• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የኢትዮጵያ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ወጪ ንግድ ገቢ እየቀነሰ ነው ተባለ

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከቆዳና የቆዳ ውጤቶች የወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ16 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ቅናሽ አለው ተባለ…ካለቀለት ቆዳና የቆዳ ውጤቶች የወጪ ንግድ 185 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት ተወጥኖ ነበር፤ ማግኘት የተቻለው ግን 116 ነጥብ 35 ሚሊየን ዶላር መሆኑን ሰምተናል፡፡

ይህም ከእቅዱ ጋር ሲመሣከር አፈፃፀሙ 63 በመቶ ብቻ ነው እንደማለት ነው፡፡ ከቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት እንደሰማነው በ2007 የበጀት ዓመት ያለቀለት ቆዳንና የቆዳ ውጤቶችን ለውጪ ሀገራት በመሸጥ 132 ሚሊየን ዶላር ማግኘት ተችሎ ነበር፡፡

በዚህ ዓመት የወጪ ንግዱ በ16 ሚሊየን ዶላር ያነሰ አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡ ከምርቶቹ መካከል ቅናሽ የታየበትም ያለቀለት ቆዳ ሲሆን ከጉድለቱ የ18 ነጥብ 81 ሚሊየን ዶላር ያህሉን ድርሻ ይዟል፡፡ በሌላ በኩል ግን መጠናቸው ትንሽም ቢሆን በሌሎች የቆዳ ውጤቶች የወጪ ንግድ ገቢ ላይ ከአምናው የተሻለ ገቢ መገኘቱንም ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዞር በተደጋጋሚ ጨረታ አልሸጥ ያሉትን ድርጅቶች በድርድር ላስተላልፋቸው አስቤያለሁ አለ

የባህር ዳርና የኮምቦል ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች በተደጋጋሚ ለጨረታ ሽያጭ ቢቀርቡም ፈላጊ ማግኘት አልቻሉም…መንግሥት እስኪ በድርድር ሽያጭ ልሞክራቸው ብሎ ከዛሬ ጀምሮ ለተደራዳሪዎች አቅርቧቸዋል ተባለ፡፡

ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ አሰበ ከበደ እንደነገሩን የባህርዳርና የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች በባለሀብቶች እጅ ቢገቡ የተሻለ ያመርታሉ በማለት በተደጋጋሚ ለጨረታ ሽያጭ ቢቀርቡም ፈላጊ ስላልመጣላቸው ከዛሬ ጀምሮ እስከ መስከረም ሰላሳ ተደራድሮ የሚገዛ ባለሃብት ከመጣ በማለት ለድርድር ሽያጭ አቅርበናቸዋል ብለዋል፡፡

ከእነዚህ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ጋር የኢትዮጵያ ቆርኪና ጣሳ ፋብሪካ ለጨረታ ሽያጭ መቅረቡንም አቶ አሰበ ነግረውናል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አሁን የሚያስተዳድራቸው 24 ድርጅቶች በእጁ እንደሚገኙም ሰምተናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 5፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ዘንድሮ በተለያዩ ክልሎች አዳዲስ የደለል ወርቅ የኢንዱስትሪ እና የብረት ማዕድኖች መገኘቱ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን የትራንስፖርት ስምሪትን የሚቆጣጠሩልኝ ከ300 በላይ ሠራተኞችን አሰልጥኜ ላሰማራ ነው አለ፡፡ (ምስክር አወል)
 • ከአንድ አመት በላይ ለእድሣት ተዘግቶ የከረመው የአዲስ አበባ ሙዚየም ዕድሣቱ ተጠናቋል በቅርቡም በአዲስ መልክ ሥራ ይጀምራል ተብሏል፡፡ (መሠረት በዙ)
 • መንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዞር በተደጋጋሚ ጨረታ አልሸጥ ያሉትን ድርጅቶች በድርድር ላስተላልፋቸው አስቤያለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ማስፋፊያ የአዋጭነት ጥናቱ እየተካሄደ ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የኢትዮጵያ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ወጪ ንግድ ገቢ እየቀነሰ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የማዕድን ላብራቶሪ አለመኖሩ የመስኩን ባለሃብቶች ጊዜና ገንዘብ እያባከነው መሆኑ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • ለኢትዮጵያ ምርጥ የተባሉ የሶፍትዌር ፈጠራዎች ተሸለሙ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሽያጭ የሚወገዱ ያገለገሉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ለጨረታ ከወጡ በኋላ የሚደርስባቸውን መጓደል ለመከላከል የሚያስችል አዲስ የመተማመኛ ሰነድ መረቀቁ ተሠማ

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በጨረታ የሸጥኳቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ተሽከርካሪዎች ንብረት ጎድሎ እየተገኘ እጀ ሰባራ እያደረገኝ ነው፣ ደንበኞቼንም እያማረረ ነው አለ፡፡

ከመሥሪያ ቤቶቹ ጋር የምፈራረመው መተማመኛም ንብረቱን ከመጉደል ስላላተረፈው አዲስ መተማመኛ ለማርቀቅ ተገድጃለሁም ብሏል፡፡

አገልግሎቱ በየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ያለአገልግሎት ቆመው ፀሐይና ዝናብ የሚፈራረቅባቸውን በደለል ተሞልተው ሳር የበቀለባቸውን ተሽከርካሪዎች በጨረታ በመሸጥ ወደ ሃብትነት ይቀይራል፡፡

በዚህ አመት ብቻ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የተያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በሽያጭ አስወግዶ 193 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ለመንግሥት አስገኝቷል፡፡ ከተለያዩ 45 መሥሪያ ቤቶችም 267 ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ 41 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር መገኘቱን ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለመኪና አደጋ ተጐጂዎች መታከሚያ ሊውል የሚገባው ገንዘብ በአግባቡ ሥራ ላይ አልዋለም ተባለ

በተሽከርካሪ የተለያየ ደረጃ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ማናቸውም የጤና ተቋማት ሄደው ያለምንም ክፍያ እስከ ሁለት ሺህ ብር የሚደርስ ህክምና ማግኘት ይችላሉ…

ተቋማቱ ህክምናውን ከሰጡ በኋላ ክፍያውን በአካባቢያቸው ካሉ የጤና ጽ/ቤቶች ማግኘት እንደሚችሉ ከመድን ፈንድ አስተዳዳር ኤጀንሲ ሰምተናል፡፡

የመድን ዋስትና ሽፋን ባላቸው ተሽከርካሪዎች ለተገጩ ተጎጂዎች የሚውል ክፍያ ከኢንሹራንስ ድርጅቶች ተሰብስቦ በጽ/ቤቶቹ ይቀመጣል ነው የተባለው፡፡

የመድን ዋስትና ሽፋን በሌላቸው እና ገጭተው ባመለጡ ተሽከርካሪዎች ለተገጩ ሰዎች የሚውለው ክፍያ ደግሞ ከመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ የሚገኝ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ይሁንና አስራሩ በተለይ በክልሎች በአብዛኛው ተግባራዊ እየሆነ አይደለም ተብሏል፡፡ በመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ የኮሙኒኬሽን፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ ወንድም እንደነገሩን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ይህ መብት እንዳላቸው ብዙ አያውቁም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ባለሥልጣን በገበያ ውስጥ የኢትዮጵያን አስገዳጅ የጥራት ደረጃ መሥፈርት ያላሟሉ የታሸጉ ውሃዎችን አግኝቻለሁ አለ

በኢትዮጵያ በተለያየ ስያሜ ለገበያ ቀርበው ከሚቸበቸቡት የታሸጉ የመጠጥ ውሃዎች ውስጥ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶችም ይገኙበታል ተባለ…

ይሄን ያለው የፌዴራል ንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ነው፡፡

በባለሥልጣኑ የፍተሻ እና የቁጥጥር ሥራም በወጡት መስፈርቶች መሰረት ደረጃቸውን ያልጠበቁ የታሸጉ ውሃዎች በገበያው ተገኝተዋል መባሉን ሰምተናል፡፡

ወሬውን ለሸገር የነገሩት የባለሥልጣኑ ምርመራ እና ክስ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ብሩክ ገመዳ ናቸው፡፡

ባለሥልጣኑ በገበያው ውስጥ ያልሆኑትን ነን የሚሉትን የውሃ አምራች ኩባንያዎች በገበያ ውስጥ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡

ምርምራዬንም ስላጠናቀኩኝ ቀጥሎም ክስ እመሰርትባቸዋለሁ ማለቱን ሰምተናል፡፡

ወደፊትም እንዲህ ያሉ የማጭበርበር ምርመራዎች በፌዴራል ፖሊስ እና ክሱ ደግሞ በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መሠረት እንደሚመሰረት አቶ ብሩክ ነግረውናል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይም ሌሎች የማጣራት ሥራው እየተሰራ ነው የተባለ ሲሆን አጠቃላይ ባለሥልጣኑ ደረጃቸውን ያልጠበቁትን የታሸጉ ውሃዎችና ያልሆኑትን ነን የሚሉትን አምራቾች እነማን እንደሆኑ ሥራዬን ካጠናቀኩ በኋላ እነግራችኋለሁ ብሏል፡፡

ተህቦ ንጉሴ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የድሬ ለገዳዲና ገፈርሳ ግድቦች ሞልተዋል ተባለ

የድሬ ለገዳዲና ገፈርሳ ግድቦች ሞልተዋል ተባለ…ከግድቡ በታች ያሉ ነዋሪዎችና ተቋማት እንዲሁም በአካባቢው የሚሄዱ መንገደኞች የጐርፍ አደጋ እንዳይገጥማቸው ተገቢውን ጥንቃቄ ያድርጉ ሲል የውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አስጠነቀቀ፡፡

ግድቡ በአመቱ አጋማሽ በገጠመው የውሃ መጠን መቀነስ ከለገዳዲና ከድሬ ውሃ የሚያገኙ የባለሥልጣኑ ደንበኞች ፈረቃ ገብተዋል ያሉት የባለሥልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወ/ሮ እፀገነት ተስፋዬ አሁን ላይ በቂ የውሃ ምርት በመኖሩ የውሃ ፈረቃው ቀርቷል ብለዋል፡፡

ይሞላሉ ተብለው ከሚጠበቁበት ጊዜ ቀድመው ሞልተዋል የተባሉት የድሬ፣ ለገዳዲና ገፈርሳ ግድቦች ፈስሰው በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ሲሉ ወ/ሮ ፀገነት መክረዋል፡፡

መሰረት በዙ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 4፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • በአዲስ አበባ ከፍተኛ የድምፅ ብክለት የበዛባቸው ጭፈራ ቤቶችና ባርና ሬስቶራንቶች ባለቤቶች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በተሽከርካሪ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ካሣ ተከፈለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • ኢትዮጵያ በአቪየሽን ኢንዱስትሪ ያስተማረቻቸው በቂ ባለሞያዎች የሏትም ተባለ፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • ዘንድሮ በህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ መንገድ የተያዙ ንብረቶች 1 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ናቸው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ለመኪና አደጋ ተጐጂዎች መታከሚያ ሊውል የሚገባው ገንዘብ በአግባቡ ሥራ ላይ አልዋለም ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • አዲስ አበባ ዕድገቷን ያገናዘበ ሙዚየም ሊገነባላት ነው ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የትራንስፖርት ባለሥልጣን የሕዝብ መጓጓዣ ተገልጋዮችን ዕርካታ የዳሰሣ ጥናት አካሂጃለሁ አለ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማኅበር ለሚያከናውናቸው ተግባራት ማገዣ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ዕርዳታ አገኘ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በሽያጭ የሚወገዱ ያገለገሉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ለጨረታ ከወጡ በኋላ የሚደርስባቸውን መጓደል ለመከላከል የሚያስችል አዲስ የመተማመኛ ሰነድ መረቀቁ ተሠማ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • የንግድ ውድድርና የሸማቾች ባለሥልጣን በገበያ ውስጥ የኢትዮጵያን አስገዳጅ የጥራት ደረጃ መሥፈርት ያላሟሉ የታሸጉ ውሃዎችን አግኝቻለሁ አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • የድሬ ለገዳዲና ገፈርሳ ግድቦች ሞልተዋል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ነሐሴ 3፣2008

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.ክፍል አምስት

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር Vegetarian Diet አትክልት ብቻ ስለመመገብ፣ ጥቅም እና ጉዳቶች  ነሐሴ 3፣2008
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በባሕርዳር ከተማ የባንኮች አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ነው ተባለ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት የባንኮች አገልግሎት በዋና ከተማዋ ባህርዳር እስካሁን መቋረጡ ተሰማ…

ሸገር ወሬውን የሰማው ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ከሆኑት አቶ ንጉሱ ጥላሁን  ነው፡፡

ተቃውሞ ከተነሳበት ቀን ጀምሮም የደህንነቱ ነገር የገንዘብ ተቋማቱ ስላሳሰባቸው ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸውን ኃላፊው ነግረውናል፡፡ በባህርዳር ከተማ የባንኮች አገልግሎት ብቻም ሳይሆን የተቋረጠው ትላልቅ ሆቴሎችና የንግድ ማዕከላትም ጭምር እንደሆኑ አቶ ንጉሱ ነግረውናል፡፡

ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ተቋማት መቼ ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ ብለን የጠየቅናቸው ኃላፊው የክልሉ መንግሥት የአካባቢውን ፀጥታ ወደነበረበት ለመመለስ እየሰራ ነው በቀናት ውስጥም አገልግሎቱ ይጀመራል ብለውናል፡፡

በአማራ ክልል በጐንደር ከተማ አስቀድሞ የተነሳው ውዝግብ፣ ግጭትና ተቃውሞ አሁን መልክ በመያዙ የከተማው እንቅስቃሴ እንደነበር ሆኗል ሲሉም ነግረውናል፡፡ በአማራ ክልል የተቋረጡትን ትልልቅ የገንዘብ ተቋማትን በተመለከተም ሸገር አንዳንዶቹን ባንኮች አነጋግሮ ስራው መቋረጡን ማረጋገጥ ችሏል፡፡ አንዳንዶቹም የሥራ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት በቀጠሮ ተለይተውናል፡፡

ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ባለፈው የበጀት ዓመት ለድርቅ ተጐጂዎች 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ቶን ስንዴ መግዛቱን የመንግሥት ግዢ መሥሪያ ቤት እወቁልኝ አለ

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በድርቅ ለተጐዱ ዜጐች ከተገዛው 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ 410 ሜትሪክ ቶን ያህሉ የተገዛው ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር ነው ተባለ…

ከተፈፀመው 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ መካከል 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ያህሉ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለተጐጂዎቹ መሰራጨቱን ሰምተናል፡፡

መንግሥት በዚህ አመት ከፈፀመው የ18 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ግዢ የ11 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ያህሉ ወጪ የተደረገው በድርቅ ለተጐዱ ዜጐች ለሚሆን የስንዴ ግዢ መሆኑን የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ተናግሯል፡፡

በአገልግሎቱ የግዢ ባለሙያ የሆኑት አቶ ወርቁ ገዛኸኝ እንዳሉት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በድርቅ ለተጐዱ ዜጐች የሚሆን 2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ ተፈፅሟል፡፡

ከመካከሉም 410 ሜትሪክ ቶኑ የተገዛው ከዓለም ባንክ በተገኘ የ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብድር ነው ብለዋል፡፡

በመንግሥት በጀት ደግሞ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በ9 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ወጪ ግዢ መፈፀሙን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers