ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2022-01-22
በኢትዮጵያ ካለው አንጻራዊ የተረጋጋ ወታደራዊ ሁኔታ አኳያ የጀርመን መንግሥት በሀገሪቱ አዲስ የፖለቲካ ሂደት እንደሚጀምር ተስፋ ማድረጉን ቡንደስታግ የተባለው የጀርመን ፓርላማ ተናገረ፡፡  የጀርመን ፓርላማ በመግለጫው፣ ሕወሓት ተፈርቶ እንደነበረው ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ ሊገባ አልቻለም ሲሉ የጀርመን የፓርላማ ፀሐፊ እና የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኔይልስ አነን ሰሞኑን በልማት ኮሚቴው ፊት መናገራቸውን ጽፏል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ገናን ምክንያት በማድረግ የሕወሓት አባላትን ጨምሮ በዛ ያሉ የፖለቲካ እስረኞችን መልቀቁ በመረጃው ተጠቅሷል፡፡  እ.ኤ.አ ከሕዳር 2020 ጀምሮ ሰሜን ኢትዮጵያ በማዕከላዊ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል ግጭት ሲካሄድበት እንደቆየ የጠቀሰው መግለጫው፣ የትግራይ ክልል የትኩረት ነጥብ ሆኖ መቆየቱን አስታውሷል፡፡  አነን ግጭቱ 9.4 ሚሊዮን ሰዎችን በሰብአዊ ርዳታ ላይ ጥገኛ እንዳደረገ ጠቅሰው፣ ከእነዚህ ውስጥ 5.2 ሚሊዮን የሚሆኑት በትግራይ ክልል ይገኛሉ ብለዋል፡፡  400 ሺህ ሰዎች ተጨማሪ ያንብቡ
2022-01-22
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለዋና መስሪያ ቤቱ ባለ 36 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው፡፡ መስሪያ ቤቱ አገልግሎቴን ለማሻሻልና ለማዘመን ያግዘኛል ያለው አዲሱ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ይገነባል ተብሏል፡፡ ለህንፃው የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ሲካሄድ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ፍትሃዊነትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አዲስ የሚገነባው ባለ 36 ወለል የዋና መስሪያ ቤት ህንፃም የተቋሙን ሥራ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግና ተወዳዳሪ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በ4 ዓመታት ጊዜ ግንባታው ይጠናቀቃል የተባለው ህንፃ በታሰበለት ጊዜ ተጠናቅቆ ወደ አገልግሎት እንዲገባ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አስገነባዋለሁ ያለው ህንፃ ሲጠናቀቅ ተቋሙ ለቢሮ ኪራይ የሚያወጣውን ወጪ ያስቀራል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ አሁን እየተካሄደ ባለው የህንፃው ተጨማሪ ያንብቡ
2022-01-22
የሚኒሰትሮች ምክር ቤት ከትናንት በስትያ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች አንደኛው የተሽከርካሪዎች የፍጥነት ወሰን ደንብን ይመለከታል፡፡  በኢትዮጵያ ያለው የተሽከርካሪ ወሰን ደንብ ከወጣ 53 ዓመት አልፎታል፡፡  ይህም ዛሬ ካለው የትራፊክ ፍሰት ጋር ፈፅሞ የሚግባባ አይደለም ሲባል ሰምተናል፡፡ 
2022-01-22
ጉዳያችን- አቶ አለምፀሀይ ማሩ በዓይነ ስውርነት ጉዳይ ዙሪያ ሲያቀርቡልን የነበረው ማብራሪያ ዛሬ የመጨረሻው ክፍል ነው፡፡ እሳቸው የልዩ ፍላጎት ባለሙያ ናቸው፡፡ በህፃናት ወይንም በታዳጊነት እድሜ ዓይነ ሥውርነት ሲከሰት ለታዳጊ ሊሰጥ የሚገባው ስልጠና እንዴት ያለ ነው?
2022-01-22
ጦርነት በሰዎች ላይ የሚፈጥረው የአዕምሮ ጠባሳ በጦርነት ውስጥ ያለፉት በደንብ ያውቁታል፡፡ ለወታደር ግን ጦርነት ጓዶቹን ቢያሳጣውም፣ ደጋግሞ ቢቆስልም፣ ረሃብና የውሃ ጥም ቢያንገላታውም ከዓላማው ወደ ኋላ የሚያስቀረው አይደለም፡፡ ጦርነት ላይ በከባድ ሁኔታ ቆስሎ በህክምና ላይ ያለውንም ቢጠይቁት ከመቼው ተሽሎኝ ወደ ግንባር ተመልሼ ዓላማዬን ባሳካሁ የሚለው ብዙ ነው፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን ያነጋገራቸቸው አንድ ወታደርም መሰል ስሜታቸውን ነግረዋታል፡፡
2022-01-22
በኢትዮጵያ ዘመናት የተሻገረውን ቁርሾና የግጭት አዙሪት በቃ ብሎ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሽግግር ፍትህ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተደጋግሞ ይነሳል፡፡  የሽግግር ፍትህ ፍሬ እንዲኖረው ደግሞ ሥራውን ለመከወን በተቋቋሙ ኮሚሽኖች መካከል መናበብ ያስፈልጋል ይላሉ ለጉዳት ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች፡፡
2022-01-22
የደቡብ ሱዳኖቹ የሙርሌ ጎሣ አባላት ዘርፈው ህፃናትም አፍነው መውሰድ የየዓመቱ ተግባራቸው ሆኗል፡፡  ትናንት በፈፀሙት ጥቃትም ዜጎችን ገድለዋል ከብቶቻቸውንም ዘርፈዋል፡፡  አፍነው የወሰዱትን አንድ ህፃን በ200 ከብት ይሸጡታል ይባላል፡፡ እንዲህ ከዓመት ዓመት የቀጠለውን ጥቃት ለመከላከል ክልሉ ምን እየሰራ ነው?
2022-01-22
ከውጪ የሚገቡ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ለሀገር ውስጥ አምራቾች አሁንም ፈተና እንደሆኑ ናቸው።  እነዚህ ምርቶች የተረጋገጠ የጥራት ደረጃ ስለሌላቸው ይመስላል ዋጋቸው ርካሽ ነው።  ተመረቱበት የሚባለው ሀገር እና ይዘውታል የሚባለው ግብዓትም ብዙ ጊዜ የተጭበረበረ እንደሆነ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይናገራል።  በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ከውጪ ከሚያስገቧቸው ግብዓቶች ጋር በተገናኘም ሚኒስቴሩ ጫና እንዳለበት ሰምተናል።
2022-01-22
ከትናንት 11 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 8 የነደደ እሳት በአባኮራን ሰፈር ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የተገመተ ንብረት አጠፋ፡፡ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፡፡
2022-01-22
የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ቢሮ ሌባ ወይንም ጉቦኛ ሰራተኞቼን ለመቆጣጠር ካሜራ እያስገጠምኩ ነው አለ፡፡ ለሥራ ጉዳይ ወደ ቢሮው የሚመጡ ባለጉዳዮችም ለዝነጣ ሳይሆን ጉቦ ለመስጠት እጃቸውን ኪሳቸው ከተው እንደሚመጡ የቢሮው ሃላፊ ግርማ ሰይፉ ተናግረዋል፡፡