ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-10-20
ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ እና በዳርቻዋ ውብ የመናፈሻ ሥፍራዎች መበጀታቸው ይበል የሚያሰኘውን ያህል፤ በከተማው መሪ ዕቅድ ላይ ለአረንጓዴ ሥፍራ የተያዙ ቦታዎች እየተቆረሱ ለሌላ ዓላማ ሲውሉ ይታያል፡፡
2021-10-20
ባለፈው መስከረም 20 በክልሉ የተካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ዛሬ የምስረታ ጉባኤ አካሂዷል፡፡ አቶ ሙስጠፌ መሀመድን የክልሉ ፕሬዘዳንት አድርጎ መርጧል
2021-10-19
በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀው የህወሓት ታጣቂ ኃይል በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ በተፈናቀሉ ዜጎች እጅግ በጣም እንደተጨናነቁ ተሰማ፡፡ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡
2021-10-19
የሶማሊ ክልል የፀጥታ ሃይል በቶጎጫሊ እና በሞያሌ በኩል የሚካሄድን ሕገ ወጥ የገንዘብ፣ የሰዎች፣ የጦር መሳሪያና የሐሺሽ ዝውውር ለመቆጣጠር እየሰራ ነው ተባለ፡፡ ከትናንት በስቲያ የተመሰረተው የክልሉ ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ አባላትን ሾሟል፡፡  
2021-10-19
በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች የፖሊዮ ቫይረስ መኖሩ ተረጋግጧል ተባለ፡፡ በዚህም ከመጪው ጥቅምት 15 ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡ የኢትዮጵጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩ እና የጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ከመጪው ጥቅምት 12 እስከ 15፣ 2014 ዓ.ም በዘመቻ ይሰጣል ተብሏል፡፡ ክትባቱ የሚሰጠው በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች የፖሊዮ ቫይረስ ታማሚዎች ሪፖርት በመደረጉ ነው ተብሏል፡፡ የክትባት ዘመቻው በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ላሉ ከ17 ሚሊየን በላይ ህፃናት እንደሚደርስ ተነግሯል፡፡ ክትባቱን ለመስጠት የሚያገለግሉ አስፈላጊ ግብዓቶች መሰራጨታቸው ተነግሯል፡፡ ክትባቱ የሚሰጠው በሰለጠኑ የክትባት ባለሙያዎች ቤት ለቤት ሲሆን በሚመጡበት ጊዜ አስፈላጊውን ትብብር አድርጉላቸው ሲል የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳስቧል፡፡
2021-10-19
በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት በክፍያ መሰጠት ሊጀምር ነው ተባለ፡፡ ሜዲቴክ ኢትዮጵያና ዋሽንግተን የህክምና ማዕከል ከቻይና የክትባት አምራች ሲኖፋርም ጋር ውል ገብተው 200,000 ዶዝ ክትባት ወደ ሀገር ቤት አስገብተዋል ተብሏል፡፡
2021-10-19
በታጣቂዎች በደረሰባቸው ጥቃት የጉዳታቸው መጠን ከፍ ላለ የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ልዩ ድጋፍ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡
2021-10-19
በአሶሳ ከተማ የሚገኘው የሼህ ሆጃሌ አልሀሰን የችሎት አዳራሽ ዳኞች ተሰይመውለት ዳግም ባህላዊውን የፍርድ አሰጣጥ እንዲጀምር ለማድረግ የእድሳት ሥራዎች መጀመራቸውን ሸገር ተመልክቷል፡፡  
2021-10-19
አሜሪካ እና የሷን ሀሳብ የሚደግፉ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የያዙትን አቋም ለማስቀየር በውጭ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ጫና ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ይነገራል፡፡ ለዚህ ደግሞ መንግስት የሰሜኑን ጦርነትም ሆነ በሀገሪቱ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ የተመለከተ የተረጋገጠ መረጃ መስጠት ይገባዋል ተብሏል፡፡
2021-10-19
በትግራይ እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መወሰኑ የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ፡፡ በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል አሸባሪነት የተፈረጀው ህወሃት በተፈጠረው ችግር ምክንያት በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኛለሁ ብሏል፡፡ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲ በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገፅ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተነግሯል፡፡ በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ ለምዝገባም ትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባስቀመጠው አድራሻ ተማሪዎች ፎርም ሞልተው እንዲመዘገቡ ጠይቋል፡፡