ማስታወቂያ

programs top mid size ad

መስከረም 6፣ 2014- በዘመን መለወጫ በዓል ሠሞን የነበረው ግብይት የተረጋጋ እንዲሆን የህብረት ስራ ማህበራት ከፍ ያለ ሚና ተጫውተዋል ተባለ

በዘመን መለወጫ በዓል ሠሞን የነበረው ግብይት የተረጋጋ እንዲሆን የህብረት ስራ ማህበራት ከፍ ያለ ሚና ተጫውተዋል ተባለ። የፌዴራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ሡሩር እንዳሉት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የኑሮ ውድነት በበዓሉ ሠሞን እንዳይባባስ የህብረት ስራ ማህበራት ከፍ ያለ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

ማህበራቱ የተለያዩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሠቡ ሲያቀርቡ እንደነበር አቶ ኡስማን ተናግረዋል ። ገበያውን በማረጋጋት ታስቦ የነበረው የኢኮኖሚ አሻጥር እንዲከሽፍ አድርገዋል ሲሉ አቶ ኡስማን አክለዋ።

ይህን በጎ አስተዋፅኦቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉበትም ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል። በህብረት ስራ ማህበራት የ2013 አፈፃፀም እና የ2014 ዕቅድ ላይ የሚመክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የህብረት ስራ ማህበራት እየተሳተፉ ይገኛሉ። አሁን ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ99,500 በላይ መሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት እንዳሉ ሠምተናል።

አጠቃላይ ካፒታላቸው ደግሞ 31.7 ቢሊየን ብር ደርሷል ተብሏል።

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ