• United Bank S.C.

  ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሕዳር 19፣ 2012/ የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል አገራት በመሪዎች ደረጃ ስብሰባቸውን ማካሄድ ጀመሩ

መሪዎቹ 13ኛውን የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እያካሄዱ ያሉት እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ነው፡፡ትናንትና በሚኒስትሮች ደረጃ ስብሰባውን ማካሄድ የጀመረው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)፣ በማህበሩ አደረጃጀትና አወቃቀር ዙሪያ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ ሰላጤ ጂኦፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአባል አገራቱን መሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋቸዋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 19፣2012/ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደረገው ስብሰባ መበተኑ ተሰማ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ መመሪያ ይዞ መጥቶ እንደነበር ተሰምቷል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዴት መመዝብ አለባቸው በሚሉና ሌሎች ግዴታዎችን የሚያሳይ መመሪያን ከፓርቲዎቹ ጋር ለመወያየት አቅዶ ነበር ተብሏል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በቀረበው መመሪያ ላይ ከመወያየታችን በፊት የፀደቀው ሕግ ላይ ቅሬታ አለን ብለዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በቀደመው ህግ ሳንነጋገር አሁን በመጣው መመሪያ ላይ አንመክርም ብለው ስብሰባው እንደተበተነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ለሸገር ተናግረዋል፡፡በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የምዝገባና የስነ ምግባር አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብን በተመለከተ ሊመክር የነበረው ጉባኤ በንትርክና ባለመስማማት ተስተጓጉሏል፡፡

ተህቦ ንጉሤ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 19፣ 2012/ አቶ ፍቃዱ ተሰማ የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሆነው ተሾሙ

የክልሉ መንግስት ከዚህ በተጨማሪ ለ5 ሰዎች ሹመት መስጠቱን ሰምተናል፡፡ ሸገር ከኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት እንደሰማው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አባል የነበሩት አቶ ፍቃዱ ተሰማ የአዲሱ የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡የኦዴፓ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ አረጋ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሆነው መሾማቸውን ሰምተናል፡፡

የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት የከተማ ፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የነበሩት አቶ ካሳሁን ጎፌ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ሆነው እንደተሾሙ ተነግሯል፡፡ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪ፤ አቶ ሳዳት ነሻ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የከተማ ፖለቲካ ዘርፍ አደረጃጀት ሀላፊ እንዲሁም አቶ አበራ ወርቁ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ሀላፊ በመሆን መሾማቸውን የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 19፣ 2012/ ማንን ምን እንጠይቅልዎ-ከካሽ ሬጂስተር ማሳደሻ ጋር የተያያዘው የቅጣት ጉዳይ ተገቢ ነውን?

ከካሽ ሬጂስተር ማሳደሻ ጋር የተያያዘው የቅጣት ጉዳይ ተገቢ ነውን? ግርማ ፍሰሐ የሚመለከታቸውን አነጋግሯል

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 19፣ 2012/ በመንግስት ተቋማት የሚከናወኑ ግንባታዎች አሁንም ድረስ አፈፃፀማቸው ላይ ጉድለት አለ፣ መረጃ ለመስጠትም ተባባሪ አይደሉም ተብሏል

በመንግስት ተቋማት የሚከናወኑ ግንባታዎች አሁንም ድረስ አፈፃፀማቸው ላይ ጉድለት አለ፣ መረጃ ለመስጠትም ተባባሪ አይደሉም ተብሏል፡፡
 • የሐዋሳ ኤርፖርት ግንባታ ከተያዘለት በጀት የ11 % ጭማሪ አሳይቶ መጠናቀቁ ሲገለፅ በተቃራኒው የጂንካ ኤርፖርት ደግሞ የ17 % ቅናሽ አሳይቶ ሊጠናቀቅ እንደቻለ ተነግሯል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 19፣2012/ በኢትዮጵያ የብሔር ጥያቄ ዛሬም ድረስ አጥጋቢ መልስ ያላገኘው ለምንድነው?

ዋለልኝ መኮንን፣ “የብሔሮች ጥያቄ በኢትዮጵያ” የሚለውን ታዋቂ አስተሳሰቡን ካወጣ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላም ጥያቄው ለምን በቅጡ አልተመለሰም?ንጋቱ ሙሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 19፣ 2012/ ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን፣ ኢትዮጵያ የተዘረፉባትን ቅርሶች ለማስመለስ የምታደርገውን ጥረት እደግፋለሁ ይላል

ኦፕን ሶሳይቲ ፋውንዴሽን የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ኢትዮጵያ የተዘረፉባትን ቅርሶች ለማስመለስ የምታደርገውን ጥረት እደግፋለሁ፣ ለዴሞክራሲ መጎልበት፣ ለፍትህ መስፈንና ለልማት የሚተጉ መገናኛ ብዙሃንን ለማገዝ ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡
 • ድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ቢሮውን በአዲስ አበባ ለመክፈት መዘጋጀቱንም ሰምተናል፡፡


ተስፋዬ አለነ የስክል ሪፖርት አለው
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 19፣ 2012/ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ 4 ተከሳሾች ላይ አዲስ ክስ መመስረቱን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተናገረ

ተከሳሾቹ ክስ የተመሰረተባቸው ከራዳር ግዢ ጋር በተያያዘ መሆኑን ሰምተናል፡፡ተከሳሾቹ 1ኛ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ 2ኛ ሌተናል ኮሎኔል ፀጋዬ አንሙት፣ 3ኛ ኮሎኔል ሸጋው ሙሉጌታ እና 4ኛ ተከሳሽ ኮሎኔል መሐመድ ብርሃን ናቸው ተብሏል፡፡ ሸገር ወሬውን ከጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ ሰምቷል፡፡ጠቅላይ አቃቤ ህግ የመንግስትን ስራ በማያመች አኳኋን በመምራት ከግዢ መመሪያ ውጪ ጥራቱን ያልጠበቀ ራዳር ከ214 ሚሊየን ብር በላይ በመግዛት ክስ እንደተመሰረተ ሰምተናል፡፡በዚህም በከባድ የሙስና ወንጀል በዛሬው ዕለት አዲስ ክስ ተመስርቷል፡፡

ተከሳሾች የብረታ ብረት ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ዋና ዳይሬክተር፣ በኮርፖሬሽኑ የሃይቴክ ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ፣ የቦርድ ፅህፈት ቤት ኃላፊ እና የኮርፖሬሽኑ የስነ ምግባር እና የህግ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ መቆየታቸው ተጠቅሷል፡፡ሰዎቹ የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በ2004 ዓ.ም በተወዳዳሪ ዋጋ፣ በጨረታ፣ ጥራት ባለው እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ግዢ መፈፀም ሲገባቸው ያለ መመሪያ እና ያለ ጨረታ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የግዢ ፍላጎት ሳይጠየቅ CELEC እና ALIT ከተባሉ የቻይና ኩባንያዎች ተመሳሳይነት ያላቸውን ራዳሮች ግዢ መፈፀማቸው ተሰምቷል፡፡

የክስ መዝገቡ እንደሚያስረዳው 2ኛው ተከሳሽ ከአንደኛው የቻይና ድርጅት 101 ራዳሮችን መጋቢት 5፣ 2004 ዓ.ም በጠቅላላ የውል ዋጋ ከ8 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ በሆነ ገንዘብ፣ SWR የተባለ ሞዴል 6 የጦር መሳሪያ ራዳር ለማቅረብ ውል ተዋውለዋል፡፡3ኛ ተከሳሽ ከሌላው የቻይና ኩባንያ ጥቅምት 30፣ 2004 ዓ.ም፣ ከ10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ገንዘብ 101 ተንቀሳቃሽ ራዳር ለማቅረብ ሜቴክን ወክሎ ያለ አግባብ ተዋውሏል መባሉን ሰምተናል፡፡ 4ኛው ተከሳሽ የህግ ጉዳይ ኃላፊ እንደመሆኑ መጠን ከኮርፖሬሽኑ የግዢ መመሪያ ውጪ ውል እንዲፀድቅ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር የግዢ ፍላጎት ሳይጠየቅ የተፃፈ መሆኑን እያወቀ ውሉን ያለ አግባብ ያፀደቀ መሆኑን የክሱ ዝርዝር ያስረዳል ተብሏል፡፡

እንደ አቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ALIT ከተባለው ኩባንያ 11 ራዳሮች CELEC ከተባለው ኩባንያ ደግሞ 100 ራዳሮች ኢንዱስትሪው የተረከበ እና ክፍያ የፈፀመ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ነገር ግን ለናሙና የመጣው ራዳር በሀገር መከላከያ ሰራዊት በመስክ በተደረገው ሙከራ ዘመናዊ ያልሆነ፣ ወጣ ገባ ለሆነ መልክዓ ምድር የማያገለግል፣ ሰው፣ እንስሳት እና ሌሎች ግዑዝ ነገሮችንም የማይለይ ነው ተብሏል፡፡ከሁሉም ድርጅቶች የተረከቧቸውን ራዳሮች እስካሁን ያለ አገልግሎት እንዲከማቹ በማድረግ በአጠቃላይ ለማይጠቅሙ ራዳሮች ግዢ ከ214 ሚሊየን ብር በላይ ክፍያ በመፈፀም በህዝብና መንግስት ላይ ጉዳት በማድረስ በከባድ የሙስና ወንጀል ተከስሰዋል፡፡ለዛሬ ህዳር 19፣ 2012 ዓ.ም ጠበቆችን ለማቅረብ ተቀጥረዋል፡፡

ተህቦ ንጉሤ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 18፣ 2012/ የሴቶች ጥቃት የሚወገዝበት የ16 ቀን የፀረ ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ

የሴቶች ጥቃት የሚወገዝበት የ16 ቀን የፀረ ፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ የዘንድሮ ትኩረቱ አካል ጉዳተኛ የሆኑና ከኤች አይ ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ሴቶች መሆናቸውን የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 18፣ 2012/ በኢትዮጵያ በ10,000 ተሽከርካሪዎች የ43 ሰው ሞት ይከሰታል

በኢትዮጵያ በ10 000 ተሽከርካሪዎች የ43 ሰው ሞት ይከሰታል፡፡ ይህን የሞት መጠን ለመቀነስ አገራዊ ንቅናቄ በያዝነው ህዳር ወር እየተካሄደ ነው፡፡
 • ከፍተኛ ቁጥር ያለው አደጋ የሚከሰተው በአዲስ አበባ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

በየነ ወልዴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሕዳር 18፣2012/ ጥቂት ወራት ለቀሩት የ2012ቱ አጠቃላይ ምርጫ ፓርቲዎች ምን እየሰሩ ነው?

ጥቂት ወራት ለቀሩት የ2012ቱ አጠቃላይ ምርጫ ፓርቲዎች ምን እየሰሩ ነው?


የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers