• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በሁሉም ዘርፍ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት እንዲኖር የተስማሚነት ምዘናና አክሪዲቴሽን ሥርዓት በአግባቡ ሊደራጅ ይገባል ተባለ

“አክሪዲቴሽን ደህንነቱ ለተጠበቀ አለም” በሚል ነገ በሀገራችን ለ8ኛ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ13ኛ ጊዜ እንደሚከበርም ሰምተናል፡፡የስራ፣ የምግብ፣ የትራንስፖርት በአጠቃላይ ሁሉም የህዝቡ የጋራ መገልገያዎች ደህንነታቸው የተጠበቁ ሊሆኑ እንደሚገባ የአለም አቀፉ አክሪዲቴሽን መመሪያ ያስቀምጣል፡፡ይህ እንዲሆን ደግሞ ደህንነታቸው በሚመለከተው አካል ሊፈተሽና ተስማሚነታቸው ሊረጋገጥ ይገባል፡፡
ይህን ሥርዓት ለማካሄድ ኢትዮጵያም አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት ከፍታ እየሰራች ነው፡፡

ጽ/ቤቱ ነገ የሚከበረውን በዓል አስመልክቶ አውደ ጥናት እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡በአውደ ጥናቱም በሀገራችን የአካባቢ ደህንነት እንዲሁም ከምግብና መድኃኒት ደህንነት ጋር የተገናኙ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ብሏል፡፡

ገለልተኛ የሆነ የአክሪዲቴሽን ሥርዓት መኖር ለንግዱ ማህበረሰብ እና ለህብረተሰቡ ለእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴ ወሳኝ ነውም ተብሏል፡፡ይህንን ነፃና ገለልተኛ የአክሪዲቴሽን ጅምር በሰፊው ለማረጋገጥ ጽ/ቤቱ እየሰራ እንደሆነ ከላከው መግለጫ ላይ ተመልክተናል፡፡

አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያን የመንግስት ግዢ ሥርዓት በዘመነው የኤሌክትሮኒክስና የኢንተርኔት የግብይት ሥርዓት ለማከናወን ይቻል ዘንድ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው ተባለ

ይህን የተመለከተ አውደ ጥናት ዛሬ በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተዘጋጀ ሲሆን በአውደ ጥናቱ ላይ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጆንሴ ገደፋ እንዳሉት ከሆነ እስካሁን ይህ ሥርዓት ተግባራዊ ሳይሆን ዘግይቷል፡፡ኔትወርክ የለም፣ ሲስተም ተቆራርጧል እየተባለ በሕዝብ ተቋማትና በግብርና መሰል ክፍያዎች ለመፈፀም ችግር በሆነበት ጊዜ እንዲህ ያለውን ግዢ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እንዴት ይታሰባል የሚል ጥያቄ አንስተን ነበር፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ጆንሴ ገደፋ በተደረገው ጥናት ይህን ለማስጀመር ያህል በቂ መሰረተ ልማት መኖሩን አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ በአውደ ጥናቱ ላይ የተለያዩ አገሮች ተሞክሮ የቀረበ ሲሆን ይህ ዘመናዊ የግዢ ሥርዓት ተግባራዊ መሆን ከቻለ ሙስናና ሌብነትን ይቀንሳል፣ ግልፅ የሆነ አሰራርንም ያሰፍናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከተለያዩ የሙያ ማህበራት ጋር በመተባበር መስራት ይኖርበታል ተባለ

ኤጀንሲው አሁን ባለው አደረጃጀት የተሰጠውን ጥራት የማስጠበቅ ሚና እየተወጣ አለመሆኑም ሲነገር ሰምተናል፡፡ኤጀንሲው ዛሬ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች ጋር ባደረገው ውይይት ከአስተያየት ሰጪዎች እንደሰማነው ለትምህርት ጥራት መውረድ የመንግስትን አሰራር ተጠያቂ አድርገዋል፡፡መንግስት ከትምህርት ተደራሽነት ይልቅም ጥራት ላይ እንዲያተኩር ጠይቀዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደግሎቹ ሁሉ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ይህንኑ ሚናውንም በአግባቡ እንዲወጣ ኤጀንሲው ራሱን የቻለ ሆኖ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ከመሆኑ ይልቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመንግስት እምነት ሊጣልባቸው ይገባል ብለዋል፡፡ተቋማቱ እምነት የተነፈጋቸው ስለመሆኑ የህግና መምህርነት ስልጠናዎች እንዳይሰጡ መከልከል እንደማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡ በትምህርት ጥራት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት እንደቀጠለ ነው፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰበር ወሬ፦ጄነራል ሰአረ መኮንንን የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ በጄኔራል ሳሞራ የኑስ ምትክ ጄነራል ሰአረ መኮንንን የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም አድርገው ሾሙ፡፡

በተያያዘ ወሬ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለሐገራቸው የከፈሉትን መስዋዕትነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ቀደም ሲል ማዕረጋቸው ተገፍፎ የነበሩትን የሜጀር ጄነራል ዓለምሸት ደገፋ እና የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ ሙሉ ማዕረግ ተመልሶላቸው የጡረታ መብታቸው እንዲከበር ወስነዋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰበር ወሬ፦ጄኔራል አደም መሐመድ፤አምባሳደር ግርማ ብሩ፤አባዱላ ገመዳ

የኢፌደሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ጄኔራል አደም መሐመድን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ሰምተናል።ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በጥር 26፣2010 ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ወታደራዊ ማዕረጎችን በሰጡበት ወቅት ለሌ/ጀኔራል አደም መሐመድ የጀኔራልነት ማዕረግ መስጠታቸው ይታወሳል።በተያየዘ መረጃ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን የነበሩት አምባሳደር ግርማ ብሩ እና የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አባዱላ ገመዳ ከግንቦት 30፣2010 ጀምሮ በጡረታ መሰናበታቸውን ሰምተናል።
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ ባለፉት 2 ዓመታት የምጣኔ ሐብት እድገት ተመዝግቧል ቢባልም 20 ሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በድህነት ውስጥ የሚገኙ ናቸው ተባለ

ይህን የሰማነው ዛሬ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የቀረበውን የ2011 በጀት አመት መግለጫ ሲያደምጥ ነው፡፡ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት 2 ዓመታት በኢትዮጵያ ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት በምጣኔ ሀብትና ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ተፅህኖ አሳድሯል ብለሏል፡፡
 
በከተሞች ያለ የስራ አጥነት ምጣኔም 16 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ መመዝገቡና አሁንም 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በድህነት ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው በድህነት ቅነሳ ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ተብሏል፡፡በተያዘው የ2010 በጀት አመት የዋጋ ንረቱ በሁለት አሃዝ የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከምግብ ሸቀጦች መወደድ ጋር ተያይዞ የተከሰተ እና በአገሪቱ የነበረው የፀጥታ መደፍረስና የወጪ ንግድ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ እንዲሁም የውጪ ምንዛሬ እጥረት ማጋጠሙ ተፅህኖ አሳድሯል ሲሉ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
  
የ2011 የፌዴራል መንግስት በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር እንዲሆንም ለምክር ቤቱ ረቂቁ ቀርቧል፡፡የታቀደው ገቢና የቀረበው የወጪ በጀት የ59 ነጥብ 3 ቢሊየን የበጀት ጉድለት የሚታይበት በመሆኑ ጉድለቱ ከአገር ውስጥ በሚገኝ ብድር እንዲሸፈን እቅድ ተይዟልም ተብሏል፡፡የምክር ቤቱ አባላት በቀረበው የ2011 በጀት አመት የበጀት መግለጫ ረቂቅ ላይ ሀሳባቸውን እየሰጡ ነው፡፡
 
ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በዘንድሮው በጀት ዓመት ከታክስ ገቢ ከሃምሳ ቢሊየን ብር በላይ ሳይሰበሰብ ሊቀር ይችላል ተባለ

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በ2011 የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት አድርጓል።የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም ተከሰተ ስለ ረቂቅ በጀት በምክር ቤቱ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
በመንግስት በጀት አፈጻጸም ረገድ በ2010 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የነበረውን የታክስ አሰባሰብም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።እሳቸው እንዳሉት በጠዘኝ ወራቱ ከታክስ ፤ ታከስ ካልሆኑ ገቢዎችና ከውጭ ቀጥታ በጀት ድጋፍ 140 ቢሊየን ብር የፌዴራል መንግስት ገቢ ተሰብስቧል።
 
የተሰበሰበው ገቢ ለአጠቃላይ የበጀት ዓመቱ ከተያዘው ዕቅድ 58 ነጥብ 8 በመቶ ነው ብለዋል።አፈጻጸሙ ከባለፉት ዓመታት በተለየ ሁኔታ እጅግ ደካማ እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።ከሃምሳ ቢሊየን ብር በላይ ታክስ ሳይሰበሰብ ሊቀር ይችላልም ብለዋል፤እንደ ዶክተር አብረሃም - የታክስ አሰባሰቡ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን በመንግስት ወጪ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል፤የወጪ ንግድ አፈጻጸምም በዓመቱ መሰረታዊ ለውጥ አለማሳየቱን ተናግረዋል።
 
ለ2011 የተያዘው የታክስ ገቢ ግምት ከ2010 ጋግ ሲነጻጸር በጣም የተለጠጠ እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፤ዕቅዱ የታክስ አስተዳደሩን በልዩ ሁኔታ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።ግብር ከፋዮችም ለበጀት ዓመቱ የተያዘው የታክስ ገቢ ተሟልቶ እንዲሰበሰብ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፤የ2011 አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር እንዲሆን በረቂቁ ቀርቧል።
 
ከ2010 በጀት ዓመት በ12 ነጥብ 1 ብልጫ ያለው እንደሆነም ተነግሯል።ከበጀቱ 91 ነጥብ 7 ቢሊየን ብሩ ለመደበኛ ወጪዎች የተያዘ ሲሆን ፤ ለካፒታል ወጪዎች ደግሞ ብር 113 ነጥብ 6 ቢሊየን ተይዟል።ለክልል መንግስታት ድጋፍም 135 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የተመደበ ሲሆን ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያም ስድስት ቢሊየን ብር ተመድቧል።
 
ከአጠቃላይ የ2011 መደበኛ እና ካፒታል በጀት ውስጥ 66 በመቶው ለትምህርት ፤ መንገድ ፤ ግብርናና ገጠር ልማት ውሃ ፤ ጤና ፤ ኢንዱስትሪ ፤ ከተማ ልማት ፤ የከተማ ምግብ ዋስትና እና ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራሞች የተመደበ መሆኑ ተነግሯል።
 
በአጠቃላይ በ2011 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ከሀገር ውስጥ የገቢ ምንጮች ፤እንዲሁም ከውጪ ዕርዳታ እና ብድር 287 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር -ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ሚኒስትሩ ዶክተር አብረሃም ተናግረዋል፤በታቀደው የፌዴራል ገቢ እና የወጪ በጀት መካከል የብር 59 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ጉድለት አለ ብለዋል፤ጉድለቱን ከሀገር ውስጥ ከሚገኝ ብድር ለመሸፈን መታሰቡን ተናግረዋል፤የሀገር ውስጥ ብድር መጠኑ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንፃር 2 ነጥብ 3 በመቶ ነው ተብሏል።
 
ንጋቱ ረጋሣ
 
 
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ውሳኔው ሰላም እንደሚያመጣ ምን ማረጋገጫ አለ?

ኢትዮጵያስ፣ እስከዛሬ እንደራደር የሚለውን አቋሟን ርግፍ አድርጋ መተዋ በጊዜው ለደረሰው ጉዳትና በተወረሱ ንብረቶች የቀረበው የካሳ ጥያቄና የወደፊቱ ግንኙነት ላይ እንዴት እንደሚመለስ ከአስመራ ምን የተጨበጠ ግምት ወስዶ ነው ይህ እርምጃ መወሰዱ ይለናል ይህ ትንታኔ፡፡

እንደስጋት ተቆጥሮ ኢትዮጵያ ባቀረበችው የድርድር ነጥቦች ላይ ትኩረት ሰጥታ የቆየችበት የባድመ እና የአካበቢው ነዋሪዎች በአፈፃፀሙ ከመልካም ተስፋ የዘለለ ምን የተጨበጠ ነገር ይዟል የሚሉ ጥያቄዎችም እየፈለቁ ነው…

ውድ የሸገር ቤተሰቦች፣ ማራኪ የአሁን እንዲሁም ቆየት ያሉ ፕሮግራሞቻችንን በYouTube ቻናላችን ማዳመጥ እንድትችሉ በቀላሉ ሊንኩን በመጫን Subscribe ያድርጉ እናመሰግናለን።

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት መሰናዶ ግንቦት 28፣2010

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮ ቴሌኮምና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሉ መንግስታዊ የልማት ተቋማት የግሉ ዘርፍ ድርሻ ይኑረው መባሉ

እንደ ኢትዮ ቴሌኮምና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሉ መንግስታዊ የልማት ተቋማት የግሉ ዘርፍ ድርሻ ይኑረው መባሉ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ታዋቂ ምጣኔ ሐብታዊ አከናዋኝ የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የአሁኑ የሕብረት ባንክ ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም የሕብረት ኢንሹራንስ አማካሪ  አቶ እየሱስወርቅ ዛፋ ተናገሩ::

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ወተትና የወተት ተዋፅኦ የምናገኝበት ዋነኛው መንገድ ያው እንደዱሮው እነላሜ ቦራን እያረቡ በሚያልቡት መሆኑ ተረጋግጧል

በፋብሪካ ተመርቶ የሚሸጠው ወተት በገበያው ያለው ድርሻ ጥቂት ነው፡፡ የወተት ፋብሪካ ምርት መቀዝቀዝ ደግሞ አነስተኛውን ገበሬ መልሶ ይጎዳል የተጠቃሚውንም ቁጥር ያሳንሰዋ ይባላል፡፡

{audio}/liyuwere/Nigatu_Regassa_Milik_And_ Milik_product_demand_And_ Supply_in_Ethiopia_Ginbot_24_2010.mp3{/audio]

ንጋቱ ረጋሣ 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers