• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ህጋዊ የውጪ ሀገር የሥራ ሥምሪትን በተመለከተ እና የዜጐችን ደህንነት ያስጠብቃል ተብሎ በወጣው አዋጅ ደንብና መመሪያው ተዘጋጅቷል ተባለ

የውጭ ሀገር ሥምሪትን በምን መንገድ ማስፈፀም ይቻላል በሚለው ዙሪያ ደንበና መመሪያው እንደተጠናቀቀ ሰምተናል፡፡ አዋጁ ከወጣም አመት ያለፈው ሲሆን የተጠናቀቀለት መመሪያ መፅደቅ ብቻ ቀርቶታል ያሉን በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አውሮፓ ህብረት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል ፕሮጀክት ሚዲያ ኤክስፐርት አቶ ሀብታሙ ደምስ ናቸው፡፡ የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት ህግና ደንቡን ጠብቆ የዜጐች መብት ሳይጣስ እንዲቀጥል በተለያዩ የሀረብ ሀገሮች ስምምነቶች እየተደረጉ ነው ተብሏል፡፡
በውጪው ሀገር እንጀራ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ጥቅማቸውን እና ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ በሚደርሱባቸው ሀገሮች ባሉ ኤምባሲዎች በሙሉ ደህንነታቸውን የሚከታተል መመሪያ አና ባለሙያ እየተዘጋጀ መሆኑንም ሰምተናል፡፡ በዚህ ቀን የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ይጠናቀቃል ለማለት እንደማይቻል አቶ ሀብታሙ ነግረውናል፡፡ ምክንያቱን የጠየቅናቸው ባለሙያ በየክልሉ ሥራውን ሊያስፈፅሙ የሚችሉ ባለሙያዎች ተመድበው መጠናቀቅ ስላለባቸው ነው ብለውናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ያላት ግንኙነት በአባይ ወንዝ ላይ ብቻ የተመሠረተ አይደለም ሲሉ በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሣደር መሃመድ ድሪር ተናገሩ

አምባሣደር መሃመድ ድሪር ከትናንት በስቲያ ከግብፁ የግል ቴሌቭዥን አል ናሀር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው ይህን ያሉት፡፡ ሦስቱ ሀገሮች ግንኙነት ከአፍሪካ ዕድሜ ጠገቡ በመሆኑ እንዲህ በጠባብ ሁኔታ መታየት የለበትም ብለዋል፡፡ በርግጥ አሉ አምባሣደር መሃመድ ድሪር በርግጥ ሦስቱም ሀገሮች በአባይ ወንዝ የየራሳቸው ፍላጐት አላቸው ይህን ፍላጐታቸውን እንዴት ወደ አንድ የጋራ ጥቅም ማምጣት ይቻላል የሚለው ላይ ነው ትኩረት መደረግ ያለበት ብለዋል፡፡ አምባሣደር መሃመድ ጨምረውም ኢትዮጵያ እየገነባቸው ያለው የአባይ ግድብ ግንባታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ነው የቀረው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የግብፅ መገናኛ ብዙሀን የታችኛው የተፋሰሱ ሀገሮችን ይጐዳል በሚል የሚያወሩት ተገቢ አለመሆኑንም በቃለ ምልልሳቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በተከሰው ድርቅ ምክንያት ከብቶቻቸው የሞቱባቸው የሶማሌ ክልል ነዋሪዎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት 75 ሚሊየን ብር መድቧል ተባለ

የሶማሌ ክልል ነዋሪዎችም በበኩላቸው 35 ሺህ ፍየሎችን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን ሰምተናል፡፡ በሶማሌ ክልል አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ሃሰን አደም ለሸገር እንደተናገሩት ከተጎዱ 475 ሺህ የክልሉ ዜጎች መካከል ከብቶቻቸው የሞቱባቸው 100 ሺህ ያህል ይደርሳሉ፡፡ የሚተዳደሩትም ከብት በማርባት በመሆኑ መልሶ ለማቋቋም 75 ሺህ ብር ተመድቧል ብለዋል፡፡ በተመደበው ገንዘብም የሚያስፈልጓቸው ፍየሎችና ግመሎች ተገዝተው እንደሚቀርቡላቸው ሰምተናል፡፡
አቶ ሃሰን እንደሚሉት በመጀመሪያው ዙር 50 ሺህ ፍየሎችን ገዝቶ ለማከፋፈል ተወጥኗል፡፡ በአንድ ቀበሌም በቅርቡ 5 ሺህ ፍየሎች ተከፋፍለዋል ብለዋል፡፡

በመጭው ጊዜም ከብቶችን ገዝቶ የማቅረቡና በክልሉ ነዋሪ ቃል የተገቡ 35 ሺህ ፍየሎችን ሰብስቦ የማከፋፈሉ ሥራ ይቀጥላል ተብሏል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 13፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በአዲስ አበባ ከተማ አውራ ጎዳናዎችና መንደሮች ተከማችቶ ለሰነበተው ደረቅ ቆሻሻ ጊዜያዊ የመጣያ ቦታ ተገኝቶለታል፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • የተራቀቀ የልብ ህክምናን በመጀመር የመቐሌው ሀይደር ቀዳሚው የመንግሥት ሆስፒታል ሆኛለሁ ሲል ተናገረ፡፡ ህክምናው በግል ሆስፒታሎች ከዘጠና እስከ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር ያስወጣል ተብሏል፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በኢትዮጵያ የጐርፍ ተጋላጮች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን በላይ ነው ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ ከአንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር ሰጠ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በደቡብ ክልል የሚገኙና ከዚህ ቀደም በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ደረጃ ተሰጥቷቸው በደረጃው ቅር የተሰኙ ሁለት ሆቴሎች ደረጃ እንደተስተካከለላቸው ሰማን፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የአባይ ግድብ ግንባታ ሊጠናቀቅ ጥቂት ነው የቀረው ሲሉ በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሣደር ተናገሩ፡፡ (ፋሰል ረዲ)
 • የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅን ማስፈፀሚያ ደንብና መመሪያ ተዘጋጅቷል ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በድርቁ ምክንያት ከብቶቻቸው ለሞቱባቸው የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የማቋቋሚያ ድጋፍ ሊደረግ ነው፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ትናንት ምሽት በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት አንጋፋዋ ሁለገብ የጥበብ ሰው አሰለፈች አሽኔን የማመስገኛ ዝግጅት ተሰናድቶ ነበር፡፡ በህይወት ታሪኳ ላይ የተሰራ ሙዚቃና ተውኔትም ቀርቧል፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በዚህ አመት መንግሥት ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ግዥ ፈፀመ

በድርቅ ለተጎዱ ዜጐች እርዳታ የተፈፀመው የስንዴ ግዢ ትልቁን ድርሻ ወስዷል ተብሏል፡፡ በዚህ አመት ከተፈፀመው 18 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የመንግሥት ግዢ መካከል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚሆን 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በ11 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መገዛቱን የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ተናግሯል፡፡ በተለያዩ ክልሎች በድርቅ ለተጐዱ ዜጎች ለምግብ ይሆን ዘንድ ከተፈፀመው የስንዴ ግዥ በተጨማሪ ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ በ32 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የትምህርት ቁሳቁሶች ተገዝተው መከፋፈላቸውን ከአገልግሎቱ ሰምተናል፡፡

በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የህዝብ ግንኙት ኃላፊ የሆኑት አቶ መልካሙ ደፋልኝ ለሸገር እንደተናገሩት በምንዛሬ እጥረት ምክንያት የስንዴ ግዥው እንዳይዘገይ አስመጭ ድርጅቶች ወረፋ ሳይጠብቁ የሚጠቀሙበት 60 ሚሊዮን ዶላር ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝተው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ትላንት አመሻሽ 12፡30 አካባቢ በጅማ ዞን በደረሰ የመኪና አደጋ የ9 ሰው ህይወት አልፏል ተባለ

አሳዛኝ ነው፡- ትላንት አመሻሽ 12፡30 አካባቢ በጅማ ዞን በደረሰ የመኪና አደጋ የ9 ሰው ህይወት አልፏል ተባለ፡፡ ከጅማ ዞን ናዳ ከተማ ወደ ኦሞ ሲጓዝ የነበረው ቅጥቅጥ አይሱዙ ጨለለቃ ዱንጋ ወረዳ ላይ ሲደርስ ተገልብጦ 9 ሰዎች የሞት፣ 18 ሰዎች ከባድ ጉዳት እና 11 ሰዎች ቀላል ጉዳት ገጥሟቸዋል ሲሉ የኦሮሚያ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት ባለሞያ ኮማንደር ንጉሴ ግርማ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ቅጥቅጥ አይሱዙው በመደበኛ 24 ሰው ጭኖ መጓዝ ሲገባው 38 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ ነበር ተብሏል፡፡ ከባድና ቀላል ጉዳት የገጠማቸው ሰዎች ወደ ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ሲሉ ኮማንደር ንጉሴ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

መሰረት በዙ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት የከፋ ጉዳት ከመድረሱ በፊት አለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ሲል ኃይሌ ገብረስላሴ ተናገረ

“ቤተሰቦች ለምግብ ፍለጋ እየተበታተኑ ከብቶችም በረሃብ ምክንያት እየሞቱ ነው” አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ…በኢትዮጵያ በኤሊኒኖ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ ብዙዎች ላይ አደጋ የጋረጠ በመሆኑ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ችላ ሊለው አይገባም ሲል ከሮይተርስ ጋር ትናንት ባደረገው ቃለ ምልልስ ተናግሯል፡፡ የኦሎምፒክ እና የአለም ሻምፒዬና ባለድል የብዙ ክብረወሰኖች ባለቤት የሆነው ኃይሌ ገብረስላሴ በድርቁ ምክንያት የከፋ ጉዳት ከመድረሱ በፊት አለም አቀፍ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያውያን ሊደርስ ይገባል ባለበት መግለጫው በትውልድ ሀገሬ ፈጣን የሆነ እድገት በቅርብ እየተመዘገበ ቢሆንም አሁን ግን ለብዙ ወራት በዘለቀው ድርቅ ምክንያት ነፍሰጡሮች እና ህፃናት ለችግር እየተዳረጉ ነው ብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 12፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት የከፋ ጉዳት ከመድረሱ በፊት አለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ሲል ኃይሌ ገብረስላሴ ተናገረ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ኢትዮጵያ ያሏት ተሽከርካሪዎች ቁጥራቸው 670 ሺህ ደረሰ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በባሌ የሚገኙት ዝሆኖች ህይወታቸው በነዋሪዎች እየተበጠበጠ ነው ተብሏል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)                              
 • ትላንት አመሻሽ 12፡30 አካባቢ በጅማ ዞን በደረሰ የመኪና አደጋ የ9 ሰው ህይወት አልፏል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ወደ ከባቢ አየር የሚለቀው ጭስ ችግር ፈጥሮብናል ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን አሰሙ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ቲ-570 አውሮፕላን ለበረራ እንድትበቃ የገንዘበ ኃይል ለማጐልበት የሚያስችል ኮንሰርት ሊዘጋጅ ነው ተባለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • መንግሥት በአመቱ ከፈፀመው ግዥዎች መካከል በድርቅ ለተጠቁ ወገኖች የገዛው ስንዴ ከፍተኛ ነበር ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በመጥፋት ላይ ያሉ ነባር የገበሬ ዝርያዎችን የመተካቱ ሥራ እየተከናወነ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መሬት አልባ ገበሬዎች በኢትዮጵያ

ከ80 በመቶ በላይ ህዝቧን አሁንም በገጠር የምታሣድረው ኢትዮጵያ እዚያው ገጠር ለሚኖረው ነዋሪ የምታቀርበው መሬት እያጠረ፣ የመሬት አልበኞቿ ቁጥር ሽቅብ እየገሰገሰ ነው… ይህን ያለው ሰሞኑን በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ አዘጋጅነት በምሁራን የቀረበ ጥናት ነው፡፡ ጥናቱ በአማራ፣ በኦሮምያ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎች ያለው የመሬት አጥነት ችግር ምን እንደሚመስል ምሣሌዎችን አሣይቷል፡፡ በገጠር እየኖሩ፣ በስማቸው የተመዘገበ የእርሻ መሬት የሌላቸው፣ ነገር ግን መሬት ተከራይተው አልያም በአጣማጅነት የዓመት ጉርሳቸውን የሚያገኙ በግብርና ሙያ ላይ የተሰማሩ አርሶ አዳሪዎች ምን ያህል እንደሆኑ ትክክለኛው መረጃ እንደማይታወቅም የጥናቱ ባለቤቶች ተናግረዋል፡፡

የመሬት አጦች ቁጥር በየዕለቱ እያየለ መምጣት፣ ብዙ ውስብስብ ችግሮችን ማስከተሉን፣ ድህነትም አቅም እንዲያገኝ እንደረዳው ይኸው ጥናት ያመለክታል፡፡ ዋና መተዳደሪያውን በገጠር መሬት ላይ ያደረገው ነዋሪ የገቢ ማግኛ ዕድሉ የተመናመነ በመሆኑ ወይ መሬት ለመከራየት አልያም ለባለ መሬት ማደር የግድ ሆኖበታል ይላሉ የጥናቱ ባለሙያዎች፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሶሻል አንትሮፖሎጂ መምህሩ ዶክተር አዱኛ የራሳቸው መሬት የሌላቸው ብዙዎቹ የገጠር ነዋሪዎች መሬት እንከራይና አርሰን እንክረም ቢሉ ዋጋው በ4 እጥፍ ንሮባቸዋል፡፡ ይህንኑም ከባለሀብት ተነጥቀው ካገኙት ነው ይላሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በሀገራችን የጤና ባለሙያዎች አንዴ ከተመረቁ በኋላ ራሳቸውን የሚያድሱበት የትምህርት ስርዓት አልነበረም

አሁን ይህን ስርዓት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ለዚሁ የሚረዱ ህጎችን እንዳወጣ ሰምተናል፡፡የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ህክምና ማህበር ደግሞ በዚሁ ውስጥ ተሳትፎ እንዳለው ፕሬዝዳንቱ ዶክተር መንግሥቱ እርቄ ነግረውናል፡፡ በሌሎች ሀገሮች ይህ አይነቱ ስልጠና በየዓመቱ የሚይዘው ነጥብ እንዳለ ነው ዶክተር መንግሥቱ የነገሩን፡፡ ነጥቡን ያላሟላ ባለሙያ የህክምና ፍቃዱ አይታደስለትም ብለዋል፡፡

ይህንን አሰራር ወደ ኢትዮጵያም ለማምጣት መታሰቡን ነው ከዶክተር መንግሥቱ የሰማነው፡፡ማህበሩ የሙያው ስነ ምግባር እንዲከበርም ከሚመለከታቸው ጋር ተቀራርቦ እየሰራ ስለመሆኑ ዶክተር መንግሥቱ ነግረውናል፡፡ የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ህክምና ማህበር ከተቋቋመ ወደ ሦስተኛ ዓመቱ እንደተቃረበ ሰምተናል፡፡ ወደ 400 የተመዘገቡ አባላትም አሉኝ ብሏል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ ሁለት ሰዎች በጐርፍ አደጋ ህይወታቸውን አጡ ተባለ

ባሳለፍነው ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 ገደማ ኮልፌ ቀራኒዬ ወረዳ 14 አስኮ አዲሱ ሰፈር ከሚገኘው ወንዝ ውስጥ የአንድ የ60 አመት ሰውዬ አስክሬን ተገኝቶ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል፡፡ በዚያው ባሳለፍነወ ቅዳሜ ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ በአቃቂ ወረዳ አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ ጀርባ ካለ ወንዝ ውስጥ አንድ የ45 ዓመት ሰውዬ ሞተው ተገኝተዋል፡፡ ዘንድሮ ክረምት ከገባ በጐርፍ አደጋ ብቻ ሰባት ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባሥልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡
                                     
ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers