• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የአሸንዳ በዓል በድምቀት ሊከበር መታሰቡን ሰማን፡፡

በሃገራችን ካሉት በዓላዊ አከባበር አንዱ የሆነው የአሸንዳ በዓል ከነሐሴ አካባቢ ጀምሮ የሚከበር ሕዝባዊ በዓል ነው፡፡ የዘንድሮው የአሸንዳ በዓል በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎችና አዳራሾች በዓሉ ሲከበር መቆየቱን አስታውሶ ነሐሴ 29/2008 ዓ.ም በድምቀት እንደሚከበር የትግራይ ሴቶች ማህበር የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ነግረውናል፡፡

ወ/ሮ ምህረት ምናሰብ ነሐሴ 29 ከ14 ሺህ በላይ ታዳጊዎች በተገኙበት በብሔራዊ ባህላዊ ማዕከል ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚከበር በፃፉልን ደብዳቤ ጠቁመዋል፡፡የአሸንዳ በዓል ለሃገራችን ቱሪዝም መስህብ ሊሆን እንደሚችልና ለወጣቶች መተላለፍ ከሚገባቸው እሴቶች አንዱ መሆኑን ወ/ሮ ምህረት ጠቅሰዋል፡፡

እሸቴ አሰፋ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በሥራ ባሕሪያቸው የተነሳ ለጉበት በሽታ ሊጋለጡ ለሚችሉ ዜጐች የመከላከያ ክትባት ሊሰጣቸው ነው

በስራ ባሕሪያቸው ምክንያት ለጉበት በሽታ ለሚጋለጡ የህክምና ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ክትባት መስጠት ልትጀምር ነው፡፡

ክትባቱን በሚቀጥሉት ሦስት አመታት ለሁሉም የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ክትባቱን ለመስጠት ታቅዷል ተብሏል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ እንደተናገሩት ለህክምናው  የሚውለው መድኃኒት በሀገር ውስጥ እንዲመረት ከአንድ የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አምራች ፋብሪካ ጋር መንግሥት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የመድኃኒቱ በሀገር ውሰጥ መመረት ታማሚዎች መድኃኒቱን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙት ያስችላል ብለዋል፡፡

መድኃኒቱን ለመጠቀም አንዱ ችግር የነበረው የዋጋው ውድነት እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

ፋብሪካው መድኃኒቱን ወደ ውጭም የሚልክበት እድል እንደሚፈጠር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ በጉበት በሽታ ሊጠቁ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡት ዜጐች ከ10 አመት በፊት የተወለዱት እንደሆኑ ዶክተር ከሰተብርሃን ተናግረዋል፡፡

ከአስር አመት ወዲህ ለተወለዱ ህፃናት ግን በሽታውን የሚከላከል ክትባት መስጠት ስለተጀመረ ስጋቱ የሣሣ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሙያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከሚወስዱት ከ60 በመቶ በላይ የሚያልፉበት ደረጃ ቢደረስም ውጤቱ አሁንም ደረት የሚያስነፋ አይደለም ተባለ

በዚህ ዓመት በአዲስ አበባ የሙያ ብቃት ምዘና ከወሰዱ አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ባለሙያዎች መካከል ብቁ ሆነው የተገኙት 62 ነጥብ 2 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ተባለ…

ተመዝነው ያላለፉትም ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ሥልጠና መስጠቱ ላይ ትኩረት እየተሰጠው አይደለም ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ምዘና ከወሰዱት መካከል የቢዝነስ ዘርፉ በዛ ያሉ ባለሙያዎችን በማስመዘን የመጀመሪያውን ደረጃ መያዙን ተናግረዋል፡፡

የግንባታ ዘርፉ በሁለተኛነት ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን የጤና ሙያተኞች በተመዛኞች ቁጥር ሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 16፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ ድርጅት ታሪፍ ማስተካከያ ላደርግ ነው አለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ለመጪዎቹ 14 አመታት የአፍሪካ ሀገራት የሚተዳደሩበት አለም አቀፍ የወባ መከላከል የተግባር ስትራቴጂ ፀድቋል፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በሥራ ባሕሪያቸው የተነሳ ለጉበት በሽታ ሊጋለጡ ለሚችሉ ዜጐች የመከላከያ ክትባት ሊሰጣቸው ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የሙያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከሚወስዱት ከ60 በመቶ በላይ የሚያልፉበት ደረጃ ቢደረስም ውጤቱ አሁንም ደረት የሚያስነፋ አይደለም ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ጂኦሎጂካል ሰርቬይ የኤሌክትሪክና የውሃ መቋረጥ ሥራዬ ላይ እንቅፋት ፈጥሮብኛል አለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

66ኛው የዓለማቀፉ የጤና ድርጅት የአፍሪካ አካባቢ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል

ጉባኤው በ5 ቀናት ቆይታው ወባ እና HIV ኤድስን ጨምሮ በተለያዩ የጤና ችግሮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በጤናው መስክ ቀላል የማይባሉ ውጤቶች በኢትዮጵያና በአፍሪካ መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡

ያም ሆኖ ግን አሁንም ብዙ ቀሪ ስራዎች አሉ ነው ያሉት፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ከሰተ ብርሃን አድማሱ በጤናው ዘርፍ እስካሁን የተገኙ ውጤቶች ቁርጠኝነቱ ካለ የማይሳካ ነገር እንደማይኖር ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

የጉባኤውን ተሳታፊዎችም በቆይታችሁ ወቅት የጎደለ ወይም ቅር ያላችሁ ነገር ካለ ንገሩን እኔና የመሰሪያ ቤቴ ሰዎች ፈጥነን እናሟላለን ብለዋል፡፡ ተሰናባቿ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማርጋሬት ቻንን ለጉባኤው ተሳታፊዎች ንግግር አድርገዋል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ በሚገኙ ሉካንዳ ቤቶች አገር አቀፍ የጤና አጠባበቅ ቁጥጥር ሊካሄድ ነው ተባለ

በወረርሽኝ መልክ የተከሰተው የአተት በሽታ አሁን የታማሚው ቁጥር ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ ግን በቁጥጥር ስር አልዋለም ተባለ፡፡ የክረምት ወቅት ስላልተገባደደ ዳግም እንዳያገረሽ ስጋት መኖሩንም ሰምተናል፡፡

የከተማዋ ጤና ቢሮ እና የምግብና የመድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርተው በሰጡት መግለጫ በ4 ክፍለ ከተሞች አልፎ አልፎ አንድ እና ሁለት ታማሚዎች ብቅ ከማለታቸው ውጪ ቁጥሩ እየጨመረ አይደለም ብለዋል፡፡

ይህም የታየባቸው ክፍለ ከተሞች አቃቂ ቃሊቲ፣ ጉለሌ፣ አራዳ፣ ቂርቆስ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ናቸው፡፡ በቦሌ የካና ኮልፌ ክፍለ ከተሞች ግን አሁንም የአተት ታማሚዎች ቁጥር የበዛ ነው ተብሏል፡፡

መሰረት በዙ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ከጥጥ አምራቾች እና ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር እየተመካከረ ነው

የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ከጥጥ አምራቾች እና ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር እየተመካከረ ይገኛል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ታደሰ ኃይሌ በተገኙበት የ2008 የበጀት ዓመት የጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም የጥጥ አምራቾች ስራን እንቅስቃሴ በተመለከተ ሪፖርቶች ቀርበው ተደምጠዋል፡፡

ከሀገር ውስጥ አምራቾች ጋር በተደረገው ንግግር ችግሮች ተብለው ከተሰሙ ነጥቦች መሃከል ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ከመንግስት የተለያዩ ድጋፎች ተሰጥቷቸው የሚያመርቱ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ፋንታ በሀገር ውስጥ ችርቻሮ ላይ ተሰማርተዋል መባሉ ነው፡፡

ኢንዱስትሪዎቹ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ድጋፍና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ከተሰጧቸው በኋላ ምርቶቻቸውን በሀገር ውስጥ መቸርቸራቸው የሀገር ውስጡ አምራቹን እየጎዳ ነው ተብሏል፡፡ የጥጥ ምርት ገበያው ካለፈው ጊዜ የተሻለ ነው፤ ይሁንና  አሁን ያሉት ኢንዱስትሪዎች አቅማቸው ካልተጠናከረ የጥጥ ምሩቱም ተመልሶ ገበያውን ያጣል ተብሏል፡፡

የ2008 ዓ.ም የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ጥጥ አምራቾች ማህበር ከኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በተወያዩ ጊዜ በ2009 ዓ.ም ስለሚሰራቸው እቅዶቹ እና ከመንግስት ሊደረግለት ስለሚገባው ድጋፍ በኢሊሌ ሆቴል እየተወያዩ ይገኛል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 13፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

 • የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ ዘንድሮ 350 ሚሊየን ብር ገቢ አግኝቻለሁ ከሁለት መቶ በላይ ቤት የያዙ ህገ-ወጦችን አስለቅቄያሁ ብሏል፡፡ (ምስክር አወል)
 • ኢዴፓ በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ነበረኝ ያለው የልዩነት ኃሳብ አልተነገረልኝም ማለቱን የዕለቱ ሰብሳቢ ሐሰት ነው ማለታቸው ተሰማ፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • ዘንድሮ ከበጎ ፍቃደኞች ከአምናው የተሻለ የደም መጠን ተሰበሰበ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ለከተማዋ መንገዶች የአገልግሎት ክፍያ የሚጠይቋችሁ ካሉ ድርጊቱ ህገ-ወጥ ነውና ጠቁሙኝ አለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በወረርሽኝ መልክ የተከሰተው የአተት በሽታ አሁን የታማሚው ቁጥር ቢቀንስም ሙሉ በሙሉ ግን በቁጥጥር ስር አልዋለም ተባለ፡፡ (መሰረት በዙ)
 • የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ከጥጥ አምራቾች እና ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር እየተመካከረ ነው፡፡ (የኔነህ ሲሳይ)
 • የመንግስት ተቋማት እርስ በርስ ተናብበው ባለመስራታቸው በመንገድ ዘርፍ ብቻ በየዓመቱ በቢሊየን የሚቆጠር ብር ይባክናል ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • በአዲስ አበባ በሚገኙ ሉካንዳ ቤቶች አገር አቀፍ የጤና አጠባበቅ ቁጥጥር ሊካሄድ ነው ተባለ፡፡ (መሰረት በዙ)
 • 66ኛው የዓለማቀፉ የጤና ድርጅት የአፍሪካ አካባቢ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡ (ንጋቱ ረጋሳ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 12፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በያዝነው የክረምት ወቅት በሶማሌ ክልል በጎርፍ ሊፈናቀሉና ጉዳትም ሊደርስባቸው ይችላሉ የተባሉ 315 ሺ ዜጎች ተለይተዋል ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያ በያዝነው ዓመት ከ42 500 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ነፃ የአንቡላንስ አገልግሎት ሰጠሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ሰፋፊ የመሬት ይዞታ ላላቸው ኤምባሲዎች ካርታ እየተሰጣቸው ነው ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በኢትዮጵያ ካሉ ተሽከርካሪዎች 60 % ያህሉ የሚሽከረከሩት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ነው ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ነሐሴ 10፣2008

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ክፍል ስድስት

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር ነሐሴ 10፣2008
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ቶታል ኢትዮጵያ ነዳጅ በየትኛው ማደያ እንዳለ ለማወቅ የሚያስችል የሞባይል አፕልኬሽን ስራ ላይ አዋልኩ አለ

በአዲስ አበባ ባሉት 35 የቶታል ነዳጅ ማደያዎች መካከል በየትኛው ማደያ ነዳጅ እንደሚገኝ ቦታው ደርሰው ሳይሆን ቀድመው ማወቅ የሚችሉበትን መላ አበጅቻለሁ ሲል ተናግሯል፡፡ አፕልኬሽኑን በዘመን አፈራሽ ስልኮች ላይ በመጫን የት አካባቢ ነዳጅ እንዳለ በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል ሲሉ የቶታል ኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ኃላፊ አቶ መስፍን ተፈሪ ተናግረዋል፡፡

አፕልኬሽኑን ለመጫን በጉግል ፕሌይ ስቶር በአፕል ስቶር ውስጥ በመግባት ቶታል ሰርቪስ የሚለውን በመፈለግ መጫን ይቻላል ተብሏል፡፡ ቶታል ቴክኖሎጂውን ባስተዋወቀበት ስነ ስርዓት ደምበኞች በማደያው የተለያዩ አገልግሎቶችን ከተጠቀሙ በኋላ ከM ብር ጋር በተመተባበር ክፍያውን በተንቀሳቃሽ ስልክ የገንዘብ ማስተላለፍ ዘዴ መክፈል ይችላሉ ሲሉ አቶ መስፍን ተናግረዋል፡፡

መሰረት በዙ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers