሽታው ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት ስላለ የመከላከል ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥለ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ለበሸታው ዋና ምንጭ ከተባሉት መካከል የወንዝና የጉድጓድ ውሃን ሳያክሙ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ማዋል እና ያልበሰሉ አትክልቶችን እንዲሁም ጥሬ ስጋን መመገብ ለበሽታው መስፋፋት መንስኤ ሆነዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሙከራ ደረጃ ላይ ያለው የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት ከ2 ዓመት በኋላ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይሰጣል ተብሏል

ካለፈው እሁድ ጀምሮ እዚህ አዲስ አበባ በአፍሪካ ህብረት የስብሰባ አዳራሽ ሲካሄድ የሰነበተው 10ኛው የማህፀን በር ጫፍ፣ የጡትና የኘሮስቴት ካንሰርን ከአፍሪካ እንናጥፋ ኮንፈረንስ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡ የኮንፈረንሱ ተሣታፊዎች በአራት ቀናት ውይይታቸው የደረሱባቸውን ስምምነቶች የተመለከተ የአቋም መግለጫም አውጥተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታ በሆኑት ዶክተር ከበደ ወርቁ የተነበበው ይህ የአቋም መግለጫ አፍሪካ ውስጥ በካንሰር በሽታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሷል፡፡ ሁኔታውን ለመለወጥ የኮንፈረንሱ ተሣታፊዎች በጋራ ለመስራትም መስማማታቸውን በመግለጫቸው አረጋግጠዋል፡፡

የጐርጐሮሣዊያኑ ዘመን 2017 የኮንፈረንሱ አስተናጋጅ ሀገር ስዋዚላንድ ስትሆን የ2018 አስተናጋጅ ደግሞ ቡርኪናፋሶ እንደምትሆን በኮንፈረንሱ ላይ ተነግሯል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 20፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በአዲስ አበባ የተከሰተው የአተት በሽታ ሊስፋፋ ስለሚችል ጥንቃቄው እንዲበረታ ምክር ተሰጠ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማህበር ለዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ድጋፉን እንደሚሰጥ ተናገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚመረትን ቡና በቀላሉ ለማጓጓዝ የሚያስችል መንገድ ለመገንባት ከ127 ሚሊዮን ዶላር በላይ የብድር ስምምነት ፀደቀ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በሮቤ በተከሰተው የምግብ መመረዝ ከሞቱ ሰዎች በተጨማሪ ወደ ሆስፒታል የገቡም ብዙ ናቸው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በሙከራ ደረጃ ላይ ያለው የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት ከ2 ዓመት በኋላ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይሰጣል ተብሏል፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የስኳር ሕሙማን ማኅበር የባለሙያ ያለህ እያለ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የተሻሻለው የንግድ ምዝገባ ሕግ ነባር ማነቆዎችን የሚያስወግድ መሆኑ ተነገረ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በእምነት ማጉደል ወንጀል ጥፋተኞች የተባሉ ሁለት የሬስቶራንት አስተናጋጆች የእስር ቅጣት ተፈረደባቸው፡፡ (ተክለማርያም ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሸገር 102.1 የለዛ ፕሮግራም 6ኛው የአድማጮች ምርጥ

እነሆ ስድስተኛው ላይ ደርሰናል!

በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የለዛ ፕሮግራም የአድማጮች ምርጦችን ለመሸለም ቅድመ ዝግጅታችንን ጀምረናል፡፡ እንደተለመደው በ http://www.shegerfm.com/102-1-fm-2008 ከነገ ሐምሌ 21፣2008 ጀምሮ የመጀመሪያውን ዙር ድምፃችሁን ላመናችሁበትና በእርግጥም ሊሸለም ይገባዋል ለምትሉት ስራና ሙያተኞች ትሰጡ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ ይህንን ስንል ለሞያተኞቹ ያላችሁን ፍቅር እና አክብሮት እንዳለ ሆኖ ምርጫችሁ ግን ኪነጥበባዊ ፋይዳዎቻቸው ከፍ ላሉ ስራዎችና ጥበበኞች ብቻ እንዲሆን፤ ለእነርሱም ድምፃችሁን በተገቢውና የምርጫው መስፈርት በሚጠይቀው መሰረት እንድትሰጡ፣ ኪነ-ጥበቡን እና ጥበበኞቹንም ታበረታቱ፣ ትደግፉና ትመርጡ ዘንድ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! 

ማስታወሻ:በዚህ ድህረ ገፅ ላይ በአስተያየት መስጫው ወይም በኢሜል አድራሻ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  ከሐምሌ 1፣2007 ወዲህ በወጡ ፊልሞች ላይ ኦሪጅናል የፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ ያቀረባችሁ ድምፃውያን የፊልሙን አርዕስት፣ የፊልሙን የማጀቢያ ዘፈን አርዕስት እና ስማችሁን ከነ አድራሸችሁ አያይዛችሁ በመጻፍ ታኖሩልን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ዘፈኑን ለአድማጮቻችን እናሰማው ዘንድ ብታቀብሉን ሸግዬ ነው፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ሐምሌ 19፣2008

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ክፍል ሶስት

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር ጤናማ አመጋገብ እና ሳይንሳዊ ህጎች ሐምሌ 19፣2008
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በፀደቀው የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት ማንኛውም ተቀጣሪ ከቅጥር ውጭ በተለያዩ ሥራዎች የሚያገኘውን ገቢ ግብር የሚከፍልበት ከደሞዙ ጋር ተደምሮ በሚገኘው መጠን ልክ ይሆናል ተባለ

ተሻሽሎ በቀረበውና ዛሬ በፀደቀው የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት ማንኛውም ተቀጣሪ ከቅጥር ውጭ በተለያዩ ሥራዎች የሚያገኘውን ገቢ ግብር የሚከፍልበት ከደሞዙ ጋር ተደምሮ በሚገኘው መጠን ልክ ይሆናል ተባለ…

ለምሣሌ አንድ ተቀጣሪ በተቀጠረበት ድርጅት የ3 ሺህ ብር ደመወዝተኛ ቢሆን ከቅጥር ውጭ በትርፍ ጊዜው ሰርቶ 10 ሺህ ብር ቢያገኝ በወሩ መጨረሻ ከስራው ውጭ ያገኘው 10 ሺህ ብር ከመደበኛ ደሞዙ ጋር ይደመራል፡፡ ግብር ሲከፍልም ለዛ ወር የ13 ሺህ ብር ደሞዝተኛ የሚከፍለውን ያህል ግብር ከደሞዙ ላይ ይቆረጣል ማለት ነው፡፡ አዋጁን ለማፅደቅ ዛሬ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባደረገው ውይይት ይህ አሰራር ተቀጣሪውን የሚጎዳ ነው የሚል አስተያየት ተሰጥቶ ነበር፡፡

በተሻሻለው የገቢ ግብር መሠረት ከ585 ብር በታች የሚያገኝ ደሞዝተኛ ከግብር ነፃ ይሆናል፡፡ ከ586 ብር እስከ 1 ሺህ 650 ብር ደሞዝተኛ የሆነ ደግሞ ከደሞዙ 10 በመቶ ግብር ይከፍላል፡፡

ከ1 ሺህ 653 እስከ 3 ሺህ 145 ብር የሚከፈለው ደሞዝተኛ 15 በመቶ የገቢ ግብር በየወሩ ይቀረጥበታል፡፡

ከ5 ሺህ 196 እስከ 7 ሺህ 758 ደሞዝ የሚያገኝ ደግሞ 25 በመቶ ፣ ከ7 ሺህ 759 እስከ 10 ሺህ 833 ብር ደሞዝተኛ ደግሞ 30 በመቶ የገቢ ግብር የሚከፍል ሲሆን ከ10 ሺህ 833 ብር በላይ የሚያገኝ ደሞዝተኛ ከደሞዙ 35 በመቶ የሚሆነው የገቢ ግብር መክፈል የሚጠበቅበት ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ከተገቢው ጊዜ በላይ በሞጆ ደረቅ ወደብ ተቀምጠው የቆዩ ከ300 የሚበልጡ የኮንቴይነር ዕቃዎች መወረሳቸው ተሰማ

በሞጆ ደረቅ ወደብ በጊዜ ያልተነሱ የተባሉ 398 ኮንቴነር ንብረቶች በመንግሥት ተወረሱ ተባለ..የወደቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታዬ ጫላ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ ባለሃብቶች ከጅቡቲ አስገብተው በሞጆ ደረቅ ወደብ ያሳረፏቸውን ንብረቶች በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ማስገባት ሲጠበቅባቸው ከዚያ በላይ እያቆዩ ወደቡ ከፍተኛ መጨናነቅ ገጥሞታል፡፡

መንግሥት 6 ወር የታገሳቸውንና 398 ኮንቴነር ንብረቶችንም በዚህም ምክንያት ወርሷል ብለዋል፡፡አሁንም በወደቡ 12 ሺህ 800 ኮንቴይነር ንብረቶች ያሉ ሲሆን ከ2 ወር ያለፉ ስላሉ ከመወረሳቸው በፊት በባለሃብቶች በጊዜ እንድታነሱ ሲሉ ሥራ አስኪያጁ አሳስበዋል፡፡ በሞጆ ደረቅ ወደብ በቀን 240 ኮንቴነሮች ወጪ ገቢ ቢሆኑም ከሚወጣው የሚገባው ብቻ እየጨመረ የወደብ መጨናነቁ ቀጥሏል ተብሏል፡፡

ወደቡ 14 ሺህ 900 ኮንቴነሮችን የማስተናገድ አቅም አለው ያሉት አቶ ታዬ 85 በመቶ ቦታው ለኮንቴነር ሲውል ቀሪው ቦታ ለማስተናገጃ የታሰበ ቢሆንም 90 በመቶ የሚሆንው ቦታ በኮንቴነር ተሞልቶ ስራችንን አክብዶብናል ብለዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በአዲስ አበባ ከሳምንት በኋላ በሚወጣው የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ የ40/60 ተመዝጋቢዎችን አይመለከትም ተባለ

ከዚህ ቀደም በቤቶች ቆጠራ የተገኘ የማንም ያልሆኑ ባለቤት አልባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት በሚወጣው እጣ ውስጥ አይካተቱም ተባለ…በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝግባችሁ ቤታችሁን እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ቤት ፈላጊዎች አትጠብቁ በመጪው ሳምንት ይወጣል የተባለው ዕጣ እናንተንም አይመለከትም ተብላችኋል፡፡ ይሄንን የሰማነው ከአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊ ነው፡፡ ስማቸውን ያልነገሩን የጽ/ቤቱ አንድ የሥራ ኃላፊ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሐምሌ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ከ39 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ለማስተላለፍ ቀጠሮ እንደተያዘለት ነግረውናል፡፡

ከሳምንት በኋላ የሚተላለፉት ቤቶች የ20/80 እና የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮግራሞች መሆናቸውን አውቀናል፡፡ ኃላፊውን ተመዝግበው ክፍያንም ከፍለው ቤታቸውን አየተጠባበቁ ያሉ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች በዕጣው ተካትተዋል ወይ ብለን ጠይቀን አለመካተታቸውን ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (3 Comments)

የኢትዮጵያ የብረት የነፍስ ወከፍ ድርሻ ጨምሯል

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 24 የብረት አምራቾች ምርታቸውን ማምረት ጀምረዋል፡፡ አምራቾቹ ከዘመናዊ የቤት ቁሣቁስ እስከ ኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ማምረት ላይ የተሰማሩ እንደሆኑ ሰምተናል፡፡ በግንባታ ላይ ቆይተው በዚህ አመት የኢንጂነሪንግና የብረት ምርቶችን ማምረት የጀመሩት 24 ኢንዱስትሪዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር በተጨማሪ የነፍስ ወከፍ የብረት ፍጆታን ከፍ አድርገውታል ተብሏል፡፡

የብረታ ብረት ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፊጤ በቀለ ለሸገር እንደተናገሩት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አዳዲስ አምራቾች በዓመት 2 ሺህ 312 ቶን ዘመናዊ የቤት ቁሣቁሶችን ያመርታሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers