• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ያሉ ዝሆኖች አልተመቻቸውም

በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ያሉ ዝሆኖች አልተመቻቸውም…በመጠለያቸው አካባቢ መኖሪያ ቤቶች መገንባታቸው እና እርሻ መስፋፋቱ ለዝሆኖቹ የሚመች አልሆነም፡፡አልፎ አልፎ የሚያጋጥመው አደንና የደን ጭፍጨፋውም ለዝሆቹ ስጋት ሆኗል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዘንድሮ ክረምት ወርቅ እያሳፈሰ ነው…

“ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት በክረምቱ ምክንያት ወራጅ ውሃ ከሸረሸረው አፈር 17 ኪሎግራም ወርቅ ሲያገኙ፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ሲኞር ዋሻ በተባለ ቦታ 4 ወንዶች ከ21 ኪሎግራም በላይ ወርቅ አግኝተዋል…”

በቤኒሻንጉል ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የዘንድሮው ክረምት ወርቅ ማሳፈስ ጀምሯል ተባለ፡፡
ሸገር ከክልሉ ማስታወቂያ ቢሮ ትላንት እንደሰማው፣ በተለይ በኩምሩክ፣ በመንጌ፣ በሸርቆሌ፣ በዳቡስ ወረጃዎችና በአሶሳ ገመዴ ወንዝ አቅራቢያ ወርቅ የሚታፈስበት ሆኗል ተብሏል፡፡
ሰሞኑን በኩምሩክ ወረዳ ዱርሼታሉ በተባለ ሥፍራ ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት በክረምቱ ምክንያት ወራጅ ውሃ ከሸረሸረው አፈር 17 ኪሎግራም ወርቅ ሲያገኙ፤ ሲኞር ዋሻ በተባለ ቦታ 4 ወንዶች ከ21 ኪሎግራም በላይ ወርቅ አግኝተዋል ተብሏል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የቦምብ ጥቃት ተጎጂዎች መረጃ

እስከዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ቀትር ስድስት ሰዓት ድረስ ያለው የተጎጂዎች ሁኔታ፣
ተጎጂዎች = 156
ሕክምና እየተደረገላቸው ያሉ = 36
አስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ = 4
ካሉበት አስጊ ሁኔታ መሻሻል የታየባቸው = 1
ሞት = 2

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ሰኔ 19፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰበር ወሬ፣አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ በራሳቸው ፍቃድ ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ምክትል ሊቀመንበርነታቸው መልቀቃቸውን ሰምተናል

የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ በራሳቸው ፍቃድ ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ምክትል ሊቀመንበርነታቸው መልቀቃቸውን ሰምተናል፡፡ አቶ ሲራጅ በአቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ተተክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር አድርገው ሾመዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ረዳት ፖሊስ ኮምሽነር ሐሰን ነጋሽ እና አቶ ዘላለም መንግሥቴን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር አድርገው ሾመዋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የጥራት ነገር አሁንም እጅጉን ሊታሰብበት ይገባል

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መሀንዲሶች ማህበር የቦርድ ሊቀመንበርና የሙያው ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ብርሃኑ ግዛው “በኢትዮጵያ ደረጃቸውን ያልጠበቁ እቃዎች ከፍተኛ ጥፋት እያደረሱና ባለሞያውን ሥራ እያስፈቱት ነው” ይላሉ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለፈው በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ከተያዘው የበጀት የገቢ እቅድ ሳይካተት ከ442.4 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቦ ተገኝቷል...

ባለፈው በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ ከተያዘው የበጀት የገቢ እቅድ ሳይካተት ከ442.4 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቦ ተገኝቷል ይላል የፌድራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት፡፡ ይህም ሕግን የጣሰ አሰራር እንደሆነ ተናግሯል፡፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በበኩሉ በበጀት እቅዴ የማካትተው እንደሚሰበሰብ እርግጠኛ የሆንኩበትን ገንዘብ ብቻ ነው ሲል ይከራከራል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በቅርቡ በሐገራችን በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠሩት ግጭቶች በርካቶች ተፈናቅለዋል...

በቅርቡ በሐገራችን በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠሩት ግጭቶች በርካቶች ተፈናቅለዋል፤ የግጭቱ ፈጣሪዎችና መነሻ ምክንያት በምርምራ ተደርሶበታል ተባለ፡፡ ይህን ያለው የኢትየጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽን ነው፡፡ በምርመራ የተደረሰበት ሪፖርት በቅርቡ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ይቀርባል ተብሏል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የዘንድሮው ክረምት ያመጣው ዝናብ ከፍ ያለ በመሆኑ አዲስ አበባን ጨምሮ፣ ደሴና ድሬዳዋ ከተሞች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ተባለ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ዮሐንስ የኋላወርቅ 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የፌዴራል ዳኞች ሥነ-ምግባር የዲሲፕሊን ደንቦች ማሻሻያ ሊደረግባቸው መሆኑን ተናገረ

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የፌዴራል ዳኞች ሥነ-ምግባር የዲሲፕሊን ደንቦች ማሻሻያ ሊደረግባቸው መሆኑን ተናገረ፡፡የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤው በስራ ላይ ያሉትን የፌዴራል ዳኞች የሥነ ምግባር ደንብ እና የዲስፕሊን አቤቱታና ክስ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ለማሻሻል እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡በደንቡ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ እና ተሟልቶ በስራ ላይ እንዲውል ተጨማሪ ሀሳብ ከሚመለከታቸው ጋር ለማሰባሰብ ምክክር ተደርጎበታል ተብሏል፡፡

የፌዴራል ዳኞች ሥነ-ምግባር ደንብ በዳኝነት ስራ እና ከዳኞች ሥነ-ምግባር ግድፈት ጋር በተያያዘ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የዳኞች ሥነ ምግባር መርሆዎች ላይ በመመስረት የሚሰራ ነው ተብሏል፡፡የዳኞችን ግዴታዎች የሚወስንና የሥነ - ምግባር ጉድለት እንዳይፈፀም የሚከላከል የአሰራር መመሪያ በመሆን በስራ ላይ ነው፡፡ አሁን ያሉበትን ችግሮች በማሻሻል ተግባራዊ እንዲሆንም የደምብ ማሻሻያው ይደረጋል መባሉን ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰምተናል፡፡ ሌላው በማሻሻያው ውስጥ የተካተተው የፌዴራል ዳኞች የዲሲፕሊን አቤቱታና ክስ ሥነ-ሥርዓት ደምብ ደግሞ ዳኞች ሀላፊነታቸው በማጓደል የሥነ-ምግባር ጥፋቶች መፈፀማቸው ሲረጋገጥ በህግ የሚጠየቁበት ሲሆን በደል ተፈጽሞብኛ የሚል ግለሰብም በዳኞች ላይ የዲሲፕሊን አቤቱታና ክስ ማቅረብ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በረቂቅ የሥነ-ምግባር ደንቦች ላይ ሊካተቱ የሚገባቸውና የማሻሻያ ሀሳቦች በባለድርሻዎች ተመክሮባቸዋል፡፡የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሥነ-ምግባር ደንብ በ1993 ዓ.ም እንዲሁም የዲሲፕሊን አቤቱታና ክስ ሥነ-ሥርዓት ደግሞ በ1998 ወጥተው እስካሁን በስራ ላይ ያሉ ደንቦች መሆናቸው ከጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰምተናል፡፡

ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ከግልገል ጊቤ አንድ እና ሁለት የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ሐይል በዋናነት የሚያሰራጨው የሰኮሩ ከፍተኛ የሀይል ማከፋፈያ የእሳት አደጋ እንደደረሰበት ተሰማ

ከግልገል ጊቤ አንድ እና ሁለት የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ሐይል በዋናነት የሚያሰራጨው የሰኮሩ ከፍተኛ የሀይል ማከፋፈያ የእሳት አደጋ እንደደረሰበት ተሰማ…የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር የጅማ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ባለሥልጣን እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥረት እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሐይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ምስክር ነጋሽ ለሸገር ተናግረዋል፡፡በዚህም ሳቢያ ጅማ፣ አጋሮ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ቦንጋ እና ሆሳዕናን ጨምሮ በአካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers