• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በአዲስ አበባ ሁለት ሰዎች በጐርፍ አደጋ ህይወታቸውን አጡ ተባለ

ባሳለፍነው ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 ገደማ ኮልፌ ቀራኒዬ ወረዳ 14 አስኮ አዲሱ ሰፈር ከሚገኘው ወንዝ ውስጥ የአንድ የ60 አመት ሰውዬ አስክሬን ተገኝቶ ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል፡፡ በዚያው ባሳለፍነወ ቅዳሜ ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ በአቃቂ ወረዳ አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ ጀርባ ካለ ወንዝ ውስጥ አንድ የ45 ዓመት ሰውዬ ሞተው ተገኝተዋል፡፡ ዘንድሮ ክረምት ከገባ በጐርፍ አደጋ ብቻ ሰባት ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባሥልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡
                                     
ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ይቀርብ የነበረው አልሚ ምግብ ከተቋረጠ 3 ወር መሆኑን ቦታው ድረስ ተገኝተው ተጎጂዎቹን የጎበኙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ተወካዮች ለሸገር ተናግረዋል

የክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ በበኩሉ በቂ የአልሚ ምግብ ክምችት አለን የተቋረጠ ነገርም የለም ብሏል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሶማሌ ክልል ስጢ ወረዳ ሰዴቶ ቀበሌ ድረስ በአካል ተገኝተው ተጎጂዎትን ያነጋገሩት የበጎ አድራጎት ድርጅት ተወካዮች ለሸገር እንደተናገሩት ተጎጂዎች አሁንም የውሃ አቅርቦት ችግር አለባቸው ሌላም አለብን ያሉትን ችግርም ነግውናል ብለዋል፡፡ የጉብኝቱ አላማም ተጎጂዎቹ ምን ችግር እንዳለባቸ ለማየትና የበጎ አድራጐት ድርጅቶችስ ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል የሚለውን ለመለየት እንደሆነ ከተወካዮች ሰምተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 11፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የሶማሌ ክልል ለድርቅና ጐርፍ ተጐጂዎች በቂ የአልሚ ምግብ ክምችት አለን ሲል የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ተወካዮች ግን አቅርቦቱ ከተቋረጠ 3 ወራት እንደሆነው ተናገሩ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • መሬት አጥነት የብዙሀኑ የገጠር ነዋሪ ችግር መሆኑ እያሣሰበን ነው ብለዋል ሰሞኑን ጥናታቸውን ያቀረቡ ምሁራን፡፡ ኑሮውን የግድ በመሬት ላይ ያደረገው የገጠር ነዋሪ ተስፋ አጥቷል ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ከ1 ሄክታር በታች በሆነ መሬት ላይ መተዳደሪያውን ያደረገው ህዝብ 60 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የአዲስ አበባ ገቢ ማስተዳደር ከጀመረ በኋላ የከተማዋ ገቢ እየጨመረ ቢመጣም ከንግድ እንቅስቃሴው አንፃር አሁንም የሚሰበሰበው ገቢ ዝቅተኛ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ያገረሸው ሁከት እንዲረጋጋ የተለመደ ትብብሯን እንድታደርግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠየቀ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ዘንድሮ በሊዝ ጨረታ የተላለፈው መሬት ከፍላጐቱ አንፃር አነስተኛ ነው ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በአዲስ አበባ የተሰጣ ልብስ የሰረቀውና የሚሰራበትን ድርጅት የዘረፈው ግለሰብ በእሥራት ተቀጡ፡፡ (ተክማርያም ኃይሉ)
 • በአዲስ አበባ ሁለት ሰዎች በወንዝ ውሃ ተወስደው ሞቱ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • የጤና ባለሙያዎች ከተመረቁ በኋላ ራሳቸውን በየጊዜው ከሚዳብሩ ዕውቀቶች ጋር የሚተዋወቁበት ሥርዓት ሊዘረጋ ነው፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 8፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ወደ ተሻለ ደረጃ ማሣደግ ትፈልጋለች ሲሉ የሀገሪቱ የፋይናንስ ሚንስትር ተናገሩ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ኢትዮጵያ ከአረብ ባንክ ኢኮኖሚ ልማት ቡድን ጋር የብድር ስምምነት መፈራረምዋ ተሠማ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዛሬ ሰባ ዓመት በፊት አንስቶ ውሣኔ የተሰጠባቸውን መዝገቦች ወደ ኮምፒውተር የመረጃ ቋት እያስገባሁ ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ተደራጅታችሁ ስሩ ተብለን ብንደራጅም ጉዳያችንን ግን ጉዳይ የሚለው አካል አጣን የሚሉ ወጣቶች ቅሬታቸውን አሰሙ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ሚድሮክ ጐልድ በመተከል የወርቅ ማዕድን ፍለጋውን ማጠናቀቁንና ወደ አምራችነት ለመግባት የመንግሥትን ፈቃድ እየተጠባበቀ መሆኑን ተናገረ፡፡ (ህይወት ፍሬስብሃት)
 • በጊዜያዊ ጠብ ፍል ውሃ በመድፋት በሰው አካል ላይ ጉዳት ያደረሰችው ተከሳሽ በእሥራት ተቀጣች፡፡ (ተክለማርያም ኃይሉ)
 • በሰሞኑ ሰሜን ጐንደር የተፈጠረው ሁከት ምንም ዓይነት ሕጋዊ ጥያቄ የሌለው ነው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ ተናገሩ፡፡ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • የመሬትና ንብረት ምዝገባ ምሩቃንን የሥራ ቅጥር ለማቀላጠፍ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከየክልል ከተማ መሥተዳድሮች ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ተመከሩ፡፡ (ፍቅርተ መንገሻ)
 • የበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማኅበራት መድረክ በአዲሱ ረቂቅ የገቢ ግብር አዋጅ የበኩሉን የማሻሻያ ኃሳብ ማቅረቡ ተሠማ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ኢትዮጵያን የሚጐበኙ ቱሪስቶችን ብዛት ለመጨመር የአገሪቱን ሰላማዊነት ይበልጥ ማጠናከር ያሻል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • በገርጂ ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት አዲስ በሚገነባው አለም አቀፍ ስቴዲየም ግቢ ውስጥ የሚገኘው መስጊድ ተለዋጭ ቦታ እየተፈለገለት ነው ተባለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

በዘንድሮ ክረምት በከሰል ጪስ 4 ሰዎች ታፍነወ ሞተዋል

አደጋው ይቀጥላል የሚል ስጋት ገብቶኛል ሲል የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ ንጋቱ ማሞ በጉለሌ ፂዬን ሆቴል ጀርባና በቦሌ ወረዳ 3 ክረምቱ ከገባ በከሰል ጪስ ታፍነው አራት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ብለዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ብርዱን ለመከላከል በማለት ጢሱ ያላለቀ እሳት ወደቤታቸው በማስገባት ዘጋግተው ሲቀመጡ እየታፈኑ ህይወታቸውን እስከማጣት ይደርሳሉ ያሉት አቶ ንጋቱ አምና በተመሳሳይ በከሰል ጢስ አደጋ 14 ሰዎች ሞተዋል ብለዋል፡፡

በአደጋው በብዛት ህይወታቸውን የሚያጡት የቤት ሰራተኞች ናቸው አሰሪዎች የጥንቃቄ መልዕክት ንገሯቸው እኛም በሰባቱ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶቻችን በኩል ስለከሰል ጢስ ጥንቃቄ የሚያስተምር በራሪ ወረቀቶችን እየበተንን ነው ብለዋል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 7፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.


 • የክረምቱን ብርድ ለመከላከል ጪስን ያልጨረሰ ከሰል የአራት አዲስ አበቤዎችን ህይወት አጠፋ፡፡ ህብረተሰቡ ቢጠነቀቅ ሲል የእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች መክሯል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በኦሞ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚኖሩ ዝሆኖች አደጋ እያንዣበበባቸው ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር አስራ አራተኛውን ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስን በአዲስ አበባ ሊያስተናግድ ነው፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • በተጠናቀቀው 2008 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዋነኛ ችግር በዳኝነት አሰጣጥ ሂደት ወቅት ብቃት ያላቸው ሞያተኞች አለመሟላትና ስራ መልቀቅ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
 • ለ7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሽልማት የላቀ የምርምርና የፈጠራ ውጤት ያስመዘገቡ ግለሰቦችን እና ተቋማትን ለመሸለም በወጣው ማስታወቂያ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመወዳደር የተመዘገቡት ጥቂት ናቸው ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)

  ተጨማሪ ያንብቡ...

  አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ ከአርመንያ ጋር የውጭ ጉዳይ ግንኙነቷን አጠናክራ መቀጠል እንዳለባት ተነገረ

መቀመጫቸው በሞስኮ የሆነው አምባሣደር ግሩም አባይ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአርመኑ ፕሬዝዳንት ሳርዝ ሳርጊስያን ሲያስገቡ ነው ከ7ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ የዘቀለው የሁለቱ ሀገሮች ትስስርን ለማሣደግ አሁንም ትብብራችን ይቀጥላል ያሉት፡፡አምባሣደር ግሩም ጨምረውም ኢትዮጵያውያን ለአርመናውያን ልዩ አክብሮት አላቸው ይህ አክብሮት የመጣውም አርመናውያን ለኢትዮጵያ ባበረከቱት አስተዋፅኦ ነው ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በከብት እርባታ ላይ ለተሰማራችሁና በግቢያችሁ የደጋ ፍራፍሬዎች እንዲኖሩ ለምትፈልጉ አዲስ አበቤዎች ይህ መልካም ወሬ ነው

የእንስሣት መኖን በነፃ የደጋ ፍራፍሬ ችግኞችን በመጠነኛ ዋጋ ውሰዱ ተብላችኋል፡፡ እንዲህ ያለው የአዲስ አበባ ግብርና ቢሮ ነው፡፡ በቢሮው የዕፅዋት ክፍል አስተባባሪው አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ ዛሬ ለሸገር ሲናገሩ ቢሮው ሱሱኒ ሜዳ በሚገኘው የአዲስ አበባ ግብርና ሰርቶ ማሳያና ብዜት ማዕከል ለወተት ምርት ይበጃሉ የተባሉ 50 ሺህ የእንስሣት መኖ ችግኞች አሉት፡፡ ለፈላጊዎች በነፃ ይታደላሉ ብለዋል፡፡ የደጋ ፍራፍሬ ችግኞችን ለምትፈልጉ ደግሞ 1 የኘሪም ችግኝ በ4 ብር ፤ 1 የአኘል ችግኝ ደግሞ በ35 ብር ዋጋ መግዛት ትችላላችሁ ተብላችኋል፡፡ ቢሮው 6 ሺህ 500 የደጋ ፍራፍሬ ችግኞች እንዳሉትም አቶ ሙሉጌታ ነግረውናል፡፡

ወንድሙ ኃይሉ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሐምሌ 6፣2008 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • ዘንድሮ በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ የቤት ውስጥ ጥቃቶች ቁጥር ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • በየመን በችግር ውሰጥ ይኖሩ የነበሩ ከ1 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት ሊመለሱ ነው፡፡ (አስፋው ስለሺ)
 • የአተት በሽታን ለመከላከል ያልበሰሉ ምግቦችን ከመመገብ ተቆጠቡ ሲል የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተናግሯል፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የዘመናዊው ኪነ-ጥበብ አባት አለ ፈለገሰላም የቀብር ስነ-ሥርዓት ዛሬ ይፈፀማል፡፡ (ሕይወት ፍሬስብሃት)
 • የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ምርት ከውጪ ገበያ እየጠፋ ነው ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ሽንኩርት፣ ቲማቲም እና አትክልቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጁ ነፃ አላደረጋቸውም የ15 በመቶ ታክስ ይጣልባቸዋል ተባለ፡፡ (መሠረት በዙ)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደንበኞቹ በሰጠው አርኪ አገልግሎት የስካይ ትራክስ ሽልማትን ለሁለተኛ ጊዜ አሸነፈ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • በግብር ሥወራ፣ ማጭበርበርና ገንዘብ ማሸሽ የተከሰሱ 17 የተለያዩ አገሮች ዜጐችና ድርጅቶች ጉዳይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እየታየ ነው፡፡ (ተክለማርያም ኃይሉ)
 • በዓመት 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የሚያስገኘው የሐዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ፡፡ ግንባታው 250 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ጠይቋል፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • ኢትዮጵያ ከአርመንያ ጋር የውጭ ጉዳይ ግንኙነቷን አጠናክራ መቀጠል እንዳለባት ተነገረ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • የአዲስ አበባ ግብርና ቢሮ የርቢ እንስሳት መኖ በነፃ የደጋ ፍራፍሬ ችግኞችን በመጠነኛ ዋጋ እሰጣችኋለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በቡድን ሆነው የዘረፋ ወንጀል ከፈፀሙት አምስት ተከሣሾች መካከል ሁለቱ ተከሣሾች እያንዳንዳቸው በአስር አመት ፅኑ እሥራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሣኔ አስተላለፈባቸው

ድጉማ ኢዴቻ፣ ደምስ አያናው እና ፍቅሩ ደበሌ የተባሉ ተከሣሾች በጊዜው ካልተያዙት ሁለት ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን እድሜዋ ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ልጅ ጠልፈው ሊያመልጡ ሲሉ በአካባቢው ነዋሪዎች ርብርብ ተይዘው ለፍርድ ቀርበዋል፡፡ ተከሣሾቹ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ክልል ልዩ ቦታው ገላን ኮንዶሙኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ድርጊቱ እንደተፈፀመ የአቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ያስረዳል፡፡ የግል ተበዳይ ተማሪ ዘውድነሽ አትክልቲ ከትምህርት ቤት ወጥታ ወደ ቤቷ በመሄድ ላይ እያለች አንደኛ ተከሣሽ ድጉማ ኢዴቻ የሞባይሉን መብራት ፊቷ ላይ እያበራ እንዳታልፈው በዳንስ እንቅስቃሴ ገቷት እሾክ ላይ እንድትወድቅ አድርጓታል፡፡

ሁለተኛ ተከሣሽ የሆነው ደምስ አያናው ደግሞ ከአንደኛ ተከሣሽ ጋር በጋራ ሆነው የወደቀችዋን ልጅ ወገብና እግሮቿን በመያዝ ፤ ሦስተኛ ተከሣሽ ፍቅሩ ደበሌ ወደ ሚያሽከረክረው ሚኒባስ መኪና ውስጥ እንድትገባ አድርገዋል፡፡ ደሜ ቶሎሳ የተባለው ለጊዜው ያልተያዘው ግብረ አበር ደግሞ ልጅቷ እንዳትጮህ አፍና አፍንጫዋን አፍኗታል፡፡ ሦስተኛው ተከሣሽ ፍቅሩ ደበሌ በፍጥነት መኪናውን አስነስቶ ከአካባቢው ለመሰወር ሲሞክር ከልጅቷ ጋር የነበሩ ተማሪዎች የጠለፋ ድርጊቱን ለማስቆም እየጮሁ ድንጋይ ሲወረውሩ አቡሌ የተባለው ለጊዜው ያልተያዘው ተከሣሽ ሽጉጥ አውጥቶ በማስፈራራት ልጆቹን አባሯል፡፡

በመጪዎቹ አራት ወራት ከአዲስ አበባ ነጋዴዎች 26 ቢሊየን ብር ግብር ለመሰብሰብ ማቀዱን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተናገረ

ገቢውን ለመሰብሰብ ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር ተባብሬ እሰራለሁ ብሏል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ በመጪው ዘመን ለሚያስፈልጓት የተለያዩ የልማት ሥራዎችና የመሠረት ልማት ግንባታ የከተማዋ አስተዳደር 34 ቢሊየን ብር በጀት አፅድቋል፡፡ ይህንን በጀት 74 በመቶ የሚሆነው ከግብር በሚሰበሰብ ገንዘብ የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል፡፡ ከግብር የሚሰበሰበው ገቢ ዝቅተኛ በመሆኑ አዲስ አበባ የሚያስፈልጋትን ወጪ አይሸፍንም መባሉን ሰምተናል፡፡ ወሬውን የሰማነው ዛሬ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን እና የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ተገኝተን ነው፡፡

ከሐምሌ 1 ቀን2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ ባሉት አራት ወራት 360 ሺህ የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ግብር ከፍለው ንግድ ፈቃዳቸውን ያድሣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የከተማዋ የንግድ ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የግብር ገቢ አሰባሰቡም እየጨመረ ቢሆንም ከንግድ እንቅስቃሴው አንፃር አሁንም ገቢው ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Leza Vote Banner
Sheger 102.1 AudioNow Numbers