• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የኢትዮጵያ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሁለተኛ ዙር በሥርዓተ ፆታ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በግብርና ልማት

የኢትዮጵያ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሁለተኛ ዙር በሥርዓተ ፆታ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በግብርና ልማት ዘርፍ የምሰራውን ፕሮግራም ልጀምር ነው አለ፡፡

የመጀመሪያውን ዙር ውጤታማ ሆኜበታለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡

ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ ዛሬ የሁለተኛውን ዙር መጀመር አስመልክቶ በድሪምላይነር ሆቴል በጀመረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት በኔፓድ የገንዘብ ድጋፍ በኖርዳ የቴክኒክ እገዛ ተግባራዊ የሆነው ፕሮግራም ውጤታማ ነበር ብለዋል፡፡

ሁለተኛው ዙር ከአንደኛው ከተገኘው ልምድና ተሞክሮ በመነሳት በስድስት ክልሎች፣ በሰላሣ ወረዳዎችና በስድስት ፕሮግራሞች እንሰራዋለን ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

ይሰራባቸዋል የተባሉት ክልሎች አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ትግራይ፣ አፋርና ሶማሌ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 9፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፋይዳ ያላቸውና ተስፋ የሚሰጡ የፈጠራ ስራዎች በመጀመሪያ የሳይንስና ፈጠራ ኤግዚብሽን ላይ ቀረቡ፡፡
 • የውበት እና ንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች አቀማመጣቸው ካላማረ ውጤታቸው የከፋ ይሆናል ተባለ፡፡
 • በገንዘብ ብድር ረገድ ተዘንግተዋል የተባሉ መሐከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከዓለም ባንክ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር አገኙ፡፡
 • የቤንሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ትላንትና አስቸኳይ ጉባኤ በማድረግ አዲስ ፕሬዝዳንት መሾሙ ተሠማ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰይፉ ፋንታሁን በ50 ሺ ብር ዋስ ተፈታ

በዛሬው ዕለት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎች በሥም ማጥፋት ክስ ተመስርቶበት የቀረበው ሰይፉ ፋንታሁን በ50 ሺ ብር ዋስ ከእስር ተፈትቶ ጉዳዩን በውጪ ሆኖ እንዲከታተል ፍርድ ቤቱ ውሣኔ ማስተላለፉን ሰምተናል...
አስተያየት ይፃፉ (3 Comments)

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሀገራዊና ወቅታዊ መረጃዎችን ይፋ የሚያደርገው ህዝቡ ከማህበራዊ ድረ-ገፅ ካገኛቸው በኋላ ነው

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሀገራዊና ወቅታዊ መረጃዎችን ይፋ የሚያደርገው ህዝቡ ከማህበራዊ ድረ-ገፅ ካገኛቸው በኋላ ነው ተባለ…የብዙሃን መገናኛና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቢኖርም ማስፈፀሚያ ደንቦች አለመውጣታቸው መረጃ ለሚነፍጉ የመንግሥት ኃላፊዎች ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸውም ሰምተናል፡፡ የተለያዩ የመንግሥት ፖሊሲዎችን፣ ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መረጃ የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡ ይሁንና ከብሔራዊ ደህንነት ጋር የተገናኘ ሥራ የማይሰሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጭምር መረጃን ምስጢር አድርገው እየያዙ ነው ተብሏል፡፡

ይህም የህዝብን የመረጃ ነፃነት የሚነፍግ ሲሆን ለዚህ ክፍተት ምክንያት የሆነው የመረጃ ነፃነት አዋጅን ለማስፈፀምና መረጃ የሚከለክሉትንም ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ደንብ አዋጁን ተከትሎ አለመውጣቱ መሆኑን ሰምተናል፡፡ ወሬውን የሰማነው ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የባህል ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤትን የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ሲመረምር ተገኝተን ነው፡፡ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተመደቡ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችም ለህብረተሰቡ መረጃ ከመስጠት ይልቅ መሥሪያ ቤቱን የሚያጐሉ መፅሔቶችን በማሣተም ጊዜያቸውን እንደሚያጠፉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አዲስ አበባ ከሚገጥሟት አደጋዎች ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው የእሣት አደጋ ነው

አዲስ አበባ ከሚገጥሟት አደጋዎች ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው የእሣት አደጋ ነው ሲል አንድ ጥናት ተናገረ፤ ተከታዬቹ ደግሞ ጐርፍ፣ የትራፊክ አደጋና የጤና እክል ነው ተብሏል…ይህን የሰማነው ዛሬ የአዲስ አበባ የእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን የአደጋ ተጋላጭነት ጥናቱን ይፋ ሲያደርግ ነው፡፡ የአንድ አመት ጊዜ ወስዷል በተባለው ጥናት 21 የአዲስ አበባ ወረዳዎች ላይ መረጃ ተሰብስቧል፡፡ በጥናቱ ውጤት ለእሣት አደጋ ተጋላጭ የሆነው ጉለሌ ወረዳ 4 ነው ተብሏል፡፡ጨርቆስ ወረዳ 10 ደግሞ በእሣት አደጋ ተጋላጭነቱ በአዲስ አበባ ካሉ ወረዳዎች ሁለተኛውን ይይዛል፡፡

የዓለም ባንክ ወደ 8 መቶ 29 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም 18 ቢሊየን የሚጠጋ ብር አበደረ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 5 የተለያዩ ፕሮጀክቶች መርጃ የሚሆን ወደ 8 መቶ 29 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም 18 ቢሊየን የሚጠጋ ብር አበደረ… ከዚህ በፊትም ከፍተኛውን ብድር የሚወስደው የትራስፖርት ሥርዓቱን ማሻሻል ሲሆን 3 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ነው ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 በታዲያስ አዲስ ፕሮግራም የስም ማጥፋት ክስ የተመሠረተበት ሰይፉ ፋንታሁን ለፍርድ ቤቱ ትላንት ሰጥቶት የነበረው ቃል እንዲሻርለት ጠየቀ

በሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 በታዲያስ አዲስ ፕሮግራም በተላለፈ ዝግጅት የስም ማጥፋት ክስ የተመሠረተበት ሰይፉ ፋንታሁን ለፍርድ ቤቱ ትላንት ሰጥቶት የነበረው ቃል እንዲሻርለት ጠየቀ… ፍርድ ቤቱ ተከሣሽ ትላንት በሰጠው የእምነት ቃል መሠረት የቅጣት ውሣኔ ለመስጠት ይዞት የነበረው ቀጠሮ ቢኖርም በተከሣሽ የቀረበውን መቃወሚያ ተከትሎ አከራክሯል፡፡

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎች የቀረበው ሰይፉ ፋንታሁን የህግ ባለሞያ ሳያማክር በጉዳዩ ብዙ ሊከራከርበት የሚችል ማስረጃ እያለው ፕሮግራሙ ተላልፏል ብሎ በሰጠው ቃል ፍርድ ቤቱ አምኗል ብሎ የጥፋተኝነት ውሣኔ የወሰነበት በመሆኑ ተከሣሹ የሰጠው ቃል አንቀፅ 135 መሠረት እንዲሻርለት ሲል ጠበቃው ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 8፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በሸገር ኤፍ.ኤም 102.1 በታዲያስ አዲስ ፕሮግራም በተላለፈ ዝግጅት የስም ማጥፋት ክስ የተመሠረተበት የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን ለፍርድ ቤቱ ትላንት ሰጥቶት የነበረው ቃል እንዲሻርለት ጠየቀ፡፡
 • የኦሮሚያ ክልል የትራፊክ አደጋ ጨምሯል፤ የትራፊክ ፖሊሶች ህግ ከማስከበር ግላዊ ጥቅማቸውን ማስቀደማቸው አሁንም ያልተፈታ ችግር ነው፤ የኮምኒቲ ፖሊሲንግ መቋቋም ደግሞ ወንጀል እንዲቀንስ አድርጓል ተባለ፡፡
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዲዩቲ ፍሪ እና ሌሎች የማኔጅመንት ሥራዎችን እንዲያከናውንለት ከቱርቬስት ኩባንያ ጋር ስምምነት መፈራረሙ ተነገረ፡፡
 • ለአዲስ አበባ አደጋ መከላከል ሥራ በ9 ሚሊየን ብር ክሬን ተገዛ፡፡
 • የሀገራችን መገናኛ ብዙሃን የህፃናትን የመብት ጉዳይ ቸል ብለውታል ሲል የአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ተናገረ፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች ደግሞ ቢሮው ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ያለው ተባብሮ የመሥራት ፍላጐቱ የወረደ ነው ብለዋል፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በድጐማ ለህብረተሰቡ የሚያቀርባቸው የምግብ ሸቀጦች በድብቅ ለነጋዴዎች እንደሚሸጡ ደርሼበታለሁ

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም መንግሥት በድጐማ ለህብረተሰቡ የሚያቀርባቸው የምግብ ሸቀጦች በድብቅ ለነጋዴዎች እንደሚሸጡ ደርሼበታለሁ አለ… ባለፉት አስር ወራት በ278 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ላይ ቁጥጥር ማድረጉንም ሰምተናል፡፡ በህዝብ የእንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ የሆኑት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ዛሬ የተቋሙን የአስር ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንደሰማነው በድጐማ ለህዝቡ የቀረቡ የምግብ ሸቀጦች በተገቢው መንገድ ለተጠቃሚው እየደረሱ አይደለም፡፡

እንደ ዘይት፣ ስኳር እና የዳቦ ዱቄት ያሉ የምግብ ሸቀጦች አቅርቦት ከህዝቡ ፍላጐት ጋር ተመጣጣኝ አይደለም፤ የቀረቡትም ቢሆን በድብቅ ለነጋዴዎች እንደሚሸጡ በተደረገው ቁጥጥር እንደተደረሰበት ዋና እንባ ጠባቂዋ ተናግረዋል፡፡ መንግሥት በድጐማ ለህዝቡ ያቀረበውን የምግብ ሸቀጥ ለነጋዴው ይሸጣሉ ከተባሉ ክልሎች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የአማራ፣ የኦሮሚያ፣ ጋምቤላና ደቡብ ክልሎች ይገኙበታል፡፡ በህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂዋ እንዳሉት ይህ ወንጀል ስለመፈፀሙ ከሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጐ ችግሮቹ መኖራቸውን አምነዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስማት የተሳናቸው አካል ጉዳተኞች ወደ ጤና ተቋም ሲሄዱ ኃሣባቸውን ለማስረዳት አይቸገሩም

ከእንግዲህ መስማት የተሳናቸው አካል ጉዳተኞች ወደ ጤና ተቋም ሲሄዱ ኃሣባቸውን ለማስረዳት አይቸገሩም ተባለ…የሚናገሩትን የሚያዳምጧቸው እና ለችግራቸውም መላ የሚሰጡ የጤና ባለሞያዎች እና የአስተዳደር ሠራተኞች የምልክት ቋንቋ ሥልጠና ወስደው እየሰሩ ነው ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡በፌዴራል እና በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሥር በሚገኙ ሆስፒታሎች እንዲሁም የጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩ 150 የሚደርሱ ባለሞያዎች የምልክት ቋንቋ ሥልጠናን ወስደው መስማት የተሳናቸውን አካል ጉዳተኞች እያስተናገዱ ነው ሲሉ የነገሩን የሚኒስቴሩ የሴቶች እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክተር ወ/ሮ ያምሮት ዓንዱአለም ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኛ ሬዲዮ ፕሮግራም

በፆታዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረው የኛ ሬዲዮ ፕሮግራምን ከ3 ሚሊየን የሚበልጡ ሰዎች ይከታተሉታል ወደ 9 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ፕሮግራሙን ያውቁታል ተባለ፡፡ ይህን የሰማነው የኛ ሬዲዮ ፕሮግራም ዝግጅቶቼን ምን ያህል ሰው ያደምጠዋል፣ የታሰበለትን ግብ መትቷል ወይ የሚል ጥናቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡ ከጥናቱ እንደተሰማው የኛ ሬዲዮ ዝግጅትን የሚያደምጡ ፆታዊ ጥቃትን እና ያለ እድሜ ጋብቻን የመቃወም አቅማቸው የተሻለ ነው ተብሏል፡፡የወጣት ሴቶች ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚሰራው የኛ የሬዲዮ ፕሮግራም ያለ እድሜ ጋብቻና ፆታዊ ጥቃትን ለማስቀረት አጋዥ እንደሆነም ጥናቱ ተናግሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers