• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች አዳዲስ ምርምርና ፈጠራ አድርገዋል የተባሉ 140 ሰዎች ዘንድሮ ይሸለማሉ ተባለ

ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች አዳዲስ ምርምርና ፈጠራ አድርገዋል የተባሉ 140 ሰዎች ዘንድሮ ይሸለማሉ ተባለ፡፡

እንዲህ የተባለው ዛሬ በተጀመረውና የፊታችን ቅዳሜ በሚጠናቀቀው 7ተኛ አገር አቀፍ የሣይንሰና ቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን ሽልማት መክፈቻ ላይ ነው፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትር ደመቀ መኮንን ፕሮግራሙ ዛሬ የተከፈተ ሲሆን እስከ ነገ በተለያዩ ውይይቶች ይቀጥላል፡፡

በሣይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጊቢ ውስጥም አዳዲስ ፈጠራዎች ዛሬ ለእይታ የቀረቡ ሲሆን በባትሪና በፀሐይ ብርሃን የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችም ለእይታ በቅተዋል፡፡

ከነገ በስቲያ ቅዳሜ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ለፈጠራ ባለሙያዎቹ ሽልማት ይበረከትላቸዋል መባሉን ሰምተናል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት የሚታየውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል የአውቶቡሶቹን ስምሪት ማሸጋሸጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተናገረ

የትራንስፖርት እጥረቱ የባሰባቸውን 24 ቦታዎች ለይቶ ድጋፍ ሰጭ አውቶቡሶችን ጨምሮ የአንበሣና ሸገር አውቶቡሶችን የትራንስፖርት እጥረት ከሌለበት አካባቢ እጥረቱ ወደ ባሰበት አካባቢ የማሸጋሸግ ሥራ መሥራቱን በባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰለሞን ጀርመን ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የአንበሣ አውቶቡስ አገልግሎት ይሰጥባቸው የነበሩና አገልግሎቶቹ ተቋርጦባቸው የነበሩ መስመሮችም ተለይተዋል፡፡ከመካከላቸውም ከፒያሳ ጐላጐልና ከጐሮ መገናኛ የአንበሣ አውቶቡስ ዳግም የተመደበ ሲሆን ከፒያሳ መገናኛም የሸገር አውቶቡስ አገልግሎት እንዲሰጥ መመደቡን ሰምተናል፡፡

የሚዞሩበትን ቦታ የማሻሻልና የሚሄዱበትን አቅጣጫ እንዲቀይሩ የተደረጉ አውቶቡሶች መኖራቸውንም አቶ ሰለሞን ነግረውናል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት እጥረት መንስኤውን ለማጥናትና መፍትሔም ለማበጀት በባለሥልጣኑ የሚመራ የማዘዣ ማዕከል /ኮማንድ ፖስት/ መቋቋሙን ሰምተናል፡፡

የከተማዋን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት እስካሁን የተለያዩ እርምጃዎች ቢወሰዱም ችግሩ ግን አሁንም እንዳለ ነው፡፡በመጭው ጊዜ ሥራ ይጀምራሉ የተባሉ የአሊያንስ አውቶቡሶች በመጠኑም ቢሆን ችግሩን ያቃልላሉ ተብሎ ተስፋ መደረጉን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

ትዕግሥት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 8፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ አሜሪካን ግቢ ለመልሶ ማልማት የሚዘጋጀው ቦታ እስከዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ይፀዳል ተባለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • የኢትዮጵያን ልዩ ቡና ስያሜ እና የንግድ ምልክት በብራዚል እና በአውስትራሊያ ለማስመዝገብ የተጀመረው ጥረት ዳር አለመድረሱ ተሠማ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • በአዲስ አበባ በሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት የሚፈጠረውን የመጓጓዣ እጥረት ለማቃለል የአውቶቡሶች ሥምሪት ሽግሽግ ተደረገ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የፖስታ አገልግሎት ድርጀት ተግባራቴን በዘመናዊ ቴክኖሎጅና አሰራር በመደገፌ ደረጃዬ ከፍ አለልኝ እያለ ነው፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት አጋጥመው የነበሩ ችግሮችን አጣርቶ ለህዝብ እንደራሴዎች እንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የሞሮኮው ንጉስ ሞሃመድ ስድስተኛ ከነገ ጀምሮ ኢትዮጵያን ይጐበኛሉ ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች አዳዲስ ምርምርና ፈጣራ አድርገዋል የተባሉ 140 ሰዎች ዘንድሮ ይሸለማሉ ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የቃሊቲን የፍሳሽ ማስፋፊያ ፕሮጀክት የማጣሪያ ጣቢያ የፍሳሽ መያዝ አቅም ከፍ ለማደረግ ከአለም ባንክ በተገኘ 100 ሚልዮን ዶላር ሥራው እየተከናወነ ነው ተባለ

የ21 የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ሳይቶችን ፍሳሽም ወደ ማጣሪያ ለማድረስ መንግሥት 82 ሚሊዮን ብር መመደቡን ሰምተናል፡፡የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ሱሌማን ጠይብ ለሸገር ሲናገሩ የቃሊቲ የፍሳሽ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በቀን 75 ሺህ ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የሚጣራበት ሲሆን ከአለም ባንክ በተገኘው 100 ሚሊዮን ዶላር ብድር የማጣራት አቅሙን 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ለማድረስ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ካሉ 21 የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ሳይቶች በመፀዳጃ ቤት መሙላት የተነሳ ብክለት ገጠመን የሚሉ አቤቱታዎች ይሰሙ ነበር የእነሱን ችግር ለማስወገድም ከአዲስ አበባ መስተዳደር 82 ሚልዮን ብር ተመድቧል በቅርቡም 16 ኪሎ ሜትር መስመር በመዘርጋት የመፀዳጃ ቤቶቹ ፍሳሾች ወደ ማጣሪያ እንዲሄድ ይደረጋል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ጨፌ አንድ እና ጨፌ ሁለት የፍሳሽ ማጣሪያዎች እያንዳንዳቸው 12 ሺህ 500 ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ እያጣሩ እንደሚገኙም አቶ ሱሌማን ነግረውናል፡፡

መኮንን ወልደአረጋይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ የሚገኘው የፋንታ የመካነ ቅርስ ሥፍራ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም ተባለ

መካነ ቅርሱ አገልግሎት ካለመስጠቱም በተጨማሪ ለጉዳት እየተዳረገ መሆኑን የነገሩን አቶ በኃይሉ ካሣ የክፍለ ከተማው የቱሪዝም ቅርስ ልማት አስተዳደር የሥራ ሂደት ባለቤት ናቸው፡፡በክፍለ ከተማው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤትና በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ ፋንታ ወንዝ አቅራቢያ ሁለት ሚሊዮን አመት ያስቆጠሩ የእንስሣት ቅሪተ አካልና የድንጋይ መሣሪያዎች መገኘታቸውን አቶ በኃይሉ አስታውሰዋል፡፡መካነ ቅርሱ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ የድንጋይ ማምረትና የአርሻ ሥራ እየተከናወነበት እንደሚገኝ አቶ በኃይሉ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የከተማዋ የቅርስ ጥበቃና ጥናት ኬዝ ቲም ጉዳዩን ያውቀው አንደሆነ ከሸገር ለቀረበለት ጥያቄ ሥፍራው መመዝገቡንና እጅግ አደገኛ ሁኔታ ላይ መገኘቱን አረጋግጧል፡፡ከ6 ዓመታት በፊት ባለሙያዎች ሥፍራው መካነ ቅርስነቱን እንዳያጣ በአካባቢው በአስቸኳይ የእርሻና የግንባታ ሥራዎች አንዲቆሙ በመረጃ መረብ አማካኝነት አሳስበው ነበር ተብሏል፡፡

ይህ የመካነ ቅርሥ ሥፍራ ለታዋቂው የኢትዮጵያ የመካነ ቅርስ ሥፍራ መልካ ቁንጥሬ 40 ኪሎ ሜትር ይቀርባል፡፡ከዚሁ አካባቢ የተገኙ የቅሪተ አካሎች ክፍል፣ አጥንት፣ መንጋጋ፣ ስብርባሪ የእንስሣት አካል ክፍሎች ናሙናዎች በብሔራዊ ሙዚየም እንደሚገኙ ሰምተናል፡፡

መኮንን ወልደአረጋይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በቅርቡ የገቡት 100ዎቹ የአልያንስ አውቶቡሶች በዚህ ወር መጨረሻ ሥራ ይጀምራሉ ተባለ…

ንብረትነታቸው የአሊያንስ ትራንስፖርት ሰርቪስስ አክሲዮን ማህበር የሆኑትና የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት ችግር ለማቃለል ሚና ይኖራቸዋል የተባሉት አውቶቡሶች ታርጋ እየተሰጣቸው መሆኑን ሰምተናል፡፡በከተማዋ የትራንስፖርት ችግሩ ብሶባቸዋል የተባሉትን ቦታዎች ለይቶ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ባለሥልጣን አገልግሎት የሚሰጡበትን ቦታ ይመድባልም ተብሏል፡፡

ከ2 ሚልዮን ብር በላይ የወጣባቸው አውቶቡሶቹ የስምሪት ቦታቸው ተደልድሎ ሲያልቅና ታርጋ ከለጠፉ በኋላ በያዝነው ወር መጨረሻ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ይግዛው ዳኘው እንዳሉት በመጪዎቹ አራት ወራት ተጨማሪዎቹ 200 የአሊያንስ አውቶቡሶች ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኀዳር 7፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

 • ተማሪዎችና የጦር ባልደረቦች ገበሬውን በሰብል ስብሰባ እንዲያግዙ ተጠየቁ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ካለጊዜያቸው ተወልደው አስፈላጊውን እንክብካቤ ያላገኙ ህፃናት ግዜያቸውን ጠብቀው ከሚለወለዱት የበለጠ ለሳንባ ምች፣ ለልብ፣ ለመስማትና ለማየት ችግሮች የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ተነገረ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በአዲስ አበባ የቃሊቲ የፍሳሽ ማጣሪያ የማስፋፊያ ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የዜጐች የውጭ አገራት የሥራ ሥምሪት መብት፣ ደህንነትና ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ ሁኔታዎች እስኪመቻቹ ይጠበቃል ተባለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ወደ ውጭ ከላከቻቸው የኤሌክትሪክና ተዛማጅ መሣሪያዎች ሽያጭ ከ9 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች ተባለ፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • በቅርቡ የገቡት 100ዎቹ የአልያንስ አውቶቡሶች በዚህ ወር መጨረሻ ሥራ ይጀምራሉ ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኅዳር 5፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • አንድ የፌዴራል ፖሊስ ትላንት ከምሽቱ 2 ሰዓት በአዲስ አበባ አንድ ሰው መግደሉ እና ራሱንም ማጥፋቱ ተሰማ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • የሙዚቀኛ ሙሉጌታ አባተ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በኢትዮጵያ የስኳር ህሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የሞጆ ደረቅ ወደብ እንደበፊቱ አይምሰላችሁ፤ ወደቡን ብላችሁ የምትመጡ ተሽከርካሪዎች አሁን ወረፋ የለባችሁም ተብላችኋል፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • የንግድና ማህበራዊ ተቋሞች ወጣቱን በሚፈለገው ደረጃ ተጠቃሚ አላደረጉም ተባለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ፍላኮን ኮች ትራንስፖርቴሽን የአገር አቋራጭ የትራንስፖርት እጥረት አለባቸው በተባሉ ቦታዎች አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ አለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በአዲስ አበባ መንገዶች ግራና ቀኝ ለረጅም ሰዓታት የሚቆሙ፣ የሚውሉና የሚያድሩ ተሽከርካሪዎች የትራፊክ ወዲህ ወዲያውን እያስተጓጐሉት ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ውሃን መጠቀም ብቻ ሳይሆን ከተጠቀሙም በኋላ መልቀቁ ክፍያ ሊጠየቅበት ነው፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በአዲስ አበባ ባለፈው ዓመት በህገ-ወጥ የንግድ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ 160 ሺህ ያህል ነጋዴዎች ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ሠራተኞች አልከርምልህ ብለውኝ ተቸግሬያለሁ አለ

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ሠራተኞች አልከርምልህ ብለውኝ ተቸግሬያለሁ አለ፡፡ኤጀንሲው እንዳለው ሠራተኞቹ የተሻለ ደመወዝ ወደሚያገኙባቸው ሌሎች ድርጅቶች ጥለውት እየሄዱ ነው፡፡በሦስት ወር ጊዜ ውሰጥ ብቻ አርባ ስምንት ሠራተኞች ኤጀንሲውን እንደለቀቁም ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ሠራተኞች በተመሳሳይ ምክንያት ጥለውኝ ይሄዳሉ ብዬ ሰግቻለሁም ብሏል ኤጀንሲው፡፡ኤጀንሲው እንዲህ ሠራተኞች በብዛት እየለቀቁበትም ባለፉት ሦስት ወራት ጥሩ እንደሰራ ኤጀንሲው ተናግሯል፡፡በሦስት ወሩ ከ390 በላይ የግል ድርጅቶች ማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራም እንዲታቀፉ ማድረጉን እወቁልኝ ብሏል፡፡በዚህ ፕሮግራም የተካተቱ አጠቃላይ የግል ድርጅቶች ብዛት ደግሞ 16 ሺህ 500 ደርሰዋል ተብሏል፡፡

ከ38 ሺህ የሚልቁ የግል ድርጅቶች ሠራተኞችም በሦስት ወሩ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ሽፋን ማግኘታቸው ተሰምቷል፡፡በአጠቃላይ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ከ157 ሺህ የበለጡ ሲሆን 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ከግል ድርጅቶች የጡረታ ክፍያ እንደሰበሰበም ከኤጀንሲው ሰምተናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከደረጃ ሃሌታ “ሀ” ግብር ከፋዮች ለመሰብሰብ ካቀድኩት 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የቻልኩት 51 በመቶውን ብቻ ነው አለ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከደረጃ ሃሌታ “ሀ” ግብር ከፋዮች ለመሰብሰብ ካቀድኩት 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የቻልኩት 51 በመቶውን ብቻ ነው አለ፡፡

እስከ ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ ግብራቸውን ማሳወቅ ከሚጠበቅባቸው የደረጃ ሃሌታ “ሀ” ግብር ከፋዮች መካከል የከፈሉት 60 በመቶ ያህሉ ብቻ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ ተናግሯል፡፡

ባለሥልኑ ለሸገር እንደተናገረው በጥቅምት ወር ብቻ ከደረጃ ሃሌታ “ሀ” ግብር ከፋዮች 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ወጥኖ ነበር፡፡ ይሁንና የሰበሰበው 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ብቻ ሲሆን ይህም የእቅዱን 51 በመቶ ብቻ ማለት ነው፡፡

ለደረጃ ሃሌታ “ሀ” ግብር ከፋዮች ዛሬ የመጨረሻው የግብር ማሳወቂያ ቀን ነው፡፡

በመሆኑም ያልከፈሉ 40 በመቶ ግብር ከፋዮችን ለማስተናገድ ግብር በሚሰበሰብባቸው 14 ቅርንጫፎች ዛሬ ከስራ ሰዓት በተጨማሪ በምሽት አገልግሎት እንደሚሰጥ ባለሥልጣኑ እወቁልኝ ብሏል፡፡

በአመቱ የንግድ እንቅስቃሴ ከስረናል ያሉና ምንም አይነት የሥራ እንቅስቃሴ አልነበረንም ብለው ሪፖርት ያደረጉ ነጋዴዎች ላይም የሒሳብ ምርመራ እንደሚደረግ ሰምተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 30፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በእርግዝናና ወሊድ እንዲሁም በትራፊክ አደጋ የደም ፍላጐት እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ብዙዎች የሀገራችን አርቲስቶች የሚያሰሙትን እሮሮ ያስቀራል፤ የቅጂና ተዛማጅ መብታቸውን በማስከበር ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል የተባለለት ቴክኖሎጂ ተዋወቀ፡፡ (ምስክር አወል)
 • የእንቦጫን አረም ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ከጐረቤት ሀገሮች ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከደረጃ ሃሌታ “ሀ” ግብር ከፋዮች ለመሰብሰብ ካቀድኩት 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የቻልኩት 51 በመቶውን ብቻ ነው አለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ሠራተኞች አልከርምልህ ብለውኝ ተቸግሬያለሁ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሳ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers