• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሰኔ 10፣2011/ አንጋፋው ደራሲ አውግቸው ተረፈ በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ደራሲው ዛሬ ከለሊቱ 11 ሰዓት በቤተዛታ ሆስፒታል አርፏል፡፡አውግቸር ተረፈ፤ ወይ አዲስ አበባ፣ እብዱ፣ ያንገት ጌጡ፣ ጩቤው፣ ፅኑ ፍቅር፣ ደመኛው ሙሽራ (በጋራ)፣ የፍቅር ረመጥ፣ ሚስኪኗ ከበርቴ፣ ጣፋጭ የግሪም ተረቶች፣ የዓለም ምርጥ ተረቶች (1፣ 2 እና 3)፣ የግሪክ እና የሩሲያ ተረቶች እንዲሁም የትውልድ እልቂት (ትርጉም) እና ሌሎች መፅሐፍትንም ያሳተመ እንደነበር የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ነግሮናል፡፡

አውግቸው ተረፈ የደራሲው የብዕር ስም ሲሆን ሕሩይ ሚናስ ትክክለኛ መጠሪያ ስሙ ነበር፡፡ ሸገር ለአውግቸው ተረፈ ቤተሰቦች፣ ዘመድ ወዳጆች እና አድናቂዎች በሙሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 7፣ 2011/ ማዳበሪያ በጊዜ አለመድረስ ሰበቡ ምን ይሆን?

ክረምቱ መጣሁ መጣሁ እያለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የክረምት ወቅት የእርሻ ምርቶችን የሚዘሩበት ጊዜ ነው፡፡ ለገበሬዎች ይኽ ወቅት ከመኖር አለመኖር ጋር የተያያዘ ነው፡፡ “አንድ ሰኔ የነቀለውን 10 ሰኔ አይተክለውም” እየተባለ የሚነገረውም ለዚህ ነው፡፡ ለእርሻ ስራ የሚያገለግለው ማዳበሪያ በአሁኑ ወቅት በገበሬው እጅ መግባት አለበት፡፡

ግን በአንዳንድ አካባቢ ያሉ ገበሬዎች ማዳበሪያ እንዳልደረሳቸው ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል ጅቡቲ ላይ የደረሰው ማዳበሪያ በማጓጓዣ ችግር እዚያው እንደተከማቸ ነው ይባላል፡፡ ንጋቱ ረጋሣ የማዳበሪያ በጊዜ አለመድረስና ችግሩስ ምንድን ነው? ሲል ጠይቋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣ 2011/ በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያረገው የተማሪዎች ምገባ 300 ሺህ ተማሪዎችን ሊያካትት እንደሆነ ተሰምቷል

በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያረገው የተማሪዎች ምገባ 300 ሺህ ተማሪዎችን ሊያካትት እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ይህን ያህል ብዛት ያላቸውን ተማሪዎች ለመመገብ ምን ያህል ዝግጁ ነው ሲል በየነ ወልዴ ተከታዩን መረጃ አሰናድቷል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣ 2011/ ድጎማ ተደርጎበት የሚገዛውን ነዳጅ ከፍ ባለ ዋጋ ለጎረቤት ሀገራት ለመሸጥ የሚሰራው አሻጥር ቢቀንስም ገና ሙሉ ለሙሉ እንዳልቆመ ተነገረ

ድጎማ ተደርጎበት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚገዛውን ነዳጅ ከፍ ባለ ዋጋ ለጎረቤት ሀገራት ለመሸጥ ታስቦ የሚሰራው አሻጥር ቢቀንስም ገና ሙሉ ለሙሉ እንዳልቆመ ተነገረ፡፡


ህይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 10፣2011/ በአዲስ አበባ ከተማ 51 ህንፃዎች ያለመጠቀሚያ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ መገኘታቸው ተሰማ

ሌሎች 66 ህንፃዎች ደግሞ የተለያዩ መሰረታዊ ነገሮችን ሳያሟሉ ከአዋጁ ውጭ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በ2010 ዓ/ም በፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በተደረገ የክዋኔ ኦዲት ተረጋጧል፡፡በናሙና ተወስደው ከታዩ የአዲስ አበባ ህንፃዎች መካከል 66 ህንፃዎች አገልግሎት ሲሰጡ የተገኙት ሊፍት ሳይኖራቸው፣ የእሳት አደጋ መከላከያ ሳይገጠምላቸው፣ ከተፈቀደው ውጭ ወለል ጨምረው ገንብተው፣ አደጋ በሚያደርስ መልኩ በውስጥና በውጭ የማጠናከሪያ ስራዎችን በመስራት መሆኑን ታዝቤያለሁ ብሏል የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቱ በሪፖርቱ፡፡

ሌሎች 37 ህንፃዎች ደግሞ ለመኪና ማቆሚያ የተፈቀደላቸውን የህንፃውን የስረኛው ወለል ለሌላ አገልግሎት ማለትም ለባንክ አከራይተው፣ ለእቃ ማከማቻ አድርገውና የመጋዘን አገልግሎት እንዲሰጥ አድርገው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 7፣ 2011/ በተማሪዎች እሮሮ የሚቀርብበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና መምህራን ግንኙነት

ዩኒቨርስቲዎቻችን የመማር ማስተማር ሂደቱ በጥንቃቄ የሚመራባቸው አልሆኑም የሚሉ የተማሪዎች እሮሮ አለ፡፡ አንጋፋውና የብዙ ነገሮች ምሳሌ ሆኖ የሚጠቀሰው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችሉ መሰናክሎች ይታይበታል እየተባለ ይተቻል፡፡ የተማሪዎችና የመምህራን ግንኙነት የሰመረ አይደለም፤ አንዳንድ መምህራን በብቃት ችግር የተተበተቡ በመሆናቸው ዩኒቨርስቲውን የምርምር ምንጭ ለማድረግ አስቸግረዋል የሚል አስተያየት በተደጋጋሚ ይሰማል፡፡

በየነ ወልዴ አስተያየቶቹን ሰብስቦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርን ጠይቋል…

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 5፣ 2011/ በዓይን ጠባሳ ምክንያት የዓይን ብርሃናቸውን ላጡ ከ200 በላይ ዜጎች ከለጋሾች በተገኘ የዓይን ብሌን ብርሃናቸው እንዲመለስ ተደርጓል

በዓይን ጠባሳ ምክንያት የዓይን ብርሃናቸውን ላጡ ከ2 መቶ በላይ ዜጎች ከበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች በተገኘ የዓይን ብሌን ብርሃናቸው እንዲመለስ ተደርጓል ተባለ፡፡ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 5፣ 2011/ የሱዳን የፖለቲካ ተቀናቃኞች በኢትዮጵያ አግባቢነት ለመነጋገር ተስማሙ ተባለ

የሱዳን የፖለቲካ ተቀናቃኞች በኢትዮጵያ አግባቢነት ለመነጋገር ተስማሙ ተባለ፡፡አንተነህ ሀብቴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 5፣ 2011/ የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካጋጠሙ መለስተኛ ችግሮች በስተቀር በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር እወቁልኝ አለ

የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካጋጠሙ መለስተኛ ችግሮች በስተቀር በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር እወቁልኝ አለ፡፡በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 5፣ 2011/ በባህርዳር፣ በሰላምና በፀጥታ ጉዳይና በዲሞክራሲ ምህዳሩን ማስፋት ላይ የሚመክር ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

ውይይቱን የሚመሩት፣ የአማራ ዴሞክራሲየዊ ድርጅት /አዴፓ/ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ሲሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ የፌደራልና የክልል መንግስት ባለስልጣኖች እና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ እየተሳተፉበት ነው፡፡ በክልሉ ምክር ቤት አዳራሽ የሚካሄደው ሕዝባዊ ውይይት፣ ለሁለት ቀናት ይቆያል፡፡ ወሬው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ነው፡፡

እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 5፣ 2011/ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ዘይቶች የአመራረት የጥራት መጓደል እንዳለባቸው ተነገረ

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከውጭ በሚገቡ እና ሀገር ውስጥ በሚመረቱ ዘይቶች ላይ በሙሉ ጥናት ማድረጉን ተናግሯል፡፡በጥናቱም በሀገር ቤት የሚመረቱት ዘይቶች የአመራረት የጥራት መጓደል እንዳለባቸው ታውቋል ተብሏል፡፡የሀገር ውስጦቹ ዘይቶች በውስጣቸው የሚይዙት የአሲድ መጠን መያዝ ከሚገባቸው በእጅጉ የበለጠ መሆኑን የጥናቱን ውጤት ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ተናግረዋል፡፡

በሀገር ቤት የሚመረቱ ዘይቶች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን የሚያመጡ ንጥረ ነገሮችን ከመያዝ አንፃር የተሻሉ ናቸው ቢባሉም በማሸጊያዎቻቸው ላይ ሊኖራቸው የሚገባውን መረጃ በአግባቡ አያካትቱም ተብሏል፡፡ተቆጣጣሪ አካላትም የሀገር ውስጥ ዘይቶችን የአመራረት ሁኔታ ሊከታተሉት ይገባል ተብሏል፡፡ከውጭ ሀገራት የሚገባው የፓልም ዘይት በጥራቱ በኩል የተገኘበት ክፍተት የለም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ይህንኑ ዘይት ለረጅም ጊዜ መጠቀም የኮሌስትሮል መጠንን ይጨምራል፤ በጤና ላይም ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ብለዋል፡፡ይሁንና ወደኛ ሀገር የሚገባው የፓልም ዘይት በዋጋውም በደረጃውም ዝቅ ያለ መሆኑ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

መንግስት የፓልም ዘይቶችን ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት በአመት ከ8 እስከ 9 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚያደርግ ሰምተናል፡፡81 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ የዘይት ፍጆታም በዚሁ በፓልም ዘይት የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡በሁሉም የዘይት ዓይነቶች ላይ በተደረገው ጥናት ከውጭ ሀገራት የሚገቡት ፈሳሽ ዘይቶች የተሻለ ጥራት እንዳላቸው መታወቁ ተነግሯል፡፡ጥናቱ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ቀርቦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አማራጭ መፍትሄ እንዲያቀርብ እየተጠበቀ መሆኑን ከመግለጫው ሰምተናል፡፡

ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers