• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ጥቅምት 29፣2009

ክፍል አስራ ሁለት

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአፍሪካ በአጉል እምነቶች፣ በአካል ጉዳትና በሌሎችም ምክንያት ህፃናት ላይ የሚደርሱ ወንጀሎችና የመብት ጥሰቶች በርክተዋል ተባለ

በአፍሪካ በአጉል እምነቶች፣ በአካል ጉዳትና በሌሎችም ምክንያት ህፃናት ላይ የሚደርሱ ወንጀሎችና የመብት ጥሰቶች በርክተዋል ተባለ፡፡ዛሬ በአፍሪካ የህፃናት ፎረም አዘጋጅነት በተባበሩት መንግሥታት የስብሰባ ማዕከል ለ7ተኛ ጊዜ የተዘጋጀው አለም አቀፍ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው፡፡

የአህጉሪቱ ህፃናት ለከፍተኛ የመብት ጥሰቶች እና ወንጀሎች የተጋለጡ ናቸውም ተብሏል፡፡አልቢኒዝም ወይም የቆዳ ቀለም ንጣት፣ በተለያዩ የአካል ጉዳቶችና በአጓጉል እምነቶች ሰበብ ህፃናቱን በመስዋትነት ማቅረብ በኮንፍረንሱ ከተነሱ ወንጀሎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በኮንፍረንሱ ከሴራሊዮን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ኡጋንዳ፣ ማሊ፣ ሌሴቶና ኮንጐ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ አገራት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡በውይይቱ የተገኙ የሀይማኖት መሪዎችም በህፃናቱ ላይ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችና ወንጀሎች ከማንኛውም የሀይማኖት አስተምህሮት ውጪ የሆኑ ናቸው ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ዘንድሮ በሦስት ወሮች ውስጥ ሁለት ሺህ ኪሎ ግራም ገደማ ወርቅ በባለፈቃዶች ለማምረት ቢታቀድም ማምረት የተቻለው 870 ኪሎ ግራም ወርቅ ብቻ ነው ተባለ

ዘንድሮ በሦስት ወሮች ውስጥ ሁለት ሺህ ኪሎ ግራም ገደማ ወርቅ በባለፈቃዶች ለማምረት ቢታቀድም ማምረት የተቻለው 870 ኪሎ ግራም ወርቅ ብቻ ነው ተባለ፡፡ይህም ካለፈው ሩብ አመት ጋር ሲነፃፀር በ519 ኪሎ ግራም ያነሰ ነው ተብሏል፡፡መቶዎች ሲሰላም 45 በመቶ ገደማ ብቻ መሆኑንም ከማዕድን የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የሩብ አመት የሥራ ክንውን ሪፖርት ተመልክተናል፡፡

የወርቅ ምርት ሊቀንስ የቻለው በአለም ዋጋ መቀነስና በወቅቱ በኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ ነው ተብሏል፡፡ከወርቅም በተጨማሪ ታንታላይት ኮንሰንትሬት ማዕድንም ከታሰበው በታች የተመረተ ሲሆን ለዚህም ምክንያት የተባለውም ይህን ማዕድን ያመርታል የተባለው ኩባንያ ወደ ሌላ ኩባንያ በመተላለፉ እና ኩባንያው በአዲስ መልኩ ለማምረት በዝግጅት ላይ በመሆኑ ነው፡፡

በሩብ ዓመቱ ሶዳ አሽ፣ ጨው እና ላይምስቶን ምርቶች ከታቀደውም በላይ የተመረቱ መሆናቸውን በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያን ምርቶችና አገልግሎቶች የሚያስተዋውቅ አለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ከፊታችን ሐሙሰ አንስቶ ለአምስት ቀናት ሊካሄድ ነው

የኢትዮጵያን ምርቶችና አገልግሎቶች የሚያስተዋውቅ አለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ከፊታችን ሐሙሰ አንስቶ ለአምስት ቀናት ሊካሄድ ነው፡፡የንግድ ትርዒቱ የሚካሄደው “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ቃል እንደሆነም ተነግሯል፡፡ከአንድ መቶ ስልሣ በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎች እስካሁን በዚህ የንግድ ትርዒት ለመሣተፍ ተመዝግበዋል ተብሏል፡፡

መረጃውን የሰማነው የንግድ ትርዒቱን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ ተገኝተን ነው፡፡በንግድ ትርዒቱ ላይ የሀገራችን የማኑፋክቸሪንግና ሌሎች የልማት ዘርፎች ጠቃሚ ናቸው የተባሉ ቴክኖሎጂዎች እንደሚቀርቡበት ተነግሯል፡፡

ለተሳታፊዎች የገበያ ትስስር፣ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ልውውጥም እድል ይከፍታል ተብሏል፡፡እንዲህ አይነቱ የንግድ ትርዒት ሲዘጋጅ የዘንድሮው ለዘጠነኛ ጊዜ እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡በንግድ ትርዒቱ ላይ የንግድ ማህበረሰብ አባላት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኙበታልም ነው የተባለው፡፡

ከአለም አቀፉ የንግድ ትርዒቱ ጐን ለጐን የንግድ በንግድ መድረክና የተሣታፊዎች ምሽትም ይኖራል ተብሏል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአረብ ሃገሮች ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ያለባቸው የመልካም አስተዳዳር ችግር ለዜጐች ግፍና በደል መበርታት አንዱ ምክንያት ነው ተባለ፡

በአረብ ሃገሮች ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ያለባቸው የመልካም አስተዳዳር ችግር ለዜጐች ግፍና በደል መበርታት አንዱ ምክንያት ነው ተባለ፡፡እንዲህ ያለው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ሲሆን ችግሮቹን ለመፍታትም የመፍትሔ ኃሳቦችን ለውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አቅርቤያለሁ ብሏል፡፡

ከሌላው አለም በተለየ በአረብ ሃገር ያሉ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ በደል እንደሚደርስባቸው ያስታወሰው ማህበሩ የሰሩበትን ገንዘብ መከልከል፣ ፓስፖርታቸውን መነጠቅና ሌሎችም አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ሰለባ ከመሆን በተጨማሪ እስከ ሞት የሚያደርስ በደል እንደሚደርስባቸው ማህበሩ በአካል ሄዶ መመልከቱን ተናግሯል፡፡

በነበረው ጉብኝት ኢትዮጵያውያንም ከኢትዮጵያ ኤምባሲና ከአሰሪዎቻቸው ጋር የተያያዙ ችግሮቻቸውን በዝርዝር ነግረዋቸው እንደተመለሱ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብርሃም ስዩም ለሸገር ተናግረዋል፡፡ከሌላው ዲያስፖራ የተለየ ትኩረት የሚሹና ብዙ መፈታት ያለባቸው ችግሮች ያሉባቸው የአረብ ሃገር ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸው ያሉት አቶ አብርሃም በጉብኝቱ ወቅት ማህበሩ ከኢትዮጵያውያኑ ያያቸውንና የሰማቸውን ችግሮች ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት አድርገናል የመፍትሔ ኃሳቦችንም አቅርበናል፡፡

በአካል ተገናኝቶ ለመምከርና ለውጥ ለማምጣት ግን ገና በቀጠሮ ላይ ነን ብለዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 28፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ቅርሶችን ለማደስና ለመንከባከቢያ ይሁን ብሎ 30 ሚሊዮን ብር መድቧል፤ ከሚታደሱት ውስጥም የቴዎድሮስ አደባባይና የዳግማዊ ሚኒልክ ሀውልት ይገኝበታል፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በእናቶች ጤና ላይ በተለይ በፌስቱላ ላይ የሚሰራው የሐምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ የልዩ ሥልጠና ፕሮግራም ማዘጋጀቱን ተናገረ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ባለፈው ዓመት የልማት ተነሺዎች የካሳ ክፍያ በ14 በመቶ ከፍ ብሎ ነበር፤ በተሻሻለው ዋጋ መሠረትም የ1 መኖሪያ ቤት ዝቅተኛ ዋጋ 144 ሺህ ብር ነው፡፡ በዚህ ዓመትም ለልማት ተነሺዋች ለመኖሪያ ቤትና ለሰብል የሚሰጠው ክፍያ ይሻሻላል ተብሏል፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ሊካሄድ ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በወቅታዊ የአየር ሁኔታ በደጋማ አካባቢ ቅዝቃዜው ሊያይል ይችላል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • በአዲስ አበባ አንበሳ አውቶብስ ተቃጥሎ ጉዳት ደረሰበት፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበር በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለባቸው ችግር እንዲቃለል ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እየተመካከርኩ ነው አለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በአፍሪካ በአጉል እምነቶች በአካል ጉዳትና በሌሎችም ምክንያት ህፃናት ላይ የሚደርሱ ወንጀሎችና የመብት ጥሰቶች በርክተዋል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሸገር ልዩ ወሬ፣ “በዚህ አይነት ስሞት ገነት የምገባ አይመስለኝም”

4 ሆስፒታሎች ሞተዋል ካሏቸው በኋላ ከሞት የተመለሱት ወ/ሮ ሉሊት አሰፋ…

የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ያነጋገራቸው ወ/ሮ ሉሊት የ4 ልጆች እናት ናቸው፡፡ ወ/ሮ ሉሊት 4 ሆስፒታሎች ሞታለች ብለው ደምድመው የቀብር ሥነ ስርዓታቸው ሊፈፀም በዝግጅት ላይ ሳለ ነበር ዳግም ሕይወት የዘሩት፡፡በሞታቸው ወቅት ያዩትን አንስተው ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፣ “በግራና በቀኝ የባህር ዛፍ ደን ባለበት ቀጭን መንገድ የማላያቸው ሰዎች እየገፉ ሲወስዱኝ ይታየኛል፡፡ ከዛም ከአንድ የፍሎረሰንት መብራት የበራበት ከመሰለ ብርሃናማ ተራራ አጠገብ ስደርስ “ይህቺን አምጡ ማን አላችሁ” የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ ከዚያም ሰዎቹ እጅና እግሬን ይዘው ወደ መሬት ሲወረውሩኝ ጮኬ ነቃሁ”

ወ/ሮ ሉሊት ከዛን ጊዜ አንስቶ በየቀኑ ሐጢያት መስራት አለመስራታቸውን ለማረጋገጥ ድርጊታቸውን የሚመዘግቡበት ደብተር አዘጋጅተዋል፡፡ እናም የ30 ቀን ድርጊቶቻቸውን መዝገበው “ከ30ው ቀን ያለሐጢያት ውሸት ሳልናገር የዋልኩት ከ30ው ቀን ሁለቱን ብቻ ነው፡፡ 28ቱን ቀን ‘ኤክስ ነኝ’፡፡ ሁለቱንም ቀን ‘ራይት’ የሆንኩት ተኝቼ ውዬ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በዚህ አይነት ስሞት ገነት የምገባ አይመስለኝም” ይላሉ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ይናገራል

ኃይሌ ይናገራል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት ሆኖ የተመረጠው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በሥልጣን ዘመኑ ምን ሊያከናውን እንዳሰበ እና ሌሎች በእሱ ዙሪያ የተነሱ ጉዳዮችን አንስቶ የሸገሩ አስፋው ስለሺ ላቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

እንዲያዳምጡ ጋብዘናል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ መውለድ እና በኑሮ ጫና የማህፀን ችግር የገጠማቸው እናቶች ከ250 ሺህ በላይ ይሆናሉ ተባለ

በኢትዮጵያ ከ250 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሴቶች በተደጋጋሚ ወሊድ እና በከባድ ሥራ ሳቢያ ማህፀናቸው የተፈጥሮ ቦታውን ለቆ ችግር ውስጥ መሆናቸውን በጥናት ደርሼበታለሁ ሲል የሀምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ ተናገረ፡፡በኑሮ ውጣ ወረድ ውስጥ ከአቅማቸው በላይ ከባደ ሥራ የሰሩ ሴቶችና ብዙ ልጅ የወለዱ እድሜያቸው ሲገፋ በዚህ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ ሲሉ የሀምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ፍቃደ አየናቸው ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የሀምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ ባደረገው ጥናት ከ250 ሺህ በላይ በማህፀን መዛነፍ ችግር ውስጥ መሆናቸውን መለየቱን የሚናገረቱ ዶክተር ፍቃደ ወደ ህክምና ያልሄዱ ነገር ግን በችግር ውስጥ ያሉ ቁጥራቸው ከዚህም ይልቃል ብለዋል፡፡ከሰው ርቀው ጓዳ የተቀመጡ የፌስቱላ ታማሚዎችን ቤት ለቤት ለማሰስ ከሀገር አቀፍ የፖሊዬ ዘመቻ ጋር በጥምረት በተሰራ ሥራ የፌስቱላ ህመም ገጥሟቸዋል ተብለው ሲመረመሩ ግን የማህፀን መውጣት ሆኖ ተገኝቷል ተብሏል፡፡

መሰረት በዙ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ከውጪ ሀገር እየገዛች የምታስገባውን ጥጥ ለማስቀረት እና የውጪ ምንዛሬን ለማዳን ያስችላል በማለት 70 ሺህ ሄክታር መሬቷ በጥጥ ዘር ተሸፈነ ተባለ

ኢትዮጵያ ከውጪ ሀገር እየገዛች የምታስገባውን ጥጥ ለማስቀረት እና የውጪ ምንዛሬን ለማዳን ያስችላል በማለት 70 ሺህ ሄክታር መሬቷ በጥጥ ዘር ተሸፈነ ተባለ፡፡ዘንድሮ ከ50 ሺህ ቶን ያህል ምርት ይጠበቃል፡፡የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ባራቲሁን ገሰሰ ለሸገር ሲናገሩ በጥጥ ዘር የተሸፈነው መሬት በደቡብ ኦሞ፣ በአፋር፣ በመተማ፣ በጋምቤላ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ የሚገኝ ነው ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ምድር ይሰበሰባል የተባለው ይሄው ጥጥ ከ142 በላይ ለሆኑ የሀገር ውስጥ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻዎች ይከፋፈላል ያሉት አቶ ባንቲሁን ምርቱን ለውጩ ገበያ ለማቅረብም እንዲቻል ለጥጥ የተመቸ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት አለ አልሚዎች ወደሥራው እንግባ ካላችሁ የባንክ ብድር እና የወጪ ገበያ ዕድል በመንግሥት ይመቻችላችኋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አሁን በጥጥ እርሻ ላይ 96 አልሚዎች ተሰማርተዋል ተብሏል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 24፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የሆቴሎችና መዝናኛዎች ግንባታና አገልግሎት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተስማማ እንዲሆን ተጠየቀ፡፡ የመስኩ ግንባታና አገልግሎት የወደፊቱን አሳሳቢ ሁኔታ ከግምት ማስገባት ያሻል ተብሏል፡፡ (ምስክር አወል)
 • የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ያመቀው ከፍተኛ እንፋሎት 10 ሺ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ እንደሚያመነጭ ቢታወቅም እስካሁን ግን ጠብ ያለ ነገር የለም፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የሁለገብ የስልጠናና የሥራ ፈጠራ ማዕከል አዲስ አበባን ለማፅዳት የጀመርኩት ተንቀሣቃሽ የማስታወቂያ አገልግሎት ስኬታማ አድርጐኛል አለ፡፡ የከተዋን ፅዳት የሚቀንሱና በየጥጋ ጥጉ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች ብዛት ቢቀንስም ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ ከደንብ አስከባሪዎች ጋር በትብብር እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በሰሜን ብሔራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ የቆዩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች በሌላ አካባቢ እንዲሰፍሩ ተደረገ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ወፍ ዘራሽ የሰብል ዝርያዎች እየተሰበሰቡ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ሁለት የግል ሆስፒታሎች በመስኩ ተባብረው ለመሥራት ተስማሙ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ መውለድ እና በኑሮ ጫና የማህፀን ችግር የገጠማቸው እናቶች ከ250 ሺህ በላይ ይሆናሉ ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • ስምንት የኢትዮጵያ ትልልቅ ከተሞች የኤሌክትሪክ ማሻሻያ ሥራ ሊከናወንላቸው ነው፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers