ማስታወቂያ

የሸገር ወሬዎቻችን

Sort by
ነባሪ
Post Date
2021-01-20
ረዥም ዕድሜ መኖር የሀብትና የኢኮኖሚ ዕድገት መለኪያ ሊሆን ይችላል? በዋሲሁን በላይ የተፃፈውን ተስፋዬ አለነ ያቀርበዋል::
2021-01-10
ኢትዮጵያ የድህነት አዙሪት ቀለበቱን እንዴት ሰብራ ትውጣ? ከዋሲሁን በላይ በተስፋዬ አለነ
2021-01-07
የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ፤ ፈተናዎቹና መውጫው መንገድ
2020-12-30
ንግድ እንዲበረታ ኢኮኖሚም እንዲለማ፤ ለንግድ ምክር ቤቶች አሠሪ ዐዋጅ-በምክክር! ክፍል ሁለት  
2020-12-30
ኢትዮጵያ 'ተይ ዘገየሽ' ወደተባለችበት የካፒታል ገበያ
2020-12-28
ንግድ እንዲበረታ ኢኮኖሚም እንዲለማ፤ ለንግድ ምክር ቤቶች አሠሪ ዐዋጅ-በምክክር!  
2020-12-27
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አጠቃላይ ገቢዬ 3.1 ቢሊየን  ብር ደርሶልኛል አለ፡፡ ባንኩ በተጠናቀቀው የጎርጎሮሲያኑ በጀት ዓመት ከግብር  በፊት 781 ሚሊዮን አትርፌአለው ብሏል፡፡ ባንኩ በዚሁ ጊዜ  8.3 ቢሊየን ብር ማበደሩን ተናግሯል፡፡ አጠቃላይ የብድር ክምችቱ 19.1 ቢሊየን ደርሷል ብሏል፡፡ የውጪ ምንዛሬ 169.6 ሚሊየን ዶላር ማግኘቱን ባንኩ ዛሬ መደበኛና ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ጊዜ ሰምተናል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 31.8 ቢሊየን ብር መድረሱን ከቀረበ ሪፖርት ተመልክተናል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ እዳ 28.3 ቢሊየን ብር የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 2.2 ቢሊየን ብር እንደደረሰ ተነግሯል፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባንኩን ቢፈትነውም የተቀማጭ ገንዘቡን በማሰባሰብ በኩል ውጤት ማግኘቱን ተናግሯል፡፡
2020-12-27
ዘመን ባንክ በ2012 በጀት ዓመት 1 ቢሊዮን 46 ሚሊዮን ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ተናገረ፡፡ ባንኩ በዓመቱ ያገኘሁት ትርፍ በእቅዴ ይዤው ከነበረው የትርፍ መጠን የ29 በመቶ ጭማሪ አለው ብሏል፡፡ የ2012 በጀት ዓመት ትርፉ ከቀዳሚው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ388 ሚሊዮን ብር ወይንም የ59 በመቶ እድገት ማሳየቱን ተናግሯል፡፡ ዘመን ባንክ ዛሬ ጉባኤውን ባለ አክሲዮኖች በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል። ባንኩ ትርፌ ለማደጉ የብድር አቅርቦት እና በአገልግሎት ዘርፍ የተመዘገበው አፈፃፀም ከፍተኛ ድርሻ አበርክቶልኛል ብሎ ሲናገር ሰምተናል፡፡ ባንኩ በ2012 በጀት ዓመት ያገኘው አጠቃላይ ገቢ 2.15 ቢሊዮን ብር ነው የተባለ ሲሆን ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ570 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡ ዘመን ባንክ በአጠቃላይ ሀብቱ 18.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን፣የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1.8 ቢሊዮን መድረሱን ተናግሯል፡፡ ባንኩ የሰጠሁት ብድር 9.7 ቢሊዮን ብር ደርሷልም ተብሏል፡፡ ባንኩ ተጨማሪ ያንብቡ
2020-12-24
ንብ ባንክ በዘንድሮው የባንኩ የበጀት ዓመት 1.3 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ፡፡  የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 3.44 ቢሊዮን መድረሱንም ሰምተናል፡፡ ንብ ባንክ በአውሮጳውያኑ 2020 የበጀት ዓመት በአጠቃላይ 25.8 ቢሊዮን ብር ማበደሩን ተናግሯል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብም 33.7 ቢሊዮን ብር መድረሱን ባንኩ ለባለድርሻዎች ዓመታዊ ሪፖርቱን ሲያቀርብ ሰምተናል፡፡በባንኩ ገንዘባቸውን ያኖሩ ሰዎች ቁጥር ከባለፈው አመት መጨመሩ ተሰምቷል፡፡ ባንኩ አጠቃላይ ገቢዬ 4.55 ቢሊዮን ብር ደርሷል ብሏል፡፡ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ባስገነባው ባለ 32 ወለል ሕንፃ ውስጥ ዘንድሮ ሥራ እንደሚጀምር ተናግሯል፡፡ ባንኩ ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቀሴዎች 21.9 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማደረጉን እወቁልኝ ብሏል፡፡  
2020-12-24
ዳሽን ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን ከ3.5 ቢሊዮን ወደ 5.5 ቢሊዮን ማሳደጉን ተናገረ፡፡ ዳሽን ባንክ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘቡ መጠን 53.49 ቢሊዮን ብር፣ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ደግሞ 68.26 ቢሊዮን ብር መድረሱን ተናግሯል፡፡ ባንኩ ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ የባለድርሻዎች ጉባዔ ላይ ዓመታዊ ሪፖርቱን ሲያቀርብ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የአውሮፓውያን ዓመት ባንኩ 1.79 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናግሯል፡፡ ዳሽን ባንክ ከ3 ዓመት በፊት የጀመረው የአሞሌ ዘመናዊ ክፍያ ገንዘብ ማስተላለፍያ ደንበኞቹ ቁጥር ከ3 ሚሊዮን እንዳለፈ ተናግሯል፡፡ ሀገሪቱ የጀመረችውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ለማደርጀትም ባንኩ በተለያዩ ፕሮጀክቶች እንደሚሰማራ ተናግሯል፡፡ የዳሽን ባንክ የዓመቱ አጠቃላይ ወጪ 5.4 ቢሊዮን ብር መሆኑን ከዓመታዊ ሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተፈለገውን ያህል የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት እንዳላስቻለው የተናገረው ባንኩ፣ እንዲያም ሆኖ ከወጭ ንግድ እና ከሐዋላ በአመቱ 562.8 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ተናግሯል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ተጨማሪ ያንብቡ