• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም በተዘጋጀ ሀሰተኛ ሰነድ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የነበረ ልባሽ ጨርቅ በጋላፊ ኬላ ተያዘ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም በተዘጋጀ ሀሰተኛ ሰነድ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ የነበረ ልባሽ ጨርቅ በጋላፊ ኬላ ተያዘ፡፡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጋላፊ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አየለ ለሸገር ሲናገሩ ሰሞኑን በከባድ ጭነት መኪና ላይ ሆኖ በኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ ህጋዊ መስሎ ሊገባ የነበረው 4 ሚሊየን ብር የተገመተ ልባሽ ጨርቅ ነው ብለዋል፡፡

በሀሰተኛ ሰነድ ሊገባ የነበረውን ልባሽ ጨርቅ የጫነው የከባድ መኪናው ሾፌር በቁጥጥር ስር ውሎ በአሳይታ ማረሚያ ቤት ይገኛል ያሉት አቶ ተስፋዬ ልባሽ ጨርቁም እንዲቃጠል ይደረጋል ብለዋል፡፡ በዚሁ ኬላ ላይ በተለያዩ መኪኖች ላይ በተሰራ ሻግ ውስጥ የተደበቁ 4 ሺ 973 የሞባይል ቀፎዎችም ተይዘዋል፤ እነዚህም ንብረቶች ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ናቸው ሲሉ የጋላፊ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አየለ ነግረውናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማክስ ቦይንግ 737 አይሮፕላን ይረከባል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማክስ ቦይንግ 737 አይሮፕላን ይረከባል፡፡እጅግ ዘመናዊ የሆነው ማክስ ቦይንግ 737፣ ዛሬ ከሰዓት በሁዋላ 9፡30 ግድም አዲስ አበባ ይደርሳል ተብሏል፡፡በደመቀ ሥርዓት በሚከናወነው ርክክብ ላይ የቦይንግ ኩባንያ ተወካዮችና የአየር መንገዱ የስራ ሀላፊዎች እንደሚገኙ ተረድተናል፡፡

አፍሪካን በንግድና በቱሪዝም ለማቆራኘት እየሰራ ነው የሚባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ቦይንግ 787 እና 16 ኤር ባስ ኤ 350 አይሮፕላኖች “አዝዣለሁ” ማለቱ ይታወሳል፡፡

እሸቴ አሰፋ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 23፣2010 መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ

ሰኔ 23፣2010 መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ ወሰነ፡፡ ምክር ቤቱ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና ግንቦት 7 የፖለቲካ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረው የሽብርተኝነት ፍረጃ እንዲነሳ የውሳኔ ሐሳብ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲሰረዙ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንዲፀድቅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል፡፡ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ሐሳብም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሐገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እንዲሳተፉ የሚያበረታታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡በተያያዘ ወሬ፣ በደርግ ጊዜ የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ካሳ ከበደ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የኮምንኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተቀብለዋቸዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአሶሳ ከተማ ለተፈጠረው ግጭት ምክንያት ናቸው የተባሉና የማረጋጋቱን ጥረት አስተጓጉለዋል የተባሉ 45 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ሲል ፖሊስ ተናገረ

በአሶሳ ከተማ ለተፈጠረው ግጭት ምክንያት ናቸው የተባሉና የማረጋጋቱን ጥረት አስተጓጉለዋል የተባሉ 45 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ሲል ፖሊስ ተናገረ፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮምሽን የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪው አቶ እንዳለው አገኘ ለሸገር ሲናገሩ በከተማው ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በፌድራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ በሐይማኖት አባቶችና በሐገር ሽማግሌዎች ጥረት የተረጋጋ ቢሆንም የመንግሥት መስሪያ ቤቶችም ሆኑ አገልግሎት መስጪያ ተቋማት ዝግ እንደሆኑ ናቸው ብለዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በተደራጀ እና በተለያዩ መንገዶች ኢኮኖሚያዊ ጫናን ሆን ብለው የሚፈጥሩና ሐገር እንዳይረጋጋ የሚሰሩ ቡድኖችን

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት መረጃ መሰረት፣ በተደራጀ እና በተለያዩ መንገዶች ኢኮኖሚያዊ ጫናን ሆን ብለው የሚፈጥሩና ሐገር እንዳይረጋጋ የሚሰሩ ቡድኖችን ተከታትሎ ለሕግ የሚያቀርብ ኮሚቴ መቋቋሙና ሥራ መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

የቴሌኮም ኔትወርክን ማጥፋት፣ መብራትና ሌሎች አገልግሎቶችን ሆን ብሎ በማቋረጥ እና በመዝጋት አሻጥር የሚፈፅሙ ቡድኖችና ግለሰቦች በኮሚቴው ይመረመራሉ ተብሏል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመጪው ሰኔ 30 ቀን 2010 የስልጣን ጊዜው የሚያበቃውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዲስ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ...

በመጪው ሰኔ 30 ቀን 2010 የስልጣን ጊዜው የሚያበቃውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዲስ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም የከተማዋን ቻርተር አዋጅ እንዲሻሻል ረቂቅ ቀርቦበት ዛሬ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተመክሮበታል፡፡

በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሳይከናወን የቀረውና የስራ ዘመኑ በመጪው ሰኔ 30 ቀን 2010 የሚያበቃው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምርጫ ባለመካሄዱ የምክር ቤቱ ሕጋዊነት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል ተብሏል፡፡የምክር ቤቱና የስራ አስፈፃሚው አካል ሌላ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስም አሁን ባሉት አባላትና አካሄድ መቆየት እንዲችል የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተነግሯል፡፡በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የሚመረጥበትንም ድንጋጌ ማሻሻያ እንዲደረግበት ሀሳብ ተካቶበታል፡፡

ምክትል ከንቲባ የሚመረጠው ከምክር ቤቱ አባል ብቻ መሆን አለበት የሚለው አሰራር ለቦታው ተገቢ የሆነና ብቃት ያለው ሰው ከምክር ቤቱ ውጪ ሊገኝ ስለሚችል ከምክር ቤት አባል ውጪ የሆነ ምክትል ከንቲባ እንዲሾምና ስራውም በአግባቡ እንዲሰራ ረቂቁም ማሻሻያ እንዲደረግበት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቧል ተብሏል፡፡ምክር ቤቱ የተሻሻለውን የከተማ አስተዳደሩም ቻርተር አዋጅ ለማሻሻል የወጣውን ረቂቅ ለዝርዝር እይታ ለሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርጧል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅም ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የመራ ሲሆን የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሥነ ምግባር ግድፈት አግኝቼባቸዋለሁ ባለቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኞች ላይ ያሳለፈውን የስንብት ውሳኔ ለማፅደቅ ምክክር እያደረገ ነው፡፡

ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ በሰመራ ለሚገነባውና ለ20 ሺ ሰዎች የሥራ እድል ይከፍታል ለተባለው የኢንደስትሪ ፓርክ...

“አፋር የሉሲ መገኛ፣ የሰው ዘር መነሻ፣ የኢትዮጵያዊነት አስኳል ነው - የኢትዮጵያን ባንዲራ የአፋር ግመል እንኳ ይለየዋል…” ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት በአፋር፣ ሰመራ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ በሰመራ ለሚገነባውና ለ20 ሺ ሰዎች የሥራ እድል ይከፍታል ለተባለው የኢንደስትሪ ፓርክ የመሰረት ድንጋይ አኑረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ ካሰፈሩት ለመረዳት ችለናል፡፡ የኢንደስትሪ ፓርኩ የሚገነባበት ቦታ 1ሺ ሄክታር ያህል ስፋት እንዳለው ተጠቅሷል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መርካቶ በሚገኘው ታላቁ አንዋር መስጊድ አካባቢ በተነሳው የእሳት አደጋ ከ50 በላይ የንግድ ሱቆች መውደማቸው ተሰማ

በሰው ላይ ግን ጉዳት አልደረሰም ተብሏል፡፡ትናንት እኩለ ሌሊት ሲሆን በተነሳው የእሳት አደጋ የቃጠሎ የደረሰባቸው ሱቆች በመስጊዱ በሴቶች መግቢያ በኩል ልዩ ስሙ ጎንደር በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያሉት መሆናቸው ተነግሯል፡፡ የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ለሸገር እንደተናገረው የእሳት ቃጠሎው ከሌሊቱ 7 ሰዓት ገደማ ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ተኩል ድረስ የዘለቀ ነበር፡፡

ሱቆቹ እንደ ቂቤ ፣ ማር ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች ፣ አልባሳትና ሌሎችም ተቀጣጣይ ነገሮችን የያዙ በመሆናቸው እሳቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት የመከላከል ስራ ባይሰራ ኖሮ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደነበር በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ሰለሞን መኮንን ነግረውናል፡፡ከሌሊቱ 7 ሰዓት ተኩል ጀምሮ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ 15 የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ መኪኖች ፣ 112 የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎችንና 3 አምቡላንስ በማሰማራት አደጋውን ለመቆጣጠር ሲሰራ ማደሩን አቶ ሰለሞን ነግረውናል፡፡
በመጨረሻም ከፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር በመተባበር 50 ሱቆችን ያወደመው እሳት ዛሬ ማለዳ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል፡፡

የአደጋው መንስኤ ገና እየተጠራ ነው ያሉት አቶ ሰለሞን አደጋው ያደረሰው የንብረት ጥፋት መጠንም እየተጠና ነው ብለዋል፡፡አሁንም የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በስፍራው መኖራቸውንና አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡ እምብዛም የሚያሰጋ ነገር ግን የለም ብለውናል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

እልፎችና እፍኞች

የመደመር ቀን፣ የመደመር ትዕይንተ ሕዝብ፣ እልፎችና እፍኞች፣ በተለያየ መንገድ ! የልብ መደመር በአደባባይ ሲታይ - በአንፃሩ…በቅዳሜው ሰልፍ ዙሪያ የተቀናበረውን የ“ወይ አዲስ አበባ” አጠር ያለች ዶክመንተሪ ያዳምጡ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“ምፅዋ ላይ ዎክ ማድረግ የናፈቃችሁ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ በረራ ስለሚጀምር ተዘጋጁ”

“ስትጣሉ በልክ አድርጉት - መታረቅ ስለሚመጣ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በትላንትናው ዕለት በብሄራዊ ቤተመንግሥት ለኤርትራ ልዑካን የተደረገው አቀባበል እጅግ ደማቅ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ መጪው እንቁጣጣሽን አዲስ አበባና አስመራ ስለምናከብር አርቲስቶች ተዘጋጁ ብለዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኦጋዴን የድፍድፍ ነዳጅ ማውጣት ሥራ በይፋ ዛሬ እንደሚጀምር...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ትናንት ፖሊ ጂ ሲ ኤል ከተሰኘው የቻይና የነዳጅ ኩባንያ ወኪሎች ጋር በመሆን በኦጋዴን የድፍድፍ ነዳጅ ማውጣት ሥራ በይፋ ዛሬ እንደሚጀምር ማስታወቃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ሃላፊው አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸው ላይ ካሰፈሩት ለማወቅ ችለናል፡፡
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers