• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በደረቅ ወደቦች የተከማቹ 2 ሺ 236 ኮንቴነሮችና 61 ተሽከርካሪዎች በመንግሥት ሊወረሱ ነው ተባለ

በደረቅ ወደቦች የተከማቹ 2 ሺ 236 ኮንቴነሮችና 61 ተሽከርካሪዎች በመንግሥት ሊወረሱ ነው ተባለ፡፡በደረቅ ወደብ ላይ ለመቆየት ከሚፈቀደው 60 ቀን በላይ ቆይተዋል ከተባሉት ኮንቴነሮች መካከል 616ቱ የመንግሥት ሲሆኑ 156ቱ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ንብረት ናቸው ተብሏል፡፡

1 ሺ 466 ያህሉ ደግሞ የግል አስመጭ ንብረቶች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ለሸገር ተናግሯል፡፡ከኮንቴነሮቹ በተጨማሪ ከሚወረሱት 61 ተሽከርካሪዎች መካከልም 2ቱ ብቻ የመንግሥት መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ከ20 ቀን በፊት በደረቅ ወደቦች የተከማቹ ኮንቴነሮችን አስመጭዎቹ እስከ ታህሣስ 30 ቀን ድረስ እንዲያነሱ ተነግሯቸው ነበር ያሉን በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ድጋፍና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደበሌ ቀበታ ናቸው፡፡አቶ ደበሌ እንዳሉት በጊዜ ገደብ ውስጥ 768 የግል ድርጅቶች ኮንቴነሮቻቸውን አንስተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ሰሞኑን በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ሳቢያ አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ተናገሩ

ሰሞኑን በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ሳቢያ አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም ሲሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡መንግሥት በበኩሉ ሰሞኑን እየተካሄደ ያለው ጥልቅ ተሀድሶ ህብረተሰቡ መልካም አስተዳደር እንዲያገኝ እና በአገልግሎት ሰበብ እንዳይጉላላ ለማድረግ የታሰበ ነው ብሏል፡፡

የፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሃብት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጌታቸው አብዲሳ ለሸገር እንደተናገሩት በህብረተሰቡ ውስጥ ሊነሱ የሚችሉ ቅሬታዎችን ለማስወገድ እና በመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ነው የጥልቅ ተሀድሶ ስብሰባው እየተደረገ ያለው፡፡አገልግሎት ሰጪዎችም ግማሽ ቀን ህዝቡን እያገለገሉ ግማሽ ቀን ስብሰባ በማድረግ ህዝቡ አገልግሎት እንዳያጣም እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ስብሰባውንም ቶሎ ጨርሰው ወደ ሥራ ለመመለስ ያሰቡ መሥሪያ ቤቶችም ቀኑን ሙሉ እየተሰበሰቡ ነው ያሉት አቶ ጌታቸው በነዚህ ቀናት ውስጥ የሚፈለግባቸውን ባለማድረጋቸው ቅጣት ወይም ሌላ ችግር ሊመጣ ይችላል ብሎ የሰጉ ባለጉዳዮች ካሉ ስጋት አይግባቸው እንዲህ እንደማይደረግ ተስፋ አለኝ ብለዋል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ እስላም መቃብር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ከረፋዱ ለአምስት ሰዓት አስር ጉዳይ ገደማ የተነሣውን ሰደድ እሣት ለማጥፋት ርብርብ እየተካሄደ ነው

በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ እስላም መቃብር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ከረፋዱ ለአምስት ሰዓት አስር ጉዳይ ገደማ የተነሣውን ሰደድ እሣት ለማጥፋት ርብርብ እየተካሄደ ነው፡፡

ከእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን እንደሰማነው እሣቱ መሬት ላይ ባሉና ሰፊ ቦታ በያዙ ቁጥቋጦዎች ላይ የተነሣ ሲሆን ወደ ቤቶችና ጋራዦች እንዳይዛመት ሁለት ከባድ መኪኖችን ፣ አንድ ቦቴና አንድ አንቡላንስን የያዙት 25 የአደጋ ተከላካይ ሠራተኞች ጥረት እያደረጉ እንደሆነ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያው አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 3፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን መኖሪያቸው፣ አዲስ አበባን የሥራ ቦታቸው ያደረጉ ነዋሪዎች የትራንስፖርት ችግር አማሮናል አስቸኳይ መፍትሄ ከመንግሥት እንፈልጋለን ይላሉ፡፡ (ምሥክር አወል)
 • በኢትዮጵያ የቡና ወጭ ንግድን ለማበርታታት የታለመ አህጉራዊ ጉባዔ ሊካሄድ ነው፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የተነሳውን ሰደድ እሣት ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በ23ኛ እና በ24ተኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ከቀረቡ ቦታዎች ወደ መሬት ባንክ የገቡት በቁጥር ከፍተኛ ናቸው፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በደረቅ ወደቦች በጊዜ ያልተነሱ ከ2 ሺ በላይ ኮንቴነሮች በመንግሥት ሊወረሱ መሆኑ ተሠማ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ባለጉዳዮች መጉላላታቸውን ገለፁ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም ጥር 2፣2009

በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

በደቡብ ሱዳንና በብሉ ናይል በተፈጠረ ግጭት ቀዬአቸውን የለቀቁ ከ50 በላይ ስደተኞች ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ ተባለ

በደቡብ ሱዳንና በብሉ ናይል በተፈጠረ ግጭት ቀዬአቸውን የለቀቁ ከ50 በላይ ስደተኞች ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ ገቡ ተባለ፡፡ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማስታወቂያ ቢሮ ዛሬ እንደሰማነው ስደተኞቹ ግጭቱን ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ ከተሻገሩ በኋላ ፆሬ በተሰኘው መጠለያ እንዲገቡ የተደረገው ከትናንት በስትያ ነው፡፡

አሁንም ሌሎች ስደተኞች ድንበር አቋርጠው ይገባሉ ተብለው ይጠበቃሉ ሲል ቢሮው ነግሮናል፡፡በሌላ ወሬ ኢትዮጵያንና ሱዳንን በንግድም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ያገናኛል የተባለ 20 ነጥብ 56 ኪሎ ሜትር ጥርጊያ መንገድ ከትናንት በስቲያ ተመርቋል ተብሏል፡፡የክልሉ የገጠር መንገድ በ15 ሚልዮን ብር ወጪ ያሰራው ይሄ መንገድ ከአሶሳ  ወረዳ አብራሞ ተነስቶ ቁሽማጋኔ የተባለ ስፍራ ይደርዳሳል መባሉንም ሰምተናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካፒታል እድገት ከባንኩ የንብረት እድገት ጋር ተመጣጣኝ አይደለም ተባለ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካፒታል እድገት ከባንኩ የንብረት እድገት ጋር ተመጣጣኝ አይደለም ተባለ፡፡ የባንኩ የሀብትና ጠቅላላ ንብረት ንፅፅርም 4 ነጥብ 4 በመቶ ሲሆን ተቀባይነት ወዳለው የንፅፅር መጠን ማለትም 13 ነጥብ 2 በመቶ ሊያድግ ይገባልም ተብሏል፡፡

ይህንን ለማድረግ 26 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የካፒታል ጭማሪ ማድረግ እንደሚያስፈልገው ሰምተናል፡፡ወሬውን የሰማነው ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ካፒታል ለማሳደግ ይረዳል የተባለ የመንግሥት እዳ ሰነድ ረቂቅ አዋጅ በቀረበበት ጊዜ ነው፡፡

በረቂቅ አዋጁ መሠረት አሁን ባንኩ ባለው ወቅታዊ የካፒታል መጠንና የሀብት መጠኑን የተመጣጠነ ለማድረግ የሚያስፈልገውን የ26 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ልዩነት ወለድ በማይከፈልበት የመንግሥት ዕዳ ሰነድ አማካኝነት የሚከፈል ይሆናል፡፡የእዳ ሰነዱም ከ5 ዓመት የችሮታ ጊዜ በኋላ በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ እንደሚያልቅ ረቂቅ አዋጁ ያስረዳል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ካፒታል ለማሳደግ ይረዳል የተባለው የመንግሥት ዕዳ ሰነድ ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር እይታ ለበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 2፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ያስገነባውን የድንጋይ ከሰል ማቃጠያ ፕሮጀክት ሥራ አስጀመረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • በቅርቡ ሀገር አቀፍ ጉባዔ በሃይማኖት ተቋማት ይዘጋጃል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለሚከበረው 16ኛው የአርብቶ አደሮች ቀን በዓል ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በኩል የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባት መጀመራቸው ተሠማ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የካፒታል እድገት ከባንኩ የንብረት እድገት ጋር ተመጣጣኝ አይደለም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ባለፉት 5 ወራት የወጪ ንግድ ገበያ እንዳሰበችው አልተሳካላትም ተባለ

ኢትዮጵያ ባለፉት 5 ወራት የወጪ ንግድ ገበያ እንዳሰበችው አልተሳካላትም ተባለ…ንግድ ሚኒስቴር ለሸገር እንደተናገረው ባለፉት አምስት ወሮች ከተለያዩ ለውጭ ገበያ ከቀረቡ ምርቶች 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ነበር፡፡የተሳካው ግን 1 ነጥብ 02 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው ብሏል፡፡ ይህም ከእቅዱ የተሳካው 60 ነጥብ 34 በመቶ ብቻ ነው እንደማለት ነው፡፡

ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀርም 49 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ያለው ገቢ እንደተገኘ ሰምተናል፡፡ኢትዮጵያ የወጭ ንግድ ገቢዋ ያሽቆለቆለው ያቀረበቻቸው ምርቶች በጥራት ተወዳዳሪ መሆን ስላልቻሉ ነው ያሉን በንግድ ሚኒስትር ተወካይ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሽመልስ አረጋ ናቸው፡፡የአለም ገበያ መቀዛቀዙም ለገቢው መቀነስ ሌላው ምክንያት ነው ብለዋል፡፡ከመቶ በመቶ በላይ መጠን ያላቸው የቅባት እህሎች ለውጭ ገበያ ቢቀርቡም ያስገኙት ገቢ ግን ከታሰበው ከ86 በመቶ እንዳልበለጠም ተናግረዋል፡፡መቶ ሺ ቶን የቅባት እህል ተልኮ አንድ መቶ ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በገና በዓል ዋዜማ በዕለቱና በማግስቱ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በተለያዩ አደጋዎች 149 ሰዎች ለአካል ጉዳት ተጋልጠው አቤት ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ

በገና በዓል ዋዜማ በዕለቱና በማግስቱ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ በተለያዩ አደጋዎች 149 ሰዎች ለአካል ጉዳት ተጋልጠው አቤት ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ፡፡የሆስፒታሉ ተወካይ ዶክተር ገሊላ መንግሥቱ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ ወደ ሆስፒታሉ ከመጡ 149 ተጐጂዎች ውስጥ 120ው ለመኪና አደጋ የተጋለጡ ሲሆኑ ሌሎቹ በጠብና በስካር ሰበብ በመውደቅ ለተለያዩ የአካል ጉዳት የተዳረጉ ናቸው ብለዋል፡፡

ዶክተር ገሊላ በገና ዋዜማ ከዕለቱና በማግስቱ በጉዳት ወደ ሆስፒታላችን ከመጡት ሰዎች ውስጥ የ1 ሰው ህይወት አልፏልም ብለዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ጥር 1፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ከትላንት በስቲያ በዋለው የልደት በዓል አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ብቻ ከ5 ሺህ በላይ ዕርድ ማከናወኑን ሰምተናል፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • የወደቁትን አንሱ የአረጋውያን መጠለያ ማዕከል የአልጋ ቁራኛ ለሆኑ አረጋውያን የንፅህና መጠበቂያ ቸገረኝ እያለ ነው፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • በአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት ለድርቅ ተጋላጭ ለሆኑ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የአስቸኳይ ጊዜ የሰብአዊ ድጋፍ እየተሰጠ ነው ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ባለፉት አራት አመታት ከፕሮጀክት ጥናት እስከ ሬዲዮ ፕሮግራም ድረስ ለ“የኛ” ዝግጅት ድጋፍ ሲያደርግ የነበረው የእንግሊዙ DFID ድጋፉን ማቋረጡ ተሰማ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ውሃ በችርቻሮ የሚሸጡ ሰዎች ቆጣሪያቸው ተወሰደባቸው፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በጋና አዲሱ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ላይ ተገኙ፡፡ (ጌታቸው ለማ)
 • ኢትዮጵያ ባለፉት 5 ወራት የወጪ ንግድ ገበያ እንዳሰበችው አልተሳካላትም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
 • በገና በዓል በትራፊክና በሌሎችም አደጋዎች 149 ሰዎች አቤት ሆስፒታል ገቡ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በምሥራቅ አፍሪካ በጐሣዎችና በፖለቲካ ልዩነት ሰበብ የታጣውን ሰላም ለማስመለስና ሊከሰት የሚችለውን ግጭት ለማስወገድ በኢትዮጵያ ለሚደረገው ምክክር ቅድመ ዝግጅቱ ተጀምሯል፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers