ማስታወቂያ

programs top mid size ad

የሸገር ልዩ ወሬ- በቅጠል እና በተበጣጠሰ ላስቲክ እንደነገሩ በተወታተፈች ጎጇ የሚኖሩት እማማ አያንቱ ክረምትን አይወዱትም

እማማ አያንቱ ደበላ ክረምትን አይወዱትም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሚሸጡትን ቅጠል ስለሚያበሰብስባቸው ብቻ አይደለም፡፡ በቅጠል እና በተበጣጠሰ ላስቲክ እንደነገሩ የተወታተፈችው ጎጇቸው ክረምት ሲመጣ ከላይ በዝናብ ከሥር በጎርፍ ውሃ ትሞላለች፡፡

እድሜዬን አላውቀውም የሚሉት እማማ አያንቱ ደበላ፣ ገና ድሮ ነው ከሜጫ ወደ አዲስ አበባ የመጡት፡፡ 

ትዳርም ሆነ ልጅ የላቸውም፡፡

ለበርካታ ዓመታት የሰው ቤት ሰራተኛ ሆነው ከኖሩ በኋላ ይህቺን ጎጆ ራሳቸው ሰርተው ቅጠል ሸጠው መኖር ጀመሩ…

እነሆ ቅጠል ሲሸጡ ብዙ ዓመታት ሆናቸው፡፡

ሁሌ ክረምት ሲመጣ ግን ሐሳብ ይገባቸዋል ይለናል እማማ አያንቱን ያነጋገራቸው የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ፡፡
ከእጅ ወደ አፍ የሆነው የእማማ አያንቱ ኑሮ የሚደጎመው በሰፈሩ ልጆች እርዳታ ነው፡፡

የክረምቱ መግቢያ ነውና፣ በቅጠል ጣራ በቅጠል እንጀራ የሚኖሩት እማማ አያንቱ ከሰሞኑም ዝናብ በባሳ የመጪው ክረምት ዶፍ ነው የሚያሳስባቸው፡፡

ሙሉውን ያዳምጡ…

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ