• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሸገር የከተማ አውቶብሶች

በሙከራ ላይ የነበሩት ሸገር የከተማ አውቶብሶች በተወሰኑ መስመሮች ላይ መደበኛ የትራንስፖርት አገግሎት መስጠት ጀምረዋል ተባለ…ግንቦት 19 የሙከራ ሥራ የጀመረው ሸገር የከተማ አውቶብስ በአራት መስመሮች  ላይ መደበኛ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ሲሉ የነገሩን የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን  ደጋፊ የሥራ ሂደት መሪ ወ/ሮ ታፈሱ አባይ ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ፈርሶ በአዲስ መልክ ሊገነባ ነው

አዲስ የሚገነባውን ማዕከል የአዋጭነት ጥናት ከሰራው ድርጅት ጋር ዛሬ የመግባቢያ ስምምነት እንደሚፈረም ተነግሯል፡፡ አዋጭነት ጥናቱን ያካሄደው ፌራ ባርሴሎና የተሰኘ የስፔይን ኩባንያ እንደሆነ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምራት አድማሱ ነግረውናል፡፡በአዲስ መልክ የሚሰራው ማዕከል በአውሮፓ ደረጃ የሚገነባ ነው ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ሸገር ልዩ ወሬ፣የእማማ ፀሐይ ላም የሆነችው “አድገሽ”

ይህቺ ላም የምትሄድበት ባይኖራትም አንዲትም ቀን ታክሲ ተራ ሳትሰለፍ ውላ አታውቅም…የታክሲ ተራ ሰልፍ አማሮታል ? የአዲስ አበባ ጎፋ ካምፕ ሰፈሯ የእማማ ፀሐይ ላም የሆነችው “አድገሽ” ግን እንደ ታክሲ ሰልፍ የምትወደው ነገር የላትም የሚለን የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ሁሌ ማለዳ ልክ እንደሰው የታክሲ ሰልፍ ስለምትሰልፈዋ ላም ያጫውተናል፡፡በዜብራ ካልሆነ የማትሻገረው፣ ባልታጠበ ዕቃ ውሃ ከሰጧት ንክች የማታደርገው፣ የ3 ጥጆች እናት “አድገሽ” ቴሌቪዥን መመልከትም ነፍሷ ነው ይላሉ ጥጃ ሆና ጀምራ ያሳደጓት እማማ ፀሐይ፡፡

“በተለይ ይሄ ማሲንቆ ምናምን ያለበት ዘፈን በቴሌቪዥን ሲመጣ በተመስጦ ነው የምታየው፣ ቻናሉን ከቀየሩባት ልትማታ ትጋበዛለች” ይላሉ እማማ ፀሐይ፡፡ ከሁሉም በተለይ ግን አድገሽ በአካባቢው ሰው ዘንድ የምትታወቀው በታክሲ ሰልፈኝነቷ ነው፡፡ የምትሄድበት ባይኖራትም አድገሽ ከታክሲ ሰልፍ ቀርታ አታውቅም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ስንክሳር ሰኔ 12፣2008 ክረምትና የጎዳና ሕጻናት ሰቆቃ

ይህ እሁድ ሰኔ 12፣2008 በሸገር የዶክመንተሪ ፕሮግራም በሆነው “ስንክሳር” ላይ የቀረበ ዶክመንተሪ የአዲስ አበባ የጎዳና ተዳዳሪ ሕፃናት በክረምት የሚያጋጥማቸውን አበሳ ያሳየናል፡፡ ከላይ ዝናብ ከሥር ጎርፉ፣ በተኙበት በመኪና መገጨቱ ሁሉ የክረምት አበሳቸው ነው፡፡ አንዳንዶቹ ክረምቱን ሽሽት ጥፋት ሰርተው እስር ቤት እስከመግባት ይደርሳሉ፡፡

ብርዱን ለመከላከል አንድ ላይ ተደራርበው በሚተኙበት ከመሀከላቸው አንዱ ሞቶ መገኙቱም ሳይረሳ ነው ታዲያ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ዮሐንስ የኋላወርቅ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 13፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የያዩ ማዳበሪያ ፋበሪካ ግንባታ 34 በመቶ ደረሰ ተባለ፡፡
 • የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ፈርሶ ዳግም ሊገነባ ነው ተባለ፡፡
 • የኮንጎ ድንበር ጠባቂዎች የ19 ኢትዮጵያውያን አስክሬን በመኪና ተጭኖ ሲጓጓዝ ማግኘታቸውን ተናገሩ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሴት አርሶ አደሮች በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚደርስባቸውን ተፅዕኖ ለመቀነስ የኢኮኖሚ አቅማቸውን በዘላቂነት ማጐልበት

ሴት አርሶ አደሮች በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚደርስባቸውን ተፅዕኖ ለመቀነስ የኢኮኖሚ አቅማቸውን በዘላቂነት ማጐልበት እንደሚገባ ተነገረ… የኢትዮጵያ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር በሥርዓተ ፆታ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በግብርና ልማት ዘርፍ ላይ ያተኮረ አለም አቀፍ የትብብር ፕሮግራም የጀመርኩት ይህንን ችግር ለመቅረፍ ነው ብሏል፡፡ ትናንት ጀምሮ ዛሬ በቀጠለው ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ካሣተፈው ውይይት ላይ እንደሰማነውና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንዳወራው የሴት አርሶ አደሮችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጐልበት እግር መንገዱንም የአየር ንብረት ለውጡን ለመታደግ የሚያስችል ሥራ ተጀምሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ ነፃ የህግ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ጠበቆች 25 ብቻ ናቸው

በኢትዮጵያ ነፃ የህግ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ጠበቆች 25 ብቻ ናቸው ተባለ…መንግሥት የገንዘብ አቅም ለሌላቸው ግን ደግሞ የህግ ድጋፍና የጥብቅና አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጠበቃ እንደሚያቆም ይታወቃል፡፡የገንዘብ አቅም እንደሌላቸው ከተረጋገጠ የትኛውንም ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች አገልግሎቱን ያገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ይህን አገልግሎት እየሰጡ ያሉ 25 ጠበቆች እንደሆኑ ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለሳይበር ደህንነት ሥራዎችና ለኢንዱስትሪው የሚያስፈልገው የሰው ኃይል ከትምህርት ተቋማት እየተገኘ አይደለም አለ… ኢትዮጵያ የሳይበር ኢንዱስትሪ እድገቷ አዝጋሚ በመሆኑ ለኢንዱስትሪ የሚያስፈልግን ሀገራዊ ፍላጐት ለመመለስ በውጪ ግዢ ብቻ እንድትወሰን ሆናለች ተብሏል፡፡የሳይበር ኢንዱስትሪ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነትን ለመፍጠርና አዳዲስ የቢዝነስ ሞዴሎች እንዲኖሩ ለማድረግ ሚናው ከፍ ያለ ነው፡፡ ዕውቀትን ለማሸጋገርና በኢኮኖሚ ዕድገትም ትልቅ ድርሻ ቢኖረውም ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪው አቅም እንዳልፈጠረች ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሁለተኛ ዙር በሥርዓተ ፆታ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በግብርና ልማት

የኢትዮጵያ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሁለተኛ ዙር በሥርዓተ ፆታ፣ በአየር ንብረት ለውጥና በግብርና ልማት ዘርፍ የምሰራውን ፕሮግራም ልጀምር ነው አለ፡፡

የመጀመሪያውን ዙር ውጤታማ ሆኜበታለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡

ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ ዛሬ የሁለተኛውን ዙር መጀመር አስመልክቶ በድሪምላይነር ሆቴል በጀመረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት በኔፓድ የገንዘብ ድጋፍ በኖርዳ የቴክኒክ እገዛ ተግባራዊ የሆነው ፕሮግራም ውጤታማ ነበር ብለዋል፡፡

ሁለተኛው ዙር ከአንደኛው ከተገኘው ልምድና ተሞክሮ በመነሳት በስድስት ክልሎች፣ በሰላሣ ወረዳዎችና በስድስት ፕሮግራሞች እንሰራዋለን ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

ይሰራባቸዋል የተባሉት ክልሎች አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ትግራይ፣ አፋርና ሶማሌ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰኔ 9፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፋይዳ ያላቸውና ተስፋ የሚሰጡ የፈጠራ ስራዎች በመጀመሪያ የሳይንስና ፈጠራ ኤግዚብሽን ላይ ቀረቡ፡፡
 • የውበት እና ንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች አቀማመጣቸው ካላማረ ውጤታቸው የከፋ ይሆናል ተባለ፡፡
 • በገንዘብ ብድር ረገድ ተዘንግተዋል የተባሉ መሐከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከዓለም ባንክ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር አገኙ፡፡
 • የቤንሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ትላንትና አስቸኳይ ጉባኤ በማድረግ አዲስ ፕሬዝዳንት መሾሙ ተሠማ፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሰይፉ ፋንታሁን በ50 ሺ ብር ዋስ ተፈታ

በዛሬው ዕለት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎች በሥም ማጥፋት ክስ ተመስርቶበት የቀረበው ሰይፉ ፋንታሁን በ50 ሺ ብር ዋስ ከእስር ተፈትቶ ጉዳዩን በውጪ ሆኖ እንዲከታተል ፍርድ ቤቱ ውሣኔ ማስተላለፉን ሰምተናል...
አስተያየት ይፃፉ (3 Comments)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers