• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ከደረጃ በታች ናችሁ የተባሉ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋሞች ተዘግተዋል ተባለ

በአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ በተደረገ ክትትል 21 የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ ተቋሞች ተሰርዘዋል ተባለ፡፡የፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የ2008 የሥራ ክንውኑን የተመለከተ ሪፖርቱ ላይ እንዳየነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የ344 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ያሉበት ደረጃ በየአመቱ ተመልክቷል፡፡

በኦሮሚያ በ91 ማሰልጠኛ ተቋሞች ተፈትሸው 10ሩ እንዲዘጉ ተደርጓል ተብሏል፡፡በትግራይ 49፣ በደቡብ ክልል 53 እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር 8 የማሰልጠኛ ተቋማትን መመልከቱን የተናገሩት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች በሁለቱ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከደረጃ በታች መሆናቸው የተለየ አንድ አንድ የማሰልጠኛ ተቋማት ተዘግተዋል ተብሏል፡፡

በትግራይ ከተዘጋው 1 ማሰልጠኛ በተጨማሪ 62ቱ ሥራ እየሰሩ በአንድ ወር ጊዜ የጐደላቸውን እንዲያሟሉ የተደረገ ሲሆን ሌሎች 11 ደግሞ ለ3 ወር ታግደዋል ተብሏል፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 29፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

 • በልተው ማደር የተሣናቸውን 20 በመቶ ያህል አዲስ አበቤዎች ለመደገፍ በአስተዳደሩ 450 ሚሊዮን ብር መመደቡ ተሠማ፡፡ (ትዕግስትዘሪሁን)
 • መንግሥት ከሀገር ውስጥ ሞባይል ገጣጣሚ ኩባንያዎች በመጪው ዓመት አርባ ሁለት ሚሊየን ዶላር አገኛለሁ ብሎ ተመኝቷል፡፡ ኩባንያዎቹ በበኩላቸው አቅማችን እየደከመ የኮንትሮባንድ ንግዱ ገበያውን እየተሻማን የተባለውን ገንዘብ ማምጣታችንን እንጃ እያሉ ነው፡፡ (ህይወትፍሬስብሃት)
 • መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሀገራችን ተከስቶ የነበረው ድርቅ ያስከተለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ማህበራዊ ኃላፊነቴን እየተወጣሁ ነው አለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሊዳሰሱ የማይችሉ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች እንዳይዘነጉና ከትውልድ ትውልድ ለማስተላለፍ ያግዛሉ ያላቸውን የጥናትና ምርምር ህትመቶችን አስመረቀ፡፡ (ምስክርአወል)
 • ከደረጃ በታች ናችሁ የተባሉ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋሞች ተዘግተዋል ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስወርቁ)
 • በአምራችና አገልግሎት ሰጭዎች ሥራ ላይ የሚውሉ አዳዲስ ደረጃዎች ወጡ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ አካባቢዎች የትዳር አጋር እናገናኛለን

አሁን አሁን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የትዳር አጋር እናገናኛለን፣ በፍቅር መሐል ጥል ከመጣም እናስታርቃለን በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሉልን የሚሉ ማስታወቂያዎች ይታያሉ…

ለመሆኑ ከነዚህ ማስታወቂያዎች ጀርባ ያለው ምን ይሆን ? በሚል የሸገሩ ተህቦ ንጉሴ የስልክ አገልግሎቱን ፈትሿል የአገልግሎቱ ሰጪ ኢትዮቴሌኮምንና ባለሞያም አነጋግሯል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የጥራት መሥፈርታቸውን ያላሟሉ የታሸጉ የመጠጥ ውሃ በሚያቀርቡ አምራቾች ላይ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተባለ

በተለያየ ጊዜ ያልሆኑትን ነን የሚሉና ጥራታቸው የተጓደለ የታሸገ የመጠጥ ውሃዎች እየተለዩ እንደሆኑ ሰማን…

አስገዳጅ የጥራት ደረጃ መሥፈርቶችን አሟልተው ወደ ገበያ መግባት ያለባቸው የታሸጉ ውሃዎች ይሄንን ሳያሟሉ በከተማው እና በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተቸበቸቡ ነው ተብሏል፡፡

በዚህ መሠረትም የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጥራት የጐደላቸው የውሀ አምራች ኩባንያዎች እንዳሉ ስላረጋገጥኩ እርምጃ ለመውሰድ ሥራዬን አጠናቅቄያለሁ ብሏል፡፡

የሚመለከተው መሥሪያ ቤት የጥራታቸውን ጉዳይ አረጋግጦ የላከልኝ የውሃ አምራች ኩባንያዎችንም ቁጥር አውቄያቸዋለው ማለቱን ነግሮናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ለአተት ተገቢውን ትኩረት አልሰጡም የተባሉ 20 ሕክምና መስጫዎች ታሸጉ፡፡ ማስጠንቀቂያም የተሰጣቸው አሉ

ለአተት በሽታ ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡ ህመምተኛውን አጉላልተዋል፣ ተገቢውን ህክምና እንዳያገኝ ወደ ህክምና ማዕከላት ፈጥነው አልላኩም የተባሉ 20 የግል የጤና ተቋማት ታሽገዋል ተባለ…

38 የሚሆኑ የግል የጤና ተቋማት ከዚሁ ጋር በተያያዘ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው የአዲስ አበባ የምግብ የመድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ተናግሯል፡፡

ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ አተት መከሰቱ ከተገነረበት ጊዜ ጀምሮ ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን በዘመቻ ቁጥጥር እያደረገ ነው ያሉት የባለሥልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ በቁጥጥሩ ለአተት በሽታ አጋላጭ ናቸው የተባሉ  800 የሚደርሱ ምግብ እና መጠጥ አምራች ተቋማት፣ ስጋ ቤት እና አትክልት ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሊካሄድ ነው

አስገዳጁ ሀገር አቀፍ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ከነገ በስቲያ ጀምሮ ይካሄዳል ተባለ፡፡

ወሳኝ ኩነቶች የሚባሉት ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺና ሞት ናቸው፡፡

ዛሬ ረፋድ ላይ ሀገር አቀፍ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ማብሰሪያ መድረክ ላይ ተገኝተን እንደሰማነው ከነገ በስቲያ የሚጀመረው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስገዳጅ በመሆኑ የማያስመዘግቡትና የማይመዘገቡት የእስራትና የገንዘብ መቀጮ ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡

ጋብቻ፣ ሞትና ፍቺ ከተፈፀሙ በ30 ቀኖች ውስጥ ልደት ደግሞ በ90 ቀኖች ውስጥ መመዝገብ አለበት ተብሏል፡፡

በተጠቀሱት ቀኖች ያልተመዘገበ ወሳኝ ኩነት አጥጋቢ ምክንያት እስካልቀረበበት ድረስ ያስቀጣል መባሉንም በዝግጅቱ ላይ ሰምተናል፡፡

ምዝገባው ለዜጐች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች ጠቀሜታቸው የጐላ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ልደት፣ ጋብቻ፣ ፍቺና ሞት የሚባሉት ወሳኝ ኩነቶች አንዴ ከተመዘገቡ በኋላ ድጋሚ ማስመዝገብ አይቻልም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ሐምሌ 28፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በአዲስ አበባ ለአተት ተገቢውን ትኩረት አልሰጡም የተባሉ 20 ሕክምና መስጫዎች ታሸጉ፡፡ ማስጠንቀቂያም የተሰጣቸው አሉ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የአዲስ አበባን ሁለት ትላልቅ ወንዞች የማፅዳት ሥራ ሊከናወንላቸው ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢትዮጵያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2008 በጀት ዓመት ከንብረት ጉዳት ከ3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የካሣ ክፍያ አግኝቻለሁ አለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የአርባ ምንጭ የአዞ ቄራ በመጪው ዓመት የእንስሣቱን ሥጋ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይጀምራል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የSOS ሳልሕ ዓለም አቀፍ ተቋም የምሥራቅ አፍሪካ ቢሮ በአዲስ አበባ ይከፈታል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በአዲስ አበባ የድጋፍ ሰጭ የመጓጓዣ አገልግሎት አቅራቢዎች ሥራው አላዋጣንም ሲሉ ከአስተዳደሩ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ጋር እየተወዛገቡ ነው፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የጥራት መሥፈርታቸውን ያላሟሉ የታሸጉ የመጠጥ ውሃ በሚያቀርቡ አምራቾች ላይ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ሊካሄድ ነው፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ሐምሌ 26፣2008

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ክፍል አራት

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር የምግብ ፒራሚድ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለፈው የበጀት ዓመት ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸው ተሠማ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በበጀት አመቱ ከ905 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ እቃዎች በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሃገር ሲገቡና ከሃገር ሲወጡ መያዙን ተናገረ…ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀርም የ342 ሚሊዮን ብር ብልጫ አለው ተብሏል፡፡

የታሸጉ ምግቦች፣ መድኃኒቶች፣ የጦር መሣሪያዎች፣ ነዳጅና ወርቅ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ጫትና ሌሎችም በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጡ ሲሉና ሲገቡ የተያዙ እቃዎች መካከል ይገኙበታል፡፡

በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት ወ/ሪት ለኢላ ይማም ለሸገር እንደተናገሩት በዚህ አመት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ሊገቡ ሲሉ ከ763 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው እቃዎች ተይዘዋል፡፡

ከ141 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ ሃገር ገንዘቦችና እቃዎች ደግሞ ከሃገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል፡፡ በአጠቃላይም በዚህ አመት የ905 ሚሊዮን 419 ሺህ ብር ያህል ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሀገራቸው ቤት ለሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ቤት ዲዛይን ተዘጋጅቶላቸዋል ተባለ

በሀገራቸው ቤት ለሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ቤት ዲዛይን ተዘጋጅቶላቸዋል ተባለ፡፡ 

እንዲህ ያለው የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ነው፡፡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ኢትዮጵያ በዴቻ ለሸገር እንደተናገሩት ለትውልደ ኢትየጵያውያኑ ሦስት ዓይነት የቤት ዲዛይን የተዘጋጀ ሲሆን አንደኛው ባለ 12 ፎቅ አፓርትማ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ለሱቅ እና ለንግድ የሚሆን ባለ ሦስት ቤዝመንት ያለው ባለ 16 ፎቅ ህንፃ ነው፡፡

ከዚሁ በተመሳሳይ ባለ 18 ፎቅ ህንፃም ሦስተኛው ዲዛይን ነው፡፡ እነዚህን ቤቶች ተደራጅተው ለመገንባት ይችላሉ ተብሏል፡፡

መሬት የረገጠ ቪላ ቤት ካሻችሁ ግን ክልሎች ያዘጋጁላችኋል ተብላችኋል፡፡አቶ ኢትዮጵያ ይህን ተፈፃሚ ለማድረግ ግን መመሪያ እየተሰናዳ መሆኑንም ነግረውናል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በሕዝብና በመንግሥት ገንዘብ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች በመጓተታቸው በሚከሰት የዋጋ ንረት ኪሣራ የሚያስከትሉ በሕግ እንዲጠየቁ የተለያዩ የሕብረተሰቡ ክፍሎች ያገባኛል ባይነት ያሻል ተባለ

በየወቅቱ፣ በየጊዜው፣ በህዝብ ገንዘብ የሚሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ሲጓተቱ ከሚጠበቀውም በላይ ወጪያቸው ሲንር ይታያል፡፡ ይህን የሚያደርጉ በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው ባውቅም በቂ ማስረጃና መረጃ ባለመኖሩ ግን የሚፈለገውን ያህል እየሰራሁ አይደለም ሲል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ተናገረ፡፡

ኮሚሽነሩ አሊ ሱሌማን ይህን የተናገሩት ትላንት ኮስት በተባለው ግልፅ የሆነ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ ከሚሰራ ድርጅት ጋር ኮሚሽነሩን ጨምሮ ሦስት መሥሪያ ቤቶች የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረሙ ጊዜ ነው፡፡

እኛ ብቻችንን የሚሰሩትን ወንጀሎች እየተከታተልን ማጋለጥ አንችልም ያሉት ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን ህዝቡ ሊያግዘንና ሊጠቁመን ይገባልም ብለዋል፡፡

ይህም ሆኖ ግን ኮሚሽኑ በተገኘው የህዝብ ድጋፍ ልክ ቀላል የማይባሉ ወንጀለኞችን ከሷል፣ ቀላል የማይባል የመንግሥት ሀብትም አስመልሷል ብለዋል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers