ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ነሐሴ 14፣ 2012/ ከዛሬ 8 ዓመት በፊት፣ በዛሬው ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ

ከዛሬ 8 ዓመት በፊት፣ በዛሬው ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕክምና ከሚያደርጉበት ብራስልስ ማረፋቸው በመገናኛ ብዙሃን የተነገረው ነሐሴ 14/2004 ዓ/ም ነበር፡፡

አቶ መለስ ሹመታቸው ላይ እንዳሉ የሞቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ በትጥቅ ትግል የመንግስትነት ስልጣን የተቆጣጠረው ኢሕአዴግ ሊቀመንበር በመሆናቸው የሃገሪቱ መሪ ለመሆን በቅተዋል፡፡

በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቆይተው በሕገ-መንግስቱ በተሰጠው ድንጋጌ መሰረት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለ21 ዓመታት ኢትዮጵያን መርተዋል፡፡

በትግራይ አድዋ ከተማ የተወለዱት አቶ መለስ ወደ ሕወሓት የተቀላቀሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትምርታቸውን አቋርጠው ነው፡፡

አቶ መለስ በስልጣን በቆዩበት ጊዜ በተለይ የምጣኔ ሐብቱ እድገት አለም አቀፍ ድርጅቶች እንዳረጋገጡት በ2 አሃዝ ከፍ ያለበት ጊዜ ነው፡፡

በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች ከመቼውም ጊዜ የተሻለ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ የተመዘገበበት ጊዜ ሆኗል፡፡

የህዳሴ ግድብንም በራስ አቅም እንዲገነባ እና ስራው እንዲጀመር አድርገዋል፡፡

በአለም አቀፍ የመሪዎች ጉባኤ ተደማጭነት አግኝተው፣ ኢትዮጵያ በበለፀጉ ሃገሮች ጉባኤ እንድትሳተፍ አድርገዋታል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ዋና ፅህፈት ቤት ከአዲስ አበባ እንዲነሳ የተደረገውን ሙከራ ተከራክረው ማስቀረታቸውም በበጎ ይታወስላቸዋል፡፡

በሌላ በኩል በእርሳቸው የስልጣን ጊዜ በየክልሎቹ እኩል ተጠቃሚነት የሌለበት፣ አድሎዓዊ አሰራር እንዲሰፍን፣ እስርና አፈና በዝቶ የዜጎች የመብት ጥያቄ በሃይል እንዲጨፈለቅና መብታቸው እንዲጣስ፣ ብሔር ብሔረሰቦች እንዲጠራጠሩ፣ የጥላቻ ቅስቀሳዎች እንዲስፋፉ አድርገዋል እየተባሉ በተቃዋሚዎቻቸው ይወቀሳሉ፡፡

በተለይ ከ1993 ዓ/ም ወዲህ ስልጣኑን ሁሉ በእጃቸው አድርገው የአንድ ሰው ፍላጎት የሚፈፅምባት ሃገር አድርጋዋታል እየተባሉ ይተቻሉ፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ በፕሬዝዳንትነትና በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለ21 ዓመታት ከመሩ በኋላ በ57 ዓመታቸው አርፈዋል፡፡

የቀብራቸው ሥነ-ሥርዓት ከ15 ቀናት በኋላ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡
 

ቁልፍ ቃላት
ምላሽ