• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

አንዳንዴ አያድርስ የሚባለው ነገር ሲደርስ የሕይወት ፈተናው ከአለትም የከበደ ሊሆን ይችላል...

አንዳንዴ አያድርስ የሚባለው ነገር ሲደርስ የሕይወት ፈተናው ከአለትም የከበደ ሊሆን ይችላል፡፡ ሸክሙን ማቅለል የሚቻው በፅናት በመታገልና በመተጋገዝ ቢሆንም የመጀመሪያው ሸክም አቅላይ መሆን ግን ሊከብድ ይችላል፡፡ እነሆ የእናትነት ሕይወት አቅላይ ምሳሌ ሲል ዮሐንስ የኋላወርቅ የአንዲትን እናት ታሪክ ይነግረናል

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ትላንት በተከሰተ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ሲጠፋ በፀጥታ ሐይሎችም ላይ ጉዳት ደርሷል ተባለ

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ትላንት በተከሰተ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ሲጠፋ በፀጥታ ሐይሎችም ላይ ጉዳት ደርሷል ተባለ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያደረጉላቸውን ግብዣ ተከትሎ ነገ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ መሪዎች ነገ በአዲስ አበባ የገፅ ለገፅ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያደረጉላቸውን ግብዣ ተከትሎ ነገ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ መሪዎች ነገ በአዲስ አበባ የገፅ ለገፅ ንግግር ያደርጋሉ ተባለ፡፡ሸገር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት እንደሰማው የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዘዳንት ሳልቫኪርና የዋነኛው አማፂ ቡድን መሪ ዶ/ር ሪያክ ማቻር ነገ በአዲስ አበባ የሚገናኙት ስለ ሰላም ለመነጋገር ነው፡፡

ሁለቱ ተቀናቃኞች በግንባር ተገናኝተው ልዩነታቸውን በማጥበብ ለሰላም እድል ሰጥተው የደቡብ ሱዳናውያን ሞትና እንግልት እንዲያበቃ እንዲወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግብዣ ያቀረቡላቸው በቅርቡ ነበር፡፡

ይሄንኑ ግብዣ ተከትሎም ነገ በአዲስ አበባ የሁለቱ ተቀናቃኞች መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኝተው በደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲወርድ ይወያያሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡የዋነኛው አማፂ ቡድን መሪ ዶ/ር ሪያክ ማቻር ባለፉት 2 አመታት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከቁም እስር ባልተናነሰ ሁኔታ ውስጥ መቆየታቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡ከ4 አመት ከመንፈቅ በላይ ያስቆጠረው የደቡብ ሱዳኑ የእርስ በርስ ጦርነት በ10 ሺ ዎችን የሚቆጠሩ ሰዎችን ጨርሷል፡፡ በሚሊየን የሚቆጠሩትን ደግሞ ለስደትና መፈናቀል ዳርጓቸዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች...

“በኢትዮጵያ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች በአመለካከት ችግር፣ ሕገመንግሥቱን ባለማወቅና ስለሰብዓዊ መብት ባለመረዳት በታራሚዎችና በተጠርጣሪዎች ላይ ያልተገባ አያያዝ ይስተዋላል” የሚሉት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮምሽን ኮምሽነር ዶ/ር አድማሱ ገብረእግዚአብሄር ችግሩ በሁሉም የሐገሪቱ አካባቢዎች የሚታይ ነው ይላሉ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እየወሰዷቸው ላሉ የለውጥ እርምጃዎች ምስጋና እና ድጋፍ ለማቅረብ በአዲስ አበባ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተጠራ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እየወሰዷቸው ላሉ የለውጥ እርምጃዎች ምስጋና እና ድጋፍ ለማቅረብ በአዲስ አበባ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተጠራ፡፡የድጋፍ ሰልፉ የፊታችን ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡

የሰልፉ አስተባባሪዎች ከደቂቃዎች በፊት በኢሌሌ ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል፡፡አስተባባሪዎቹ እንዳሉት የተጀመሩት የለውጥ እርምጃዎች ያለምንም መስተጓጎል እንዲቀጥሉ የድጋፍ ሰልፉ ተጠርቷል፡፡
ሰልፉ ኢትዮጵያዊነት ብቻ የሚንፀባረቅበት መሆኑን ሰምተናል፡፡

በመጪው ቅዳሜ በአዲስ አበባ ይካሄዳል የተባለው የድጋፍ ሰልፍ ተከትሎ በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ ሰልፎች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ለቅዳሜው ሰልፍ ፈቃድ ተጠይቆ ምላሹን እየተጠባበቁ መሆኑን አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሐዋሳ ከተማ

በዛሬው ዕለት በሐዋሳ ከተማ ተገኝተው በከተማዋ እና በአካባቢው በተፈጠሩት ግጭቶች ዙሪያ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት እያደረጉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከቀትር በኋላ በወላይታ ሶዶ ከተማ፣ በነገው ዕለት ደግሞ በወልቂጤ ከተማ በመገኘት ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል…
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ዶ/ር ይናገር ደሴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ሆነው መሾማቸው ተነገረ

ዶ/ር ይናገር አሁን ከተሰጣቸው ሹመት በፊት በተለያዩ የመንግስት ሀላፊነቶች ላይ ሲሰሩ መቆየታቸው ተነግሯል፡፡የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው አገልግለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበራቸው ሀላፊነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ የኢትዮጵያ ሆቴሎች አስተዳደር አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የቦርድ አባል ሆነው ማገልገላቸውም ተነግሯል፡፡ዶ/ር ይናገር ደሴ ለ13 አመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ የነበሩትን አቶ ተክለወልድ አጥናፉን ይተካሉ ተብሏል፡፡

አቶ በቃሉ ዘለቀ ደግሞ ምክትል የብሄራዊ ባንክ ገዢ እንዲሁም የባንኩ ዋና ኢኮኖሚስት ሆነው ተሸሙዋል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ:-በሽብርና በሙስና የታሰሩት ሰዎች ይቅርታ መደረጉን በተመለከተ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትናንት ከሰዓት በኋላ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስስ ንግግር አድርገዋል፡፡ ከምክር ቤቱ እንደራሴዎችም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሸገርም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽና ማብራሪያ በዘውግ በዘውጉ ተመልክቶታል፡፡

በሌላም በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሽብርና በሙስና የታሰሩት ሰዎች ይቅርታ መደረጉን በተመለከተ ከምክር ቤቱ ለቀረበላቸው ጥያቄም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ:- የሀገራችን የህግ ሥርዓት

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትናንት ከሰዓት በኋላ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስስ ንግግር አድርገዋል፡፡ ከምክር ቤቱ እንደራሴዎችም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሸገርም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽና ማብራሪያ በዘውግ በዘውጉ ተመልክቶታል፡፡

የሀገራችን የህግ ሥርዓት በርካታ ክፍተቶች ስላሉበት ከመሰረቱ መለወጥ አለበት የሚል ፅኑ በመንግስት መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናግረዋል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ንጋቱ ረጋሣ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ:-ወደ ግሉ ዘርፍ ይዘዋወራሉ ስለተባሉ ትላልቅ የመንግስት ተቋማት

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትናንት ከሰዓት በኋላ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስስ ንግግር አድርገዋል፡፡ ከምክር ቤቱ እንደራሴዎችም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሸገርም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽና ማብራሪያ በዘውግ በዘውጉ ተመልክቶታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ከሰጡባቸው ጥያቄዎች አንዱ ወደ ግሉ ዘርፍ ይዘዋወራሉ ስለተባሉ ትላልቅ የመንግስት ተቋማት ነው፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ:- የአልጀርሱን ስምምነት በሚመለከት

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትናንት ከሰዓት በኋላ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስስ ንግግር አድርገዋል፡፡ ከምክር ቤቱ እንደራሴዎችም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ሸገርም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽና ማብራሪያ በዘውግ በዘውጉ ተመልክቶታል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአልጀርሱን ስምምነት በሚመለከት የቅርብ ጊዜው የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ውሳኔ ነባር እንጂ አዲስ ጉዳይ እንዳልሆነ ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጡ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.እሸቴ አሰፋ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers