• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የዛሬ ጥቅምት 28፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የስኳር ህሙማን የህመሙ ታማሚ መሆናችንን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘን መድኃኒት ለመግዛት ብንጠይቅም ከሀኪም ማዘዣ አምጡ ተብለን ተቸግረናል አሉ፡፡ መንግሥት በበኩሉ የሀኪም ማዘዣው የሚጠየቀው ለራሳቸው ለህሙማኑ ሲባል ነው ብሏል፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የአለም ወጣቶች ቀን ሰሞኑን እየተከበረ ነው፡፡ መሪ ቃሉም “መነጋገር አለብን” የሚል ነው፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • ለካንሰር የጨረራ ህክመና የሚያገለግሉ በአይነታቸው አዲስና ዘመናዊ የጨረራ መሣሪያ /ራዲዮ ቴራፒ/ ማሽኖች ተገዝተው ሃገር ቤት መግባታቸውን የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ማኅበር 28ኛውን የአፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ያካሂዳል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፉት 3 ወራት ከቀረቡልኝ አቤቱታዎች ለ116ቱ መፍትሄ ሰጥቻለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የግል ትምህርት ቤቶች የመማሪያ መፃሕፍት ችግር አሁንም አልተቃለለም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ኢትዮጵያን ጨምሮ የኢጋድ አባል አገሮች የሕገ-ወጥ የዱር እንስሳት አደንን ለመከላከል በአዲስ አበባ መላ ሊመቱ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ባለውለታ ሆኖ የቆየው ቡና የሚያስገኘው ገቢ ማሽቆልቀሉ ያሳሰበው መንግሥት ገቢውን ከፍ ለማድረግ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል

ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ባለውለታ ሆኖ የቆየው ቡና የሚያስገኘው ገቢ ማሽቆልቀሉ ያሳሰበው መንግሥት ገቢውን ከፍ ለማድረግ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ችግሮቹ ሙሉ በሙሉ መላ ባያገኙም የቡና የግብይት ሥርዓት ለውጥ መደረጉና ላኪዎችም የፈለጉትን አካባቢ ቡና ያለማንም ከልካይ መግዛት መቻላቸው ገቢውን አንዳሻሻለው ንግድ ሚኒስቴር ለሸገር ተናግሯል፡፡

በሩብ ዓመቱ 215 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፡፡ ገቢው ከዓምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲመሣከርም የ34 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል፡፡የሚላከው ቡና መጠንና በገቢም ከፍ እንዲል ያስችላል የተባለ የቡና ግብይት ማሻሻያ መመሪያ ፀድቆ ከወራት በፊት ሥራ መጀመሩ ለገቢው ማደግ አንዱ ምክንያት መሆኑን የቡና ላኪዎች ማኅበር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው አድማሱ ነግረውናል፡፡

የቡናና የወጪ ንግድ የሚከታተል ራሱን የቻለ ባለቤት ያስፈልገዋል ተብሎ ከዓመት በፊት የቡናና ሻይ ባለሥልጣን መቋቋሙ ለገቢው ከፍ ማለት ሌላው ምክያት ነው ብለዋል፡፡ መንግሥት ያደረጋቸው ማሻሻያዎች ድምር ውጤትም ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ ያቀረበችው ቡና በሩብ ዓመቱ በመጠን በ8 ቶን፣ በገቢ ደግሞ በ34 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ከፍ አድርጐታል ብለዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥቅምት 27፣ 2010 ዓ.ም የሸገር ወሬዎቻችን

 • ኢትዮጵያ ለዓለም ገበያ ያቀረበችው ቡና በሩብ ዓመቱ ከአምናው በመጠን በ8 ቶን፣ በገቢ ደግሞ በ34 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ብልጫ አለው ተብሏል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • አዳዲስ የሽንብራና የምስር ዝርያዎች በምርምር ተፈጠሩ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የአዲስ አበባ ነዋሪ በጋራ መኖሪያ ቤቶች መጠቀም ከጀመረ ሰነበተ፡፡ ይሁንና ሕንፃዎቹ ሲገነቡ፣ ለሕፃናት መዋያ ትኩረት የሚሰጡ ባለመሆናቸው ታዳጊዎች የሚውሉበት አጥተዋል የሚል ሮሮ ይሰማል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በተደጋጋሚ ቢነገርም አዲስ የሚሰሩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉድለቱን ለማስተካከል ሲጥሩ አይታይም፡፡ ነዋሪዎችም ቅሬታቸውን ከማሰማት አልታገዱም፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር የሚገኘው የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት እንፋታ ብለው ለፍርድ ቤት ካመለከቱ ሰዎች ግማሽ ያህሉን በትዳራቸው እንዲቀጥሉ አስማምቻለሁ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በአዲስ አበባ ከተማ ከማዘጋጃ ቤታዊ እና ከቤት ኪራይ ገቢ ግብር ተገቢው ገንዘብ እየተገኘ አይደለም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • ባለፉት አምስት ዓመታት የወባ ስርጭት በኢትዮጵያ በ50 በመቶ ቀንሷል ተብሏል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • መገናኛ ብዙሃን ፆታን መሠረት ያደረጉ ዘገባዎች ላይ የሚሰሩት ሥራ የተመጣጠነ ባለመሆኑ የሚመሩበትን ፖሊሲ ሊፈትሹ እንደሚገባ ተነገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራትን ለመቆጣር የተቋቋመው ኤጀንሲ ሥራውን በአግባቡ ማካሄድ የሚችልበት አደረጀጀት የለውም ተብሏል፡፡ ኤጀንሲው በበኩሉ ስራዬን ለማካሄድ የሚያስችለኝ መዋቅር በማዘጋጀት ለትምህርት ሚኒስቴር  ልኬያለሁ ብሏል፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • የቤት እንስሣት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ሲነዱ ተገኙ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የትራፊክ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

እናቶች ያላቸውን ባለማወቅ ህፃናት ልጆቻቸውን መመገብ ባለመቻላቸው ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተዳረጉ ነው ተባለ

እናቶች ያላቸውን ባለማወቅ ህፃናት ልጆቻቸውን መመገብ ባለመቻላቸው ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተዳረጉ ነው ተባለ፡፡እንዲህ ያሉት የአማራ ክልል የጤና ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አበባው ገበየሁ ናቸው፡፡ዶክተር አበባው እንዳሉት ከሆነ በክልሉ 46 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት በከፍተኛ ምግብ እጥረት የተዳረጉ ናቸው፡፡ይህን ከፍተኛ ቁጥር ለመቅረፍም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በጋራ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ከነዚህም አንዱ አላይቭ ኤንድ ትራይቭ የተሰኘው ድርጅት ሲሆን ባለፉት ሦስት ዓመታትም በክልሉ 19 ወረዳዎች በሰራው ሥራ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡የድርጅቱ የýሮጀክት ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር የውልሰው አበበ ባለፉት ሦስት ዓመታት 50 በመቶ ችግሩ መቃለሉንና ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡እናቶች በቤታቸውና በጓሯቸው ያለውን ምግብ አመጣጥነው እንዲመግቡ በማድረግ ለውጡ እንደመጣ ተናግረዋል፡፡

በእርግጥ የተመጣጠነ ምግብ በሚገባ ማግኘቱ ፈተና ቢሆንም ቤት ያፈራውንና የተገኘውን ምግብ በማመጣጠን ግን ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በወጣቶች ዘንድ በቴክኒክና ሙያ ሥራዎች ላይ ለመሠማራት ያለው ፍላጎት ከ10 በመቶ በታች ነው ተባለ

በወጣቶች ዘንድ በቴክኒክና ሙያ ሥራዎች ላይ ለመሠማራት ያለው ፍላጎት ከ10 በመቶ በታች ነው ተባለ፡፡ይህም ከግንዛቤ እጥረት የመጣ ነው ተብሏል፡፡እንደየማሰልጠኛ ቦታዎች፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦቶችና ተዘዋዋሪ የወጣቶች ፈንድን የመሳሰሉ የገንዘብ ድጋፎች ቢደረጉም ለውጥ እየታየ አለመሆኑን ነው ፤ ዛሬ የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር ወይም ወወክማ የአፍሪካ የወጣቶች ቀንን አስመልክቶ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የሰማነው፡፡

በመድረኩ ላይ የቀረበው ጥናት እንደሚያመለክተው መንግሥት ለወጣቶች ከመደው 10 ቢሊየን ብር ወጣቱ የተጠቀመው ከ50 በመቶ በታች የሆነውን ነው፡፡ለዚህም ምክንያቱ በመደበኛ ትምህርቶች ስለ ቴክኒክና ሙያ ሥራዎችና ሥልጠናዎች ግንዛቤ የሚሰጡ ýሮግራሞች ስለሌሉ እንደሆን የጥናቱ አቅራቢና የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆነው ወጣት አሸናፊ መንግሥቱ ነግሮናል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ከሚገኙ ወጣቶች 43 በመቶ የሚሆኑት ተቀጥረው መሥራት የሚፈልጉ መሆናቸውንና ቀሪዎቹም በአብዛኛው በጊዜና በቦታ ያልተገደቡ እንዲሁም መደበኛ ያልሆኑ ሥራዎችን መሥራት የሚፈልጉ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር /ወወክማ/ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ዜጎችን ለማፍራት በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጌ እየሰራሁ ነው ሲል ተናግሯል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈረሙ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ለማጥበቅ ቋሚ ኮሚቴዎቹ ...

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈረሙ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ለማጥበቅ ቋሚ ኮሚቴዎቹ በጠቀሷቸው የምክር ቤቱ አሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥርና አንቀፅ ላይ ሳይግባቡ አዋጆቹን ሲያፀድቁ አርፈደዋል፡፡ሊፀድቁ ከቀረቡ አዋጆች ገሚሱ በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 በመጥቀስ የፀደቁ ሲሆን ገሚሶቹን ደግሞ ዘንድሮ በተሻሻለው ደንብ ቁጥር 7/2010 መሠረት አፅድቀዋቸዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴዎቹ ረቂቅ አዋጆቹን ለማፅደቅ የሚጠቀሙት ደንብ የቀድሞውን ነው ወይንስ የአሁኑን የሚለው በሌላ ጊዜ የሚታይ ይሆናል ሲሉ ምክትል አፈ ጉባዔዋ አስታራቂ ኃሣብ አቅርበዋል፡፡ከአሥር ቀን በፊት በምክር ቤቱ ቀርበው ለዝርዝር እይታ ወደ ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ የተመሩ አራት ስምምነቶች ላይ የተጠቀሰው ዘንድሮ የተሻሻለው የምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 7/2010 ነው፡፡

የምክር ቤቱ አባልና የህግ ባለሙያው አቶ ተስፋዬ ዳባ በበኩላቸው ዘንድሮ የተሻሻለው የምክር ቤቱ የሰራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ አንድ አንቀፅ ብቻ  ያሻሻለ በመሆኑ መጠቀስ ያለበት የቀድሞ ደንብ ነው የሚል አቋም አላቸው፡፡ በመሆኑም በሰብሣቢነት የሚመሩት የውጭ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በምክር ቤቱ ያቀረቧቸው አምስት የስምምነት አዋጆች የቀድሞውን የምክር ቤቱን ደንብ ቁጥር 6/2008 በመጥቀስ ፀድቀዋል፡፡

የዛሬውን የእንደራሴዎቹን ስብሰባ የመሩት ምክትል አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ በቋሚ ኮሚቴዎቹ የተጠቀሱት የደንብና አንቀፅ ቁጥሮች የተለያዩ ቢሆኑም በሚፀድቁ አዋጆች ይዘት ላይ መሠረታዊ ለውጥ ስለማያመጡ ችግር አይፈጥርም ብለዋል፡፡በመጪው ጊዜም ቋሚ ኮሚቴዎቹ ለዝርዝር እይታ የሚመሩላቸውን አዋጆች ለማፅደቅ የውሣኔ ኃሣብ ሲያቀርቡ የትኛውን የአዋጅ ደንብ ቁጥር ይጠቀሙ የሚለው በመጪው ጊዜ ይታያል ብለዋል፡፡እንደራሴዎቹ ዛሬ ባካሄዱት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አራተኛ መደበኛ ስብሰባ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈፀሙ አስር ስምምነቶችን አፅድቀዋል፡፡

ትዕግሥት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥቅምት 23፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • እናቶች ያላቸውን ባለማወቅ ህፃናት ልጆቻቸውን መመገብ ባለመቻላቸው ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት እየተዳረጉ ነው ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በወጣቶች ዘንድ በቴክኒክና ሙያ ሥራዎች ላይ ለመሠማራት ያለው ፍላጎት ከ10 በመቶ በታች ነው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • በቆሎን አጥቂው የአሜሪካ መጤ ተምች አሁንም በበቆሎ የመስኖ ማሳዎች ውስጥ አልጠፋም ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን በአየር ትራፊክ ቁጥጥር ያሰለጠናቸውን አስራ ሰባት የጁቡቲ ዜጐች በመጪው እሁድ ሊያስመርቅ ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአገር አቋራጭ አውቶብሶች ትኬት በተጓዦች አቅራቢያ መገኘት በመቻሉ ተቀባይነታቸው እየጨመረ መጥታል፤ እየተለመደም ነው ተብሏል፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የአዳማ ከተማ ፖሊስ አባላት በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች በተከሰተው ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ ሰጡ ተባለ፡፡ (ማኅሌት ታደለ)
 • የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በአዋጅ ማፅደቂያ የአሰራርና የአባላት የሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥርና አንቀፅ ላይ ሲወዛገቡ አረፈዱ፡፡ አዋጆችን ግን አፅድቀዋል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የጊዜ ቀጠሮ ማስቻያ ችሎት በተጠርጣሪዎች ላይ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ (እሸቴ አሰፋ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ጥቅምት 21፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከውጪ ሃገር ባስገባው የልብ ህክምና ማሽን ከመስከረም 8 ወዲህ...

የቅዱስ ጳውሎስ  ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከውጪ ሃገር ባስገባው የልብ ህክምና ማሽን ከመስከረም 8 ወዲህ ብዛት ያላቸው ህሙማንን ማከሙን ተናገረ፡፡የህክምና ኮሌጁ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ነዋይ ፀጋዬ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ በ120 ሚሊየን ብር ወጪ ከውጪ በተገዛው የልብ ህክምና ማሽን በሚሊኒየም የጤና ኮሌጅ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመጡ ብዙ ሰዎች የልብ ህክምና አግኝተውበታል ብለዋል፡፡

ይህ ዘመናዊ የልብ ህክምና ማሽን ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የጤና ህክምና ኮሌጅ በተጨማሪ በጥቁር አንበሣና በመቐሌ ሀይደር ሆስፒታል ብቻ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡የህሙማኑን ብዛት ከግምት በማስገባት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የልብና የካንሰር ማዕከል ግንባታም እየተፋጠነ እንደሆነ አቶ ነዋይ ነግረውናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የዛሬ ጥቅምት 22፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ባለፉት አምስት ዓመታት አባት አይደለንም በሚል በፍርድ ቤት ሲከራከሩ ከቆዩና ወደ ሁለት መቶ ከሚጠጉ ሰዎች የዘጠና በመቶዎቹ አባትነት በባህሪያ ወሳኝ ቅንጣት /ዲ ኤን ኤ/ ምራመራ ተረጋግጧል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች በተመሳሳይ የትምህርት መስኮች ላይ ሲከተሉት የነበረውን የተለያዩ አሰራር የሚያስቀር ወጥ የሆነ ስርዓተ ትምህርት በሥራ ላይ ውሏል ተባለ፡፡ (ማኅሌት ታደለ)
 • የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በ2010 ከ4 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ሥራ አስይዣለሁ ሲል ለተወካዮች ምክር ቤት ማኅበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ተናገረ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ጥንታዊና ታሪካዊ ቤቶች ላልተገባ አገልግሎት እንዳይውሉ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የጥቁር አንበሣ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ከውጭ ሀገር ባስገባሁት አዲሱ የህክምና ማሽን ብዛት ያላቸው ህሙማንን እያከመ እንደሆነ ተነገረ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ተሾመለት

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ተሾመለት፡፡የዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኙነት አቶ አሰማኸኝ አስረስ እንደነገሩን በግዚያዊነት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት የዩኒቨርስቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ጀይሉ ኡመር ናቸው፡፡

ዶክተሩ አሁን ላይ ሁለቱን ኃላፊነት ተረክበው እንዲሰሩ የተሾሙት ትምህርት ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ መሠረት ነው ተብሏል፡፡ስለ ሹመቱ በደብዳቤው ተጠቅሷል ያሉት አቶ አሰማኸኝ ዶክተሩ የተመረጡት በከፍተኛ ትምህርት አመራር ምልመላና ምደባ መመሪያ መሠረት ሲሆን ፕሬዝዳንት ተመርጦ እስኪሾም ያገለግላሉ ብለዋል፡፡

የቀድሞ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት የነበሩት ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ በኢንዶኔዢያ የኢትዮጵያ አንባሳደር ሆነው መሾማቸው ይታወቃል፡፡ፕሮፌሰሩ በቅርቡ ኢትዮጵያን የጎበኙትን የህንዱን ፕሬዝዳንት ራም ናት ኦቪንድን በዩኒቨርስቲያቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ይታወሣል፡፡

ምስክር አወል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers