• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ነሐሴ 3፣2011/ በኢትዮጵያ ሕፃናትን ከመቀንጨር ለመታደግ የተነደፈው የሰቆጣ ቃል ኪዳን አፈፃፀሙ አስቀድሞ እንደታሰበው አይደለም ተባለ

በኢትዮጵያ ሕፃናትን ከመቀንጨር ለመታደግ የተነደፈው የሰቆጣ ቃል ኪዳን አፈፃፀሙ አስቀድሞ እንደታሰበው አይደለም ተባለ፡፡ማህሌት ታደለ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 3፣ 2011/ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በደቡብ አፍሪካ እየታሰሩ ስላሉት ኢትዮጵያውያኖች እየተከታተልኩ ነው ብሏል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በደቡብ አፍሪካ እየታሰሩ ስላሉት ኢትዮጵያውያኖች እየተከታተልኩ ነው ብሏል፡፡ የኔነህ ሲሳይ በስፍራው ተገኝቶ መግለጫውን ተከታትሏል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 3፣ 2011/ ከፍተኛ የሰራተኞች ፍልሰት ይፈትናቸዋል በሚባሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች የስራ ሁኔታው የተረጋጋ እንዲሆን የተቀጣሪዎች ደመወዝ ሊታሰብበት ይገባል ተባለ

ሰራተኞቹ ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊትም የሕይወት ክህሎት ስልጠና ቢወስዱ መልካም ነው ተብሏል፡፡በዚህም የሰራተኞችን ፍልሰት መቀነስና የፓርኮቹን ደህንነት ማስጠበቅ እንደሚቻል ተነግሯል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንም ዛሬ በጉዳዩ ላይ በሒልተን ሆቴል እየመከረበት ነው፡፡በውይይቱ ላይ ባለሀብቶች፣ የተቋማት ተጠሪዎች እና ሌሎችም ጉዳዩ የሚያገባቸው ተቋማትና ግለሰቦችም ተሳትፈዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ እንዳሉት በአንዳንድ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ ሰራተኞች በደመወዝ ማነስ ምክንያት ስራቸውን እየለቀቁ ይገኛሉ፡፡ስለሆነም እነዚህ ሰራተኞች ተረጋግተው እንዲሰሩና ለራሳቸውም ለአገራቸውም ለውጥ እንዲያመጡ የደመወዛቸው ነገር ቢታሰብበት መልካም ነው ብለዋል፡፡የቅጥር የእድሜ ክልልም ከ18 እስከ 24 ከሚለው በተጨማሪ በሌላ የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰራተኞችንም ቢቀላቅል መልካም ነው የሚል ሀሳብ ቀርቧል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 3፣ 2011/ ከአንድ ወር በፊት ተግባራዊ የሆነው የከባድ ተሽከርካሪዎች የሰዓት ገደብ ሥራችንን እያስተጓጎለው ነው የሚሉ ቅሬታ አቅራቢዎች በርክተዋል

ከአንድ ወር በፊት ተግባራዊ የሆነው የከባድ ተሽከርካሪዎች የሰዓት ገደብ ሥራችንን እያስተጓጎለው ነው የሚሉ ቅሬታ አቅራቢዎች በርክተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮም የሰዓት ገደቡ ያመጣው አዎንታዊ እና አሉታዊ ውጤቶች ላይ ዛሬ በዝርዝር ምክክር አደርጋለሁ ብሏል፡፡አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 3፣ 2011/ የመንግሥትን ሐብት አባክነዋል የተባሉ ሹማምንትን እና ባለሞያዎችን ሕግ ፊት ስለማቅረብ

የመንግሥትን ሐብት አባክነዋል የተባሉ ሹማምንትን እና ባለሞያዎችን ሕግ ፊት ለማቅረብ የምርመራ ቡድን አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ተናገረ፡፡ በቅርቡ ማንነታቸውን ይፋ አደርጋለሁ ብሏል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 3፣ 2011/ በሐገራችን የሚታዩት የዋጋ ንረት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና የእዳ ጫና አጠቃላይ ማክሮ ኢኮኖሚው የተናጋ እንደሆነ ጠቋሚ ናቸው ተባለ

ባለፉት አመታት የነበረው ምጣኔ ሐብታዊ እድገት ድህነትን የቀነስ አይደለም ተባለ፡፡ በሐገራችን የሚታዩት የዋጋ ንረት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና የእዳ ጫና አጠቃላይ ማክሮ ኢኮኖሚው የተናጋ እንደሆነ ጠቋሚ ናቸው ተባለ፡፡ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 2፣2011/ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎችና ባለቤቶች አስተዳደሩ ያወጣውን የአፈፃፀም መመሪያ ማስተካከያ አድርጎ ቶሎ ወደ ስራ እንዲያስገባቸው ጠየቁ

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የሞተር ብስክሌት የማሽከርከር ስልጣን ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ላይ እያወያያቸው ነው፡፡መመሪያው ሞተር ብስክሌቶች የፍጥነት መቆጣጠሪያ ማስገጠም እንዳለባቸው እንዲሁም የንግድ ስራ የሚሰሩ ሰሌዳቸውን ወደ 3 ቁጥር መለወጥ እንደሚኖርባቸው፣ በከተማዋ መንቀሳቀስ የሚችሉ ሞተሮች ሰሌዳቸው አዲስ አበባ የሆነ ብቻ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ይህም በቢሮው ሀላፊ በዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በዝርዝር ለውይይት ቀርቧል፡፡

ተወያዮቹ የሞተር ብስክሌቶችን በህግ ሥርዓት ውስጥ ማስገባቱ ላይ ቢስማሙም መመሪያው ግን እንዲስተካከል ተሰማምተዋል፡፡ከተነሱት ሀሳቦች መካከል የሚገጠሙ ጂፒኤሶች ገንዘባቸው ውድ የመሆኑ ጉዳይ፣ የተማረ የሰው ሀይል ማስፈለጉ፣ የክልል ሰሌዳዎች ያሉን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስላለን መመሪያው ሊካተት ይገባል የሚሉት ናቸው፡፡የቢሮው ሀላፊዎች በተነሱት ሀሳቦች ላይ በድጋሚ በቢሮ ደረጃ እንደሚነጋገሩባቸው ተናግረዋል፡፡የሞተር ብስክሌት ባለቤቶች ግን መመሪያው ከወጣ ጀምሮ የከፋ ችግር ውስጥ ስለወደቅን ቢሮው ለጥያቄያችን አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠን ይገባሉ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

አስፋው ስለሺ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 2፣ 2011/ የላብራቶሪ መሳሪያቸውን አስፈትሸው፣ የባለሙያዎቻቸው ብቃትም ተረጋግጦላቸው ትክክለኛ የምርመራ ውጤት እንደሚሰጡ የተረጋገጠላቸው ሆስፒታሎች ዛሬ ከሰዓት በኋላ እውቅና ይሰጣቸዋል ተባለ

የላብራቶሪ መሳሪያቸውን አስፈትሸው፣ የባለሙያዎቻቸው ብቃትም ተረጋግጦላቸው ትክክለኛ የምርመራ ውጤት እንደሚሰጡ የተረጋገጠላቸው ሆስፒታሎች ዛሬ ከሰዓት በኋላ እውቅና ይሰጣቸዋል ተባለ፡፡ትዕግስት ዘሪሁን
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 2፣ 2011/ የኢትዮ አሜሪካን ዶክተሮች ግሩፕ በኢትዮጵያ በሚገኙና በስፖርት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ነፃ የቀዶ ህክምና ማዘጋጀቱን ተናገረ

የኢትዮ አሜሪካ የዶክተሮች ቡድን በኳስ ጨዋታ ወቅት ጉዳት ላገኛቸው ዜጎች ነፃ ህክምና እሰጣለሁ ያለው በአዲስ አበባ አቤት ሆስፒታል ነው፡፡በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እስካሁን 15 ታካሚዎች ከአጥንት ቀዶ ህክምና ጋር በተገናኘ ነፃ የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡በአቤት ሆስፒታል ከአጥንት ጉዳት ጋር በተገናኘ የቀዶ ህክምና አገልግሎቱን ለማግኘተ ከ2 መቶ በላይ ታካሚዎች ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን በቡድኑ የተሰናዳው የነፃ ቀዶ ህክምና በገንዘብ ቢተመን በአንድ ግለሰብ እስከ 2 መቶ ሺ ብር ወጪ የሚጠይቅ እንደነበር ማህበሩ ከላከለን መግለጫ ተመልክተናል፡፡

በአቤት ሆስፒታል ከአጥንት ቀዶ ህክምና ጋር በተገናኘ አገልግሎቶች ሲሰጡ ቢቆዩም አሁን በቡድኑ የተደረገው ዓይነት በተሟላ መሳሪያ የህክምና እርዳታ መገኘቱ በታካሚዎችም ይሁን በሆስፒታሉ የሚመሰገን ነው ሲሉ በአቤት ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር አብይ ወርቁ ተናግረዋል፡፡የህክምና ቡድኑ አባላት ለነፃ ቀዶ ህክምና የሚገለገሉባቸውን የህክምና መሳሪዎች ለአቤት ሆስፒታል ድጋፍ የሚያደርጉ ሲሆን በተመሳሳይ ከፍለው የመታከም አቅም የሌላቸው ዜጎችን ለመርዳት ፍላጎት እንዳላቸው የኢትዮ አሜሪካን ዶክተርስ ቡድን ሜዲካል ዶክተር ክብረት ከበደ ተናግረዋል፡፡

ምህረት ሥዩም
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 2፣ 2011/ የኢትዮጵያ ያለፉት አመታት የኢኮኖሚ እድገት በአብዛኛው በብድርና በገንዘብ ማተም የመጣ ነው ተባለ

በዚህም ምክንያት አጠቃላይ ኢኮኖሚው ተናግቶ መቆየቱ ተነግሯል፡፡የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ እና “በኢኮኖሚው ውስጥ የመንግስት ሚና” በሚል ርዕስ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡በውይይቱ ላይ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ እንዳሉት ባለፉት አመታት የኢኮኖሚ እድገት ተመዘግቧል ቢባልም እድገቱ በአብዛኛው በብድርና በገንዘብ ማተም የመጣ ነው፡፡እድገቱ በአገራችን ያለውን የድህነት መጠን እምብዛም ያህል እንዳልቀነሰም ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡

እሳቸው እንዳሉት መንግስት ከውጪ የተበደረው የዕዳ መጠን አሁን 29 ቢሊየን ዶላር ያህል ነው፡፡ከአገር ውስጥ የወሰደው ብድርም ከዚህ እንደማይተናነስ ተናግረዋል፡፡ከ11 አመታት በፊት በአገራችን በዝውውር ውስጥ የነበረ የገንዘብ ኖት 68 ቢሊየን ብር እንደነበረ ያስታወሱት ፕሮፌሰር አለማየሁ አሁን ይህ መጠን 740 ቢሊየን ብር መድረሱን ተናግረዋል፡፡የገንዘብ ኖት መጠኑ በየአመቱ በ27 በመቶ ሲያድግ ቆይቷል ብለዋል፡፡

የገንዘብ ኖት እድገቱ፣ መሆን ከነበረበት 4 እና 5 እጥፍ የበለጠ እንደሆነ ፕሮፌሰር አለማየሁ አክለዋል፡፡ክስተቱ ከፍተኛ የብር ኖት እየታተመ ለዝውውር ይበቃ እንደነበር ያሳያል ብለዋል፡፡መንግስት ባለፉት 10 አመታት በልማታዊ መንግስት ቅኝት ከፍ ያለ መዋዕለ ነዋይ በመሰረተ ልማት ላይ እንደዋለም ተናግረዋል፡፡የኢኮኖሚ እድገቱ መዋቅራዊ ለውጥ እንዳላመጣም በምክክሩ ወቅት ተነስቷል፡፡ለዚህም አገሪቱ ከደካማ ምርታማነት አለመላቀቋ በማጠቃሻነት ተጠቅሷል፡፡በማህበራዊ የጥናት መድረክ አዘጋጅነት በተጠራው ውይይት ላይ ተጨማሪ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ምክክር እየተደረገበት ነው፡፡

ንጋቱ ረጋሳ
አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ነሐሴ 2፣ 2011/ ኢትዮጵያውያን በመንግስት ተቋማት ላይ ያላቸው እምነትና እርካታ 49 በመቶ ብቻ መሆኑ ተነገረ

እንደ መከላከያ ያሉ የመንግስት ተቋማት ላይ ኢትዮጵያውያን ያላቸው እምነትና እርካታ 49 በመቶ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡በሌላ በኩል በአለም አቀፍ ተቋማት ላይ ዜጎች ያላቸው እርካታና እምነት 58 በመቶ መሆኑ ተነግሯል፡፡ዛሬ በኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በቀረበ ጥናት ላይ እንደሰማነው ከሆነ በአገሪቱ ዴሞክራሲ ላይ ዜጎች ያላቸው እርካታ ከ48 በመቶ የዘለለ ባለመሆኑ ምክንያት ለመንግስት ተቋማት ያላቸው እምነትና እርካታ ዝቅ ሊል ችሏል፡፡ለዴሞክራሲ ያላቸው እርካታ ዝቅ ያለበት ምክንያትም መገናኛ ብዙሃን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መንግስት፣ የበጎ አድራት ማህበራትና ዜጎችም ራሳቸው ዴሞክራሲ እንዲሰርፅ የነበራቸው ሚና ዝቅተኛ ሆኖ መቆየቱ እንደሆነ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡

ዜጎች በደል ይደርስብናል ብሎ በማሰብ የፍትሃዊነት መጓደልንና የሹማምንትን ጥፋት እያዩ እንዳላዩ ማለፋቸው፣ መንግስት ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ሥርዓትን ሲከተል አለመቆዩቱ፣ መገናኛ ብዙሃን ከመንግስት ተፅዕኖ ሳይላቀቁ መቆየታቸውና የበጎ አድራጎት ማህበራት ከሚጠበቅባቸው ልክ ሚናቸውን አለመወጣት ዴሞክራሲን በአግባቡ እንዳያሰርፁ ካደረጓቸው ምክንያቶች ውስጥ ናቸውም ተብሏል፡፡“በሕዝቦች ተሳትፎ ዴሞክራሲን ማስረፅ” በሚል ርዕስ የተካሄደው ይኸው ጥናት ከሁሉም በላይ የፍትህ ተቋማት ገለልተኛ እንዲሆኑ ምክረ ሀሳቡን አስቀምጧል፡፡

ቴዎድሮስ ብርሃኑ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers