ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2020-11-29
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 492 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,406 የላብራቶሪ ምርመራ 492 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ባለፋት 24 ሰዓታት የ9 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,695 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 744 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 68,250 አድርሶታል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 108,930 ደርሷል፡፡
2020-11-29
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሠራዊት መቀሌን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ተናገሩ።
2020-11-29
የትግራይ ክልልን ሲመራ የነበረው ህወሓት ፓርቲና በፌደራል መንግሥት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ወደ ከፋ ግጭት ማደጉ የሀገር ስጋት ሆኗል፡፡ የፌደራል መንግሥት ታግሼ ታግሼ ጨርሻለሁ ብሎ አጥፊ ባለው የጥፋት ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ ከገባ አንድ ወር ሊሞላው የቀራት ጥቂት ቀናት ናቸው፡፡ መንግሥት እንዳሰበው ዘመቻውን ቢያጠናቅቅ ሌሎች ለግጭት መንስኤ የሚሆኑ የቤት ስራዎች ይኖሩ ይሆን? ትዕግስት ዘሪሁን በዚህ ጉዳይ ምሁራንን አነጋግራለች፡፡
2020-11-29
የፌደራል መንግሥት ከሰሞኑ የህልውና ህግ የማስከበር እርምጃ በሚል በህወሓት ቡድን ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖው ቀላል አይደለም ይላሉ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን፡፡ በቀጠናው ትልቅ ስፍራና ሚና ያላት ኢትዮጵያ በዚሁ ሁኔታ ውስጥ ስትሆን ወትሮውኑ አይናቸውን ከማይነቅሉና አመቺ ጊዜ ከሚጠብቁ ወገኖችን ነቅታ መጠበቅ ተገቢ እንደሆነ በአፅንኦት ይናገራሉ፡፡  
2020-11-29
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 769 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,271 የላብራቶሪ ምርመራ 769 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ባለፋት 24 ሰዓታት የ14 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,686 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 505 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 67,506 አድርሶታል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 108,438 ደርሷል፡፡
2020-11-27
ዩኒሴፍ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ፡፡
2020-11-27
ቶታል ኢትዮጵያ የአሽከርካሪዎቹን ሁኔታ የሚቆጣጠርና አደጋን መቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ አድርጎ ውጤታማ መሆኑን ተናግሯል፡፡  የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ቴክኖሎጂውን መሰል ተቋማት ተግባራዊ እንዲያደርጉት መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ብሏል፡፡
2020-11-27
ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ተልኮ አዲስ አበባ የሚገኘው ልዑክ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር የሚነጋገር ቢሆንም ጉዳዩ ግን ከህወሓት ጋር በሚደረግበት ሁኔታ አለመሆኑ ተነገረ፡፡ 
2020-11-27
የፋይናንስ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ለፍራንስ 24 በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡  ሚኒስትሩ አሁን በትግራይ የሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ የመጨረሻውን ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝና በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚደመደም ለቴሌቪዥን ጣቢያው ነግረዋል፡፡ 
2020-11-26
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 560 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5,789 የላብራቶሪ ምርመራ 560 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ባለፋት 24 ሰዓታት የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 1,672 አድርሶታል። በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 427 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 67,001 አድርሶታል፡፡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 107,669 ደርሷል፡፡