• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረገው ጨዋታ - ሁለተኛው ክፍል

የዛሬ 8 ዓመት በናንተው ሬድዮ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የተላለፈውንና መዓዛ ብሩ ከተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ጋር አድርጋው የነበረውን የቅዳሜ ጨዋታ ቆይታ ሁለተኛውን ክፍል ወደ ሸገር ኦፊሺያል የዩትዩብ ቻናል ጎራ ብላችሁ እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

https://www.youtube.com/watch?v=SmFchBKpJh0&feature=youtu.be

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ የጥር 23፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ችግር ዋናው ምክንያቱ አመራሩ ከተመሪው በታች የሆነ የአመራር አቅም በማሳየቱ መሆኑ ተነገረ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የሕዳሴ ግድብ የቴክኒክ ጉዳይ ላይ የነበረውን ልዩነት እስከ አንድ ወር ድረስ መፍትሄ ለመስጠት ሶስቱ መሪዎች ተስማምተዋል፡፡ (እሸቴ አሰፋ)
 • የአዲስ አበባ ከተማ ብክለትን ለመቆጣጠር የነዋሪዎች እገዛ እንደሚያስፈልግ ተናገረ፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሩዋንዳውን የሙዋንዛ የመስኖ ግድብ በሩዋንዳውያን ኩባንያዎች የዕቃ አቅርቦት ችግር በግዜው ማጠናቀቅ አልቻልኩም አለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለማስቀረት የሚረዱ የምርምር ውጤቶች ስራ ላይ ይውላሉ ተባለ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • የኢትዮጵያዊያን ታዳጊ ሴቶች ሕይወት በድርቅ ይበልጥ ተጎጂ እየሆነ መምጣቱን ወርልድ ቪዥን ተናገረ፡፡ (ምስክር አወል)
 • በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም የጤና ኮሌጅ አዲስ ምርመራ ተጀመረ ተባለ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረገው ጨዋታ - የመጀመሪያው ክፍል

ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረገው ጨዋታ - የመጀመሪያው ክፍል

የዛሬ 8 ዓመት በናንተው ሬድዮ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የተላለፈውንና መዓዛ ብሩ ከተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ጋር አድርጋው የነበውን የቅዳሜ ጨዋታ ቆይታ የመጀመሪያውን ክፍል ወደ ሸገር ኦፊሺያል የዩትዩብ ቻናል ጎራ ብላችሁ እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

https://www.youtube.com/watch?v=SeV0Js8kLNU

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ጥር 22፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥር 22፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት ፈተናውን የሚወስዱ የICT ባለሙያዎች ቁጥር ዝቅተኛ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን በአመት የሚገናኙበትን የጋራ ኮሚሽን ለመመስረት ትናንትና በሸራተን አዲስ ተስማሙ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን በኢትዮጵያ ህጋዊ አደን በሚካሄድባቸው ፓርኮች የሚሰሩ አስጎብኚዎች ያለባቸውን ችግሮች እንዲያስተካክሉ እያገዝኳቸው ነው አለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በተለያዩ ተቋማት በር የሚተላለፉና የሚወጡ መረጃዎች የግንዛቤ እጥረት ያለባቸውን ሰዎች ታሳቢ አድርገው አይዘጋጁም ተብሏል፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • በአማራ ክልል የ598 ተጠርጣሪዎች ክስ መቋረጡ ተነገረ፡፡ (እሸቴ አሰፋ)
 • የአፍሪካ ካፓሲቲ ቢውልዲንግ ፋውንዴሽን ለሃያ ስልሳ ሶስት አጀንዳ ስኬት እየሰራ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ባለፉት 6 ወሮች በተለያየ ምክንያት እንደተፈለገው ግንባታቸው ሊከናወን አልቻለም ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአዲስ አበባ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የተለያዩ እንከን አግኝቼባቸዋለሁ ያላቸውን 19 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ማገዱን ተናገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • ቻይና በአዲስ አበባ በገነባችው ከአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ውስጥ ባለፉት 5 አመታት ሰነዶችን ስትመነትፍ ነበር መባሏን አስተባበለች፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥር 21፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ እንዲሻሻል ምክክር እያደረግኩ ነው አለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • በአንፃሩ ኢትዮጵያውያን የምህንድስና ባለሞያዎች ከመላው የአፍሪካ ሀገሮች የተሻለ ልምድና እውቀት ስላላቸው ኢትዮጵያ ገበያውን ለመጠቀም ከወዲሁ መዘጋጀት ይኖርባታል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የቆዩ ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ቦታዎችን በማስለቀቅ ለስራ ፈላጊ ወጣቶች አዘጋጅቻለሁ አለ፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • ባለባቸው ኢኮኖሚያዊ ችግር ምክንያት በልተው ለማደር ተቸግረዋል የተባሉ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ዜጎች መንግስት ቀጥተኛ ድጋፍ እያደረግኩላቸው ነው አለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በአዳማ ከተማ እስረኛውን የገደለ ፖሊስ ታሰረ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • የሶስትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችን ለማስቀረት ከአካባቢው ተሰሚ ሰዎች ጋር እየተሰራ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • ከአመት አመት እየወደቀ የመጣውን የማዕድን ምርትና ገቢን ለማሳደግ የማዕድን ሀብቱን በሚገባ ማስተዋወቅና ፖሊሲና መመሪያዎችን ምቹ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነገረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በእንግዳ አቀባበል ጊዜ ያልተገባ ሥነ-ምግባር ካጋጠማችሁ ጠቁሙን ተብላችኋል፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አለም አቀፍ የአደጋ መከላከል ፈንድ ለኢትዮጵያ 10 ሚሊዮን ዶላር መለገሱን ተናገረ፡፡ (ምስክር አወል)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ድምፃዊ፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲ ኪሮስ ዓለማየሁ (1948 - 1988)

ድምፃዊ፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲ ኪሮስ ዓለማየሁ (1948 - 1988)

ሥመጥሩ የትግርኛ ሙዚቀኛ እና ሥራዎቹ ለትግርኛ ሙዚቃ እድገት አስተዋፅኦ እንዳደረጉ የሚነገርለት ድምፃዊ፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲ ኪሮስ ዓለማየሁ ሥራ እና ሕይወት የተዳሰሰበትን የሸገርን የስንክሳር የሬዲዮ ዶክመንተሪ ወደ ሸገር የዩትዩብ ቻናል ጎራ ብላችሁ እንድታዳምጡ ጋብዘናል…

https://www.youtube.com/watch?v=GIsnfaCsAvQ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የወልዲያ ከተማ አሁን ላይ መረጋጋቷ ተነገረ…

የአማራ ቴሌቭዥን፣ መናሃሪያዎች አገር አቋራጭ አውቶብሶች እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ስራ መጀመራቸውን ዘግቧል፡፡ሸገር ወልዲያ ካሉ ምንጮች እንደሰማው የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ቢጀመሩም ማክሰኞ እለት የሚውለው የገበያ ቀን እንዳልተከወነና ክፍት የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንደነበር ሰምቷል፡፡በትናንትናው እለትም የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴ ቢጀመሩም ገባ ወጣ ከማለት ውጭ ያን ያክል ተጀምሯል ማለት አይቻልም ያሉን ምንጮቻችን ምናልባትም ከሰኞ በኋላ ወደ መደበኛ ስራ ይመለስ ይሆናል ሲሉ ግምታቸውን ነግረውናል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች እንዲሁም የሀይማኖት አባቶች ጋር መነጋገራቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡በውይይቱ የተካፈሉት ለርዕሰ መስተዳድሩ ካነሱዋቸው ጥያቄዎች ውስጥ የታሰሩት እንዲፈቱና በክልሉ የፖሊስ ሀይል ብቻ ፀጥታ እንዲከበር አንስተዋል፡፡በአሁኑ ጊዜ ከተማዋ በክልሉ ልዩ ሀይል ብቻ እየተጠበቀች መሆኗን ሰምተናል፡፡የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በደረሰው አደጋ መንግስት ማዘኑና የሰው ሕይወት ሳይጠፋ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የፀጥታ ሀይሎችም የሰው ሕይወት ሳይጠፋና አካል ሳይጎድል የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚገባ በመገንዘብ የመፍትሄ አካል መሆን ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውም ይታወሳል፡፡በወልዲያ በበዓል አክባሪዎችና በፀጥታ ሀይሎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ከወልዲያ 50 ኪሎሜትር በምትርቀው ቆቦ ከተማ ግጭት መቀስቀሱን የክልሉ የቴሌቪዥን ጣቢያ በፌስቡክ ገፁ ዘግቧል፡፡

ምስክር አወል

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ዜጎች ወደተለያዩ የአረብ ሀገራት ለቤት ሰራተኝነት በህጋዊ መንገድ እንዳይሄዱ መንግስት ጥሎት የቆየውን እገዳ እንዲያነሳ...

ዜጎች ወደተለያዩ የአረብ ሀገራት ለቤት ሰራተኝነት በህጋዊ መንገድ እንዳይሄዱ መንግስት ጥሎት የቆየውን እገዳ እንዲያነሳ ጥያቄ ማቅረቡን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ስራ ፈላጊዎችን በህጋዊ መንገድ ለመላክም ከ3 ሰራተኛ ተቀባይ ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ለመፈራረም ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅቶ መጨረሱን ሰምተናል፡፡

ስምምነቶቹ የሚፈረሙት ከሊባኖስ፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ከባህሬን ጋር ነው ተብሏል፡፡ሚኒስትሩ አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ እንዳሉት የተሰናዳው የስምምነት ረቂቅ አስተያየት እንዲሰጥበት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተልኳል፡፡ከሳውዲ አረቢያ ጋር ስምምነት ላይ መደረሱ የሚታወስ ሲሆን ስምምነቱ በመንግስት እንዲፀድቅ የሚቀርብ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ከሊባኖስ ጋር በቅርቡ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በቀድሞው የስራ ስምሪት አዋጅ መሰረት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ 21 ነባር ኤጀንሲዎች ፈቃዳቸው መሰረዙን ሚኒስትሩ ዛሬ የመስሪያ ቤታቸውን የ6 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርት ለሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት ሲያቀርቡ ሰምተናል፡፡በአዲሱ አዋጅ መሰረት በውጭ ሀገር ስራና ሰራተኛን ለማግኘት ካመለከቱ 820 አዳዲስና 178 ነባር ኤጀንሲዎች መካከል መስፈርቱን አሟልተዋል ተብለው ፈቃድ የተሰጣቸው 6 ኤጀንሲዎች ብቻ ናቸው፡፡ ሰነዳቸው እየታየ ያሉም አሉ ተብሏል፡፡

አዲሱ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አዋጅ ከፀደቀ 2 አመት ቢሞላውም ወደ አረብ ሀገራት ለስራ የሚሄዱ ሰራተኞች እገዳ እስካሁን አልተነሳም አሁን ግን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያገባደድን ነው ያሉት ሚኒስትሩ መንግስት እገዳውን እንዲያነሳ ጥያቄ አቅርበን መልስ እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዛሬ ጥር 17፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ካሣ ተክለ ብርሃን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አቀረቡ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የእንጦጦ ሙዚየም ምንም አይነት እድሳት ሳይደረግለት ብዙ አመታት አስቆጥሯል ተባለ፡፡ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሙዚየሙን ብቻ ሳይሆን አካባቢውን ጭምር ላለማ ነው ብሏል፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
 • ኢትዮጵያ ተፈጥሮ የለገሳትን ውሃ የሰላሟ ጋሻ አድርጋ ልትጠቀምበት ይገባል ተባለ፡፡ ለዚህም የምህንድስና ዘርፍ ሚና ከፍተኛ እንደሆነም ተነግሯል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በሊቢያ በስደት ላይ የሚገኙ 21 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ምሽት ሀገር ቤት ይገባሉ ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የመድሃኒት ፈንድ ኤጀንሲ የህፃናት የቲቢ መድኃኒት በነፃ እያሰራጨ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ሀይሉ)
 • የወልዲያ ከተማ አሁን ላይ መረጋጋቷ ተናገረ፡፡ (ምስክር አወል)
 • በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚከሰቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና አለመረጋጋቶች ምክንያታቸው ሙስና ነው ተባለ፡፡ (በየነ ወልዴ)
 • እዚህ አዲስ አበባ ለሚደረገው የአፍሪካ ሀገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ለመገኘት ልዑካን መግባት ጀምረዋል፡፡ (እሸቴ አሰፋ)
 • ለአመታት ታግዶ የቆየው የውጪ ሀገር የስራ ስምሪት እንዲጀመር ጥያቄ ቀረበ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢራፓ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ድርጅት ወጥቼበታለሁ አለ

ኢራፓ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ድርጅት ወጥቼበታለሁ አለ፡፡ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ገና ዝግጁ አለመሆኑን ተረድቻለሁ ያለው ኢራፓ ከዛሬ ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር መውጣቱን ተናገረ፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ዛሬ በፀረ ሽብር ህጉ ላይ እየተደራደሩ ባሉበት ወቅት ነው ኢራፓ አቋሙን ያሳወቀው ድርድሩንም አቋርጦ ወጥቷል፡፡

የኢራፓ ዋና ፀሐፊ አቶ መላኩ መሰለ እንዳሉት የፀረ ሽብር ህጉ ሰላማዊ ትግልን ያፈነ፣ የዜጎችን በነፃነት የመናገርና የማሰብ መብት ጭምር የገፈፈ ነው፡፡ህጉ ዜጎቹን ከሽብር አደጋ ከመጠበቅ ይልቅ የዜጎችን መብት በመግፈፍ ገዢውን ፓርቲ አይነኬ ያደረገና ያፈረጠመ ነው ሲሉ ገልፀውታል፡፡

በመሆኑም ህጉ ሙሉ በሙሉ እንዲሻርና ለኢትዮጵያ ስጋት የሆነውን አለም አቀፍ ሽበርተኝነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ሌላ የፀረ ሽብር ህግ እንዲረቀቅ ጥያቄ አቅርበን ኢህአዴግ ሊሰማን አልፈለገም ያሉት የኢራፓ ዋና ፀሐፊ ይህም ገና ለመደራደር ዝግጁ አለመሆኑን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ከዚህ በኋላም በድርድሩ አንቀጥልም የሚል አቋማቸውን ተናግረው የስብሰባ አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል፡፡

ኢህአዴግ በበኩሉ የፀረ ሽብር ህጉ የወጣው የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ነው ሲል ተከራክሯል፡፡ሕዝቡ ከፈለገ ገዢውን ፓርቲ በምርጫ ካርድ መቀየር ይችላል ብሏል፡፡በፀረ ሽብር ህጉ ላይም እንዲሻሻሉ ካነሷቸው አንቀፆች መካከል የምናያቸው ይኖራሉ የሚል መልስ ሰጥቷል ኢህአዴግ፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በፀረ ሽብር ህጉ ላይ ለመደራደር በፌዴሬሽን ምክር ቤት ስብሰባ ሲቀመጡ ዛሬ 5ኛ ቀናቸው ነው፡፡ከዚህ ቀደም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅች መካከል እንዲሰረዙ የጠየቋቸውን ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
 
ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers