ማስታወቂያ

programs top mid size ad

መስከረም 8፣ 2014- ከኢትዮ ቴሌኮም በ4 ወር ውስጥ በቴሌ ብር ገንዘብ ማስተላለፍያ መላ ለ1 ቢሊየን ጥቂት የቀረው ገንዘብ መዘዋወሩ ተሰማ

ከኢትዮ ቴሌኮም በ4 ወር ውስጥ በቴሌ ብር ገንዘብ ማስተላለፍያ መላ ለ1 ቢሊየን ጥቂት የቀረው ገንዘብ መዘዋወሩ ተሰማ።

ኩባንያው በ128 ቀን ውስጥ የቴሌ ብር ደንበኞች ቁጥር 9 ሚሊየን ደርሷል ማለቱን ሰምተናል።

ኩባንያው ደንበኞቹ ወደ ኢትዮቴሌኮም መሸጫ ሱቅ ሳይሄዱ ባሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን አገልግሎት በቅርቡ ይጀምራል ብሏል።

ደንበኞች ግዜያቸው ገንዘባቸው እና ጉልበታቸው ሳይባክን ሲም ካርዶችን መግዛት መቀየር እና ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት የሚችሉበት ሥራ እያከናወነ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ሲናገሩ ሰምተናል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በመላው ሀገሪቱ በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግ በማሰብ ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ማውጣቱ ተሰምቷል።

በሁሉም ቀጠና እጅ ላጠራቸው ወላጆች እና ተማሪዎች 600,000 ግድም የመማርያ ደብተሮችን ሰጥቷል ተብሏል።

ወሬውን የሰማነው ኩባንያው በምዕራብ ቀጠና የ4ጂ ‘ኤል ቲ ኢ አድቫኝስድ’ አገልግሎት መጀመሩን በነገረበት ግዜ ተገኝተን ነው።

ኩባንያው የ4G እና Lte Advanced የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራውን አጠናቆ ዛሬ በነቀምቴ ከተማ አስጀምሯል።

የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ አገልግሎቱ በነቀምቴ ደምቢዶሎ ጊምቢ ባኮ እና ሻምቡ አገልግሎቱ እንደተጀመረ ነግረውናል።

 የዛሬውን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በ14 ቀጠናዎች ለሚገኙ 78 ከተሞች አገልግሎቱን አግኝተዋል።

በበጀት ዓመቱ 106 ከተሞች የላቀውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲያገኙ ማስፋፊያ እየተከናወነ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ሲናገሩ ሰምተናል።

ኢትዮ  ቴሌኮም የዳታ አጠቃቀም በብርቱ በሚታይባቸው የሐገሪቱ ከተሞች የላቀውን የኢንተርኔት አገልግሎት እያስጀመረ ነው።

ኩባንያው የተቸገሩ ተማሪዎች ከተማሪ ቤት ገበታቸው ላይ እንዳይቀሩ መማርያ ቁሳቁስ እንዲሟሉላቸው ማገዙን ሰምተናል።

የተማሪዎች ቦርሳ ደብተር የኪስ ገንዘብ ላፕቶፕ እና ዘመናዊ ስልክ  ኩባንያው ያስፈልጋቸዋል ላላቸው ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሰጥቷል ተብሏል።

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ