• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ጥር 18፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአፍረካ ሕብረት ኮምሽን ሊቀመንበርን ለማስመረጥ በእንግሊዝኛና በፈረንሳይኛ ተናጋሪ አባል ሐገራት መካከል ድምፅ የማሰባሰቡ ዘመቻ ተጧጡፏል ተብሏል፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የሕዳሴው ግድብ የውሃ መግቢያና መውጫ መቆጣጠሪያ በሮች ግንባታ በሀገር ውስጥ እየተከናወነ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በኦሮሚያ ልዩ ዞን ጀዌ በተባለ ቦታ በትላንትናው ዕለት በተከሰተ የመኪና አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት ጠፋ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የአፍሪካ የልማትና ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ የምታካሂዳቸውን የኤሌክትሪክ ሀይል ማስፋፊያ ስራዎች ለመደገፍ እያጤንኩ ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሳ)
 • የጣሊያን የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኩባንያዎች ባለቤቶች ከኢትዮጵያውያን ጋር የሽርክና ስራ ማከናወን እንፈልጋለን አሉ ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የታላቁ የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከ6000 ሜጋ ዋት በተጨማሪ አንድ አነስተኛ የኃይል ማመንጫ ግድብ ያህል ተጨማሪ ኃይል እንዲያመነጭ ተደረገ

የታላቁ የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከ6000 ሜጋ ዋት በተጨማሪ አንድ አነስተኛ የኃይል ማመንጫ ግድብ ያህል ተጨማሪ ኃይል እንዲያመነጭ ተደረገ፡፡የበለስን የኃይል ማመንጫ ያህል 400 ሜጋ ዋት ያህል የኤሌክትሪክ የኃይል መጠን እንዲያመነጭ የተደረገው በተደረገለት የማሻሻያ ዲዛይን ነው፡፡

ይህም የሚሆነው ያለምንም የገንዘብና የግድብ መጠንም ሆነ የውሃ ብዛት ሳይጨመር ነው፡፡የግድቡን የተለያዩ አካሎች እየሰራ ካለው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እንደሰማነው ቀደም ከ5400 ወደ 6000 ሺህ ሜጋ ዋት ከፍ ያለው ግድቡ አሁን ደግሞ 6400 ሜጋ ዋት ኃይል እንዲያመነጭ እየተደረገ ነው፡፡

በኮርፖሬሽኑ የፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ሻለቃ አማኑኤል አብርሃ እንደነገሩን እና እኛም እንዳየነው ለህዳሴው ግድብ የተርባይን አካል የሆኑ የብረታ ብረት ምርቶች በአዲስ አበባ እየተሰሩ ነው፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 17፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በቤንሻንጉል ክልል ካሉ ሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ አግኝተው የሚያድጉት 11 % ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • የመንግሥት ልማት ኤጀንሲ ለልማት ከፈረሱበት ቤቶች ከ8 ሚሊየን ብር በላይ አልተከፈለኝም አለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ዛሬ 4ኛ ቀኑን በያዘው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በነፃ የንግድ ቀጠና ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • አግሮ ፕላስት ፓክ ኢትዮጵያ የንግድ ትርዒት ከጥር 26 እስከ 28 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄል ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከ6ሺ ሜጋዋት በላይ እንዲያመነጭ ተደረገ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዐት እና ልማት ድርጅት ቆዳ እያለፋሁ ለፋብሪካዎች ማቅረብ ጀመርኩ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 16፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአመት አንድ ጊዜ ከሚደረገው የተሽከርካሪ ብቃት ምርመራ በተጨማሪ፣ ከእንግዲህ በየጎዳናው ድንገት ምርመራ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • በከተሞች አካባቢ ለተነሱ ችግሮች የስራ አስፈፃሚዎች የብቃት ችግር እና የፖሊሲዎች በተገቢው መንገድ አለመተግበራቸው ዋና ዋናዎቹ ናቸው ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ለውጭ ገበያ የተሰጣቸውን ማበረታቻ ያላከበሩት መብታቸው መነሳቱ ተሰማ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ለ28ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ውሳኔ በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ በቋሚ መልዕክተኞች ደረጃ ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • ኪነጥበብ ለአፍሪካ ሰላምና እድገት በምታበረክተው አስተዋፅኦ ላይ ያተኮረ ምክክር በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የሥነ-ምግባር ችግር አለባቸው ያላቸውን አምስት የአሽከርካሪ ማሰልጠኛዎች እንዲዘጉ አደረገ

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የሥነ-ምግባር ችግር አለባቸው ያላቸውን አምስት የአሽከርካሪ ማሰልጠኛዎች እንዲዘጉ አደረገ፡፡የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ይግዛው ዳኘው ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ ከተዘጉት አምስቱ ማሰልጠኛዎች አራቱ ፈቃድ እንዲያሣድሱ በተደጋጋሚ ተነግሯቸው ያላሳደሱ፣ አንዱ ደግሞ ተደጋጋሚ ጥፋቶች የተገኙበት ናቸው ብለዋል፡፡

አቶ ይግዛው እንደነገሩን ከእንግዲህ አሽከርካሪዎችን ከማሰልጠን ሥራ አንዲታቀቡ የተከለከሉትና የተዘጉት አዲስ አበባ ያለው ኤም.ቲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩ የሚገኘው ዊከን የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ፣ በገላን ከተማ የሚገኘው ሚዜኤል የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ፣ በትግራይ የሚገኘው ፈንቅል የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋሞች ፈቃድ ባለማሳደሳቸው የተዘጉ ሲሆኑ ተደጋጋሚ ጥፋቶች ተገኝቶበታል ተብሎ የተዘጋው ደግሞ የአዲስ አበባው GR ሺመራልድ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ነው በማለት አቶ ይግዛው ለሸገር ተናግረዋል፡፡

እነዚህ በአዋጅ ከተሰጣቸው መመሪያ ውጪ ሲሰሩ የነበሩ ተቋሞች እውቅናቸውን ስለተነጠቁ እነርሱ ዘንድ ሄዶ መሰልጠን ተቀባይነት የለውም ተብሏል፡፡በሌላ ወሬ በኢትዮጵያ አምና በደረሱ የመኪና አደጋዎች ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል እንዲህ ያለውን የከፋ የመኪና አደጋ ለመቀነስ ይረዳል የተባለ ምክክር በመጪው ሀሙስ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

ተመካካሪዎቹ የክልል ትራንስፖርት ኃላፊዎች ናቸው በማለት አቶ ይግዛው ነግረውናል፡፡አደጋዎቹ በአንዳንድ ሾፌሮች የሥነ-ምግባር ችግር በመንገዶች ብልሽት በመኪኖች የቴክኒክ ችግሮች የተከሰቱ ናቸው ተብሏል፡፡አቶ ይግዛው ከውጪ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ቁጥርም እየጨመረ ነው ባለፉት 6 ወራት ከ48 ሺህ በላይ መኪኖች ገብተዋል ሲሉም ነግረውናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 15፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ የድሬዳዋን ደረቅ ወደብ ግንባታ እጀምራለሁ ብሏል፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • በኢጋድ አባል ሀገራት መሀከል የሚደረጉ ታላላቅ ድንበር ዘለል ኘሮጀከቶችን በተመለከተ ትላንትና ንግግር መደረጉ ተሠማ፡፡ የመጀመሪያው የኘሮጀክቱ ክፍል በኢትዮጵያና በኬኒያ ድንበር አካባቢ የሚሰራው ሥራ ነው ተብሏል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ከኢትዮጵያ የጥጥ እርሻዎች 55 ሺህ ቶን ምርት ተሰበሰበ ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በኢትዮጵያ 5 የመኪና አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ተዘጉ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ጥምቀትን የዓለም ቅርስ አካል አድርጐ ለማስመዝገብ በጐንደርና በአዲስ አበባ መረጃ እየተሰበሰበ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሥራ ላይ ያዋልኩት የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓት አንዳንድ ሕገ-ወጥ አሰራሮች በከፍተኛ መጠን እንዲቀንሱ ረድቶኛል አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • 28ኛው የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ በዋና ዋና የህብረቱ አጀንዳዎች ላይ መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2009 በጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት 10 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው 246 ሺ 752 ሜትሪክ ቶን ምርት አገበያየሁ አለ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2009 በጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት 10 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው 246 ሺ 752 ሜትሪክ ቶን ምርት አገበያየሁ አለ፡፡ምርት ገበያው ቡና፣ ነጭ ቦሎቄ፣ ሰሊጥ፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላና ቀይ ቦሎቄ ማገበያየቱን ለሸገር ተናግሯል፡፡

የተገኘው ውጤት ከእቅዱ ጋር ሲነፃፀር የምርት ግብይቱ 96 በመቶ የምርት ዋጋውን ደግሞ 94 በመቶ ማሳካቱንም ነግሮናል፡፡አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር አጠቃላይ የምርት ግብይት መጠን ስድስት በመቶ ቢቀንስም የቡና ግብይት መጠን በ15 በመቶ የነጭ ቦሎቄ ደግሞ በ23 በመቶ ጨምሯል መባሉንም ሰምተናል፡፡

እንዲሁም የምርት ግብይት ዋጋ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጊዜ ጋር ሲመሣከር በ19 በመቶ ብልጫ አለውም ተብሏል፡፡ከዚህ ውስጥ የቡና ግብይት ዋጋ በ35 በመቶ የነጭ ቦሎቄ የግብይት ዋጋ በ82 በመቶ እድገት ያሳዩ ሲሆን ሰሊጥ በ14 በመቶ ቅናሽ አስመዝግቧል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ አጠቃላይ የኤሌክትሮኒክስ የምርት ግብይት መጠን 89 በመቶ መድረሱንም ተነግሯል፡፡ቀሪው 11 በመቶው ደግሞ ቀድሞ በነበረው በድምፅ የማስተጋባት ሥርዓት ይከተላል መባሉ ተሰምቷል፡፡ምርት ገበያው ዛሬ የስድስት ወር አፈፃፀሙን  አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ያልነበራት አረንጓዴ ፓርክ ነገ ሊመረቅላት ነው ተባለ

አዲስ አበባ ከዚህ ቀደም ያልነበራት አረንጓዴ ፓርክ ነገ ሊመረቅላት ነው ተባለ፡፡በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ በተለምዶ ካራማራ ድልድይ ተብሎ በሚጠራው ተሻጋሪ መንገድ ድልድይ ሥር የሚገኘው ቦታ ነው ሌሎች አገልግሎቶችን ጨምሮ ነገ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ይመረቃል መባሉን የሰማነው፡፡

ቦታው 6 ሺ 64 ሜትር ስኩዌር ስፋት አለው የተባለ ሲሆን ለአዲስ አበባ ልዩ ውበት የሚጨምርና ሌሎች አገልግሎቶችንም የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡አረንጓዴ ፓርኩን ገንብቶ እነሆ ለአዲስ አበባ ያለው አሰር ኮንስትራክሽን ነው፡፡አሰር ኮንስትራክስን ለከተማዋ በፈቃዴ ለገነባሁት አረንጓዴ ፓርክ 15 ሚሊዮን ብር አውጥቻለሁ ብሏል፡፡

ወሬውን ለሸገር የተናገሩት የኮንስትራክሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ብሩክ አመንዴ ናቸው፡፡ፓርኩ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ በቅርቡም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡የተለያዩ አረንጓዴ ዕፅዋቶችን አብቅሎ የመኪና ማቆሚያንም ጨምሮ የፓርክ ወንበሮችን ደርድሮ፣ የዘመኑ መፀዳጃ ቤቶችን ገንብቶ፣ የኢንተርኔትና ሌሎች አገልግሎቶችንም አካቶ አዛውንቶችና ወጣቶች እንዲያርፉበት ተሰርቷል ሲሉ አቶ ብርኩ ተናግረዋል፡፡

ፓርኩ አገልግሎት መስጠት ሲጀምርም ከ70 በላይ ለሚሆኑ እንጀራ ፈላጊዎች እድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡አሰር ኮንስትራክሽን በመንገድ፣ በህንፃ፣ የውሃ ሥራዎችን ግንባታ ጨምሮ ታሪካዊውን የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ ቀድሞ ሥፍራው የመመለስ ሥራውን ይታወቃል፡፡

ተህቦ ንጉሴ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ጥር 12፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ኢትዮጵያ ከውጪ ለምታስገባቸው ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች በየአመቱ ሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ወጪ ታደርጋለች ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ለስራው ስኬታማነት ህብረተሰቡ ላደረገው ድጋፍ ፖሊስ አመስግኗል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በማህበረሰብ አገልግሎት በኩል ግሩም ትጋት እያሳዩ መሆኑን ዩኒቨርስቲው ተናገረ፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ለ84 አዳዲስ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ፈቃድ ሲሰጥ የ14 ድርጅቶችን ፈቃድ ደግሞ ሰርዟል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • አሰር ኮንስትራክሽን ለአዲስ አበባ በነፃ የሰራሁላት አረንጓዴ ፓርክ ነገ ሥራ ይጀምራል አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • ከትላንት በስቲያው የከተራና በትናንቱ የጥምቀት በአል ሦስት አደጋዎች ደርሰው የአንድ ሰው ህይወት አለፈ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ያለው ምርት በስድስት ወሮች ውስጥ ግብይት ተፈፀመ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የከተራና የጥምቀት በዓላት ካለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ከሌሎች የፀጥታና የፍትህ አካላት እንዲሁም የፀጥታው ዋና ባለቤት ከሆነው ከአዲስ አበባ ነዋሪ ጋር እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽራ ተናግሯል

የከተራና የጥምቀት በዓላት ካለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ከሌሎች የፀጥታና የፍትህ አካላት እንዲሁም የፀጥታው ዋና ባለቤት ከሆነው ከአዲስ አበባ ነዋሪ ጋር እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽራ ተናግሯል፡፡

ኮሚሽኑ በዓላቱ በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባር ላይ ትኩረት በመስጠት በርካታ የሰው ኃይል ማሰማራቱን ገልፆ የታቦት ማደሪያ ስፍራዎች በተለይ በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በሚገኙበት ጃልሜዳ ጊዚያዊ ፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤት ተከፍቶ ግልጋሎት የሚሰጡ መሆኑን ኮሚሽኑ ከላከልን መረጃ መረዳት ተችሏል፡፡

ህብረተሰቡ ፀበል በሚረጭበት ወቅት በሚፈጠር ግፊያ ጉዳት እንዳይደርስበት ንብረቶች እንዳይሰረቅበት እንዲሁም የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበትና የእምነቱ ተከታዮች በተለይም ወጣቶች ከዚህ በፊት እንደሚያደርጉት በተደራጀ መንገድ ከፖሊስና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጐን በመቆም ለበአሉ በሰላም መከበር ከወዲሁ እገዛ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ህብረተሰቡ በማንኛውም ወቅት ከፀጥታ ሥራ ጋር ተያያዥና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት እንዲሁም የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት ከፈለገ 0111 26 43 77 /0111 26 43 59 /0118 27 41 51 / 0111 11 01 11 እና በ991 ነፃ የስልክ መስመሮች መጠቀምና መደወል እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም ታቦታቱ በሚያልፉበት ወቅት የአሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት ለሚሰጡት ትዕዛዞች የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደርጉ ኮሚሽኑ አስታውቆ በአሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በጃልሜዳ ዙሪያ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑን እወቁት ብሏል፡፡

አስፋው ስለሺ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢህአዴግና በተቃዋሚ የፖለቲካ ማኅበራት መሀከል የሚደረገውን ውይይትና ድርድርን በቦታው በመገኘት እንዲከታተሉ ለሁለት የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ብቻ ተፈቀደ

በኢህአዴግና በተቃዋሚ የፖለቲካ ማኅበራት መሀከል የሚደረገውን ውይይትና ድርድርን በቦታው በመገኘት እንዲከታተሉ ለሁለት የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ብቻ ተፈቀደ፡፡ዛሬ ፓርላማው ቅጥር ጊቢ ውስጥ በተጀመረው የሁለቱ ወገኖች ውይይት የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት አካባቢ ለሁሉም የመገናኛ ብዙሃን አባላት ተፈቅዶ የነበረው በቦታው የመገኘት እድል ክልከላ ተጥሎበት እንዲወጡ ሲደረግ የፋና እና የኢቢሲ ጋዜጠኞች በቦታው እንዲቀሩ ተፈቅዷል፡፡

በኢህአዴግና በተቃዋሚ የፖለቲካ ማኅበራት መሀከል ውይይትና የምርጫ ህጉን በተመለከተ ማስተካከያዎች እንደሚደረጉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ከተናገሩ በኋላ ጉዳዩን የሚከታተል ክፍል መቋቋሙም ተሰምቷል፡፡የኢህአዴግ ምክር ቤት የሥራ አስፈፃሚ አባልና የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሁሉም ህጋዊ እውቅና እና ሰላማዊ ከሆኑ አባላት እና በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ከሚሉ ወገኖች ጋር ለመነጋገር ኢህአዴግ ዝግጁ ነው ማለታቸው ይታወሣል፡፡

የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ትላንትና ባወጣው መግለጫው በመንግሥትና በተቃዋሚ የፖለቲካ ማህበራት ማሀከል የሚደረገው ውይይት ውጤታማ እንዲሆን ከይስሙላ የራቀ መሆን ይገባዋል ብሏል፡፡በኢህአዴግና በምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ህጋዊ እውቅና ከተሰጣቸው ከ23 አገር አቀፍ የፖለቲካ ማህበራት ጋር የሚደረገው ውይይትና ንግግር በምን ዓይነት ነጥቦች ላይ አንዳተኮረ ለጊዜው ማወቅ አልተቻለም፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers