• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሐምሌ 13፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጣ የነበረ 240 ኩንታል ቡናን ጨምሮ የተለያዩ 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ እቃዎች መያዛቸውን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በዘውዲቱ ሆስፒታል ለሚካሄደው የኩላሊት እጥበት ህክምና /ዲያሊስስ/ ተጨማሪ 14 ማሽኖች ተገዝተው ሊጨመሩ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የከተማዋን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ዘመናዊ የቁጥጥር መሣሪያዎችን ማደራጀት መላ ካላቸው ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በጥብቅና የሚተዳደሩ ሞያተኞች አመታዊ ግብር ለመክፈል ተቸገርን ሲሉ ቅሬታቸውን ለሸገር አቀረቡ፡፡ ቅሬታ የቀረበበት አካል በበኩል ትዕዛዝ እየጠበኩ ነው ብሏል፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • በኢትዮጵያ መዋለ ነዋይ ፈሰስ በማድረግ የቻይና ኩባንያዎች ቀዳሚ ናቸው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በዚህ ዓመት ከ59 ሺ በላይ ቱሪስቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ፓርኮችና የዱር እንስሣት መጠለያዎች ጎብኝተዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • አዲስ አበባን መልሶ ለማልማት ከ3 ሺ 500 በላይ ቤቶች ፈርሰዋል ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በሂሣብ ምርመራ የተገኘበትን ጉድለት ለማስተካከል ኮሚቴ አቋቁሞ እያጣራ መሆኑን ተናገረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ኢትዮጵያ ከጎረቤትና ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚኖራትን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዎች መሠረት ያደረገ ሥልጠና ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ተዘጋጀ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • አዲስ አበባ ውስጥ በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ 4 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ተመረቁ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 14፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • የሳውዲ አረቢያ መንግሥት የሰጠው ተጨማሪ የአንድ ወር ጊዜ ሊጠናቀቅ የቀሩት ሦስት ቀናት ቢሆኑም ሀገር ቤት የደረሱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር አነስተኛ ነው ተባለ፡፡ የኔነህ ሲሣይ
 • የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የማያገለግሉ ንብረቶችን በመሸጥ ያገኘው ገቢ ከአምናው በግማሽ ያነሰ ነው ተባለ፡፡ ትዕግሥት ዘሪሁን
 • በተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ የበጎ አድራጎት ተግባር ላይ የተሰማራው የእናት ወግ ማህበር ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተሰጠው፡፡ ምህረት ስዩም
 • በኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽንና በኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የተዘጋጀው ሞዴል የህብረት ስምምነት ትላንት በኢሊሌ ሆቴል ቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እንዲወያዩበት ተደርጓል፡፡ አስፋው ስለሺ
 • የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ያለመ ምክክር ሊካሄድ ነው፡፡ ምህረት ስዩም
 • ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት የሚሹ ተብለው የተለዩ በሽታዎች መከላከያና መፈወሻ የሚውሉ ከ4 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው መድሃኒቶች ተሰራጭተዋል ተባለ፡፡ ንጋቱ ረጋሣ
 • በአዳማ ከተማ ወላጅ እናቱን የገደለ ግለሰብ በእሥራት ተቀጣ፡፡ ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ተንቀሳቃሽ ፊልምን በሕዋስ ውስጥ ባለው ዲ ኤን ኤ ላይ...

ከሰሞኑ ሳይንቲስቶች አጭር ተንቀሳቃሽ ፊልምን በሕዋስ ውስጥ ባለው ዲ ኤን ኤ ላይ ማከማቸት መቻላቸው አግራሞትን አጭሯል፡፡ ስኬቱ በሕክምና ዘርፍ ትልቅ እመርታን ያመጣል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል…

ዘካርያ መሐመድ በዚህ ዙሪያ ይህን አዘጋጅቷል… 

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ሐምሌ 11፣2009

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የገጠር መሬት አስተዳደርን በተመለከተ ቀደምት የሆነው የአማራ ክልል አዋጅ ከአሥር አመታት በኋላ ፀድቋል ተባለ

የገጠር መሬት አስተዳደርን በተመለከተ ቀደምት የሆነው የአማራ ክልል አዋጅ ከአሥር አመታት በኋላ ፀድቋል ተባለ፡፡የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምክር ቤት የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ፍቅሬ ሙሉጌታ ለሸገር ዛሬ በስልክ እንደነገሩት በአምሥተኛው ዙር በሁለተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ከፀደቁ አዋጆች መካከል የገጠር መሬትን የሚመለከተው ቀደምት አዋጅ አንዱ መሆኑን ነው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያጠናቅቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የዳኞችን ሹም ሽር አድርጓል መባሉንም ከፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሰምተናል፡፡ምክር ቤቱ በጉባዔው ላይ ለረጅም ዓመታት የክልሉ ፈተና ሆኗል ባለው በውሃና በመብራት አቅርቦት ዙሪያ  በብርቱ መነጋገሩን ከጽሕፈት ቤት ኃላፊዋ ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ የ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል የያንግ ሩት እንግሊሽ ስኩል ተማሪዎች ውጤት ተለይቶ የጠፋበት...

በአዲስ አበባ የ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል የያንግ ሩት እንግሊሽ ስኩል ተማሪዎች ውጤት ተለይቶ የጠፋበት ምክንያት በህትመት ወቅት ከፍተኛ የመብራት ኃይል መቆራረጥ በማጋጠሙ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተናገረ፡፡ቢሮው በዚህ ዓመት የተፈተኑ 65 ሺ የ8ተኛ ክፍል ተማሪዎችን ፈተና ውጤት አርሞ ለመጨረስ ከ10 ቀን በላይ አልወሰደበትም ብለዋል የቢሮው ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ኃይለስላሴ ፍስሃ፡፡

ውጤቱ በሚታተምበት ወቅት ግን የኃይል መቆራረጥ ስላጋጠመን ያልታተሙ ካርዶች መኖራቸውን አውቀናል ብለዋል፡፡የ8ተኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ከተደረገ ሣምንት ቢሆነውም በቦሌ ክፍለ ከተማ የያንግ ሩት እንግሊሽ ስኩል ትምህርት ቤት የ8ተኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ እንዳልደረሰው ነግረናችሁ ነበር፡፡

ለመፍትሄውም ትምህርት ቢሮን ደጅ ሲጠና መቆየቱን የትምህርት ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ትምህርት ቢሮ ግን ችግሩ ስለመኖሩም ያወኩት ትላንት በሸገር ዜና ላይ ነው የሚል ምላሽ ሰጥቶናል፡፡ከሣምንት በላይ ውጤታቸውን ሳያውቁ የቆዩት የያንግ ሩት እንግሊሽ ስኩል  ተማሪዎች ውጤት ኮምፒዩተር ላይ ታይቶ በአንድ ቀን ውስጥ ታትሞ እንዲሰጣቸው ትዕዛዝ መሰጠቱንም የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊው አቶ ኃይለስላሴ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 12፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የያንግ ሩት እንግሊሽ ስኩል ትምህርት ቤት ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ውጤት ጠፍቷል ምክንያቱ በህትመት ወቅት ባጋጠመው የኃይል መቆራረጥ ነው ሲል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተናግሯል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የተለያዩ ጥፋት የተገኘባቸው ዘጠና ስምንት አቅራቢዎች በማንኛውም የመንግሥት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ታገዱ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች አለመናበብ ምክንያት የመጀመሪያው የግል ባህል ማዕከል ሊፈርስ ነው ይላሉ የማዕከሉ ባለቤት፡፡ አፍራሹ አካል የተሻሻለው ማስተር ፕላን እንዲፈርስ ስላስገደደ ነው ይላል፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከ2 ሚሊዮን በላይ መፅሐፎችን አሳትሞ ለመጪው የትምህርት ዘመን አያከፋፈለ መሆኑን ተናገረ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የጨሞ ሃይቅ አሳዎችን ከህገ-ወጥ አስጋሪዎች ለመጠበቅ 24 ሰዓት ይሰራል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • አሥር ዓመታት ያለፈው የመሬት ይዞታ አዋጅ ፀደቀ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የከፋ የገንዘብ አጠቃቀም ችግር እንዳለባቸው የተናገሩ ተቋማትን የክትትል ትኩረቴ አደርጋለሁአለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • እየፈረሱ ያሉ ሁለት የሀረር ታሪካዊ ቤቶች እድሣት ሊደረግላቸው ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የቀን ገቢ ግምትን በመቃወም በአምቦና በወሊሶ ከተሞች ዛሬም የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና የትራንስፖርት አገልግሎት ለሁለተኛ ቀን ዝግ...

የቀን ገቢ ግምትን በመቃወም በአምቦና በወሊሶ ከተሞች ዛሬም የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና የትራንስፖርት አገልግሎት ለሁለተኛ ቀን ዝግ ሆነዋል ተባለ፡፡ሸገር ወሬውን የሰማው ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ አዲሱ አረጋ ነው፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሥር የሚገኙ የአምቦና የወሊሶ ከተማ ነጋዴዎች በአብዛኛው የቀን ገቢ ግምቱን በመቃወም ግብር አንከፍልም በሚል አድማ ላይ መሆናቸውና የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡በመላው የኦሮሚያ ክልል ከ45 ሺ የሚበልጡ ነጋዴዎች በህገ-ወጥ መንገድ ያለምንም ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ሲሰሩ ተገኝተዋል ያሉት አቶ አዲሱ በአምቦና በወሊሶ አካባቢ የታየው የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና መንገዶችን በድንጋይ የመዝጋት ድርጊቱ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡

በአምቦና በወሊሶ ከተሞች ከሁለት ቀናት በፊት የተዘጉትን የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስከፈት የክልሉ መንግሥት ከነጋዴው ጋር እየመከረ ነው ያሉት ኃላፊው ይሁንና ዛሬም ትራንስፖርትን ጨምሮ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት በሁለቱም ከተሞች አለመከፈታቸውን ለሸገር ነግረዋል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ ዘመናዊ የጋዜጠኝነት ታሪክ ቁጥር አንድ ተብለው የሚጠቀሱት፣ አቶ ነጋሽ ገብረማርያም አረፉ

በኢትዮጵያ ዘመናዊ የጋዜጠኝነት ታሪክ ቁጥር አንድ ተብለው የሚጠቀሱት፣ አቶ ነጋሽ ገብረማርያም አረፉ፡፡በ92 ዓመታቸው፣ ትላንት ሐምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አቶ ነጋሽ ገብረማርያም፣ በአዲስ ዘመንና በኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጦች በዋና አዘጋጅነት፣ ዜና አገልግሎትን በዳይሬክተርነት አገልግለዋል፡፡

በዘመናዊ ጋዜጠኝነት፣ ትምህርታቸውን በአሜሪካ ሞንታና ዩኒቨርስቲ፣ ተከታትለው በማስተርስ ድግሪ የተመረቁት አቶ ነጋሽ ገብረማርያም፣ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ከኋላ፣ የተማሩትን ሙያ ወደ ተግባር ለውጠው አሳይተዋል፡፡አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ አሁን ያለውን ቅርፅና አፃፃፍ መልክ ያሳያዙ አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ናቸው፡፡

በዜና ትንታኔያቸውና በቃለ መጠይቆቻቸው፣ እንዲሁም ጐንታይ በሆኑ አስተያየታቸው፣ በአንባቢዎቻቸው ዘንድ የታወቁና የተመሰገኑ ነበሩ፡፡አቶ ነጋሽ ገብረማርያም፣ ከጋዜጠኝነት ሙያቸው በተጨማሪ ታዋቂ ደራሲ ነበሩ፡፡“ሴተኛ አዳሪዋ” የተሰኘው ልብወለድ ድርሰታቸውና “የድል አጥቢያ” አርበኛ የተሰኘው ተውኔታቸው፣ የአቶ ነጋሽን የደራሲነት አቅም የመሠከሩ ናቸው፡፡

ከተማሩበትና ልምድ ካካበቱበት የጋዜጠኝነት ሙያ፣ በደርግ የሥልጣን ዘመን ተነስተው፣ በቢሮ ሥራ እንዲወሰኑ ተደርገውም፣ የፈጠራ ጽሁፎቻቸውን አላቋረጡም፡፡ጡረታ ከወጡ በኋላ፣ “የአዛውንቶች ክበብ” የተሰኘው ተውኔታቸው በጊዜው የነበረውን የጡረተኞች ችግር በግልፅ አሳይተዋል ተብሏል፡፡በአጭር አርፍተ-ነገርና በሚያዋዙ ቃላት አሳክተው በሚያቀርቧቸው ጽሁፎች አንባቢዎቻውን መያዝ የሚችሉት አቶ ነጋሽ ገብረማርያም፣ ለጋዜጦኞችና ለመጽሔቶች በርካታ ጽሁፎች አበርክተዋል፡፡

አቶ ነጋሽ ገብረማርያም ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነበሩ፡፡የቀብራቸው ሥነ-ሥርዓት፣ በሰዓሊተ ምህረት ቤተ-ክርስቲያን ዛሬ ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት እንደሚፈፀም ቤተሰቦቻቸው ነግረውናል፡፡

እሸቴ አሰፋ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በአዲስ አበባ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ አድርገዋል የተባሉ የንግድ ተቋማት ፍቃድ ታግዷል ተባለ

በአዲስ አበባ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ አድርገዋል የተባሉ የንግድ ተቋማት ፍቃድ ታግዷል ተባለ፡፡የከተማ አስተዳደሩ በንግድ ቢሮ በኩል ባደረገው ቁጥጥር በኮንትሮባንድ እና በህገ-ወጥ ንግድ ተሳትፈዋል ባላቸው የንግድ ተቋማት ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከ ንግድ ፍቃድ መቀማት እርምጃ ወስዷል ተብሏል፡፡

ቢሮው በ11 ወራት ውስጥ በ189 ሺ 328 የንግድ መደብሮች ላይ ቁጥጥር ያደረገ ሲሆን 13 ሺ ለሚሆኑት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ 8 ሺ 597 የሚሆኑት ታሽገው እንዲቆዩና 158 የሚሆኑትን ደግሞ ንግድ ፈቃዳቸው እንዲታገድ መደረጉን አስተዳደሩ ተናግሯል፡፡በሸቀጦች ዋጋ ላይ ያለ አግባብ የሚታየውን ህገ-ወጥ ጭማሪ ለመከላከልም ቁጥጥር ተደርጓል ተብሏል፡፡

የዋጋ ጭማሪውንም ለማረጋጋት በሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በኩል መሠረታዊ ሸቀጦችን በማቅረብ የዋጋ ማረጋጋት ሥራ በንግድ ቢሮው መሠራቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተናግሯል፡፡

ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ክልላዊ የ8ተኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ከተደረገ ሣምንት ቢሆነውም በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የያንግ ሩት እንግሊሽ እስኩል ትምህርት ቤት...

በአዲስ አበባ ክልላዊ የ8ተኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ከተደረገ ሣምንት ቢሆነውም በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የያንግ ሩት እንግሊሽ እስኩል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ፈተና ውጤት ግን እምጥ ይግባ ስምጥ አልታወቀም ተብሏል፡፡ ተማሪዎችና ወላጆችም መረበሻቸውን ሰምተናል፡፡የትምህርት ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ታፈሰ ዋቺሶ ለሸገር እንደተናገሩት ለጠፋው የተማሪዎች የ8ተኛ ክፍል ውጤት መላ ለመጠየቅ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮን ደጅ እየጠኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ውጤቱ ወደ ሌላ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤቶች ተቀላቅሎ ሄዶ ይሆናል የሚል መላ ምት እንደተሰጣቸውና ውጤቱ እስከሚገኝም ተማሪዎቹ በቀጣይ የትምህርት ዘመን በሚፈልጉበት ትምህርት ቤት የ9 ክፍል ትምህርታቸውን መቀጠል ይችላሉ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸውም ነግረውናል፡፡ተማሪዎችና ወላጆች ግን ውጤታችንን አምጡ ብለው አስጨንቀውናል ይላሉ ምክትል ዳይሬክተሩ፡፡

ከያንግ ሩት እንግሊሽ እስኩል በተጨማሪ የሌሎች 2 ትምህርት ቤቶች የ8ተኛ ክፍል ውጤትም ሳይጠፋ እንዳልቀረ ከክፍለ ከተማው መስማታቸውን የተናገሩት አቶ ታፈሰ ለተማሪዎቹ ሥነ-ልቦና ሲባልም ትምህርት ቢሮ አስቸኳይ የሆነ መላ እንዲፈልግላቸውም ጠይቀዋል፡፡ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ስለ ጉዳዩ መልስ ለማግኘት ደጋግመን ብንደውልም ለጊዜው ምላሽ ማግኘት አልቻልንም፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers