ወጐች

03/25/2020 - 13:55
በእድር በማህበር… በጀማ በደቦ፣
ቢለምድም ወገኔ…
መኖር ተሰባስቦ፣
ጨብጦና አቅፎ...
ስሞ ተሳስሞ፣
ፍቅሩን ካልገለፀ…
ባይረካም ፈፅሞ፣
“በቃ አትሰብሰቡ!
02/10/2015 - 09:28
በድሮ ጊዜ ነው አሉ፡፡ ከጠላት ወረራ በኋላ ከተማዎቻችን እየተሰፋፉ መብራትና ውሃ በየቤቱ እየገባ የመብራትና የውሃ ቆጣሪዎች እየተሠማሩ ሂሳብ ያሰከፈሉ ነበር፡፡ እንደዛሬው መጥታችሁ ክፈሉ ለሁሉም የሚባል ነገር አልነበረም፡፡

ታዲያ አንድ በጠላት ዘመን ለሃገራቸው በዱር በገደሉ ሲዋደቁ የነበሩ ሰው የውሃ አልከፍፈም አሉ፡፡ ‹‹ለምን አይከፍሉም?›› ሲባሉ ለመብራቱ ይሁን ዘመን ያመጣው ጥሩ ጠቃሚ ነገር ነው እከፍላለሁ፡፡ ለውሃውም ቢሆን ውሃው ለመጣበት…
02/06/2015 - 08:29
የቀጥታ ስርጭት

ውድ አድማጮጫችን የቀጥታ ስርጭታችንን ተስተካክሎ ላለፋት 72 ሰዓታት ያለምንም መስተጓጎል ተላልፎአል:: ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ እየጠየቅን በተሻለ መንገድ ለማዳመጥ የስልክ አፕሊኬሽኖቻችን Update ስላደረግን Download በማድረግ መጠቀም ትችላላችሁ:: በTunein.com ላይ በተሻለ እየሰራ ቢሆንም ለአስተማማኝ ስርጭት የራሳችንን ስልክ አፕሊኬሽኖች(Android/iOS) Download አድርጋችሁ እንድትጠቀሙ እንመክራለን::…
01/23/2015 - 13:13
ፍርሀተ- እስርቤት ወይም ፈረንጆቹ ስር የሰደደ፣ ምክንያት አልባ የሚሉት አይነት የመታሰር ፍርሀት(phobia) ገና ህክምናው እውቅና አልሰጠውም፡፡ ነገር ግን ሌሎች ህክምናው ቅጥ የለሽ ፍርሀት (phobia) ናቸው ከሚላቸው ጋር ሊዛመድ ይችላል፡፡ ለምሳሌ Cleithrophobia በተወሰነ ስፍራ ተቆልፎ መቀመጥ የሚፈጥረው የፍርሀት ዓይነት ነው፡፡ Claustrophobia የጠባብ እና የታጠረ ቦታ ፍርሀት ይባላል፤ Isoolophobia- ከሌላው ሰው የመነጠል ፍርሀት ነው፤…
01/02/2015 - 08:53
በአለም ከጫፍ እስከ ጥግ በኑሮ ውጣ ወረድ በየሁሉም ማዕዘን የፈለጉትን ለማግኘት የታለመውን ለመፍታት ከታሰበው ለመድረስ በየሁሉም መንገድ ችግሮች እንደ አሽን የበዙ ናቸው፡፡ መሰናክሎችን መዝለል እና ማለፍ ይደክማል ፈተናዎችንም መቁጠር ይታክታል፡፡ ታዲያ በዚ ሁሉ መመላለስ ግን ችግሮችን ለመፍታት ከማሰብ ይልቅ ለእክሎቹ መፍትሄ የሚሆኑ ሃሣቦችን ከመምዘዝ ውጪ እና የተፈጠሩትን ችግሮች በትዕግስት ጠብቆ ከመፍታት ባሻገር ባልተገባ አቋራጭ እና በተሰባሪ ድልድይ ላይ ለማለፍ…
12/27/2014 - 09:17
በኢትዮጵያ እና በኢጣሊያ መካከል ስለተወደረገው ጦርነት ስታስቡ መጀመሪያ ወደ አእምሯችሁ የሚመጣው በቪዲዮ ምስል የትኛው ነው? ወይም በየአመቱ የአርበኞች መታሰቢያ ወይም የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ሲከበር ተደጋግሞ ለቴሌቪዥን ዘገባ ጥቅም ላይ የሚውል ባለ ነጭ እና ጥቁር ተንቀሳቃሽ ምስል?
12/20/2014 - 09:40
ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ የቆየ አና የተለመደ የአማርኛ ምሳሌያዊ አነጋገር ነው፡፡ ልጅ ለጉርምስና እድሜ ደርሶ ያልተለመደ ባህሪ ሲያወጣ፤ቤተሰቡ ያልጠበቀውን ችግር ሲያመጣ፤ ፀብ ሆነ ፍቅር ከጎረቤት ሲጎትት ይህም ላሳደጉት ወላጆቹ እንግዳ ሲሆን፤ የልጆች እድገት ቤተሰቡን ሠላም እና የተረጋጋ ህይወት ሲያናጋ ‹ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ› ማለት እንደሚቻል የተለያዩ ሰዎች የተለያየ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል የአማርኛ ምሳሌያዊ አነጋገር እና…
12/09/2014 - 07:59
ሰውዬው በተወለደበት ሀገር ኑሮውን ይገፋል አሉ፡፡ ይህ ሰው ፂሙን ማሳደግ የሚወድ አይነት ነው፡፡ እናም ይህ ዠርጋጋ ሪዙ መለያው ሆኖ፣ እሱም ወዶት ይኖራል፡፡ ይህ ሰው ምግብ ሲመገብ የተወሰነው ሪዙ ላይ ይንጠባጠባል ግን በፍፁም አፅድቶት አያውቅም፡፡ ከጊዜ ጊዜ ይህ ነገር ሲደጋገም ሪዙ ላይ የሚንጠባጠበው ምግብ ተበላሽቶ መጥፎ ጠረን ያመጣበት ጀመር፡፡ ይህ ሰው ምንድን ነው የሚሸተኝ እያለ ዙሪያውን ማሰስ ጀመረ፡፡ ከዛ ችግሩ ከከተማው ነው በማለት ወደ ሌላ ከተማ ተጓዘ…
12/05/2014 - 11:41
በአንድ ወቅት ወደ አንዱ የሀገራችን የገጠር አካባቢ ለስራ ጉዳይ በሄድኩኝ ጊዜ ከዋናው መንገድ ዳር በማስታወቂያ ቦርድ ላይ ተፅፎ ያየሁት ነው፡፡ ፅሁፍ ምን ማለት ነው የሚል ስሜትን ፈጥሮብኛል፡፡ መልዕክቱ ‹‹እንኳን አደረሳችሁ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የወጣንበት ክብረ በዓል›› ብሎ ከጐኑ ቀን ከነ ወርና ዓመቱ ተፅፏል፡፡

የአካባቢውን ሰዎች ስለዚህ መልክት ጠየኩኝ ሰዎቹም በኩራትና በራስ መተማመን በፊት እዚህ አካባቢ መፀዳጃ ቤት ብሎ ነገር የለም፡፡…
11/11/2014 - 20:02
ብንድማመጥ ልንግባባ እንችላለን፤ ከተግባባን ደግሞ ሁሉም ጥሩ ይሆናል፡፡ ግን የምንደማመጥ ይመስላችኋልን? አብዛኛዎቻችን፣ ሌላው የሚናገረውን ከማደመጥ ይልቅ፣ የሚያሰበውን እናውቃለን ባዮች ለመሆን በመፈለጋችን ማዳመጥ ትተናል፡፡ የምናገረውን ስማ እንጂ የምትናገረውን ልስማህ ማለት አቅቶናል፡፡ ጠርጣሪ ስሜታችን አሸንፎናል፡፡ ስለዚህ የምንሰማውን ከማመን ይልቅ የተናገረውን ማንነት፣ ‹‹ልቡንና ኩላሊቱን›› ለመመርመር እንባጃለን፡፡ ስለዚህ የማዳመጥ ሃይላችንን፣የመረዳት…