• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በኢሊባቡር ዞን የሰብል ተምች መታየቱ ተሠማ

በኢሊባቡር ዞን የሰብል ተምች መታየቱ ተሠማ፡፡ ተምቹ ከፍተኛ ጉዳይ እንዳያደርስና ሰብልም እንዳያጠፋ የግብርና ቢሮ ሥራዎችን እየሰራ ነው ተብሏል፡፡በዞኑ 13 ወረዳዎች የተከሰተው የሰብል ተምች በመስኖ በለማ ሰብል ላይ ሰፊ ጉዳት እንዳያደርስ የመከላከል ሥራ እየተሰራ ነው መባሉን ከዞኑ ግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ሰምተናል፡፡

ፉል አርሚ ዎርም የተባለው ተምች በዞኑ በመስኖ የለማውን ሰብል እየጐዳ መሆኑ ሲነገር አርሶ አደሩ በባህላዊ ዘዴና ፀረ-ተባይ መድሐኒት በመርጨት ለመቆጣጠር እየሞከረ መሆኑን ቢሮው ተናግሯል፡፡የሰብል ተምቹ በአካባቢው በምን ያህል ሄክታር መሬት ላይ አደጋ አደረሰ የሚለውን ያልተናገረው ቢሮ ተምቹ በታየባቸው ከ3 ሺ እስከ 4 ሺ ሄክታር መሬት ማሳዎች ላይ ከ5 ሺ ኪሎ ግራም በላይ ፀረ-ተባይ እርጭት ማድረጉን ተናግሯል፡፡

አደገኛ የሰብል ተምች የሚራባውና የሚንቀሣቀሰው በምሽት በመሆኑ ተምቹን ለማጥፋት አስቸጋሪ እንደሆነበት ቢሮው ተናግሯል፡፡የግብርና ቢሮው ተምቹን ለመከላከል ከ50 ሺ የሚበልጡ የአካባቢው አርሶ አደሮችን በማስተባበር በባህላዊና በዘመናዊ መንገድ ተምቹን ለማጥፋት ሥራዎችን እየሰራ መሆኑንም ከቢሮው ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሣይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 10፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በሀረር የማሽከርከሪያ ፈቃድ ማግኘት አልቻልንም፣ ማሰልጠኛዎችም ተዘግተዋል፣ የሚመለከተውን ክፍል ብንጠይቅም መልስ አላገኘንም ሲሉ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ለእኛም ግራ ገብቶናል ብለዋል፡፡ (አስፋውስለሺ)
 • ታላቁ የህዳሴ ግድብ በግርጌ ሃገሮች ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ጥናት ላይ ሦስቱ ሃገሮች ስምምነት ላይ አልደረሱም፡፡ ወደፊት በካርቱም በሚደረግ ስብሰባ በልዩነታቸው ላይ ሊመክሩ ተስማምተዋል ተባለ፡፡ (እሸቴአሰፋ)
 • በኦሮሚያ ኢሊ አባቦራ ዞን ተምች በሰብልና እፅዋት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ከፍተኛ የመከላከል ሥራ እየተከናወነ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • በቡራዩ አንድ የዘይት ፋብሪካ የቃጠሎ አደጋ ደረሰበት፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • ብሔራዊ ሙዚየም በአገሪቱ የተለያዩ ማዕዘናት ያሉ ቅርሦችን አሰባስቦ እዩልኝ ለማለት ውስንነቱ ያመዝናል ተባለ፡፡ (ምህረትስዩም)
 • የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የቀን ገቢ ግምት ምዝገባዬን ከግማሽ በላይ አከናውኛለሁ አለ፡፡ (ምሥክር አወል)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ግንቦት 8፣2009

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበራት ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ድርጅት የሥራ ኃላፊ ሆነው እንዲመረጡ እንደግፋለን ሲሉ ተናገሩ

ማኅበራቱ ዛሬ በሂልተን ሆቴል መግለጫ ሲሰጡ አንደሰማናቸው ድጋፋቸውን የገለፁት የኢትዮጵያ ሜዲካል አሶሴሽን፣ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ጤና አሶሴሽን፣ የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ማኅበር፣ የአዋላጅ ነርሶች ማኅበርን ጨምሮ ሌሎች 6 የጤና ማኅበራት ዶክተሩ የአለም ጤና ድርጅትን እንዲመሩት ፍላጎታቸው መሆኑንና እንደሚደግፉት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

ማኅበራቱ ለዶክተር ቴዎድሮስ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ያደረጓቸው ምክንያቶች በሀገሪቱ በጤና ጥበቃ ሚኒስትርነት ባገለገሉበት ወቅት ያስመዘገቧቸው ስኬታቸው መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

 • የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ መቻላቸው በሚለው ሙገሳቸው ሥር ከ3 ሺ 500 በላይ መሠረታዊ የጤና መከታተያ ተቋማት በሀገሪቱ እንዲቋቋሙ ማገዛቸው፡፡
 • የጤና ባለሙያዎችን ሥልጠናና አቅም በማጠንከር ላይ በመስራት 16 ሺ 500 የነበረውን የጤና ባለሙያዎች ወደ 115 ሺ ከፍ አንዲል መስራታቸው፡፡
 • ታች ድረስ ወርደው የማህበረሰቡን ጤና የሚያግዙ ከ38 ሺ በላይ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ማስማራታቸው፤ ድጋፋችንን እንድንሰጥ አድርጐናል ሲሉ ሰምተናቸዋል፡፡

የህፃናትን ሞት በ2/3ተኛ እንዲቀንስ ማድረጋቸው፣ የወባ በሽታን ገዳይነት በ75 በመቶ እንዲቀንስ መስራታቸው፣ በኤች.አይ.ቪ መሞትን በ70 በመቶ በአመራር ዘመናቸው እንዲቀንስ በመስራታቸው ማኅበራቱ እንደ ስኬት አንስተውላቸዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሙሉ ድጋፍ ያገኙት ዶክተር ቴዎድሮስ ውድድሩን አሸንፈው የዓለም ጤና ድርጅትን ከመሩ በ70 ዓመት ታሪኩ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ይሆናሉ መባሉን ሰምተናል፡፡

ምሥክርአወል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 9፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ቴክኖ ሞባይል በቅርቡ ያመረተውን ቅንጡ ስልክ ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ፡፡ (ንጋቱሙሉ)
 • በኢትዮጵያ የተጀመሩ የመስኖ ልማቶች፣ የመጠጥና ውሃ አገልግሎቶች እንዲሁም የኢነርጂ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ የበጀት እጥረት እየገጠማቸው እንደሆነ ተነገረ፡፡ (ህይወትፍሬስብሃት)
 • የኦሮሚያ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክር ቤቶች የመሠረተ ልማት ግንባታዎችንና ፕሮጀክቶችን በመቆጣጠሩ ዙሪያ ክፍተት እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡ በቤት ካርታ ጉዳይም ህብረተሰቡ የሙሥና መረብ ውስጥ እንዳይገባ አሳስቧል፡፡ (ምሥክርአወል)
 • የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ (አስፋውስለሺ)
 • ሰሞኑን በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተከናወነው አለም አቀፍ የግብርና እና የምግብ ዐውደ ርዕይ ላይ የተገኙት ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካና ቻይና የሽግግር ፋይናንስ ብድር ለኢትዮጵያ የመስጠት ኃሣብ እንዳላቸው ተሠማ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ 8 ቁጥር ማዞሪያ በሚባል አካባቢ የኤሌክትሪክ መስመር ተበጥሶ ድንኳን ላይ በመውደቁ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሠማ፡፡ (አስፋውስለሺ)
 • ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም የጤና ድርጅት የሥራ ኃላፊ ሆነው እንዲመረጡ ድጋፍ እንደሚሰጡ ማኅበራት ተናገሩ፡፡ (ምሥክርአወል)
 • በአፍሪካ ዘላቂ የልማት አጀንዳ ላይ የሚመክረው ጉባዔ በአፍሪካ አዳራሽ መጀመሩ ተሰማ፡፡ (የኔነህሲሣይ)
 • በየካ ክፍለ ከተማ ላምበረት መናኸሪያ ጀርባ በደረሰ የእሣት አደጋ 18 ሱቆች ተቃጠሉ፡፡ (ንጋቱሙሉ)
 • የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከዚህ በፊት ሲመራበት የነበረውን ዕቅድ በቅርቡ በአዲስ ሊተካ ነው ተባለ፡፡ (ምህረትስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአክሱም ሃውልት ከሮም በተመለሰ ጊዜ በቦታው መልሶ የማቆም ሥራ ሲከናወን መናጋት ለገጠማቸው ሃውልቶች የማጠናከሪያ ሥራ ሊከናወን ነው

የአክሱም ሃውልት ከሮም በተመለሰ ጊዜ በቦታው መልሶ የማቆም ሥራ ሲከናወን መናጋት ለገጠማቸው ሃውልቶች የማጠናከሪያ ሥራ ሊከናወን ነው፡፡ከሮም ተመላሹ ሃውልት ጐን ያለው ሌላው ሃውልትም የታሰረበት ብረትና ሸራ እንዲነሳ ጥናት ይካሄዳል ተብሏል፡፡

ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የቅርስ ኢንቨንተሪ ደረጃ ማውጣት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ኤፍሬም አማረ ለሸገር ሲናገሩ የአክሱም ሃውልቶችን ለመንከባከብና ለማጠናከር እንዲቻል ከጣሊያኑ ስቱዲዮ ክሮችና ሀገር በቀል ከሆነው MH መለሰ ሀይሌ ጋር የሥምምነት ፊርማ ተከናውኗል ብለዋል፡፡

ከሮም ተመላሹ ሃውልት ጐን ያለውን ሃውልት ብረትና ሸራውን ፈትቶ በራሱ የማቆም፣ ሌሎች መናጋት የገጠማቸውና እድሳት የሚፈልጉም ተጠንተው በቅርቡ ወደ ሥራው ይገባል ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አዲስ አበባ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችንና አደጋዎችን ለመቀነስ በሚደረገው አለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ መቀላቀሏ ተሠማ

አዲስ አበባ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችንና አደጋዎችን ለመቀነስ በሚደረገው አለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ መቀላቀሏ ተሠማ፡፡ከተማዋ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችንና አደጋዎችን ለመቀነስ በሚደረገው አለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ ውሰጥ ከዛሬ ጀምሮ መቀላቀሏን የተናገሩት ከንቲባ ድሪባ ኩማ ናቸው፡፡በከተሞች ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች እና አደጋዎችን ለመቀነስ የሚደረገው አለም አቀፋዊ እንቅስቃሴ በ50 ከተሞች የተዋቀረ መሆኑን ሰምተናል፡፡

አዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ ራሷን ተላላፊ ካልሆኑ ህመሞችና አደጋዎች ለመቀነስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ መቀላቀል መጀመሯን ስትገልፅ ደስታ ይሰማኛል ያሉት ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፕሮግራሙ በቡልንበርግ ፊላንትሮፒስ እና አጋር ድርጅቶች የሚደገፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ለ18 ወራት የሚቆየው አለም አቀፍ እንቅስቃሴ ከተማዋን ከተላላፊ ህመሞችና አደጋዎች በመጠበቅ የነዋሪዎቿን የመኖሪያና የመስሪያ አካባቢዎች ምቹ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በየአመቱ ከሚመዘገቡት የሞት ቁጥሮች ውሰጥ 51 በመቶ የሚሆነው ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞችና አደጋዎች የሚደርስ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባው በአለም አቀፉ እንስቃሴ ውሰጥ አንደተቀላቀለ ከተማ በህመሞቹ ላይና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የምናደርገው ዘመቻ የተጠናከረ ይሆናል ብለዋል፡፡አዲስ አበባ በ50 ከተሞች የተዋቀረውን እንቅስቃሴ በመቀላቀሏ ተላላፊ ህመሞችና አደጋዎችን ለመቀነስ በምታደርገው ጥረት ሥራውን በሚደግፈው አካል በኩል ሙያዊ ድጋፍ ይደረግላታል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ጥሩ ተሞክሮዎች ካላቸው አገሮች ትምህርት ለማግኘት ያስችላታል መባሉን ሰምተናል፡፡ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች የሚባሉት እንደ ካንሰር፣ ስኳር፣ የመተንፈሻ አካል ህመሞች ከትራፊክ አደጋ ጋር ተደማምረው በአመት የ44 ሚሊዮን ሰዎች  ህይወትን አንደሚቀጥፉ የዓለም የጤና ድርጅት /WHO/ መረጃ ያሣያል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ግንቦት 8፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የፀረ ተባይና የፀረ አረም ርጭትና ድርቅ ለማር ሰጭዎቹ ንቦች ፈተና ነው ተባለ፡፡ (ምሥክርአወል)
 • ለአክሱም ሐውልቶች የማጠናከሪያ ዕድሣት ሊደረግላቸው ነው፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • አዲስ አበባ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመቀነስ የተጀመረው ዓለም አቀፋዊ ጥረት አካል ሆናለች ተባለ፡፡ (ንጋቱሙሉ)
 • ኢትዮጵያ ከቡና ሽያጭ በርከት ያለ ገቢ ለማግኘት አዲስ አሰራር ልትጀምር መሆኑ ተሰማ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • ከጅቡቲ ወደብ ማዳበሪያ የሚጭኑ መኪኖች እየተፈለጉ ነው፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዘመናዊ ቤተ-መፅሕፍት መሆኑ የሚነገርለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዋናው ጊቢ የሚገኘው የጆን ኤፍ ኬኔዲ መታሰቢያ ቤተ-መፃህፍት ትላንት የተመሠረተበትን 50ኛ አመት ማክበር ጀምሯል፡፡ (ንጋቱሙሉ)
 • ለዓመታት ሲጓተቱ የቆዩ የመስኖ ፕሮጄክቶች ከዝግመታቸው እየተላቀቁ ነው ተባለ፡፡ (ሕይወትፍሬስብሃት)
 • በአፍሪካ ከሀገር ሀገር የሰዎችን ነፃ ዝውወር ውጥን የሚያበረታታ በዓል በአዲስ አበባ ሊከበር ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የፍሬገነት ህልም … ፍሬገነት ኪዳን ለሕፃናት ትምህርት ቤት….

የወጣት ፍሬገነት የዘወትር ህልም በችግር ምክንያት የትምህርት ቤትን ደጃፍ መርገጥ ያልቻሉ ሕፃናትን የሚያስተምር ትምህርት ቤት መክፈት ነበር፡፡ የዛሬ 15 ዓመት፣ በ1995 ዓ.ም አንዲት ዕለት ግን ይህን ሕልም ሊያጨናግፍ ያለ ክስተት ሆነ - በወቅቱ በሚኒያፖሊስ ከተማ ነዋሪ የነበረችው ፍሬገነት የምታሽከረክረው መኪና ከፖሊስ ከሚሸሽ እፅ አዘዋዋሪ መኪና ጋር ተጋጭቶ ፍሬገነት ለሕልፈተ በቃች…

ፍሬገነት በአደጋው ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን አጠናቃ ገና ሁለት ወሯ ነበር፡፡ ብቸኛ ልጃቸውን በሞት የተነጠቁት ወላጆች ግን የፍሬገነትን ሕልም እውን ለማድረግ ተነሱ፡፡

ለዚህም የዛሬ 13 ዓመት የፍሬገነት ወላጆች 30 የችግረኛ ቤተሰብ ልጆችን የሚያስተምረውን “ፍሬገነት ኪዳን ለሕፃናት ትምህርት ቤት”ን አቋቋሙ…አሁን ላይ ትምህርት ቤቱ 335 ልጆችን የትምህርት ቁሳቁስ እየሰጠ፣ ዩኒፎርም እያለበሰ እና እየመገ ያስተምራል! ትምህርት ቤቱ ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ 4ኛ ክፍል የሚያስተምር ሲሆን፤ ከዚያን በኋላ ያሉትን ክፍሎች ምግብ ማብላቱም ሆነ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉ ሳይለይ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እንዲማሩ ያደርጋል…

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የህዳሴ ግድብ በታችኛው የወንዙ ተፋሰስ ሀገሮች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ ካለ የሚያጠናው ድርጅት ባቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ላይ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በአዲስ አበባ መነጋገራቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው የህዳሴ ግድብ በታችኛው የወንዙ ተፋሰስ ሀገሮች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ ካለ የሚያጠናው ድርጅት ባቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ላይ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በአዲስ አበባ መነጋገራቸው ተሰማ፡፡ሦስቱ ሀገራት አጥኚ ቡድኑ ያቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ላይ ከግንቦት 3 እስከ 6 በአዲስ አበባ መነጋገራቸውን በውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ ተሾመ አጥናፌ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ንግግሩ በሚያዝያ ወር በግብፅ ካይሮ ለ4 ቀናት ተካሂዶ የነበረው ውይይት የተከተለ መሆኑን ሰምተናል፡፡ሦስቱ ሀገራት አጥኚ ቡድኑ ባቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ላይ በአዲስ አበባ ለሦስት ቀናት ያደረጉት ውይይት ቴክኒካል ወይም ሙያዊ ጉዳዮች የተነሱበት መሆኑን አቶ ተሾመ ተናግረዋል፡፡

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በታችኛው የወንዙ ተፋሰስ ሀገሮች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ ካለ የሚያጠናው አጥኚ ቡድን ያቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ላይ የሚካሄደው ንግግር ወደፊትም እንደሚቀጥል ዳይሬክተሩ ነግረውናል፡፡ከአባይ ተፋሰስ ሀገሮች አንዷ የሆነችው ግብፅ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በወንዙ ላይ ያለኝን ጥቅም ይነካብኛል የሚል ኃሣብ ያላት ሲሆን ኢትዮጵያ በበኩሏ የግድቡ መገንባት የግብፅንም ሆነ የታችኛውን የወንዙ ተፋሰስ ሀገሮች ጥቅም የሚነካ አይደለም ስትል በተደጋጋሚ መናገሯ ይታወሣል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአማራ ክልል እስከ 8ኛ ክፍል በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሲሰጡ የነበሩ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶችን ወደ አማርኛ ቋንቋ ሊመልሳቸው ጥናት እያደረገ መሆኑ ተሰማ

የአማራ ክልል እስከ 8ኛ ክፍል በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሲሰጡ የነበሩ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶችን ወደ አማርኛ ቋንቋ ሊመልሳቸው ጥናት እያደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡የሳይንስ ትምህርቶቹ ከ10 ዓመታት በፊት ነበር በእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲሰጡ የተደረገው፡፡ሆኖም ተማሪዎች በአግባቡ ተረድተውት ስኬታማ የመሆናቸው ነገር አጠራጣሪ ነው የሚሉት የክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዋ ዶክተር ሂሩት ካሳው ቢሯቸው ስለ ጉዳዩ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር እየሰራበት ነው ብለዋል፡፤

ወደ እንግሊዘኛ ሲቀየር መጀመሪያውኑ በጥናት የተደገፈ አልነበረም የሚሉት ኃላፊዋ አሁን ወደ አማርኛ ለመመለስ ጥናት ውስጥ ያስገባቸውን ምክንያት ነግረውናል፡፡የክልሉ ተማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ሲገቡ ቀጥታ እንግሊዘኛ ቋንቋ ጋር መገናኘታቸው ተፅእኖ አያሳድርባቸውም ወይ ተፎካካሪ የመሆን አቅማቸውንስ አይፈታተንም ወይ ምን ያክል ታስቦበታል ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ የሌሎች ክልሎችን ልምድ ጠቅሰው ስኬታማ እንደሚሆን ነግረውናል፡፡

የአማርኛ ቋንቋ የምርምር የማስተማርያና መማሪያ ቋንቋ የመሆን ሙሉ አቅም እንዳለው የሚናገሩት ዶክተር ሂሩት አንዳንድ ቋንቋው ውስጥ የሌሉ የሳይንስ ቃላትን ተመራምሮ ከአማርኛ ጋር የማስማማቱንና የማዋደዱን ስራ የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የቋንቋ ማበልፀጊያ ተቋም ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ምርምር አካዳሚ የሳይንስ መዝገበ ቃላትና የሙያ ቃላት እንዳለ ያስታወሱት ዶክተር ሂሩት በየጊዜው የሚወጡ አዳዲስ ፅንሰ ሃሳቦችን ማካተት ባለመቻሉ ለአሁኑ የትምህርት ደረጃ እንዲበቃ የቴክኖሎጂና የምርመራ ቋንቋ እንደሆነ ይሰራል ብለዋል፡፡

ከመጀመሪያ ደረጃም በላይ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጭምር በሰፊው እንዲያገለግል እየተሰራ ነውም ተብሏል፡፡ከዚህ በተጨማሪ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ለግዕዝ ቋንቋ በቀጣይ ዓመት የትምህርት ክፍል ሊከፍትለት እንዳሰበ ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ምስክር አወል
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers