ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2020-06-29
ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3693 የላብራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር ተናገረ፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5846 ደርሷል። ባለፋት 24 ሰዓታት 5 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ይህም በሀገራችን በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሰው ቁጥር 103 ደርሷል። በተጨማሪም በትናንትናው ዕለት 298 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ብዛት 2430 አድርሶታል፡፡
2020-06-29
የማንን ጨዋታ መልሰን እናስደምጣችሁ… ባለፉት 20 ዓመታት የጨዋታ ፕሮግራም ቆይታ በመቶዎች የሚቆጠሩ እንግዶች እውቀት፣ ጨዋታ እና ልምዳቸውን አጋርተውናል… እነሆ ዛሬ ላይ ሆነን የጨዋታ መሰናዶን 20 ዓመት ስናከብር ከእንግዶቻችን ጨዋታዎች የትኛውን ደግመን እንድናስደምጣችሁ እንደምትሹ ምክንያታችሁን ጨምራችሁ ፃፉልን… ከጨዋታ እንግዶቻችን በከፊል፣ ጥበበ ተርፋ ራሔል ዩሐንስ ህይወት ተፈራ ፍቃዱ ተክለማርያም ደስታ ሐጎስ እያሱ በርሔ ዳንዔል ክብረት ኃይማኖት ዓለሙ ጥላሁን ገሠሠ ነቢይ መኮንን አባተ መኩሪያ ሚካዔል በላይነህ ብርሐኑ አስረስ ኤልሳቤት መላኩ ቴዎድሮስ ካሳሁን ጃርሶ ሞትባይኖር ኪሩቤል ተስፋዬ ሳህሉ ተስፋዬ ገሠሠ ዘውዴ ረታ ንጉሴ አክሊሉ ተሾመ ገ/ማርያም ዶ/ር በላይ አበጋዝ ካሳዬ ጨመዳ ታደለች ሀ/ሚካሜል ንጉሴ መንገሻ መዓዛ አሸናፊ አበበች ጉበና ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ አቡነ ማቲያስ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ ጌታቸው ደስታ አሰፋ ጨቦ ነጋሽ ገብረማርያም ፕ ተጨማሪ ያንብቡ
2020-06-29
የቅዳሜ ጨዋታ ፕሮግራም ሐምሌ 1፣2012 20 ዓመት ሞላው፡፡ የቅዳሜ ጨዋታ አዘጋጆች በወጣትነታቸው በሬዲዮ ፍቅር የተጠመዱበትን የኢትዮጵያ ሬዲዮን የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ለዛን ይዞ፤ ዘመኑ የሚፈልገውን ቃና አክሎበት በ97.1 የFM ሬዲዮ ለ8 ዓመታት፣ በሸገር ሬዲዮ ለ12 ዓመታት ከእናንተ አድማጮቹ ጋር 20 ዓመታት በጨዋታ አሳለፈ፤ ለሸገርም እርሾ ሆኖ ቀጠለ፡፡ ጨዋታ አዲስ ጣዕም ይዞ ሸገርን ወለደ፡፡ የጨዋታ አዘጋጆች የዛሬ 20 ዓመት በአገራችን ሚዲያ ተዘንግቷል ብለው ያሰቡትን ኢትዮጵያውያንን እርስ በርስ አጋምዶ፣ አዛምዶና አስማምቶ ያኖረውን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በትዝታ ዘአራዳ፣ በእንግዶች ጨዋታ፣ በድራማና የሥነጽሁፍ ትረካ በሙዚቃ አጣፍጦ በጥበብ አሳምሮ ቀጠሮውን ሳያዛንፍ 20 ዓመታት ከአድማጮቹ ጋር ዘለቀ፡፡ ሁላችንንም እንኳን ደስ ያለን፡፡ ሃያ ዓመታት በጨዋታ ሲያልፍ ሁልጊዜም በምቾት አልነበረም፡፡ በሚቀርቡት አንግዶች፣ በታሪክ ትውስታው፣ በአድማጭ መወቀሱ በባለስልጣን መከሰሱ አልቀረም፡፡ ይሄ ይበልጥ ወዳጅነታችንንም ተጨማሪ ያንብቡ
2020-06-29
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ እንዲቀጥል የሚያደርግ አማራጭ ሥርዓት ያስፈልጋል ሲሉ ተማሪዎች እየጠየቁ ነው፡፡
2020-06-29
የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በርካታ ችግሮች ያሉበት ቢሆንም ህጉ እስካልተቀየረ ድረስ ለሚነሱ የመብት ጥያቄዎች ባለው ህግ መሰረት መልስ ሊሰጥ ይገባል ተባለ፡፡
2020-06-29
የኢትዮጵያውያንን የነፍስ ወከፍ ገቢ 2,248 ዶላር ያደርሳል ተብሎ ተስፋ በተጣለበት የ10 ዓመት የመሪ የልማት እቅድ ላይ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ውይይት ተደርጓል፡፡
2020-06-29
በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሀገራችንን አቋም ለተቀረው ዓለም ለማስረዳት ከምንጊዜውም በላቀ እየሰሩ እንደሚገኙ ተነገረ። ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የሀገራችንን አቋም ለተቀረው ዓለም በስፋት እያስረዱ የሚገኙት በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን እና በተለያዩ ቋንቋዎች ነው ተብሏል። በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ እነዚሁ ወገኖች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረገው የኢትዮጵያ አቋም በሌሎች እንዲታወቅ ረድተዋል ተብሏል። የኢትዮጵያ የዲያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሠላማዊት ዳዊት ዛሬ ለሸገር እንዳሉት እነዚህ ወገኖቻችን ለግድቡ ስራ በተለያየ መንገድ የገንዘብ አስተዋፅኦም እያደረጉ ነው። የቦንድ ሽያጭ በሚፈቀድባቸው ሀገራት የሚኖሩት ቦንድ እየገዙ ነው ብለዋል። የቦንድ ሽያጭ በማይፈቀድባቸው አካባቢዎች ያሉት ደግሞ የገንዘብ ስጦታ እያደረጉ እንደሚገኙ ነግረውናል።
2020-06-29
የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ከነገ ሰኔ 23 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2012 እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተናገረ፡፡ ክትባቱ እድሜአቸው ከ9 ወር እስከ 5 ዓመት ለሆናቸው ሕፃናት በሁሉም የጤና ተቋማትና በጊዜያዊ የክትባት ጣቢያዎች ይሰጣል ተብሏል፡፡ በተጠቀሰው የእድሜ ክልል ያሉ ሕፃናት ከዚህ ቀደም የኩፍኝ ክትባት ቢከተቡም ባይከተቡም ይኸኛውን ክትባት መውሰድ እንደሚኖርባቸው ተነግሯል፡፡ የኩፍኝ በሽታ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ሲደርስ የዐይን መጥፋት፣ የአእምሮ በሽታ፣ የጆሮ ህመም፣ የሳንባ ምችና ሞት ሊሚያስከትል የሚችል ነው ተብሏል፡፡ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከራስ ፀጉር ጀምሮ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚዛመት ሽፍታ፣ የዓይን መደፍረስ፣ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽና ሳል የበሽታው ምልክቶች መሆናቸው ተነግሯል፡፡ 90 በመቶ ያህል ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል የተባለው የኩፍኝ በሽታ ከጎሮሮ እና ከአፍንጫ በሚወጡ ፈሳሾች እንዲሁም በትንፋሽ ይተላለፋል፡፡ ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 2 ይሰጣል የተባለው የኩፍኝ መከላከያ ክትባት በአዲስ ተጨማሪ ያንብቡ
2020-06-29
በባህላዊ መንገድ የሚመረትን ሸክላ ለማቃጠል የሚረዳ ዘመናዊ የፈጠራ ውጤት በእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተሰርቶ ለስራ ዝግጁ መሆኑ ተነግሯል፡፡ቴክኖሎጂው ከውጪ ቢገባ እስከ ግማሽ ሚሊየን ብር ያስወጣ ነበር ተብሏል፡፡  
2020-06-29
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በየእለቱ 300,000 ብር እያጣ ነው፡፡ የ3 ወራት ኪሳራውም 27 ሚሊዮን ብር ደርሷል ተባለ፡፡