• Slider One

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Slider Two

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

 • Sldier Three

  የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

25 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት የሚያስችል ግድብ

25 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት የሚያስችል ግድብ ለመገንባት የአዋጭነትና የዲዛይን ጥናት ዘንድሮ ይጠናቀቃል ተባለ፡፡በወይጦ ወንዝ ላይ የሚገነባውን የወይጦ ግድብ ለመገንባት ባለፈው ዓመት ዝርዝር ጥናትና የዲዛይን ሰነድ ዝግጅቱ የተጀመረ ሲሆን ዘንድሮ ይጠናቀቃል መባሉን ሰምተናል፡፡

ከውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር እንደሰማነው የፕሮጀክቱን ዝርዝር ጥናት ለማጠናቀቅ 15 ሚሊዮን ብር ወጪ ይደረጋል ተብሏል፡፡ግድቡ በተለይም ለምግብ ዋስትና ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል የተባለ ሲሆን ሃይል እንዲያመነጭም ይደረጋል ነው የተባለው፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 18፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በፊት ገፃችሁ ላይ ጉዳት የደረሰባችሁ ሰዎች ነፃ ህክምና ይሰጣችኋል ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
 • ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አምና ያገኘሁት ትርፍ ካቀድኩት የበለጠ ነው አለ፡፡ ያለበትን የጥራት ችግር ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እየሰራ ስለመሆኑም ተናግሯል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በሰራኋቸው መንገዶች የሚታየው ጎርፍ እና ፍሳሾች አማሮኛል አለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
 • ትናንት ሌሊቱን በአቃቂ ቃሊቲ በደረሰ የቃጠሎ አደጋ 3 ሚሊዮን ብር በተገመተ ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ በቅርቡ የመሪዎች ሽግሽግና ለውጥ ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጠ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
 • ኢትዮጵያ በየዕለቱ ለጭነት አጓጓዦች 10 ሚሊዮን ብር እየከፈለች መሆኑ ተሠማ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የአሜሪካ ባለ ሥም ቆዳ አምራች ኩባንያዎች ተወካዮች በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ለዛ የምሳ ሰዓት ፕሮግራም መስከረም 17፣2009

ክፍል አስራ አንድ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.በለዛ ብርሀኑ ድጋፌ ከነርስ/የስነ ምግብ እና የምግብ ሳይንስ ባለሙያው አቶ አንለይ ተፈራ ጋር የፋይበር ምግብ ጥቅም እና ጉዳቶች
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ለማርገብ ለችሮቹም በምክክር የመፍትሄ ኃሣብ አመንጭቶ ለመንግሥት ለማቅረብ ዛሬ የሰላም ጉባዔ እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ የሰላም የልማትና የዴሞክራሲ ህዝባዊ የምክክር መድረክ ዛሬ በተዘጋጀው የሰላም ጉባዔ ላይ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ምሁራን እየተሳተፉበት ነው፡፡ለኢትዮጵያ ሠላም መደፍረስ ዋና ዋና ምክንያት ናቸው ያሏቸውን ችግሮች ነቅሰው ለማውጣትም የጉባዔው አባላት በቡድን ተደልድለዋል፡፡ ለነቀሷቸው ችግሮች መፍትሄ የሚሏቸውን ኃሳቦችም ለመንግሥት እንደሚያቀርቡ የመድረኩ ሰብሣቢ ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን ለሸገር ተናግረዋል፡፡

ውይይቱ በዝግ እንዲቀጥል የተወሰነ ሲሆን የውይይቱ ውጤትም በመጨረሻ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡ግጭት በተከሰተባቸው የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ተወካይ አባቶች በሰላም ጉባዔው ላይ አልተገኙም፡፡ለምን እንዳልተገኙ የጠየቅናቸው ኢንጂነር ጌታሁን ጥሪያችን በዘር፣ በክልል፣ በኃይማኖትም አይደለም፤ ኢትዮጵያዊ የሆነ ለኢትዮጵያ ሠላም እና እድገት ያገባኛል ያለ በጉባዔው እየተሳተፈ ነው የሚል ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

ለኢትዮጵያ ችግሮች መፍትሄ አመንጪ ቡድን ነው የተባለው ይህ መድረክ ከዚህ ቀደም የኑሮ ግሽበት ነዋሪውን አማረረ፤ መጤ ባህልም የኢትዮጵያዊያንን ማንነት አደጋ ላይ እየጣለው ነው በሚሉና በሌሎችም ችግሮች ላይ ጥናት አስደርጐ የመፍትሄ ኃሳቦችን ለመንግሥት ማቅረቡ ይታወሳል፡፡በዛሬው የሰላም ጉባዔ ላይ ግን ከመድረኩ ለኢትዮጵያ ሰላም መደፍረስ ችግሩ ይህ ነው የሚል ጥናት አልቀረበም፡፡ታዲያ ችግሮቹ ሳይጠኑ እንዴት ያለ መፍትሄ ነው የሚፈለገው ያልናቸው ኢንጅነር ጌታሁን ሲመልሱ ችግሮቹን ነቅሶ ሊያወጡ የሚችሉ ሰዎች በመሀላችን አሉ ብለዋል፡፡

ለችግሮች ሁሉ በጠመንጃ መፍትሄ መስጠት አይቻልም ያሉት ኢንጂነር ጌታሁን የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ምሁራን ዛሬ በጀመሩት ጉባዔ የሚያፈልቋቸውን የመፍትሄ ኃሣቦች ለመንግሥት ያቀርባሉ ብለዋል፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክ ፋካልቲ እየተካሄደ ያለው የሰላም ጉባዔ ከሰዓት በኋላም ይቀጥላል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፓሬሽን በአጠቃላይ ከያዘው 4 ሺህ 744 ኪ.ሜ መሀከል የአዲስ አበባ ሜኤሶ መስመርን በተያዘው ወር መጨረሻ ለማስመረቅ እየጣርኩ ነው አለ

የፕሮጀክቱ 99 በመቶ መጠናቀቁንም የስራው ኃላፊዎች ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ ከሰበታ ተነስቶ ጅቡቲ ነጋድ ወደብ የሚደርሰው የኢትዮጵያ ጅቡቲ የባቡር መስመር በጥቅሉ 55 መዳረሻዎችን የያዘ ሲሆን ከኢትዮጵያ ወገን 656 ኪ.ሜ እንዲሁም ከጅቡቲ ወገን ደግሞ 100 ኪ.ሜ በመጓዝ እንደሚገጥም ሰምተናል፡፡

ኢትዮጵያ የባቡር መስመሩን ከቻይናው አግዜም ባንክ በተገኘ 70 በመቶ ብድር እና ከኪሷ ደግሞ 30 በመቶውን በማውጣት የምትገነባው ነው ተብሏል፡፡ከህዳሴው የኤሌክትሪክ ኃይል ግንባታ ፕሮጀከት ቀጥሎ በገንዘብ አቅሙ ሁለተኛው የሆነው የኢትዮጵያ ጅቡቲ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሥራ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የወጣበትና ስራውም ተጀምሮ  99 በመቶ የደረሰው በአራት አመታት ውስጥ መሆኑን ሰምተናል፡፡

የሰበታ መኤሶ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር መኮንን በኢትዮጵያ የሚሰሩት የባቡር መስመሮች እርስ በርስ የሚተሣሰሩ ይሆናሉ ብለዋል፡፡በቻይናዎቹ CRC እና CCC ገንቢነትና CIC አማካሪ ድርጅትነት የተገነባው የሰበታ ሜኤሶ የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር 61 ድልድዬችን መያዙንም ኢንጂነር መኮንን ነግረውናል፡፡የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ ስራም ወደ አገልግሎት ከመቀየሩ በፊት ሁለቱ ሀገሮች አስተዳዳሪ ይቀጥሩለታል የሙከራ ጊዜውም ከ3-6 ወራት ሊፈጅ ይችላል መባሉን ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 16፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • የደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከእሳት አደጋ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ መስሪያ ቤት እና ከፖሊስ መልዕክት ተላለፈ፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • ከሠራተኛ ጋር ተመካክሮ ችግርን መፍታት  አንዱ ኃላፊነታቸው እንደሆነ የማይረዱ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መሪዎች አሁንም አሉ ተባለ፡፡ (ንጋቱረጋሣ)
 • አቤት ሆስፒታል ሥራ ከጀመርኩ ጀምሮ ከሦስት ሺህ በላይ ሰዎች ድንገተኛ አደጋ ገጥሟቸው መጥተው እርዳታ አድርጌላቸዋለሁ አለ፡፡ የበዛውም የመኪና አደጋ ነው ብሏል፡፡ (ወንድሙኃይሉ)
 • ኢትዮጵያ ከቆዳው ዘርፍ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ እንዲቻል ሜድ ባይ ኢትዮጵያ የሚል ፕሮጀክት ተቀርፆ ሥራ ጀምሯል ተባለ፡፡ (ትዕግስትዘሪሁን)
 • የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፓሬሽን በአጠቃላይ ከያዘው 4 ሺህ 744 ኪ.ሜ መሀከል የአዲስ አበባ ሜኤሶ መስመርን በተያዘው ወር መጨረሻ ለማስመረቅ እየጣርኩ ነው አለ (የኔነህ ሲሳይ)
 • በኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ለማርገብ ለችሮቹም በምክክር የመፍትሄ ኃሣብ አመንጭቶ ለመንግሥት ለማቅረብ ዛሬ የሰላም ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • ለመሥቀል ወደ ትውልድ ቀያቸው የተጓዙትን ዜጐች ያሣፈሩ ከ5 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች መሰማራታቸው ተሠማ፡፡ (ቴዎድሮስ ወርቁ)
 • የአዲስ አበባ ፖሊስ በደመራ ምክንያት ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ዝርዝር እወቁልኝ አለ፡፡ (ተኅቦ ንጉሴ)

 

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የቆዳ ገበያ ተፎካካሪ ለመሆን ለጥራት ትኩረት መስጠት አለባት ሲሉ አንድ ምሁር ተናገሩ

የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ዘንድሮ ከ7 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡ ተሠማ፡፡በበጀት አመቱ ለካፒታል ፕሮጀክቶችና ለመደበኛ ሥራዎች ማስፈፀሚያ 7 ቢሊዮን 884 ሚሊዮን ብር መመደቡን ሰምተናል፡፡ከዚህ ውስጥም 7 ቢሊዮን 8 መቶ ሚሊዮን የሚሆነው ብር ለፕሮጀክት የተመደበ ሲሆን 84 ሚሊዮን ያህሉ ደግሞ ለመደበኛ ሥራዎች የተያዘ በጀት ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ውስጥም 5 ቢሊዮን ብሩ ከመንግሥት ወጪ የሚደረግ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ ደግሞ ከውጭ እርዳታና ብድር የሚገኝ መሆኑ ተነግሯል፡፡በተያዘው በጀት አመትም የ5 ትላልቅ ግድቦች ማለትም የርብ፣ የመገጭ፣ የጊዳቦ የአርጆ ዴዴሳ እና ዘሪማ ሜይ ዴይ ቀጣይ ግንባታዎች የሚጠበቁ ሥራዎች ናቸው የተባለ ሲሆን፤ 41 የተለያዩ የመስኖ ድሪኔጆች ልማት፣ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት፣ የሃይል አቅርቦት ልማቶች ይሰራሉ ከተባሉት መሀል ይገኙበታል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ
አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

መንግሥት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የቤት ችግርን በኮንዶሚኒየም ፕሮግራም መፍታት አልችልም አለ

መንግሥት የአዲስ አበባን የቤት ችግር በጋራ መኖሪያ ቤቶች ብቻ ልፈታው አልችልም አለ፡፡ችግሩንም ለመፍታት የተለያዩ የቤት አማራጮችንም ወደ ተግባር መቀየር አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡ እስካሁንም 11ኛውን ዙርን ሳይጨምር 136 ሺህ ገደማ ቤቶች ቢተላለፉም ከፍላጐቱ ጋር አልተገናኘም ተብሏል፡፡

ቤት ለሚፈልጉ አዲስ አበቤዎች የሚገነቡት የጋራ መኖሪያ ቤቶች አንደኛውን የቤት ልማት አቅርቦት እንጂ የሚያሟላው አጠቃላይ የቤት ፍላጐቱን እንደማይመልሰው ለሸገር የተናገሩት የአዲስ አበባ ቤቶች እና ልማት አስተዳዳር ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ እያሱ ማርቆስ ናቸው፡፡

መንግሥት ባፀደቀው ስትራቴጂ ሰነድ መሠረትም በማህበር፣ በግል፣ በሪል እስቴት፣ በሽርክና እና በሌሎችም አማራጮች የቤት ፈላጊው ችግርን ለማቃለል መሠራት አለበት ብሏል ቢሮው፡፡ አጠቃላይ የአዲስ አበቤን ቤት ፈላጊ የጋራ መኖሪያ ቤት ብቻ አንደማይመልሰው እና ሌሎች አማራጮችም መተግባር እንዳለባቸው ኃላፊው ነግረውናል፡፡ እስካሁን ድረስም የቤት ግንባታው ከፈላጊው ጋር ሲወዳደር አቅርቦቱ በሚፈለገው ደረጃ እየሄደ እንዳልሆነም ሰምተናል፡፡

ተህቦ ንጉሴ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በመጪው አመት የሚደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ ምንም አይነት ስህተት እንዳይኖር በዘመናዊ አሰራር የታገዘ ይሆናል

የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በመጭው አመት የኢትዮጵያን ህዝብ ለመቁጠር ቅድመ ዝግጅት እያደረግኩ ነው አለ…ከዚህ ቀደም በተካሄደው የህዝብ ቆጠራ ውጤት ምክንያት የተፈጠረው ጭቅጭቅና አለመግባባት እንዳይደገም በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

በኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳፊ ገመዲ ለሸገር እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት ለህዝብ ቆጠራው ውጤት ትክክለኛነት ይረዳ ዘንድ ባሳተላይት በመታገዝ ከ150 እስከ 200 ቤተሰብ የሚገኝባቸው ቦታዎች እየተለዩ የማካለል ሥራ እየተሰራ ነው፡፡ እስከ 200 ቤተሰብ የሚኖርባቸውን ቦታዎች ማካለሉ በመላው ኢትዮጵያ የሚሰራ ሲሆን እስከ አመቱ አጋማሽ ስራው ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በካርታ የማካለል ስራው ሲጠናቀቅም 145 ሺህ የቆጠራ ቦታዎች ይፈጠራሉ ተብሎ እንደሚገመት አቶ ሳፊ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በአዲስ አበባ መጠጥ ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቀረት ይረዳል የተባለው ዘመቻ ዛሬ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቀረት ቫይታል ስትራቴጂ ከተሰኘው አለም አቀፍ ተቋም ጋር በጋራ በመሆን የታቀደው ዘመቻ ዛሬ ይፋ ሆነ...ይህን የሰማነው ዛሬ የዘመቻውን መጀመር አስመልክቶ በጌት ፋም ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተገኝተን ነው፡፡

በቫይታል ስትራቴጂ እና በብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ ኢኒሼቲቭ ፎር ግሎባል ሮድ ሴፍቲ ፕሮግራም ትብብር የተዘጋጀው የፀረ ጠጥቶ ማሽከርከር የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ጠጥቶ ማሽከርከር በአሽከርካሪው፣ በተጐጂው አካል ላይ እና የሁለቱንም ወገን ቤተሰቦች ላይ የሚያስከትላቸው ችግሮች ላይ ትኩረቱን አድርጐ ይሰራል ተብሏል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ላይ አደጋዎች ሞትን በማስከተል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው እና ከነዚህም ውስጥ ጠጥቶ በማሽከርከር የሚደርሱት አብላጫውን እንደሚይዙ ተነግሯል፡፡ ችግሩም በአጭሩ ካልተቋጨ ስፋቱ እየጨመረ እንደሚሄድ በስጋት ተቀምጧል፡፡

በመግለጫው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው እና የአቤት ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር በዘመቻው ላይ ድጋፋቸውን በማድረግ በጋራ የሚሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ  ዛሬ የሚጀመረው የፀረ-ጠጥቶ ማሽከርከር ዘመቻ ለውጥ እንዲያመጣና ግንዛቤ እንዲፈጥር በተለይ በመገናኛ ብዙሃን በኩል ብዙ ሥራዎች እንዲሰሩበትና ህግ የማስከበሩንም ሥራ በማጠናከር የከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባም በቅርቡ የአልኮል መጠጥን በትንፋሽ መለየት የሚያስችሉ መሣሪያዎችን ወደ ሀገር ቤት እንደሚገቡና በተጨባጭ ጠጥቶ የማሽከርከር አደጋ በሚደጋገምባቸው በከተማዋ ያሉ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግም ሰምተናል፡፡

ምህረት ስዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መስከረም 13፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

 • በአዲስ አበባ መጠጥ ጠጥቶ ማሽከርከርን ለማስቀረት ይረዳል የተባለው ዘመቻ ዛሬ ተጀመረ፡፡ (ምህረት ስዩም)
 • መንግሥት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የቤት ችግርን በኮንዶሚኒየም ፕሮግራም መፍታት አልችልም አለ፡፡ (ተህቦ ንጉሴ)
 • በመጪው አመት የሚደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ ምንም አይነት ስህተት እንዳይኖር በዘመናዊ አሰራር የታገዘ ይሆናል ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
 • በቀን እስከ አምስት ሺህ የሚደርሱ በጎችና ፍየሎች እርድ ማከናወን የሚችል ቄራ ግንባታ ወደ መጠናቀቁ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • በ2009 ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ምደባ ትናንት ምሽት ላይ መታወቅ ጀመረ፡፡ (ፋሲል ረዲ)
 • ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የቆዳ ገበያ ተፎካካሪ ለመሆን ለጥራት ትኩረት መስጠት አለባት ሲሉ አንድ ምሁር ተናገሩ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
 • የህይወት ዘመን የመሪነት ስኬት ሽልማት ስነ-ሥርዓት ትናንት ምሽት ተከናውኗል፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
 • የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ዘንድሮ ከ7 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers