• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ባለፉት 3 ወሮች ለ3 ሺ 126 ጉዳዬች ነፃ የህግ ድጋፍ ሰጠ ተባለ

ማህበሩ ከተመለከታቸው ጉዳዮች 80 በመቶዎቹ በባልና ሚስት መካከል የተፈጠሩ ግጭቶች ሲሆን ከተስማሙት የተለያዩት ይበልጣሉ ተብሏል፡፡የፕሮግራም አስተባባሪዋ ወ/ሮ ሜሮን አራጋው ለሸገር ሲናገሩ የባልና ሚስት አለመግባባቶች፣ የአሰሪና ሠራተኛ ግጭቶች፣ የውርስና የአስገድዶ መድፈር እክሎች ያጋጠሟቸው 3 ሺ 126 ጉዳዮች ወደ ማህበሩ ቀርበው በስምምነት ሊወገዱ የቻሉት 220ዎቹ ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

ቀሪዎቹ መስማማት ያልቻሉ ባልና ሚስቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲለያዩ የተለያዩ የቤት ውስጥ ጥቃት አድራሾችም በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ መፍትሄ የተሰጣቸው ናቸው ተብሏል፡፡የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ባሳለፍነው ሳምንት በሶዶ ገና በ15 ዓመቷ በ35 ዓመት ሰው ጋር ጋብቻ አንድትፈፅም የተገደደች ታዳጊም በሰዎች ጥቆማ ካለእድሜ ጋብቻው መታደግ ተችሏል ጉዳዩ አሁንም እየታየ ነው ሲሉ ወ/ሮ ሜሮን ነግረውናል፡፡ ማህበሩ በየአመቱ 10 ሺ ያህል ጉዳዮችን እንደሚመለከትም ሰምተናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

መኪኖቻችሁ ከየመንገዱ ጥጋ ጥግ ወጥተው በየፎቁ ላይ አረፍ እንዲሉ መቆሚያ እየተገነባላቸው ነው ተባለ

የናንተ ተሽከርካሪዎች እንዲያርፉበት በመገንባት ላይ ያሉት ህንፃዎች ባለ 15 አና 10 ፎቆች መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰምተናል፡፡የጽ/ቤቱ የኮሙኒኬሽን ባለሞያ ወ/ሮ ታፈሱ አባይ ዘመናዊ እና ለከተማዋ አዲስ ናቸው የተባሉት የመኪና ማቆሚያ ህንፃዎች ግንባታ ወጪ ከ100 ሚልዮን ብር በላይ ነው ብለዋል፡፡

በዘፍመሽ፣ በቸርቸል እና በአንዋር መስኪድ አካባቢ የተጀመሩት የመኪና ማቆሚያ ህንፃ ግንባታዎች በወጪው ሁለት ወር ተጠናቆ ሥራ ይጀምራል ያሉት ወ/ሮ ታፈሱ 90 መኪኖችን የመያዝ አቅም ያላቸው 3 ባለ 15 ፎቆች፣ 60 መኪኖችን የመያዝ አቅም ያላቸው 3 ባለ 10 ፎቆች እንዲሁም 80 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችሉ 4 ባለ 10 ፎቆች ግንባታ ከ2 ወር በኋላ ተጠናቆ ሥራ ይጀምራል ብለዋል፡፡በሾላ ገበያ 1 ሺ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል ባለ 7 ፎቅ ህንፃ ግንባታም በቅርቡ ይጀምራል በ2 ዓመት ውስጥም ይጠናቀቃል መባሉን ሰምተናል፡፡

መሰረት በዙ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ዛሬ ከቀኑ አምሰት ሰዓት ላይ በተለያዩ ተቋሞች የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በመስቀልና ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ዘጠነኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

በወቅቱ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን እንደወትሮው ህዝባዊ ሰልፍና በአደባባይ አልተከበረም፡፡በአዲስ አበባ የከንቲባ ፅህፈት ቤት ቢሮ፣ በትምርት ቢሮ፣ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አንዲሁም ሌሎች ተቋሞች ከቀኑ አምስት ሰዓት ላይ ሰንደቅ ዓላማ በመስቀልና ብሔራዊ የህዝብ መዝሙር በመዘመር መከበሩን ከአዲስ አበባ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ቃል አቀባይ ቡድን አስተባባሪ አቶ ጥላሁን ገብረእግዚአብሔር ለሸገር ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የሰንደቅዓላማ እሴቶች የሚያሳውቁ ሙዚቃዊ ድራማዎች፣ ግጥምና ፅሁፎች በሥነ-ሥርዓቱ መካተታቸውን ሰምተናል፡፡የሰንደቅዓላማ ቀን በተሻሻለው የሰደንቅዓላማ አዋጅ መሠረት ከአምና ጀምሮ በጥቅትም ወር በገባ በመጀመሪያው ሰኞ ቀን እየተከበረ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሰንደቅዓላማ ቀንን ስታከብር የአሁኑ 9ኛዋ ነው፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 7፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ከአነስተኛና ጥቃቅን ንግድ ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ያደጉ ተቋማት በብድር ችግር ግንባታቸው ፈቀቅ አላለም ሲል የመስኩ ተቋማት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ተናገረ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ለቀድሞ ቅንጅት ፓርቲ እና ለመኢአድ ፕሬዝዳንት ለኢንጅነር ሀይሉ ሻወል መታሰቢያ የሚሆን ሥነ-ሥርዓት በመኢአድ ፓርቲ በኩል ትላንት መዘጋጀቱ ተሰማ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በአዲስ አበባ መምህራን መኖሪያ ቤት የሚያገኙበት መላ እየተፈለገ ነው ተባለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • በአዲስ አበባ 10 የመኪና ማቆሚያ ሕንፃዎች ግንባታቸው ተጠናቆ በቅርቡ ለአገልግሎት ይበቃሉ ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የሰንደቅ ዓላማ ቀን እየተከበረ ነው፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የግንባታውን ዘርፍ ለማሳደግ ባለ ድርሻ አካላት ተናብበውና ተቀናጅተው መሥራት ይጠበቅባቸዋል ተባለ፡፡ (ፍቅርተ መንገሻ)
 • ሙስና፣ ያልተገባ ጥቅም መሻትና ብልሹ አሰራር ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ስጋት መሆናቸው ተነገረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ባለፉት 3 ወራት የሕግ ድጋፍ ከሰጠባቸው ጉዳዮች በስምምነት የተቋጩት በጣም ያነሱ እንደሆኑ ተሰማ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በ2008 የትምህርት ዘመን በህክምና የትምህርት ክፍል ማስተማር እንዳይችሉ...

ኮሌጆቹ ባለፈው 1 ዓመት የሜድስን ትምህርት ለማስተማር ተማሪዎችን እንዳይቀበሉ ቀድመው የተቀበሏቸውንም ፈቃድ ወዳላቸው ተቋማት እንዲያዛውሩ ውሣኔ አሣልፎባቸው ነበር፡፡

በሜድስን እንዳያስተምሩ ከታገዱ የግል ኮሌጆች መካከል በ2009 የትምህርት ዘመን ማሻሻያ አድርገው ተገኝተዋል የተባሉ 3 ኮሌጆች ዕገዳው ተነስቶላቸዋል፡፡ እነዚህም ሀያት ሜዲካል ኮሌጅ፣ ቤቴል ሜዲካል ኮሌጅና አፍሪካ ጤና ኮሌጅ ሲሆኑ ኮሌጆቹ በዘንድሮ የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብለው አዲስ አበባ ባላቸው ቅርንጫፍ እንዲያስተምሩ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በዴንታል ሜድስን ትምህርት እንዳይሰጥ ያገደው አትላስ ሜዲካል ኮሌጅ ዘንድሮም የሚጠበቅበትን አሟልቶ ባለመገኘቱ ተማሪዎችን መመዝገብ እንደማይችል የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገረሱ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ባለፉት 3 ወራት በ36 በምግብ ፋብሪካዎች ላይ በተደረገ የምርት ጥራት ፍተሻ 14 ፋብሪካዎች የጥራት ጉድለት ተገኝቶባቸዋል ተባለ

ባለፉት 3 ወራት በ36 የምግብ ፋብሪካዎች ላይ በተደረገ የምርት ጥራት ፍተሻ 14 ፋብሪካዎች የጥራት ጉድለት ተገኝቶባቸዋል ተባለ፡፡ፋብሪካዎቹ ምርት በማቆም ማስተካከያ እንዲያደርጉ ምርታቸውን ከገበያ እንዲሰበስቡ እና አምርተው ወደ ገበያ እንዳያቀርቡ ተገደዋል ሲል የኢትዮጵያ የምግብ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ተናግሯል፡፡

የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን አብርሃ በሰነድ አያያዝ፣ በባለሞያ ብቃት እና ጤና ላይ እንከን የተገኘባቸው 25 ፋብሪካዎችም ማስተካከያ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ለ6 ወራት እንዳያመርቱ የታገዱት እና ሙሉ ለሙሉ ፈቃዳቸው ተሰርዟል የተባሉት ምግብ ማቀነባበሪያዎች እነማን ናቸው ብለን ለጠየቅነው ጥያቄ ምላሽ አላገኘንም፡፡

የምርት ጥራት ጉድለት ተገኝቶባቸው ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ ተደርጓል የተባሉት የምርት አይነቶች ማንነትም አልተነገረም፡፡

መሰረት በዙ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥቅምት 4፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ባለፉት 3 ወራት በ36 በምግብ ፋብሪካዎች ላይ በተደረገ የምርት ጥራት ፍተሻ 14 ፋብሪካዎች የጥራት ጉድለት ተገኝቶባቸዋል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • በኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥረት እንደሚያደርግ ተናገረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • የኢንዱስትሪ ማዕድናት በሃገር ውስጥ ገበያ ተፈላጊነታቸው እየጨመረ ነው ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ ስልት አባት በሚባል የሚታወቀው ሙዚቀኛ ሙላቱ አስታጥቄ ዛሬ ከጣሊያን መንግሥት የላቀ የክብር እውቅና ሽልማት ይቀበላል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በ2008 የትምህርት ዘመን በህክምና የትምህርት ክፍል ማስተማር እንዳይችሉ አግዷቸው ከነበሩ የግል ኮሌጅ መካከል የሦስቱን ዕገዳ አነሣ፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • የአሰሪዎች ፌዴሬሽን የአሰሪና ሠራተኛውን አለመግባባት በመቀነስ ለኢንዱስትሪ ሰላም የሚበጅ የህብረት ድርድር ሰነድ አዘጋጀሁ አለ፡፡ ሰነዱ በኢትዮጵያና በኖርዌይ የመስኩ ባለሙያዎች የተሰናዳ መሆኑ ታውቋል፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ጉድለቶችን ለመፍታት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፖሊሲ አማካሪ ከኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ኃሳብ ተለዋወጡ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ማዕድናት የገበያ ተፈላጊነት ጨምሯል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • አፍሪካን የተመለከተው የዓለም የአየር ጠባይ ለውጥ ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊስተናገድ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ አሰሪዎች ፌዴሬሽን የሠራተኛውንና አሰሪውን ሊያስማማ የሚችል ሰነድ አዘጋጅቶ ባለሀብቱን እያወያየ ነው

ሰነዱ በአሰሪና ሠራተኛ መካከል የሚደረገውን የህብረት ድርድር ስርዓትና የህብረት ስምምነት ምን መምሰል ይኖርበታል የሚሉትን ኃሳቦች ይዟል ተብሏል፡፡በውይይቱ መግቢያ ላይ ኢ/ር ፈቃዱ ሀይሌ የፌዴሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ሲናገሩ እንደሰማነው በውጤታማ የህብረት ድርድር ስርአትና አፈፃፀሙ ምቹ የሆነ የህብረት ስምምነት እንዲኖር ካስፈለገ የሰራተኛ የመደራጀት መብቱ ሊረጋገጥለት ይገባል ብለዋል፡፡

በአንዳንድ አሰሪዎች ዘንድ ያለውን የተሳሳተ አመለካከትንም በግንዛቤ መለወጥ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ይህ ዛሬ እየተነጋገሩበት ያለው ሰነድም በአሰሪና ሰራተኛው መካከል ክፍተት ሊፈጥሩ ይችላሉ ያሏቸውን ጉዱዮች የተመለከተና በህብረት ስምምነቱ ሊታሰሩ የሚገባቸውን ያየ ነው ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና በኖርዌይ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ከፍተኛ ባለሙያዎች ተዘጋጅቷል በተባለው ሰነድ ላይ ባለሀብቶች እየመከሩበት ነው፡፡የኢትዮጵያ የአሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝደነት አቶ ታደለ ይመርም የአሰሪውንና ሰራተኛውን ክፍተት ለማጥበብ ሰላማዊ የኢንዱስትሪ መስክ መፍጠር ያስፈልጋልና ፌዴሬሽኑ ይህንን ሰነድ አዘጋጅቷል፣ ሰነዱም ለዚህ እንዲረዳ ተደርጐ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

አስፋው ስለሺ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በፓርላማው መክፈቻ ባቀረቡት የመንግሥት ዕቅድ ላይ በቅርቡ እንደሚወያይበት ተነገረ

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ መስከረም 30 ቀን 2009 ዓ.ም ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ያቀረቡትን የዚህን ዓመት ዝርዝር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራው እቅድ ለማፅደቅ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየት እንዲታከልበት ይጠበቃል ተባለ፡፡

ዛሬ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ለ20 ደቂቃ ባደረጉት አጭር ስብሰባ በፕሬዝዳንቱ ንግግር የድጋፍ ሞሽን አዳምጠው በመጪው ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በምክር ቤቱ ተገኝተው አስተያየታቸውን ካከሉበት በኋላ እንደሚፀድቅ ተነጋግረው የዕለቱ መደበኛ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ባለፈው ሰኞ ምክር ቤቱን በንግግር በይፋ በከፈቱበት ጊዜ የኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሳደግ በመጪው ጊዜ የምርጫ ህጉን ማሻሻልና የሁሉም ህብረተሰብ ድምፅ የተወከለበት የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት እንዲኖር ለማድረግ ሥራ መጀመር አለበት ማለታቸው ይታወሣል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኤልኒኖ ምክንያት በተከሰተው የዝናብ እጥረት ድርቅ ለጐበኛቸው 10 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎች 13 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን እህል ተከፋፍሏል ተባለ

በድርቁ ምክንያት የአንድም ሰው ህይወት አልጠፋም ሲል የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ተናግሯል፡፡ኮሚሽኑ በአደጋ ምክንያት ሞት እንዳይከሰት ከህብረተሰቡ እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ይህን የሰማነው ዛሬ አለም አቀፍ የአደጋ ቅነሳ ቀን “መኖር ለዚህ አበቃኝ” በሚል መሪ ቃል ሲከበር ነው፡፡

የበልግና የመኸር ዝናብ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ሥር በመውደቁ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ህዝብ ለድርቅ ተጋልጦ የአንድም ሰው ህይወት ሳይጠፋ ድርቁን ለመቋቋም ተችሏል ሲሉ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ተናግረዋል፡፡

በድርቅ ለተጋለጡት 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች በ6 ዙር 13 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን እህል ተከፋፍሏል፤ የእህል ድጋፍም እስከ ታህሣስ ይቀጥላል ተብሏል፡፡ድርቅ ከጐበኛቸው 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች መካከል 2 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚሆኑት ተማሪዎች ናቸው ያሉት አቶ ደበበ ለተማሪዎቹ በ6 ሺ 626 ትምህርት ቤቶች ከ599 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በየትምህርት ቤቶቻቸው እንዲመገቡ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በድርቅ የተጐዱ ሰዎች ቁጥር በበልግ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት 9 ነጥብ 7 ሚሊየን መሆናቸው ተለይቷል ሲሉ አቶ ደበበ ተናግረዋል፡፡

መሰረት በዙ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ባለፉት 3 ወሮች ከውጪ ሀገር የጨርቃ ጨርቅ ገበያ 21 ሚሊዮን ዶላር አገኘች ተባለ

ከአልባሳት፣ ከባህላዊ የስፌት ውጤቶች፣ ከብትን ጨርቆችና ከድርና ማግ የውጪ ገበያ 21 ሚሊዮን ዶላር የተገኘው ምርቶቹ ለአውሮፓ፣ ለአሜሪካና ለምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች ተሸጠው ነው በማለት ከኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ባንቲሁን ገሰሰ ነግረውናል፡፡

ጀርመን ብዛት ያላቸው የስፌት ውጤቶችን ከኢትዮጵያ የምትገዛ ሃገር ናት ያሉት አቶ ባንቲሁን፤ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ መንደር የስፌት ውጤቶች በዘመናዊ መንገድ መመረታቸው የውጪ ምንዛሪውን እየጨመረ ነው ሲሉም ነግረውናል፡፡አምና ከጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ገበያ 78 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱንም አቶ ባንቲሁን አስታውሰዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers